TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሰንደቅ አላማ ቀን⬆️

ሰንደቅ አላማ በመፈቃቀድ ላይ ለተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን የቃል ኪዳን ማህተም ነው አሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት #ዶክተር_ሙላቱ ተሾመ።

11ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተከብሯል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ⬆️ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከክቡር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን በጅማ ሰቃ አስደናቂ የተፈጥሮ ፏፏቴን ጎበኙ። ሰቃ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁን አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጅማ_ሰቃ የነበረው ደማቅ አቀባበል!

ቪድዮ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ፎቶዎች⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድና የኤርትራ ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ የሚገኘውን የሰቃ ፏፏቴን ዛሬ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ:- የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ቀናት⬆️የከፍተኝ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዚህ ጥሪ መሰረት ለጉዞ እንድትዘጋጁ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንድታዘጋጁ ትኬት መቁረጥ ይጨምራል።

ከዚህ ውጪ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ብቻ የሚያተኩረውን ቻናላችንን መጎብኘት ትችላላችሁ @tikvahuniversity
#update የስሎቬኒያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀምረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ቦሩት ፕሆር ከኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር ዛሬ ማለዳ በሁለትዮሽ በአህጉራዊና በወቅታዊ ጉዳዮች ጋር መምከራቸውን ተሰምቷል፡፡

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ⬇️

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የከተማውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ትዕዛዝ ከሰጣቸው 850 አውቶብሶች 700ዎቹን እስካሁን እንዳልተረከበ ተሰምቷል። ለአውቶብሶቹ 3.4 ቢሊዮን ብር #ተከፍሏል ነው የተባለው፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ወ/ሮ እፀገነት አበበ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 ሲናገሩ፣ ከሜቴክ ጋር የአውቶብሶቹን ስራ ውል የገባነው በሰኔ ወር 2009 ዓ/ም ሲሆን አውቶብሶቹን መረከብ የነበረብን ሰኔ 2010 ነበር ብለዋል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አውቶብሶቹን በቃሌ መሰረት ያላስረከብኩት በውጪ ምንዛሬ ችግር ነው ብሎናል ያሉት ወ/ሮ እፀገነት ከዚህ ወር ጀምሮ ግን ቀስ በቀስ ቀሪ 700 አውቶብሶቹን ሊያስረክበን ቃል ገብቶልናል ብለዋል፡፡

#ሜቴክ ለአውቶብሶቹ መስሪያ የሚያስፈልገውን እቃዎች አስቀድሞ ገዝቷል፣ በተባለው ጊዜም ያደርስልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ወ/
ሮ እፀገነት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia