TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢሳት🔝የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ራድዮ "ቢቢሲ አፍሪካ" የሀሰት ዘገባ እንደሰራሁ በማስመሰል ያቀረበው ዘገባ #የተዛባ ነው ሲል ለቢቢሲ ዋና ዳሬክተር የፃፈው የቅሬታ ደብዳቤ ከላይ የምትመለከቱት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ካንሰር‼️ የኛ ድርሻ #ሌባዎቹን አሳልፎ ለህግ መስጠት ነው። ምክንያቱም ካንሰርን በጋራ መከላከል የሁሉም ዜጋ ግዴታ ስለሆነ። ከተማችን ደግሞ "የሌቦች መሸሸጊያ ዋሻ መሆን ስለማትችል። መልካም ቀን ይሁንላችሁ!"

🔹🔹ኢንጂነር ታከለ ኡማ🔹🔹

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት‼️

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም #የብሔራዊ_ዕርቀ_ሰላም_ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ማህበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅን ለማውረድ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ምክር ቤቱ የማንነትና አስተዳደር ወሰን ጉዳዮችም ላይ ኮሚሽን ለማቋቋም ተወያይቷል። ኮሚሽኑ በክልሎች የአስተዳደር ወሰንና በማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ የሚታዩ ችግሮች በተለያዩ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል የቅራኔ ምንጭ በመሆናቸው አገር አቀፍ በሆነና በማያዳግም መንገድ ለመፍታት እንዲያስችልም እንደሆነ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #መገደላቸው ተገለፀ።

በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም አስከባሪ ሃይሉ ከመንግስት ሃይሎች ጋር በመተባበበር አዲኤፍ በተባለው አማጺ ቡድን ላይ በከፈቱት ጥቃት ወቅት ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት መሞታቸው ነው የተገለጸው፡፡

#የኢቦላ በሽታ ተጠቂ የሆነው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኒ ግዛትን ከአማፂ ቡድኑ ነጻ ለማድረግ በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል እና የመንግስት ወታደሮች በጋራ ዘመቻ ማድረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ #ስቴቨን_ዱጃሪክ አስታውቀዋል፡፡

በዘመቻው አስር የሚሆኑ የሰላም አስከባሪ ሃይሎች መቁሰላቸውን እና አንድ ሰላም አስከባሪ መሰወሩን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል፡፡

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የአማፂ ቡድኑ በርካታ አባላት ተገድለዋልም ነው ያሉት፡፡

ከሞቱት የተባባሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት ስድስቱ የማላዊ ተዋላጆች ሲሆኑ አንዱ ታንዛንያዊ ነው ተብሏል፡፡

በማዓድን ሃብታም የሆነው ምስራቃዊ የዲሞክራቲክ ኮንጎ አካባቢን ለመቆጣጠር አዲኤፍ የተባለ አማፂ ቡድንን ጨምሮ በርካታ ታጣቂዎች ከመንግስት ሃይል ይዋጋሉ፡፡

ምንጭ፦ አልጃዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
አቶ ቶሌራ አዳባ-ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ እና የኦሮምያ ገዥ ፓርቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ በመተማመን እና በመግባባት መንፈስ እንደሚሠሩ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ #ቶሌራ_አደባ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በትጥቅ ትግል መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንግሥት በሰላም አሳምኖ ለመመለስ ጥረት ማድረግ አለበት፤ ካለበለዚያ “መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ግዴታ ስላለበት በወሰነበት መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር ይችላል” ብለዋል።

በኦዴፓና በኦነግ መካከል ሰሞኑን የተደረሰው ስምምነት አዲስ አለመሆኑን የጠቆሙት አቶ ቶሌራ በግንባራቸውና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ሰኔ 1/2010 ዓ.ም. አሥመራ ላይ የተደረሰውን ባለሦስት ነጥብ ስምምነት በፈጠነ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል።

የአሥመራው ስምምነት “ኦነግ #በሰላማዊ መንገድ ትግሉን በሃገር ቤት እንዲቀጥል ማድረግ ማስቻል፤ ካለው መንግሥትና በተለይም ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር የኦሮሞን ጉዳይ በተመለከተ መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር በጋራ የሚሠራበትን ሁኔታ በመደጋገፍ መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ትግላቸውን በመንግሥት ድጋፍ የሚቀጥሉበትን ሁኔታ በመመካከርና በመነጋገር ማመቻቸት” እንደሆነ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደራሜ🔝በአሁን ሰዓት በዱራሜ ከተማ ሰላማዊ ሰልፉ በመደረግ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2011 የካናዳ መንግስት ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ክብርት #ማሪ_ክሎድ_ቢቦን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ክብርት ቢቦም የካናዳ መንግስት ኢትዮጵያ እየተጟዘች ያለችበትን የዲሞክራሲንና የልማት ለዉጥ ጉዞ እንሚደግፍ ገልፀዋል።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የምታደርገዉን የልማት ጥረቶች የካናዳ መንግስት ስለመደገፉ የተሰማቸዉን ደስታ ገልጸዉ፣ ክብርት ቢቦ እንዳርጋገጡት በቅርብ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ጉብኝት አንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia