#Alert🚨
ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወሰደው ዋና የመኪና መንገድ አጉላዕ በተባለ ቦታ መዘጋቱ ተጓዦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" መንገዱ ከዲሞብላይዜሽን (DDR) ጋር በተያያዘ ጥያቄ ባነሱ የቀድሞ የትግራይ ታዋጊ አባላት ነው የተዘጋው " ብለዋል።
ጥያቄው በዝርዝር ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።
መንገዱ ከዛሬ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከወጣበት ከቀኑ 7:00 ድረስ ተዘግቷል።
መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ከመቐለ የተነሱ መኪኖች 40 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ አጉላዕ ከተማ ደርሰው ወደ ውቕሮ ዓዲግራት እና ሌሎች ቦታዎች ማለፍ አይችሉም።
ከዓዲግራት ፣ ወቕሮ እና ሌሎች ከተሞች የመጡት ደግሞ አጉላዕ ደርሰው ወደ መቐለ ከተማ ማለፍ አይችሉም ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ መንገደኞች።
ተጓዦች መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ለከፍተኛ እንግልት መጋለጣቸው ገልፀው ፤ እስካሁን መንገዱን የዘጉትን የቀድሞ ተዋጊዎች አባላትን ጥያቄ ሰምቶ መልስ የሰጣቸው የለም ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያለውን መረጃ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይጠቁማል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር። በርካታ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መንቀጥቀጡ እና ንዝረቱ ከእንቅልፋቸው እንደቀሰቀሳቸውና ጠንክሮ እንደተሰማቸው መልዕክት ልከዋል። በተለይ አዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጠንከር ብሎ ንዝረቱ ተሰምቷል። ከንዝረቱ ጋር በተያያዘ መልዕክት የላከ የቤተሰባችን አባል ፥…
🚨 #Alert
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 23 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲሆን የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.0 መመዝገቡን አሳውቋል።
የአሜሪካ ጃኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 መለካቱን አመላክቷል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች ተሰምቷል።
@tikvahethiopia
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 23 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲሆን የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.0 መመዝገቡን አሳውቋል።
የአሜሪካ ጃኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 መለካቱን አመላክቷል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች ተሰምቷል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ጉዳይ ወዴት ? በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች እንደሆኑ የገለጹ መኮንኖች ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ' የተዳከመ ' ያሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር መወሰናቸውን ገልጸዋል። " የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ አሳልፈናል " ብለዋል። " በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ…
🚨#Alert
" የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ! " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን ደግፎ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማፍረስ ፤ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን እና ሰራዊቱን ለመበተን መንቀሳቀስ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ጥር 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ስም የወጣው መግለጫ አላማውን የሳተ እና ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ነው ብሏል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " በሰራዊት ከፍተኛ አዣዦች ስም የወጣው መግለጫ እንደማያውቀው በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ያልተለመደ ተግባር ነው " ብሎታል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ " ያልተለመደ ተግባር " ሲል የገለፀውን ውሳኔ አስመልክቶ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን እና ሁኔታውን መርምሮ ዝርዝር ማብራርያ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
" በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።
" ሃላፊነት የጎደለውን ውሳኔው ወደ ታች ለማውረድ ጥድፍያ የተሞላበት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑ ደርሼቤታለሁ " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ " የሚያስከትለው አደጋው እጅግ ከፍተኛ መሆኑ በመረዳት ተግባሩ በአስቸኳይ መቆም አለበት " ሲል አስጠንቅቋል።
" መላው የፀጥታ አካላት ህገ-ወጥ ውሳኔው የህዝቡን ችግር የሚያባብስ የጦርነት አዋጅ እና ስርዓት አልበኝነት የሚያስከትል መሆኑ በመገንዘብ በፅናት እንድትቃወሙት ትእዛዙን ተግባራዊ እንዳታደርጉ አስታውቃለሁ " ሲልም አክሏል።

Photo
🚨#Alert
ከደቂቃዎች በፊት ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል።
ንዝሩት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ተሰምቷል።
ቃላቸውን የላኩልን የቤተሰባች አባላት " ዛሬ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ሰሞኑን ድግግሞሹ ቀንሶ ነበር። ዛሬ በድንገት በሚያስፈራ ሁኔታ ነው የተሰማን " ብለዋል።

🚨 #ALERT
አሁን ከደቂቃዎች በፊት በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰቀሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ንዝረቱ በአዲስ አበባ እና የተለያዩ ከተሞች ከፍ ብሎ ተሰምቷል።
መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " የዛሬው ንዝረት ከእስካሁኑ የተለየና የሚያስደነግጥ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።
በርካቶችም በንዝረቱ ምክንያት ከእንቅልፍ መባነናቸውን ጠቁመዋል።