TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የሚመራውን የአሜሪካ የልዑካን ቡድንን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸውም #በሁለትዮሽ እና #ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድም በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየታየ ስላለው የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ለልኡካን ቡድኑ እንዳብራሩላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቬትናም ፕሬዝዳንት የሆኑትን ትራን ዳይ ኩዋንግን አመሻሽ ላይ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ሁለቱ አገራት በባህል፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የሁለቱን አገራት ትብብር የበለጠ ለማጠናከር #ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ፈጣን እድገትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካት ከቻሉት የምስራቅ እስያ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ቬትናም ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ 1976 መሆኑ ይታወሳል፡፡

©የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱማሌ ክልል⬆️

የሱማሌ ክልል ከ10 አመት በፊት የቀየራቸውን #ሰንደቃላማና የክልሉን #መጠሪያ ስም እንደገና ሊጠቀም እንደሆነ የVOAው ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ ጠቆመ።

የቀድሞ የክልሉ ፕሬዘዳንት አብዲ ሞሀመድ ኡመር(አብዲ ኢሌ) ከዛሬ አስር አመት በፊት ክልሉን ለማስተዳደር ሲሾሙ የሱማሌ ክልልን ኢትዮጵያዊነት የበለጠ ለማረጋገጥ በማለት የክልሉን ስም "ከሱማሌ ክልል" ወደ "ኢትዮዽያ ሱማሌ ክልል" ቀይረውታል። በተጨማሪ አብዲ ኢሌ የክልሉን ሰንደቃላማ እንዲቀየር አድርገው ነበር።

©ሀሩን ማሩፍ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መግለጫ⬆️በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ሲከናወኑ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/አስታውቋል፡፡ ኢሶህዴፓ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል ከላይ ባሉት ምስሎች ላይ ሙሉ መግለጫውን ማንበብ ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነሀሴ 26 ወደ ሀገሩ ይገባል። ይህን ተከትሎም የአቀባበል ስነ ስርዓቱን በተመለከት በነገው ዕለት በጌትፋም ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀርጌሳ⬇️

በሽሽት ላይ የነበሩ የተባሉ የሶማሌ ክልል ሁለት ባለስልጣናት ሶማሊላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘገበ።

የሶማሊላንድ ፖሊስ እንዳስታወቀው የኢትዮ ሶማሊ ክልል የፍትህ ቢሮ ሀላፊ #አብዲ_ጃማ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ #ኢብራሒም_አደን መሀድ ሀርጌሳ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ እጅ ይገኛሉ ተብሏል።

ሁለቱ ሀላፊዎች የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በፌደራል መንግስት ሀይሎች መያዛቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ወደ ጎረቤት ሶማሊላንድ እንደሸሹ #ጋሮዌ የተባለው የሶማሊላንድ ጋዜጣ ጠቅሶ ዋዜማ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ለዓመታት በስደት የቆዩት የሶማሌ ክልል የመብት ተሟጋቾች የቀድሞ የፓርላማ አባል መሀመድ ድርዬ እና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ አማካሪ አብዱላሂ ሁሴን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በሶማሌና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል የነበረውን ግጭት ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል። ለውጡን ለመደገፍም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋለ።

@tsegabwolde @tikahethiopia
#update ኮንግረስማን ክሪስ⬆️

የአሜሪካው ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ለውጥ #እጅግ አስገራሚ ነው ሲሉ ማምሻውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የመንግስት #ተቃዋሚ ሰልፈኞች አሁን ላይ #ሊረጋጉ እንደሚገባም ገልፀዋል።

HR 128 የተባለውን እና የኢትዮጵያ መንግስትን የሚነቅፈውን ህግ ያስፀደቁት ክሪስ ህጉ በቅርቡ እንደ አዲስ ለግምገማ ይቀርባል ብለዋል።

©Elias Meseret(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር አብርሀም በላይ በኢንጅነር አዜብ አስናቀ ምትክ ከነሐሴ 21/2010 ጀምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኅይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንደተሾሙ የሚገልፅ የአምባሳደር ግርማ ብሩ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ።

©Sheger 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ጌታቸው አሰፋ⬇️

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው እና ከአገር እንደሸሹ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን በስፋት ሲዘግቡት ሰንብተዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሔርን ስለጉዳዩ BBC ጠይቋቸዋል።

ወ/ሮ ፈትለወርቅ ''እንደ ድርጅት በዚህ ደረጃ #የምናውቀው ነገር የለም። ለድርጅት #የክስ መጥሪያ አይመጣም'' ይላሉ።

በአንድ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ላይ ድርጅቱ ሳያውቀው ክስ ሊመሠረት ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤
''ውይይት የሚያስፈልገው ነገር ካለ ፖለቲካዊ ግምገማና ይደረጋል እንጂ ክስን በተመለከተ የመንግሥት ሥራ ነው የሚሆነው'' ሲሉ መልሰዋል። ኾኖም የአቶ ጌታቸው ጉዳይ በግምገማም እንዳልተነሳ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ተናግረዋል።

የኢህአዴግና የሕወሓት የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው አሁን በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ #እንዳልተገኙ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠቁመዋል።

የአቶ ጌታቸው በስብሰባው ያለመገኘት ጉዳይ "የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ከሚለው ዜና ጋር የሚያያዝ ነው ወይ?" ተብለው የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ''አንድ ሰው ሰብሰባ ላይ በግል ጉዳይ ላይገኝ ይችላል። በስብሰባዎች ላይ ሁሉም ሰው ይገኛል ማለት አይደለም። የእሱ ከስብሰባ መቅረት ከዚህ ጋር ይገኛል ማለት #ላይሆን ይችላል። በሥራ ጉዳይም ላይገኙ ይችላሉ'' ብለዋል ወ/ሮ ፈትለወርቅ።

ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ጌታቸውን መቼ እንዳይዋቸው ከቢቢሲ የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ በቅርቡ ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ #መቀሌ እንዳገኟቸው አረጋግጠዋል።

📌በሌላ በኩል የፌዴራል አቃቢ ሕግ በአቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update በቴፒ ተቀስቅሶ የነበረው አለመረጋጋትና ውጥረት መርገቡ ተነገሯል። ካላይ ባለው የድምፅ ፋይል የVOAን ዘገባ ታገኛላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia