#update የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በአሁኑ ሰዓት ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጋር በሸራተን አዲስ #እየመከሩ ይገኛል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሙስጠፋ ማን ናቸው?⬆️
አቶ ሙስጠፋ ሙሐሙድ ዑመር በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሶማሌ ክልል #ጊዜያዊ መሪ ሆነው ተመርጠዋል።
አቶ ሙስጠፋ በክልሉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባል ባይሆኑም በጊዜያዊነት ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሥልጣን የቆዩትን አሕመድ አብዲ መሐመድን ተክተው ለመጪዎቹ ሁለት አመታት ክልሉን ይመራሉ።
በርዕሰ-መሥተዳድርነት እንዲያገለግሉ መመረጣቸው እስከተሰማ ድረስ ከነ ቤተሰቦቻቸው ኬንያ ይኖሩ የነበሩት አቶ ሙስጠፋ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶማሊያ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በመስራት ላይ ነበሩ።
ኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ የሕጻናት አድን ድርጅትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ አገልግለዋል።
አቶ ሙስጠፋ የተወለዱት ከጅጅጋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አዋሬ የተባለች አነስተኛ ከተማ በ1964 ዓ.ም. ነው። ትምህርታቸውን በደገሐቡር እና በሐረር የመድሐኒዓለም ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪቸውን በኤኮኖሚክስ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዚያው በኤኮኖሚክስ ከለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ በተልዕኮ ትምህርት አግኝተዋል።
ከዚህ ቀደም የሶማሌ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የዶክተር አብዱል መጂድ ሑሴን መምህራን ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
ከኢትዮጵያ ለምን ወጡ⬇️
አቶ ሙስጠፋ በቅርቡ ከሥልጣናቸው የተነሱት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክልሉን የርዕሰ-መሥተዳድርነት ሥልጣን ሲቆጣጠሩ ነው የሶማሌ ክልልን የለቀቁት።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤኮኖሚክስ ተማሪ ሳሉ የአቶ ሙስጠፋ ጓደኛ የነበሩት አቶ ዚያድ አሕመድ የቀድሞው ርዕሰ መሥተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር "ያደርሱባቸው የነበረውን ችግር #ሸሽተው" ከነ ቤተሰቦቻቸው #ኬንያ ለመግባት መገደዳቸውን ያስታውሳሉ።
ከሁለት አመታት በፊት አቶ ሙስጠፋ በክልሉ መንግሥት ላይ የሚሰነዝሩትን ተቃውሞ እንዲያቆሙ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ አሻፈረኝ በማለታቸው የምኅንድስና ባለሙያ #ወንድማቸው ፋይሰል ኦማር በልዩ ፖሊስ ከደገሐቡር ከተማ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ #መገደላቸው ይነገራል። አቶ ዚያድም "ውጪ ያሉት አራማጆች በአብዲ ኢሌ ላይ ወይም በነበረው አገዛዝ ላይ ተቃውሞ ካሰሙ ወይም አንድ ነገር ካደረጉ ቤተሰቦቻቸው ይታሰራሉ ወይም ይገረፋሉ። አቶ ሙስጠፋም ወንድማቸውን ያጡት በዚህ አጋጣሚ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ዚያድ የድሮ ጓደኛቸው የሶማሌ ክልልን ለመምራት ይመረጣሉ የሚል ቅድሚያ ግምት አልነበራቸውም። "አልጠበቅኩም። እሱ የውጪ ሰው ነው። የፓርቲ አባልም አልነበረም" ይላሉ። አቶ ሙስጠፋ ከዚህ ቀደም ክልሉን ይመሩ የነበሩት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ የለውጥ አቀንቃኝ ነበሩ። በክልሉ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጋልጡ የቀድሞውን አስተዳደር
የሚሞግቱ ጽሁፎች በሶማሊኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ ቆይተዋል። በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጎላ ተሳትፎ ነበራቸው።
የሶማሌ ክልል ፖለቲካን በቅርብ የሚከታተሉት አቶ ዚያድ ተመራጩ ፕሬዝዳንት በርካታ እና ውስብስብ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው አልዘነጉም። "የሕግ የበላይነት፣ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት አለበት። ሥራ አስፈፃሚው፣ ሕግ አውጪው እና ሕግ ተርጓሚው ሪፎርም ይፈልጋል" ይላሉ አቶ ዚያድ።
ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ (DW Amharic)

#update 693 የህግ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት መለቀቃቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡ በህገ- መንግስታዊ ስርአቱ ላይ የሚደረግ ወንጀል፣ የጦር መሳሪያን ይዞ ለእርስ በእርስ ጦርነት ማነሳሳት፣ በሀገር ክደት፣ በስለላ ወንጀልና ሌሎች መሰል ወንጀሎች ተከሰው በቀጠሮ የነበሩ እንዲሁም የተፈረደባቸው 209 ታራሚዎች ከእስር እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ባሳዩት መልካም ስነ- ምግባር በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው በማረሚያ ቤት ለነበሩ 484 የህግ ታራሚዎች #ይቅርታ በማድረግ ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ መደረጉ ተገልጿል፡፡
©etv
@tsegbwolde @tikvahethiopia

#update የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ⬇️
‹‹የድርጅቱ #ስያሜ እና #ዓርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም በመባሉ ይመከርበታል፡፡››
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን ወደፊት የሚመራባቸውን የፖለቲካ መስመሮች ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ እናሻሽል ወይም አናሻሸል በሚሉ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ካሉ አመራሮች የሰበሰባቸውን መሰረታዊ የማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና ድርጅቱ በቀጣይ ስለሚከተላቸው የፖለቲካ መስመሮች ላይ ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና በብአዴን ጽ/ቤት የገጠር ፖለቲካ ና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ማዕከላዊ ኮሚቴው በ12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከፍተኛ ጊዜ ሰጥቶ ይወያል ብለዋል፡፡
ብአዴን ከ11ኛ መደበኛ ጉባኤ በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት የታዩ ለውጦችን ይገመግማል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው በ12ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ ድርጅቱ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለይቶ ለማቅረብ እንዲቻል ትኩረት ሰጥቶ ይወያያል፡፡
ድርጅቱ ባለፉት ጊዜያት ይመራባቸው የነበሩ ህጎች አንዳንዶቹ ወቅቱን ያላገናዘቡ በመሆኑ እና የድርጅቱ አመራሮችም ቢሻሻሉ ብለው ያቀረቧቸው በመሆኑ ማዕከላዊ ኮሚቴው በጥልቀት ተወያይቶ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል የሚላቸውን ጉዳዮች ውሳኔ በማሳለፍ በጉባየው ላይ ያቀርባል ብለዋል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው ሌላው የድርጅቱን የ2011ዓ.ም ዕቅድ እና በጀትን ጨምሮ የጉባኤው ሪፖርት እና የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በምክክሩ ላይ የድርጅቱ ስያሜ እና አርማ ምን ይሁን በሚሉ ጉዳዮች ላይ ተመክሮ እንደሚወሰን አቶ አቶ ምግባሩ ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ ባለፈው የአመራር ስብሰባው ላይ አመራሮች የድርጅቱ ስያሜ እና አርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም የሚሉ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ማዕከላዊ ኮሚቴውም ይህን ጉዳይ አንድ እልባት ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ብአዴን ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ምን መሆን አለበት እና የአማራን ህዝብ ጥቅም ድርጅቱ እንዴት ማስጠበቅ አለበት በሚሉ ጉዳች ላይ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
©አብመድ

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#ለፈገግታ ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ አደረገ የሚለውን ዜና በወፍ በረር ሰምቶ ባለ 5 ብር ካርድ ስንት ብር ገባ? ብሎ በኢንቦክስ ከሚጠይቅ ሰው ይሰውራችሁ😢ምን ብዬ ልመልስለት?
©ቴድዎድሮስ ወለደሚካኤል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ቴድዎድሮስ ወለደሚካኤል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2011 የምዝገባ ቀናት እንዲሁም የዓመቱን ትምህርት መጀመሪያ ቀን ከላይ ባለው ምስል ማግኘት ትችላላችሁ።
#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Vacancy
Hello Tsega, We're looking to hire candidates for a new chain hotels we're setting up.Three people for now.
1. Hotel Management Assistant
2. Hotel Sales and Marketing (2 people)
They need to have fitting experiences in the hotel field.
They can contact us through 0111262921.
Thank you.
#Addis_Abeba
©Is

#ክፍት_የስራ_ቦታ፦
◾️የስራ አይነት-ፀሀፊ
◾️ክፍያ-በስምምነት
መስፈርት፦
-እንጊልዘኛ መፃፍ እና ማንበብ የሚችል
-መሰረታዊ የሆነ ኮምፒዩተር መጠቀም ሚችል
ቦታ- አዲስ አበባ,
0913628772 ይደውሉ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
◾️የስራ አይነት-ፀሀፊ
◾️ክፍያ-በስምምነት
መስፈርት፦
-እንጊልዘኛ መፃፍ እና ማንበብ የሚችል
-መሰረታዊ የሆነ ኮምፒዩተር መጠቀም ሚችል
ቦታ- አዲስ አበባ,
0913628772 ይደውሉ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድንን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው እያነጋገሩ ነው፡፡ የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነትን አንድ ምዕራፍ ከፍ የሚደርጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል፡፡
©የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር #አብረሃም_በላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው #ተሹመዋል። ዶ/ር አብረሀም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ ኢኒስቲቲዩት ዳይሬክተር ነበሩ።
©capital
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©capital
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መጪው አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በዓሉ ከ25 ሺህ በላይ ህዝብ በሚገኝበት #በሚሊኒየም_አዳራሽ በድምቀት እንደሚከበር ተናግረዋል።
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia