TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጎንደር⬆️

"ዛሬ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 127 ወንድ እና 31 ሴት ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ እና ክቡር ዶ/ር አርቲስት መሃሙድ አህመድ በክብር እንግድነት ተገኝተው ነበር። ተማሪ ፍሬህይወት በከፍተኛ ነጥብ የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች። "

©Dave ከጎንደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ማርቆስ⬇️

"በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በከሠዓቱ መርሃ ግብር የአመቱን የስራ ሪፖርት የሚያቀርብ ሲሆን አጠቃላይ የተቋማት የተማሪዎች ህብረት አዲስ የምርጫ ደንብ ውይይት ተደርጎበት ከተወሰነ በኋላ MoE ከፍተኛ ትምህርት ድኤታ ይፀድቃል። ጎን ለጎንም በሰላማዊ መማር ማስተማር፣ መልካም አስተዳደር፣ ልዩ ድጋፍ ስለሚሹ ተማሪዎችን በተመለከተ እና ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ለተማሪዎች ህንረት ተልዕኮ የሚሰጥ ይሆናል። ጉባኤው "እኛ ተማሪዎች ሀገራችን በምታደርገው የላውጥ ጉዞ ሚናችን የጎላ ነው!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።"

©መሌ ከWKU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ተራዝሟል። ነገእ ግን 2ኛ አመት እና ከዚያ በላይ የመደበኛ ጤና ተማሪዎች ጥቅምት 1 እና 2 ወደተቋሙ እድትገቡ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬆️

"ፀግሽ መስከረም 27 በአካባቢያችን ወረዳ 4 የሚገኙ ውጤታማ ተማሪዎችን "ውጤታማ ተማሪዎችን በማበረታት ለተሻለች ኢትዮጵያ እንትጋ" በሚል መሪ ቃል እንሸልማለን:: በእለቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ #ኤፍሬም የወረዳ አመራሮች የሃይማኖት አባቶች አቲስቶች የሚገኙ ይሆናል። በከተማችን የላይበራሪ አጠቃቀማችንን የንባብ ባህላችንን አስመልክቶ ግሩም ዶክመንተሪ ይቀርባል። የዚህ ግሩፕ አባላትንም ጋብዘናል። አድራሻ መሳለሚያ ወርዳ 4 ወጣት ማእከል አዳራሽ፦ ኢትዮ የልማትና መረዳጃ እድር ከቀድሞ 01 ወጣት ተስፋ መረዳጃና የልማት ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ።እናመሰግናለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬆️

የኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ጉባዔ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ ከያንያን፣ የመብት ተሟጋቾች እና የማኅበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡ ‹‹ማኅበራዊ ሚድያ ለኢትዮጵያ አበርክቶቹ፣ ይሁንታዎች እና መርገምቶች›› የሚል የመነሻ ጽሑፍ በሥነ-ጽሑፍ ተመራማሪው ቴዎድሮስ አደላው ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopja
#update የቴክኒክ እና ሙያ መግቢያ⬆️

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ በ2011 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ #ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው #ዛሬ እንዳስታወቀው በየዓመቱ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል የሥራ ገበያውን መሰረት በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መስፈርት ተመርኩዞ የመቁረጫ ነጥቡን ይፋ እንዳደረገ አመልክቷል፡፡

በዚህም መሰረት በ2010 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል 725 ሺህ 652 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመደበኛው ዘርፍ እንደሚገቡ ኤጀንሲው አመልክቷል፡፡

ከዚህም ውስጥ 230 ሺህ 828 ሴቶች ናቸው፡፡ በመምህራን ኮሌጅ እንዲሁም በፖሊስና መከላከያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡት ቁጥር በዚህ መግለጫ አለመካተቱም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከላሊበላ⬇️

"ታላቅ ሰልፍ በላስታ ላሊበላ በነገው ዕለት ይካሄዳል። ቅርሱ ያለበት አሳሳቢ ሆኔታና የመሰረተልማት ጥያቄዎች ይነሳሉ። አስተባባሪዎች ጋር ውይይት አየተካሄደ ይገኛል፡ 8-12 የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማት ተገኝተዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢህአዴግ 36 ስራ አስፈፃሚ አባላት፦

1. ዶክተር #አብይ_አህመድ =ከኦዴፓ ሊቀመንበር
2. አቶ #ደመቀ_መኮንን =ከአዴፓ ምክትል ሊቀመንበር
3. አቶ ለማ መገርሳ =ከኦዴፓ
4. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ =ከኦዴፓ
5. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ =ከኦዴፓ
6. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ =ከኦዴፓ
7. አቶ አዲሱ አረጋ=ከኦዴፓ
8. አቶ ሽመልስ አብዲሳ =ከኦዴፓ
9. አቶ ፍቃዱ ተሰማ =ከኦዴፓ
10. ዶክተር ዓለሙ ስሜ =ከኦዴፓ
11. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው =ከአዴፓ
12. ዶክተር አምባቸው መኮንን =ከአዴፓ
13. አቶ ብናልፍ አንዷለም =ከአዴፓ
14. አቶ ተፈራ ደርበው =ከአዴፓ
15. ዶክተር ይናገር ደሴ =ከአዴፓ
16. አቶ መላኩ አለበል =ከአዴፓ
17. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ= ከአዴፓ
18. አቶ ምግባሩ ከበደ =ከአዴፓ
19. ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/አሚካኤል =ከህወሓት
20. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር=ከህወሓት
21. አቶ ጌታቸው ረዳ =ከህወሓት
22. አቶ አለም ገብረዋህድ= ከህወሓት
23. አቶ አስመለሽ ወልደስላሴ= ከህወሓት
24. ዶ/ር አብርሃም ተከስተ= ከህወሓት
25. ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም= ከህወሓት
26. አቶ ጌታቸው አሰፋ= ከህወሓት
27. ዶ/ር አዲስ አለምባሌማ= ከህወሓት
28. ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል =ከደኢህዴን
29. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ= ከደኢህዴን
30. አቶ ሞገስ ባልቻ =ከደኢህዴን
31. ዶክተር ጌታሁን ጋረደው =ከደኢህዴን
32. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ= ከደኢህዴን
33. አቶ መለስ አለሙ= ከደኢህዴን
34. አቶ ክፍሌ ገብረማርያም =ከደኢህዴን
35. አቶ ጥላሁን ከበደ =ከደኢህዴን
36. አቶ አብርሃም ማርሻሎ=ከደኢህዴን
ሆነው የተመረጡ ሲሆን በተጨማሪ የአጋር ድርጅት ሊቀመናብርቶች በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንዲሳተፉ ጉባኤው ወስኗል።

ምንጭ፦ ሶደሬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ⬆️የተማሪዎች የመግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች የ2011 ዓ.ም. የተማሪዎች የምዝገባ ቀን በድጋሜ መራዘሙን በይፋዊ #ፌስቡክ ገፃቸው እና በተቋማቸው ግቢ ውስጥ በለጠፉት ማስታወቂያ ላይ ገልፀዋል፦

. አክሱም ዩኒቨርሲቲ
. ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
. ዲላ ዩኒቨርሲቲ
. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
. አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
. ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
. ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
. ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ(esp.)
. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ
. ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
. ወሎ ዩኒቨርሲቲ
. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
. አምቦ ዩኒቨርሲቲ
. ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
. አርሲ ዩኒቨርሲቲ

ማሳሰቢያ፦ የተለወጠ ወይም የተሳሳተ መረጃ ካለ በፍጥነት አሳውቃችኋለሁ ወይም ማስተካከያ ሰጥበታለሁ።

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው #ለመመለስ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የአካባቢው ነዋሪዎችና ለጋሽ ድርጅቶች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ያሳዩት ተነሳሽነት ከፍተኛ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር #ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንደተናገሩት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ #በባህላዊና #ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ዕርቅ ለማውረድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

በተለይ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የየአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግስት አካላት በተገኙበት እርቅና ሰላም የማውረድ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ኮሚሽኑ ተፈናቃዮቹ ከሚገኙበት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ሲሆን ድጋፉን ለማጠናከር ተጨማሪ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች 17 ሺህ 468 ኩንታል ስንዴ ሩዝና አልሚ ምግብ፣ 146 ሺህ 194 የመመገቢያ ቁሳቁስ መጠለያና አልባሳትና 1 ሺህ 101 ካርቶን የዱቄት ወተት ወደ ስፍራው መላኩን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከዳሸን ባንክ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሲደረግ ከቡራዩና አካባቢዋ ለተፈናቀሉም እንዲሁ በሲውዘርላንድ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን 600 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ 10 ወረዳዎች የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 91 ሺህ 348 ደርሷል።

▪️በተጨማሪ በመላው አገሪቱ በመደበኛነት #በድርቅ አደጋ የሚረዱ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሉ ሲሆን ለጋሽ አካላት የተለመደ ትብብራቸው እንዲያደርጉ ጠይቋል።

በተለይ ዲያስፖራው፣ ባለሃብቶችና ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ይህንን ለመምራት የሚያስችል ኮሚቴ መዋቀሩንም ገልጸዋል።

በቅርቡ በምዕራብ ጉጂ፣ በጌዲኦ፣ በሶማሌና በቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በባህላዊ ስነ-ስርዓት የሕዝብ ለሕዝብ ስራ መሰራቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
162,400ባለፉት 3 ቀናት ብቻ TIKVAH-ETHIOPIAን የተቀላቀላችሁ 4,000 (አራት ሺ) ኢትዮጵያዊያን እንኳን ወደ ሁላችን ቤት መጣችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው ኢትዮጵያዊያን‼️

"በመላው አገሪቱ በመደበኛነት #በድርቅ_አደጋ የሚረዱ ከሰባት #ሚሊዮን በላይ ዜጎች አሉ ለጋሽ አካላት የተለመደ #ትብብራቸው እንዲያደርጉ ተጠይቋል።"
.
.
አንዳንዶቻችን ይሄን ረስተነው ይሆን በትንንሽ ጉዳዮች ተለያይተን እየተባላን የምንውለው?? ዛሬም በብሄር ተከፋፋለን የምንበሻሸቀው?? በጥላቻ ተሞልተን ስንሰዳደብ የምንውለው?? ዛሬም ሀገራችን #ለጋሾች እጃቸውን እንዲዘረጉላት #እየተማፀነች ነው። ዛሬም በሀገራችን በድርቅ አደጋ የሚረዱ በሚሊዮኖች ናቸው። ወገኖቼ ይህን ታሪካችንን እስከወዲያኛው ልንቀይር ይገባናል። ይህን መጥፎ ስም የምንቀይረው #በፌስቡክ ብሽሽቅ እና ስድብ፤ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሚሰጡን አጀንዳዎች እየተባላን አይደለም‼️ ተባብረን ሰርተን ከዚህ የደህነት እና የችግር ስም መውጣት አለብን‼️

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Walta Tv! አቶ ልደቱ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄ እየመለሱ ይገኛል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia