TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ወጫሌ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

ዛሬ ጥዋት ወጫሌ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን ጨምሮ በርካቶች ነው የተገደሉት።

የወጫሌ ወረዳ አጎራባች ይሆነው አለልቱ ወረዳ ፥ የቀድሞው የወረዳው አሁን ደግሞ የወጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ መገደላቸውን አረጋግጧል።

ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ አንዲት ነዋሪው " የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል። የጉዳቱ መጠን እስካሁን የተጣራ አይመስለኝም " ብለዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።

የወረዳው ዋና ከተማ ሙከጡሪ ከአዲስ አበባ 82 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት ብዙዎችን ያነጋገር መልእክትና ፎቶ በይፋዊና በተረጋገጠ የX ገጻቸው ላይ አጋርተዋል። ፎቶው ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር አብረው ያሉበት ነው። አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት…
ፎቶ ፦ የህወሓት አመራሮች ዛሬ በመቐለ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል።

የፊት ለፊት ግንኙነቱ በክልሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች የተመራ ነበር።

ጥዋት በመቐለ ኖርዘርን ስታር ሆቴል አዳራሽ  የነበረው የፊት ለፊት ውይይት ግማሽ ቀን የፈጀ እንደነበር ታውቋል።

የሃይማኖት አባቶቹ ፥ " ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ባቀረብናላቸው ጥሪ መሰረት ተገናኝተው ችግራቸውን በፓለቲካዊ እና በህጋዊ አሰራር እንፈታለን ብለውናል " ሲሉ አብስረዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በመወከልና በመምራት በፊት ለፊት ውይይቱ የተገኙት ጌታቸው ረዳ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሚድያ የሰጡት መግለጫ የለም።

አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከቀናት በፊት ተገናኝተው አብረው የተነሱትን ፎቶ አቶ ጌታቸው በ X ገጻቸው ላይ አጋርተው መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia            
" ህጻናት ፣ እናቶች፣ አሮጊቶች ፣ ሽማግሌዎች ተነስታ መሮጥ የማትችል አራስ እናት ሳትቀር ነው የተገደለችው " - ነዋሪዎች

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከመቂ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታጣቂዎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ፥ " ድርጊቱ የተፈጻመው በሸኔ ታጣቂዎች ነው። እጅግ በጣም አሳዛኝ ልብን የሚሰብር ነገር ነው የተፈፀመው " ብለዋል።

ቦታው በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ ዱግዳ ወረዳ ኩሬ፣ ጋሌ፣ ቢቂሲ የሚባሉ ቀበሌዎች እንደሆነና ቦታው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ እንደሚዋሰን ጠቁመዋል።

" ድንገት ምሽት ላይ ነው ግድያው የተፈጸመው። በወቅቱ ከባድ ዝናብ ይዘብ ነበር " ብለዋል።

" ድንገተኛ ስለነበረ ማሳ ውስጥ ሲሮጥ በተባራሪ ጥይት የተመታ አለ ፤ በቆሎ ውስጥ ያልተነሳ ሬሳ አለ፣ ተቃጥሎ መለየት ያልተቻለ ሬሳ አለ ፤ እስካሁን ባለው 44 ሰው እንደሞተ ነው የሰማነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ግድያው ምሽት በድንገት ነው የተፈጸመው። ከሟቾቹ 80% የሚሆኑ ማምለጥ የማይችሉ ህጻናት፣ አሮጊቶች ፣ ሴቶች ፣ ሽማግሌዎች ናቸው " ብለዋል።

" ህጻናት ናቸው የተገደሉት ፣ አሮጊቶች ናቸው ፤ ተነስታ መሮጥ የማትችል አራስ እናት ሳትቀር ነው የተገደለችው " ሲሉ አክለዋል።

ግድያ ብቻ ሳይሆን ማቃጠልም ሲፈጽሙ ነበር።

" በወቅቱ የመንግሥት ኃይል አልነበረም። ከምሽት 2 ሰዓት አንስቶ እስከ ለሊት 8 ሰዓት ነው የዘለቀው። አብዛኛው የመንግስት ፀጥታ ኃይል መቂ ነው ያለው " ብለዋል።

ግድያ በተፈጸመባቸው ስፍራዎች ላይ በወቅዩ ግጭት እንዳልነበረም ጠቁመዋል።

" የአካባቢው ሰው በታጣቂዎች ጥቃት ብዙ ተሰቃይቷል። መጨረሻ ሲደክመው እነሱን (ታጣቂዎቹን) ማዳመጥ አቆመ ፤ ከዛም በጎጥ እየተደራጀ ሰፈሩን መጠበቅ ጀመረ ፤ ታጣቂዎቹ ከጠፉ ከ6 ወር በኃላ አዘናግተው ነው አሁን መጥተው ግድያው ያፈጸሙት " ብለዋል።

በአጋጣሚ ከባድ ዝናብ ስለነበር ሰውም ወጥቶ አካባቢውን የሚጠብቅበት ሁኔታ እንዳልነበርና (ቤት ውስጥ እንደበር) በዚህ መሃል ሰብረው ገብተው ግድያውን እንደፈጸሙ ተናግረዋል።

" ያለ ርህራሄ ፣ ያለ ልዩነት ሲገድሉ የነበረው ነዋሪውን ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ ተጎጂ አይን እማኞች ረቡዕ ከምሽት ጀምሮ እስከ ለሊት በዘለቀ ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ እናቶች እና አረጋዊን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብለዋል።

አንድ ተጎጂ በሶዶ ወረዳ አዋሳኝ የደረሰው አስከፊ ጉዳት እንደሆነ ገልጸዋል።

" ሰው መግደል ፣ ማቃጠል ነው። ' የኛን ሃሳብ ለምን አልተከተላችሁም ለምን ከመንግስት ጋር ትሆናላችሁ ' የሚል ነው። ገበሬው ሸኔ ከሚባለው ብዙ ጊዜ ጥቃት ስለደረሰበት እራሱን ለመከላከል እየተደራጀ ነበር። መሳሪያም ይዞ፣ መንግሥትም እያበረታው እራሱን ለመከላከል እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር። እየወጣም ይጠብቅ ነበር። ያንን በመቃወም ነው ጥቃቱ " ብለዋል።

" ብዙ ጊዜ ሰው ይታገታል ገንዘብ ይጠየቃል፣ ብዙ ሰው ተሰቃይቶ ከስፍራው ለቋል ፣ መንገድም ዘግተው ቆይተዋል (ታጣቂዎቹ) " ሲሉ አክለዋል።

የአሁኑ ጥቅት ግን እጅግ በጣም የከፋና ከዚህ በፊት ያልታየ እንደሆነ አክለዋል።

" በብዙ አቅጣጫ ሆነው ይገባሉ ቤት ከውጭ ይዘጋሉ እሳት ይለኩሳሉ ለማምለጥ የሚሮጠውን በጥይት ነው ሲመቱ የነበረው የተቀበረው ብቻ 40 አካባቢ ነው ፤ 4 ፣ 5 ቤተሰብ ነው ሲቀበር የነበረው " ብለዋል።

ከሰው እልቂት ባለፈም እንስሳት ተቃጥለዋል ፤ በርካታ ንብረት ወድሟል።

ነዋሪው ሌላ ጥቃት እንዳይፈጸም በመስጋት ከቦታው እየወጣ እንደሆነ የአይን እማኙ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamily #ዶቼቨለ

@tikavhethiopia
#ኢትዮጵያ

የኩላሊት እጥበት ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ በሳምንት 3 ጊዜ እጥበት የሚያደርጉ ሕሙማን ከባድ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን፣ የኩላሊት ሕክምና እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል።

ከሰሞኑም የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤ " መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ካደረገ በኋላ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም የሕክምና ተቋማት የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት አንድ ታካሚ የኩላሊት እጥበት ለአንድ ጊዜ ሲያደርግ ይፈጸም የነበረው ክፍያ 2,000 ብር እንደነበር፣ ነገር ግን የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ሲደረግ አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ተቋማት ከ3,000 እስከ 4,100 ብር እያስከፈሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ከውጭ ስለሚገቡ፣ የአገልግሎት ክፍያው በእጥፍ መጨመሩንና በሳምንት ሦስት ጊዜ የሚጠቀም ታካሚ አንድ ጊዜ ብቻ ለማድረግ መገደዱን አክለው ገልጸዋል፡፡

በሞት ከተለዩ ሰዎች ኩላሊት እንዲወሰድ የሚፈቅድ የሕግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ድርጅቱ ጥረት ማድረጉን፣ ጉዳዩም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩ በሕግ ማዕቀፍ ሲታገዝ በርካታ ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ በቀላሉ እንደሚያደርጉ፣ እስከዚያው ግን ማኅበረበሰቡ ለኩላሊት ሕሙማን የተሻለ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡  

አሁን ላይ የሚመሩት ድርጅት ድጋፍ በዘውዲቱ፣ በምኒልክና በጳውሎስ የሕክምና ተቋማት የሚገኙ 210 ሕሙማን ነፃ የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ናቸው።

ይሁን እንጂ በግል ሆስፒታሎች አገልግሎት የሚያገኙ ሕሙማን በ15 ቀናት ውስጥ እጥበት ሲያደርጉ፣ ከፍተኛ ወጪ እንደሚጠብቃቸው ተጠቁሟል። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ' ማርያም ማዞሪያ ' አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ያደረሰው ውድመት።

Via @tikvahethmagazine
#ቦትስዋና 👏 #ዴሞክራሲ

" ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " - ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

በአህጉራችን አፍሪካ የተረጋጋ የዲሞክራሲ ስርዓት ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደሟ ቦትስዋና ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ለ58 ዓመታት ስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዢ ፓርቲ ድምጻቸውን ነፍገውታል።

ፓርቲው አስደንጋጭ ነው የተባለ ሽንፈትን ተከናንቧል።

የፓርቲው መሪና የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ ከፍተኛ ድምጽ አግኝቷል።

የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ቦትስዋና ፕሬዝደንት ለመሆን ተቃርበዋል።

ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለተቀናቃኛቸው ቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን ነግረዋቸዋል።

" በዲሞክራሲ ሂደቱ እጅግ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " ብለዋል ፕሬዜዳንት ማሲሲ።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ማሲሲ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ሂደት ደስ እንደተሰኙ ገልጸው " የህዝቡን ፍላጎት እና ምርጫ አከብራለሁ " ብለዋል።

ደጋፊዎቻቸውን ረጋ እንዳሉ በእርጋታቸው እንዲቀጥሉና ከአዲሱ የሀገሪቱ መንግስት ጀርባ ተሰልፈው እንዲደግፉ በይፋ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደም ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ ማግኘቱን ይገልጻል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#EarthQuake " በኢትዮጵያ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ለ22 ቀናት ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት የመወጠር ሁኔታ አሁን ረገብ ብሏል " ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤልያስ ሊዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን/ኢቲቪ ተናግረዋል። " አሁን ባለን መረጃ ቅልጥ አለቱ ወደታች እየወረደ ነው ፤ በዚህም ምክንያት ባለፉት…
#Awash🚨

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር  " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም ከነዋሪዎች የሚመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ  ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።

ዝርዝር መረጃ ከባለሞያዎችን እንደሰማን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia