TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጨማሪ ፎቶዎች⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድና የኤርትራ ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ የሚገኘውን የሰቃ ፏፏቴን ዛሬ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ:- የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ቀናት⬆️የከፍተኝ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዚህ ጥሪ መሰረት ለጉዞ እንድትዘጋጁ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንድታዘጋጁ ትኬት መቁረጥ ይጨምራል።

ከዚህ ውጪ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ብቻ የሚያተኩረውን ቻናላችንን መጎብኘት ትችላላችሁ @tikvahuniversity
#update የስሎቬኒያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀምረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ቦሩት ፕሆር ከኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር ዛሬ ማለዳ በሁለትዮሽ በአህጉራዊና በወቅታዊ ጉዳዮች ጋር መምከራቸውን ተሰምቷል፡፡

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ⬇️

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የከተማውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ትዕዛዝ ከሰጣቸው 850 አውቶብሶች 700ዎቹን እስካሁን እንዳልተረከበ ተሰምቷል። ለአውቶብሶቹ 3.4 ቢሊዮን ብር #ተከፍሏል ነው የተባለው፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ወ/ሮ እፀገነት አበበ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 ሲናገሩ፣ ከሜቴክ ጋር የአውቶብሶቹን ስራ ውል የገባነው በሰኔ ወር 2009 ዓ/ም ሲሆን አውቶብሶቹን መረከብ የነበረብን ሰኔ 2010 ነበር ብለዋል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አውቶብሶቹን በቃሌ መሰረት ያላስረከብኩት በውጪ ምንዛሬ ችግር ነው ብሎናል ያሉት ወ/ሮ እፀገነት ከዚህ ወር ጀምሮ ግን ቀስ በቀስ ቀሪ 700 አውቶብሶቹን ሊያስረክበን ቃል ገብቶልናል ብለዋል፡፡

#ሜቴክ ለአውቶብሶቹ መስሪያ የሚያስፈልገውን እቃዎች አስቀድሞ ገዝቷል፣ በተባለው ጊዜም ያደርስልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ወ/
ሮ እፀገነት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update "ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም" በሚል የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ እዲለቀቁ የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ እንደሆነ ለማየት ተችሏል። ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ጦላይ የተላኩት ወጣቶች "እያሰለጠናቸው" እንገኛለን በቀናት ውስጥ ይፈታሉ ብለው ለሚዲያ ተናግረው ነበር። ወጣቶቹ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ከጦላይ እንዳልተለቀቁ ለማወቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደሴ ከተማ በጽዳት የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በስራ አጋጣሚ ወድቆ ያገኙትን 59,950 (ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ብር ) ለፖሊስ
አስረክበዋል፡፡

ምንጭ፦ አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

የአምና ወይም 2010 #የወርቅ_ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች እስካሁን ስኮላርሺፕ እንዳላገኙ ለTIKVAH-ETHIOPIA በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የወርቅ ሜዳሚያ ተሸላሚ ተመራቂዎቹ እንዳሉት፦ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ ቃል በገቡልን መሰረት ውጪ ሀገር scholarship እንደ ሚሰጠን በሁሉም የሚዲያ የተነገረ ነበር። ፕሬዘዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ በበኩላቸዉ የውጪ ሐገር scholarship ባይሳካ ሐገር ውስጥ ታገኛላቹ ተብለን ነበር። ነገር ግን እስከ አሁን ምንም ነገር የለም። በተለያየ ሚዲያ እንዳገኘን ሲወራ ነበር። በተደጋጋሚ ትምርት ሚኒስቴር Dr. ጥላዬን እና ዶክተር #ሳሙኤልን ብንጠይቅም #መልስ ሊሠጡን አልቻሉም።" ብለዋል። ብዛታቸው 395 አካባቢ እንደሚሆን የተናገሩት ተመራቂዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሰኔ 16ቱ ጥቃት⬇️

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ባልደረባ የነበሩት አቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ ፖሊስ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያጠናቅቅ የመጨረሻ ቀጠሮ ሰጠ፡፡

ፖሊስ ችሎቱ በፈቀደለት 10 ቀናት የሰው ምስክር መቀበሉን ብሎም ከመስሪያ ቤታቸው የተገኘው ቦምብ ለምርመራ መወሰዱንና ሌሎች ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሷል፡፡ ለተጨማሪ የምርመራ ስራ 10 ቀናት እንዲፈቀድለትም ጠይቋል፡፡

የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በቁጥጥር ስር ከዋሉ 4 ወራት መቆጠሩንና ፖሊስ የሚጠይቃቸው የግዜ ቀጠሮዎች ተገቢነት የላቸውም በማለት ቅሬታችውን አቅርበዋል፡፡

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ቦምብ ከቤቴ ሳይገኝ ከቤቱ ተገኝቷል እያሉ በመዘገባቸው ሰብአዊ መብቴ ተነክቶብኛል የሚለውንም ጠቅሰዋል
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመጨረሻ ግዜ በማለት ትእዛዝ እንዲሰጥም አመልክተዋል፡፡

ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ] ከእውነታው ውጭ የሚዘግቡ መገናኛ ብዙሃን እንደሚጠየቁና ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የመጨረሻ ቀጠሮ በማለት 7 ቀናት በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለጥቅምት 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ኮሚቴ በኮንጎ #የኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ ሊወያይ ነው። ኮሚቴው በመጪው ረቡዕ ተሰብስቦ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ ተወያይቶ ዓለም አቀፋዊ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ላይ መድረስ አለመድረሱን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዲጂታል ቴክኖሎጂውን እያዘመነ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንተርኔት ሽያጩ ወደ 21 በመቶ ማደጉ ተገለፀ። አየር መንገዱ አገልግሎት አሰጣጡን #ቀልጣፋ እና #ተደራሽ ለማድረግ የትኬት ሽያጩንም ሆነ የክፍያ አማራጮቹን እያሰፋ ይገኛል። አሰራሩ በአየር መንገዱ የጥሪ ማዕከል፣ ድረ ገፅ እና ሞባይል አፕሊኬሽን ትኬት መቁረጥ የሚያስችል ስርዓት ነው።

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ ስሙን ሊቀይር ነው⬇️

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወታደራዊ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በማስረከብ በአዲስ ስያሜ ሊደራጅ ነው።

ከተቋቋመ ጀምሮ በጥቂት ጊዜ በርካታ የመንግስት ፕሮጀክቶችን እንዲይዝ ተደርጎ የነበረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከብቃት፣ እጦትና ከብክነት ጋር ተያያዘ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።

እጁ ላይ የነበሩ በርካታ የስኳር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ አቅቶት ፕሮጀክቶቹን ሲቀማ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሃይድሮ መካኒካል ስራዎችን ወስዶ መስራት ባለመቻሉም ቢሊየን ብሮች እንደባከኑ ተሰምቷል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኮርፖሬሽኑን አመራሮች ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድበት እያደረገ ነው።

የኮርፖሬሽኑ የኮመርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #አብዱልዓዚዝ_መሀመድ ለfbc፥ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ማስተካከል ነው።

ይህም በሜቴክ ስር ወታደራዊ ምርቶችን ሲያመርቱ የነበሩ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በመስጠት ቀሪዎችን በስሩ የሚያስቀጥል መሆኑንም ይናገራሉ።

በዚህ መሰረት ሜቴክ አዲሱን ስያሜ ይዞ የሲቪልና የንግድ ምርቶችን ብቻ የሚያመርት ሲሆን፥ የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል አዲስ ስያሜ ሊሰጠው እንደታሰበም ተናግረዋል።

ለዚህ አዲስ አደረጃጀት ረቂቅ ደንብ የተዘጋጀ ሲሆን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸቀደ በኋላ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

#ሜቴክ እስካሁን 14 ኢንዱስትሪዎችን ሲያስተዳድር የቆየ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወታደራዊ ምርቶችን የሚያመርቱ አራት ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ በመንግስት ተወስኗል።

ሆሚቾ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሽን፣ ጋፋት አርማመንት እና ልዩ ትጥቆች አምራች ኢንዱስትሪ የተባሉትን ነው ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ የተወሰነው።

ቀሪ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች በሜቴክ ወይም ወደፊት የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ በሚሰጠው ተቋም ውስጥ የሚተዳደሩ ይሆናል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ወታደራዊም የሲቪል ምርቶችንም ስለሚያመርት በማን እጅ መሆን ይኖርበታል የሚለውን ጉዳይ ለማጥናት ኮሚቴ መቋቋሙን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

አዲሱ ኮርፖሬሽንም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ የሚያንደረድሩ ምርቶች ላይ የሚሰማራ ይሆናል ብለውናል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ።

የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ አግኝቶ እንዲቋቋም የታሰበው ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ካፒታሉ እንደሚሻሻልለትም አቶ አብዱልዓዚዝ አንስተዋል።

ሜቴክ ከአመታት በፊት ሲቋቋም በ10 ቢሊየን ብር የተጠየ ካፒታል ነበር፤ ከዚህ ውስጥ የተከፈለው 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ አሁን ወታደራዊ ምርት አምራቾቹ ሲቀነሱ የተከፈለ ካፒታሉ ዝቅ ይላል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም ካፒታሉ ይከፈልለታልም ነው ያሉት አቶ አብዱላዚዝ።

አዲሱ ኮርፖሬሽን ከብቃት ማነስና ከብክነት ጸድቶ ለመሄድም እንደበፊቱ ኮርፖሬሽኑ አቅም ሳይኖር ብዙ ስራን ከመውሰድ ይልቅ፥ የተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ የሰው ሀይሉን በአግባቡ ለመጠቀም ታስቧል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኤርትራው ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በኢትዮጵያ ያደረጉት የሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ አስመራ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 6 እና 8 ቀን 2011 ዓ.ም 2ኛ እና 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል። ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት፥ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ #ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia