TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዳማ⬆️

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ "ሕገወጥ ነው" ያለውን አካባቢ ለማፍረስ በሄደበት ወቅት ከነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች #መቁሰላቸው ተገልጿል።

በተፈጠረው ችግር እጃቸው አለበት ያላቸውን ሰዎች ፖሊስ #በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

©voa amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፤ ደዋ ጨፋ ወረዳ በታጠቁ ሰዎችና በጸጥታ አካላት በተካሄደ ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በኢንቨስትመንት የተያዘ መሬት በአግባቡ ልማት ላይ አልዋለም በሚል ቅሬታ ግጭቱ ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2010 ዓም መከሰቱን ነው የወረዳው ጸጥታ ኃላፊ የተናገሩት፤ በድርጊቱ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ #በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ከ40 በላይ የሚሆኑ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት #በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ፡፡

የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት ትናንትና ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለስብሰባ ከተጠሩበት ስፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ከፍተኛ አመራሩና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር የዋሉት ገርጂ አካባቢ በሚገኘውና ቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ተብሎ ይጠራ በነበረውና አሁን የኮርፖሬሽኑ ንብረት በሆነው አሞራው ሕንፃ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ምክንያት ባይነለጽም፣ የፌዴራል ፖሊስ ጌዜያዊ እስር ቤት በሆነው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ቤት መታሰራቸውን ምንጮቹ አክለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia