TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ህወሓት ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ። በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ተወስኗል። የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት  6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ…
#Update #TPLF

" ቦርዱ ከፌደራል መንግስት ጋር የጀመርነውን ተከታታይ ውይይት ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት  6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር  ፤ ይህንን ባለማድረጉ ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታደግ ፤ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ መወሰኑ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። 

ህወሓት ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረ አንጋፋ ፓርቲ መሆኑ የገለፅው መግለጫው ፤ " ጥቅምት 23/2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካዋ የፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ውል ከተፈራረመ ጀምሮ ህጋዊነት የተመለሰ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓትን በአዲስ ህግ እንደ አዲስ ፓርቲ " መዝግቤዋለሁ ማለቱን " አስገራሚ እና ተቀባይነት የሌለው ፤ ፓርቲው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ማግስት ህጋዊነቱ ያረጋገጠ ነው " ብሏል።

" የምርጫ ቦርድ አካሄድ በመሰረቱ ተቀባይነት የሌለው ፤ ህግን መሰረት ያላደረገ ተቀባይነት የሌለው ትርጉም አልባ ውሳኔ ነው " ብሎታል።

" ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ተሰጣጥቶ የሰላም ውል የፈረመ ፓርቲ ነው " ያለው ህወሓት ፤ " ከኢፌዲሪ መንግስት ተከታታይ የፓለቲካ ውይይት በማካሄድ ላይ ነን። ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰላማዊ ውይይቱ ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ " ሲል አቋሙ ግልጿል።

ህወሓት ከኢፌዴሪ መንግስት በተከታታይ በማካሄድ ላይ ያለው ውይይት ውጤታማ በቅርቡ ወደ ፍሬ የሚቀየር መሆኑ የገለፀው ህወሓት " የምርጫ ቦርድ ይህንን መልካም ሂደት የሚፃረር አካሄድ በመሄድ ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።

የኢፌዴሪ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመተግበር ህገ-መንግስቱ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠየቀው ህወሓት ፥ የምርጫ ቦርዱ ውሳኔ 50ኛው የፓርቲው የምስረታ በዓል ከማክበር እንደማያግደው በመግለፅ " ህዝቡ በዓሉ ለማክበር የጀመረው እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥል " ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Breaking : የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሚኒስትሩ አብረዋቸው ለውድድር የቀረቡትን የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እንዲሁም የማዳጋስካሩን ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው የተመረጡት። @tikvahethiopia
#Update

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ 6 ዙር ከፈጀው የድምጽ አሰጣጥ በኋላ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው መመረጥ ችለዋል።

የምርጫ ሂደቱ ምን ይመስላል?

በምርጫው የሚያሸንፈው ተመራጭ ድምጽ መስጠት ከሚችሉት 48 አባል ሀገራት ሁለት ሶስተኛውን ድምጽ (33 ድምፅ) ማግኘት ይጠበቅበታል።

በሚደረገው ምርጫ ለማሸነፍ የሚያስፈልገውን 33 ነጥብ ማግኘት ካልተቻለ ተከታታይ ምርጫዎች የሚካሄዱ ሲሆን ዝቅተኛ ድምጽ ያገኘው ከውድድሩ ተሰናብቶ ቀሪ ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ የሚያስችላቸውን ነጥብ እስኪያገኙ ይወዳደራሉ።

በዚህም ለ7ኛ ጊዜ በተደረገው በዚህ ውድድር አሸናፊውን ለመለየት 6 ዙሮች ፈጅቷል።

በመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዙሮች የኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መምራት ቢችሉም የማሸነፊያ ነጥብ ሳያገኙ ቀርተዋል።

በስድስተኛው ዙር ድምጽ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለማሸነፍ የሚያስፈልጋቸውን 33 ነጥብ በማግኘታቸው ምርጫውን አሸንፈዋል።

በዚህም ለቀጣይ 4 ዓመታት የቀድሞውን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂን በመተካት 7ኛው የኅብረቱ ሊቀመንበር በመሆን መመረጥ ችለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 “ የተሰጠው መልስ ከእውነት የራቀና በህዝቡ ስቃይ እንደመሳለቅ የሚቆጠር ነው ” - አርሶ አደሮች

➡️ “ አንድ ኩንታል እንደዬአካባቢው ስለሚለያይ ይህን ያክል ነው ብለን ለመግለጽ ያስቸግረናል ” - ግብርና ሚኒስቴር 


ሀዋሳ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና በበቆሎ ምርጥ ዘር ዘንድሮ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ከአምናው እጥፍ በላይ በመጨመሩ ማምረት እንደማይችሉ ሰሞኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ድምፃቸውን ማሰማታቸው አይዘነጋም።

“ አምና 3,600 ብር ስንገዛው የነበረውን ማዳበሪያ ዘንድሮ 8,400 ብር ለመግዛት ተገደናል። አምና 1,800 ብር  የነበረው የአንድ ፕሎት ምርጥ ዘር በቆሎ ዘንድሮ 4,600 ብር ገብቷል ” ሲሉ ነበር ያማረሩት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ምላሽ የጠየቀው የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ፣ “ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። የጨመርነው ነገር የለም። የትራንስፓርት ብቻ ነው የጨመርነው ” ብሎ፣ የምርጥ ዘር በቆሎ ዋጋም ከትራክተር፣ ከነዳጅ ዋጋ ጋር በተያያዘ መጨመሩን ቢሮው አልደበቀም።

አርሶ አደሮቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በድጋሚ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

“ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ የሰጠው ምላሽ አጥጋቢ ካለመሆኑም አልፎ ከእውነት የራቀና በህዝቡ ስቃይ እንደመሳለቅ የሚቆጠር ነው። ምላሹ ‘ማዳበሪያ ላይ  የተደረገው ጭማሪ የትራንስፖርት ብር ብቻ ነው’ ብሏል።

የትራንስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ለማዳበሪያ በአመት 4,000 ብር መጨመር ዝርፊያ እንጂ ጭማሪ አይባልም። የበቆሎውን በተመለከተም ቢሮው፣ የትራክተርና የነዳጅ ጭማሬን በመጥቀስ ነው ምላሽ የሰጠው።

ለህዝቡ ማሳውን የሚያርሰው መንግስት አይደለም ህዝቡ በራሱ ገንዘብ እንጂ። ስለዚህ የማይገናኝ ነገር አገናኝቶ ህዝቡን ማሰቃየት አግባብ አይደለም። 

በቆሎ የሚዘራው ከታህሳስ 15 ጀምሮ ነው። የሻመና ህዝብ ለአንድ ፕሎት እስከ 17,000 ብር በላይ አውጥቶ እንዴት ሊገዛ ይችላል ? ምንስ ሊያተርፍ ነው ? በዚህ ኑሮ ውድነት ገንዘቡንስ የት ነው የሚያመጣው ? ነው ወይስ ህዝቡን ነገ በረሃብ መቅጣት ነው የተፈለገው ? 

በአንድ በኩል ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ የማይጠቀም አርሶ አደር እንዳይኖር ያስገድዳሉ፣ በሌላ በኩል ዋጋ በማናር እንዳይጠቀም ማድረግ አይጋጭም ? አርሶ አደሩ ዘንድሮ ምርት አያመርትም። መንግስት ችግሩን ይፍታልን ”
ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሩ ሲከፋፈል ዋጋው ምን ያክል ነው ? አርሶ አደሮች ዘንድሮ የተጋጋነ ዋጋ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል። ጭማሬው ከላይ ነው ከታች ? ኩንታል ማዳበሪያ (ለምሳሌ ዳፕ) ዋጋው ስንት ነው ? ሲል ለግብርና ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ምን መለሱ?

“ አንድ ኩንታል እንደዬአካባቢው ስለሚለያይ ይህን ያክል ነው ብለን ለመግለጽ ያስቸግረናል። ምክንያቱም በርቀቱ ስለሚወሰን። በትራንስፓርት ነው የሚለያዩት። 

ከዚያ ውጪ በሁሉም የአገራቷ ክፍል የሚሰራጨውን ማዳበሪያ ሴንትራሊ ዋጋ አውጥቶ የሚልከው ግብርና ሚኒስቴር ነው። ዋጋ ስናወጣ በግብርና ሚኒስቴር በኩል የሚጨመር ምንም አይነት የፕሮፊት ማሪጅን የለም። 

ማዳበሪያው የተገዛበት፣ የትራንስፓርትና ሌሎች እንዲሁም ወጪዎች ተደርገው የአንድ ኩንታል ዋጋ ተሰልቶ ነው ወደ ታች የሚወርደው። መንግስት 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል።

ማዳበሪያ ከአምናው አንጸር ሲወዳደር ዋጋ በተወሰነ መንገድ ጨምሯል። ስለዚህ ታች የጨመረ ዋጋ ሳይሆን ማዳበሪያው የተገዛበት፣ ከሪፎርሙ ጋር የተወሰነ የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ ስላለ፣ በዚያ ምክንያት የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። 

ማዳበሪያ በዶላር ከውጪ ነው የሚገዛው። ታች ሊጨመር የሚችለው ትንሽዬ ወይ 100 ብር ወይ 50 ብር የዩኒየን ማሪጅን፣ ወደ ታች ደግሞ ሲወርድ እኛ እስከ ማዕከላዊ መጋዘን ነው የምናቀርበው። 

ከማዕከላዊ መጋዘን ወደ መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማኀበር ሲያወርዱ ሁሉም ክልሎች እንደየርቀቱ የትራንስፓርት ዋጋ ልዩነት ይኖራል። 

ስለዚህ አንድ ኩንታል ዋጋ ይሄን ያክል ብር ነው ብልህ ሀገራዊ ዋጋን ሪፕረሰንት ስለማያደርግ እንደዬ አካባቢው የተለያዬ ነው የሚሆነው። ግን ሴንትራሊ ለሁሉም የተገዛበትም ድጎማውም እኩል ነው የሚሰራው ”
ብለዋል።

በአጠቃላይ ያለውን አቅርቦት ሲያስረዱም፣ “ 24 ሚሊዮን ኩንታል ነው የምናቀርበው። እስካሁን የ13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ ፈጸመናል ” ነው ያሉት።

(ማዳበሪያን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ። ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ…
#Update

" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል። 

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።

በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።

ከቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በተጨማሪ ተመሳሳይ ክስ ተመሰርቶባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራም በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 “ የአማራ ክልል ምሁራንና ሊህቃን በሰፊው እስር ቤት ነው ያሉት። አንድ ህዝብ ሊህቃን ታስሮበት ሊሳተፍ አይችልም ” - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) 

➡️ “ ጫካ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጀንዳ አልመጣም ብዬ አላስብም ” - ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)


የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመታት ሪፓርት ለፓርላማ ማቅረቡ፣ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ/ም ሦስት አመቱን የሚደፍነው የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ በቋሚ ኮሚቴው ለአንድ አመት መራዘሙ ታውቋል።

ኮሚሽኑ በሪፓርቱ፣ በ10 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች የምክክር፣ የአጀንዳ ልየታ እና ለሀገራዊ ምክክር የሚሳተፉ ተወካዮች የማስመረጥ ተግባራትን እንዳጠናቀቀ አመልክቷል።

በአማራ ክልል ያለው ሥራ መቀጠሉን፣ የትግራይ ክልል ገና መሆኑም ተመላክቷል።

ሪፓርቱ በቀረበበት ወቅት የፓርላማ አባት ያነሷቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ?

የኮሚሽኑ ሪፓርት ከቀረበ በኋላ አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት በተለይ የጸጥታ ችግር ያሉባቸው አካባቢዎች ለምክክሩ የገጣማቸውን የተሳትፎ ውጥንቅጥ የሚመለከቱ ጥቄዎችን ሰንዝረዋል።

አንድ የፓርላማ አባል፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ማኅበረሰቡ በንቃት ነው የተሳተፈው? ለሀገር እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ለማስቀረት ኮሚሽኑ ምን እየሰራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

ሌላኛው የፓርላማ አባል ደግሞ፣ ፓርቲዎች ከምክክሩ የወጡበት ምክንያት ምንድን ነው? አጀንዳቸውን አሁንስ በምን መልኩ ነው የሚሰጡት? በማለት ጠይቀዋል።

የታጠቁ ኃይሎችና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምክክሩ እንዳልተሳተፉ ሲናገሩ የተደመጡት ሌላኛው የፓርላማ አባል፣ ወደ ፊት ኮሚሽኑ በዚሁ ጉዳይ ምን ለመስራት እንዳሰበ ማብራሪያ ጠይቀዋል።

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጠው ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎችም የህዝቡ ተሳትፎ ጥሩ እንደነበር፣ ፓርቲዎችም ሆኑ ታጣቂዎች አሁንም አጀንዳቸውን ካቀረቡ በሩ ክፍት መሆኑን ገልጿል።

የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ምን ጠየቁ?

ጠንከር ያሉ ሀሳቦችን በማቅረብ የሚታወቁት የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)፣ “የአማራ ክልል ምሁራንና ሊህቃን በሰፊው እስር ቤት ነው ያሉት። አንድ ህዝብ ሊህቃን ታስሮበት ሊሳተፍ አይችልም” ሲሉ ተችተዋል።

በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ አካላት አጀንዳቸውን እንዳላቀረቡ፣ የአካታትነት ችግር እንዳለ ገልጸው፣ “ይህ ባልተካሄደበት ሁኔታ ምን አይነት ምክክር ማድረግ ይቻላል?” ሲሉም ጠይቀዋል።

በአማራም ሆነ ኦሮሚያ ክልሎች ባለው ጦርነት ኮሚሽኑ የተኩስ አቁም ጥሪ ማድረግ እንደሚገባው ገልጸው፣ “ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቁርጠኝነት ችግር እንዳለ አያለሁ” ነው ያሉት።

እንዲሁም የጸጥታ ችግር ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የመመካከር ደኅንነታቸው ላይ ችግር መፍጠሩንም የተናገሩ ሲሆን፣ “አማራ ክልል ህዝቡ ከፍተኛ ትራውማ ውስጥ ገብቷል። ከክልሉ ውጪ ያሉትም የማንነት ጥቃት ሰለባ ሆነዋል” ብለዋል።

ሥጋት ለሚያነሱ ሰዎች የተለያዩ ፍረጃዎች እየተሰጠ የሚኬደው ነገር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ፣ ኮሚሽኑ በትጥቅ ትግል ያሉ አካላትን እንዲያካትት አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ፣ መንግስትና በልጽግና አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ለዚሁ ጥያቄ አጸፋ የሰጡት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ እነደሳለኝና አብን ፓርቲያቸው ምን አስተዋጽኦ አድርጓል? ሲሉ ጠይቀዋል።

የታጠቁ አካላት በምክክሩ ባለመሳተፋቸው ደሳለኝ (ዶ/ር) ባቀረቡት ትችት የተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) አጸፋ፣ “የታጠቁ ቡድኖችም ሁሉም አይደሉም ያልተሳተፉት” ሲሉ ተደምጠዋል።

የተሰወሱ የፋኖ ክንፎች ሁኔታም አንስተው፣ እነ ጃል ሰኒ ደግሞ በምክክሩ እንደተሳተፉ የገለጹ ሲሆን፣ “የቀሩት የሸኔ ክፋይ የተለዬ ሀሳብ አላቸው ብለን አናምንም” ብለዋል።

ተስፋዬ ዶ/ር)፣ ጉዳዩን እያጋጋልን ነው የቆየነው ወይስ ጉዳዩ ወደ መሀል እንዲመጣ አድርገን ለመፍትሄ እየሰራን? ሲሉም ፓርቲዎችን የተመለከተ ጥያቄ አቅርበዋል።

የሀገሪዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) በበኩላቸው፣ ኮሚሽኑ በአማራ ክልል የተሳትፎ ልየታ እንዳደረገ፣ የቀሩት 8 ወረዳዎች ብቻ እንደሆኑ ምላሽ ሰጥተዋል።

በጫካ ስላሉ አካላት አጀንዳ አለመቅረብ በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ሲመልሱም፣ “ጫካ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጀንዳ አላመጡም ብዬ አላስብም” ብለው፣ በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ጎንደር ያሉ ክላስተሮች የሕዝቡን ችግር እንዳስረዷቸው ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ። የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም…
#Update

የቀድሞዉ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች ነፃ ቢሆኑም የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀሪ መዝገቦች አሉባቸው።

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተመሰረተባቸው ሁለት ክሶች ነፃ መባላቸዉን መዘገባችን አይዘነጋም።

ነገርግን የቀድሞ ከንቲባ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀሪ አራት ክሶች እንዳሉባቸዉና ፍርድ ቤቱ ለዉሳኔ ቀነ ቀጠሮ መስጠቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጠበቆች አረጋግጧል።

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የነበራቸዉን ሁለት የክስ መዝገቦች አስመልክቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ ያደረሱት ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክላይ " አንድ ዓመት ሙሉ ስንከታተል የነበረው የሙስና (ወይንም) ጉቦ የመቀበል ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የመጠቀም ወንጀል " በሚል ቀርቦባቸዉ ከነበረዉን ክስ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳና አከባቢዋ ምድብ ችሎት ዛሬ ሙሉ በሙሉ በነፃ አሰናብቷቸዋል።

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ ቀሪ የክስ መዝገቦች እንዳሏቸዉ የጠቀሱት ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክላይ እሳቸዉ ግን ጥብቅናቸዉ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለነበራቸው ሁለቱ መዝገቦች ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጊዜ ቀጠሮ ላይ ባሉ መዝገቦች ዙሪያ ጉዳዩን ከያዙ ጠበቆች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ ለጊዜዉ አልተሳካም።

መረጃዎችን እንዳገኘን ተጨማሪ ዘገባ የምናደርስ ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል። በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። ያጋጠመ ሞት የለም። ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ?  በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት…
#UPDATE

" ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር

" ሃይል በመጠቀም የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ የሚደረግ ህገ-ወጥ እርምጃ ተቀባይነት የለውም " አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ። 

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ የካቲት 13 /2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ ገበሬ ማህበር የትግራይ ኃይል አባላት በነዋሪ አርሶ አደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት አውግዟል።

" የተወሰኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን ነው " ያለው መግለጫው " በሰሓርቲ ወረዳ የተከሰተው አሳዛኝ ተግባር እንደ አንድ ማሳያ መውሰድ ይቻላል " ብሏል።

" ሰራዊቱ የህዝብ ህልውና ለመጠበቅ እንጂ የአንድ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት የተሰለፈ አይደለም " ያለው ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።

" ማንኛውም የህግ ወይም የአስራር ክፍተት ሲኖር የሚሊሻና የፓሊስ ሃይል ከህዝባቸው በመተባበር የሚፈቱት እና የሚያርሙት እንጂ ሰራዊት ወደ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ማሰማራት የሚያስገድድ ሁኔታ ፈፅሞ እንደሌለ የለም " ሲል ገልጿል።

" ይህንን ህገ-ወጥ አካሄድ የሚያበረታቱ እና የሚያግዙ ፓለቲከኞች እና የሰራዊት አመራሮች አደብ እንዲገዙ " ሲልም አስጠንቅቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Update

በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ሚስቱና የእህቷ ባል የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸዉ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ።

ባሳለፍነዉ ዓመት መጋቢት 17/2016 ዓ/ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህርዳር ከተማ ተጫዋች የነበረዉ አለልኝ አዘነ በአርባምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ በርካቶችን ያሳዘነ እንደነበር አይዘነጋም።

በተጫዋቹ አሟሟትና ሌሎች ሁኔታዎችን መነሻ አድርጎ ፖሊስ ሚስቱንና የእህቷን ባል በቁጥጥር ስር አዉሎ ክስ መመስረቱ የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቀደምሲ ል በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን ሰሞኑን ከጋሞ ዞን ፍትሕ መምሪያ ባገኘዉ መረጃ እስካሁን በነበረዉ ሂደት ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸዉን የሰዉ፣ የሰነድና የምርመራ ማስረጃዎችን በማቅረብ ለፍርድ ቤቱ ክሱን አስረድቷል።

ጉዳዩን የያዘዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሾች የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለየካቲት 10/2017ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ተከሳሾች አሟልተዉ ማቅረብ ባለመቻላቸዉ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ለመጋቢት 10/2017 ዓ/ም መሰጠቱን የጋሞ ዞን ፍትህ አካላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

አርባ ምንጭ ከተማ በተለምዶ ልማት ሰፈር ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ተወልዶ ያደገው አለልኝ አዘነ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ተስፋ ከተጣለባቸውና በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በተለያዩ ቡድኖች ዉጤታማ እንቅስቃሴ የነበረዉ አማካይ ተከላካይ ነበር።

ተጫዋቹ ሕይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስ የባሕር ዳር ከተማ ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋች የነበረ ሲሆን ከዚያ አስቀድሞ በሐዋሳ ከተማ እና በመቐለ 70 እንደርታ ዉጤታማ ጊዜ አሳልፏል።

ጉዳዩን እስከመጨረሻ የምንከታተለው ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“የባለስልጣናት ያልተገሩ ንግግሮችና የመንግስትም ተቀዳሚ ተግባሩን ፍጹም መርሳት ሕዝብን ለእልቂት እየዳረገ ነው”- ፓርቲው እናት ፓርቲ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣውና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ፣ “መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ መላ ኢትዮጵያውያንን የደኅንነት ዋስትና ያሳጣው ሀገራዊ እልቂት አሁን አሁን ወደ ሀገራዊ ቀውስነት እያደገ ነው ለማለት ያስደፍራል” ሲል ተችቷል። አክሎ፣ “ለዚህ…
#Update

በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ በተፈጠረው ችግር የተፈናቀሉና ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ሰዎች ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ፣ በጥቃቱ የተሳተፉት አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡ እናት ፓርቲ አሳሰበ።

ወደ 10 ሺሕ ወገኖችን የከፋ ዞን በቀናነት ተቀብሎ እንዳስጠለለና የተወሰኑት ወደ ቄያቸው እየተመለሱ እንደሆነ መገንዘቡን፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለሱን ተግባር በመልካሙ እንደተረዳው፣ ይሁን እንጂ አሁንም ትኩረት የሚሹ ወገኖች እንዳሉ በላከንልን መግለጫ ገልጿል።

“ በአንጻሩ ቤት፣ ንብረት የተቃጠለባቸው በትምህርት ቤቶች ተጠልለው ስለሚገኙ፣ አሁንም አላስፈላጊ ወከባዎችና ‘ያላስረከባችሁት መሣሪያ አለ አምጡ’ በሚል ማንነት ተኮር ማሳደድ እየደረሰ እንደሚገኝ” አስረድቷል።

“እንዲያውም የተወሰኑ ሰዎች ተመልሰው ለመፈናቀል እየተዳረጉ መሆኑን፣ በግድያና ማቃጠል የተሳተፉ በውል ተጣርቶ ለፍርድ አለመቅረባቸውና ፍትህ አለመስፈኑ ችግር እንደፈጠረ፣ ሕዝቡ ሀብትና ንብረቱን ስላጣ ለረሃብ እንደተጋለጠ ለመረዳት ችለናል” ነው ያለው።

“ ስለሆነም አሁንም በአቅራቢያ የሚገኘው የመከላከያ ኃይል የማረጋጋቱን ሥራ ወስዶ እንዲሰራና ቤታቸው ተቃጥሎ በድንኳንና ትምህርት ቤት የተጠለሉ ወገኖቻችን በአፋጣኝ የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻች በአጽንዖት እንጠይቃለን ” ሲል አሳስቧል።

የተፈጠረውን “ሞትና ከፍተኛ የንብረት ውድመት” ያስከተለ፣ “እጅግ አስከፊ ማንነት ተኮር ጥቃት” በማውገዝ የመከላከያ ኃይል ቦታውን እንዲቆጣጠረው፣ ተፈናቃዮች ወደ የቄያቸው እንዲመለሱ፣ “ወደ እልቂት የሚመሩ የባለስልጣናት ያልተገሩ ንግግሮች እንዲታረሙ” ከዚህ ቀደም ማሳሰቡን ፓርቲው አስታውሷል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
            
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከ3,000 ወጣቶች ወደ 130 የሚሆኑት ወጡ ተብሎ ዝም የሚባል ከሆነ ለቀሪዎቹ አደጋ ነው " - የወላጆች ኮሚቴ ሰርተው ለመለወጥ በሚል ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች በማይናማር በአጋቾች የከፋ ስቃይ እያሳለፉ በመሆኑ መንግስት ከስቃይ እንዲታደጋቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ አይዘነጋም።  የወላጆች ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያዊያኑ በታገቱበት የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ አጋቾች ልጆቹን ዶላር ማጭበርበር…
#Update

🔴 “ መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ ከእገታው የወጡት ኢትዮጵያዊያንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል ” - ቤተሰብ

🔵
እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም? ” - ኢትዮጵያዊ በታይላንድ

➡️ “ ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው ” - የወላጆች ኮሚቴ

ሰርተው ለመለወጥ ሲሉ ተታለው ወደ ታይላንድ የተሰደዱና በታጣቂዎች በማይናማር ታግተው ቆይተው የወጡና አሁንም በእገታ ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስት እንዲደርስላቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል።

በሺዎች ከሚቆጠሩት ኢትዮጵያዊያን ታጋቾች ውስጥ 13ዐ የሚሆኑት ከሳምንታት በፊት ከእገታ እንደተለቀቁ፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ገና ከእገታው እንዳልወጡ፣ የወጡትም ሆኑ ያልወጡት የመንግስትን ድጋፍ እየተጠባበቁ መሆኑን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

በታይላንድ ያሉ ኢትዮጵያዊያኑ አሁንስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

“ ከመግደል ያላነሰ ድብድባ ነው የሚካሄደውኮ። እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታይላንድ በረራ እንዳለው እያየን ነው። እሺ ገበያውም አይዘጋበት ቢያንስ ሰው ይዞ ወደ ታይላንድ መጥቶ ሲመለስ የተወሰኑ ሰዎችን እየቀላቀለ ቢመልሰን ማቃለል አይችልም ? 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኛ አይደለም እንዴ ? ለሥራ ብለን ነው የመጣነዎኮ ስለተቸገርን ገንዘብ ለማግኘት። ገንዘብ ይዘን ደግሞ ወደ ሀገራችን ለመመለስ። 

‘መንግስት አላችሁ?’ ተብለን እስከምንጠየቅ መድረሳችን በጣም ያሳፍራል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሌላ አገር ‘ገንዘብ ረዳሁ’ ብሎ ከሚያወራ እዚህ ያሉትን ዜጓቹን አያስወጣም እንዴ ? 

እኛስ መቼም ምግብ ባይቀርብልም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ምንም አይመስለንም። ትኩረት የሚሹት በማይናማር ከእገታ ያልወጡት እኛ ባለን መረጃ ብቻ እንኳ ከ400 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ነው። እነርሱ የሚወጡት ደግሞ እኛ ቦታውን ስንለቅላቸው ነው።

እኛ ማይናማር ቦርደር ላይ ነው ያለነው። ሞኤ የሚባል ወንዝ እንደተሻገን። በጣም ሐበሻዎች አሉ። ከአንድ ካምፓኒ ብቻ እስከ 500 የሚደርሱ ሐበሻዎች አሉ።

አብዛኛው ኢትዮጵያ ያለበት አንዱ ካምፓኒ ‘ወደ ሌላ ቦታ እንስዳችኋለሁ’ እያለን ነው። ሌላ ቦታ የሚወስደን ሁሉንም ነገሮች ቁጥጥሩ ለማድረግ ነው። አሁን ያለንበት ቦታ ላይ ደኀንነታችን የተጠበቀ ነው። 

ማይናማር ግን ብዙ ሰው እየተጎዳ፣ እየተሰቃዬ ያለበት ፎረይን ፓሊሶች የሌሉበት አካባቢ ነው። ያለንበትን ካምፓኒ አቋርጠን ለመውጣት 2,500 ዶላር ይከፈላል። ያለንበት ግቢ እስከ 25 ካምፓኒዎች አሉ። ወደ ሌላ ግቢ ላለመሄድ ነው ጥረት እያደረግን ያለነው።

ሐበሾችን እየጠበቅን ነው ገና ከእገታ ያልወጡ ስላሉ። አመት ድረስ የቆዩ አሉ። በራሳችን ፈቃድ ስለማያስወጡን። 

እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ያልመጣንበት ዋነኛው ምክንያት ሙሉ ወጪ መሸፈን ስላማይችል ነው። 

ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ልከው ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙ ነው መረጃ የሰጡን። የታይላንድ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ልኳል። ግን እስከ ሳምንት ምላሽ አልተሰጠም።

ካለንበት ካምፕ ወጥተን ወደ ታይላንድ/ሜኢሶት ኤርፓርት ነው መሄድ ያለብን። ከታይላንድ መንግስት ጋር በመነጋገር ወንዝ ያሻግሩናል። ፓስፓርት የሌለው አንድ ወር መቆየት እንደሚችል ነው የተነገረው። 

የተጎዱ ሀበሿች፣ ጀርባቸው ላይ ለምጥ ያለ፣ የታመሙ፣ የተደበደቡ በሙሉ ካምፕ ነው ያሉት። እኛን ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ነው ያልጠየቁን እንጂ ህንዶችን፣ ቻይናዎችን ‘አለንላችሁ’ የሚሉ አሉ። 

ምን እያደረጉ እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም። የምናውቀው ዘገባ እያደረጉና ዜግነታችንን ለይተው ብዙ ነገር እየጠየቁ እንደሆነ ነው። 

የኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ናቸው የቀሩት። ከኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ስላላገኙ። ምላሽ ቢያገኙ ይወጡ ነበር የሚቆዩበት ምክንያት የለም። ለኛም ስጋት የሆነው እነርሱ ባለመሄዳቸው የተነሳ ምናልባት የታይላንድ መንግስት ላይቀበለን ይችላል ” ሲሉ ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያዊያኑ ቤተሰቦችስ በሰጡን ቃል ምን አሉ ?

“ ከእገታው ያልወጡ ኢትዮጵያዋያን ስቃይ ላይ ናቸው። ከእገታ ከወጡት 261 ዜጎች 138 ኢትዮጵያዊያ ናቸው። ከማይናማር ተነስተው ታክ በሚባል ካምፕ ነው ያሉት፤ ከቦርደሩ 82፣ ለባንኮክ 377 ኪሎ ሜትር ርቀት።

ቦታው አሁን ለደኀንነታቸው አስተማማኝ እየሆነ አይደለም። ምክንያቱም ከወጡት 261 የ18 ሀገራት ዜጎች በስምንት ቀናት ሁሉም ወደ ሀገራቸው ሂደዋል። የቀሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ናቸው።

ከእገታው እንደወጡ ኢንተርቪው ተደገው ነበር በዛው አካባቢው አካላት፣ የደረሰባቸውን ስቃይ ተናግረው ነበር። ቃለመጠይቁን የሰሙ የታይላንድ ፓሊሶችም መልሰው ወስደዋቸዋል። መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ የወጡት ኢትዮጵያዊንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል። የተመለሰ የለም።

የሌሎቹ ሀገሪት ዜጎችም ኢንተርቪው ተደርገው የነበር፤ ነገር ግን ኤምባሲዎች ሂደው በቀናት ውስጥ ነው የወሰዷቸው። 138ቱ ኢትዮጵያዊን ከእገታው ቢወጡም ወደ ኢትዮጵያ ስላልወጡ አደጋ ላይ ናቸው።

በታይላንድ ካምፕ ላይ ያሉት 138፣ በሌላ ጉዳይ ምክንያት በታይላንድ ፓሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ፣ ገና ቦርደር ላይ እየጠበበቁ ያሉ 100 በአጠቃላይ 259 ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝራቸው እንደተላከለት ውጪ ጉዳይ ነግሮናል።

በስም ዝርዝራቸው መሠረት መረጃዎችን እያደራጀ እንደሆነ ቢገልጽልንም እስካሁን ድረስ ግን ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰራ ነገር የለም።

የወጡት ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ መንግስት የሚጠብቁት ምን እንደሆነ፥ የአገልግሎት ጊዜው ያለቀ ፓርፓርት ያላቸው ልጆች ስላሉ ማንንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ወደ ታይላንድ መንግስት እንዲልክላቸው፣ የበረራ ትኬቶች እንዲስተካክልላቸው ነው” ብለዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ፦

“ የታይላንድ መንግስት ‘ዜጎቻችሁን ውሰዱ’ ካለ በኋላ ብዙ ሀገራት ልጆቻቸውን አስወጥተዋል። የኢትዮጵያ ልጆች ግን እየተሰቃዩ ነው ያሉት።

የተወሰኑት አምልጠው ሲወጡ ተከትለው ለወጣት የምከሩ ኢትዮጵያዊያን ማይናማር በወታደሮች ካምፕ ታጉረዋል። ከእገታ የወጡት ወደ ሀገቸው ስላልመጡ ሌሎች ያልወጡት ታጋቾችም እየተሰቃዩ ነው።

አሁንም ወታደራዊ ካምፕ ያሉ ኢትዮጵያዊያኑ ብቻ ናቸው። ምግብም እየተሰጣቸው አይደለም። ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው። ልጆቹ ያልወጡበት ምክንያት ያገራችን መንግስት ባለመቀበሉ ብቻ ነው” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለምን ከእገታ የማጡት ኢትዮጵያዊንን በአፋጣኝ ማምጣትና የታገቱትን ወገኖች ለማስለቀቅ ለምን እንዳልተቻለ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አላገኘም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔊 #የጤናባለሙያዎችድምጽ 🔴 “ የጸጥታ አካላት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ድብደባ ፈጽመዋል፣ ዘጠኝ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላትን አስረዋል ” - የሆስፒታሉ ሠራተኞች ➡️ “ እነርሱ ጋ ብቻ አይደለም ያልተከፈለው፤ ከ2000 በላይ ሠራተኞች እንደ ዞን ያልተከፈላቸው አሉ ”  - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ፣ የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ባለሙያዎች “ በጸጥታ…
#Update

🔴 “ ወደ አራት ጤና ባለሙያዎች ገና አልተፈቱም። የጠየቁት መብታቸውን ስለሆነ ሊፈቱ ይገባል ” - ቤተሰቦች

➡️ “ ሰልፍ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው የተያዙት ” - ጤና ባለሙያ


የአራት ወራት አዲሱ ደወመዝ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው የሥራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ከታሰሩት የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች መካከል አራቱ እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸውና የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መጀመሪያ የታሰሩት ዘጠኝ እንደነበሩ ሠራተኞቹ ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ እስራቱ ቀጥሎ በአጠቃላይ 12 ሰዎች ታስረው እንደነበርና አራቱ እንዳልተፈቱ ነግረውናል።

የታሳሪ ቤተሰቦችና ጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

አንድ ጤና ባለሙያ በሰጡን ቃል፤ “ የተፈቱና ሌሎቹም በሥራ ገበታ ላይ ናቸው። የነዚህ የአራቱ አለመፈታት ግን እስካሁን ምስጢር ሆኖብናል። ሰልፍ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው የታሰሩት ” ሲሉ ተናግረዋል።

የታሳሪ ቤተሰቦች በበኩላቸው “ አራት ጤና ባለሙያዎች ገና አልተፈቱም። የጠየቁት መብታቸውን ስለሆነ ሊፈቱ ይገባል ” ብለዋል።

“ ጥያቄው የሆስፒታሉ አካላት ሁሉ ነው። የፓለቲካ ጉዳይ የሌለበት የደመወዝ ጥያቄም ነው። ከደመወዝ ይከፈለን ውጪ ያነሱት ጥያቄ የለሞ ” ሲሉም ሞግተዋል።

አንዲት የታሳሪ ቤተሰብ በሰጡን ቃል፣ ባለቤታቸው ከታሰሩ ቀናት እንዳስቆጠሩ፣ እስካሁንም እንዳልተፈቱ፣ ያሉበትን ሁኔታም እንደማያውቁ ገልጸዋል።

ሌላኛው የታሳሪዋ የቅርብ ሰው የ10 ወር ጨቅላ ህፃን ያላት ጤና ባለሙያ እንደታሰረች ገልጸው፣ በዋስ እንደትለቀቅ እንኳ ቢሞከር ፈቃደኛ አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል።

“ አጥቢ ከመሆኗ አንፃር ቀነ ገደብ ተጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤት ዋስትና እንዲሰጣት ውሳኔ ቢያስተላልፍም እንዳትወጣ በፓሊስ ተከልክላለች ” ሲሉ ነው የወቀሱት።

የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የታሰሩት የጤና ባለሙያዎች እንደሆኑ፣ ብዙ የህክምና ተገልጋዮች መጉላላታቸውም ከግምት ሊገባ እንደሚገባ አሳስበው፣ በፍጥነት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የታሰሩት ለምን እንዳልተፈቱ ምላሽ ለማግኘት የጸጥታ አካላትን ለማካተት የተደረገው መከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኞች ባለሆናቸው ለጊዜው አልተሳካም።

የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ከዚህ ቀደም  ጠይቀነው፣ በሌሎች ሆስፒታሎችም ጭምር ከ2000 በላይ ሠራተኞች ክፍያው እንዳልተፈጸመላቸው፣ የታሰሩትን ለማስፈታትም እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia