TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አረጋዊ ካህኑ ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ አረጋዊ ካህን ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል። መ/መ/ቀ/ወ/ኢየሱስ…
#EOTC

በአረጋዊው መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና አራት ቤተሰባቸው ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን በልዩ  ሁኔታ እንደሚከታተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አሳውቋል። 

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ (ሞጆ )  ወረዳ ቤተ ክህነት  በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ  ለ41 ዓመታት ያህል ከድቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትኅትና ሲያገለግሉ የቆዩት መልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይታወቃል።

ግድያው " ማንነታቸው ለጊዜው አልታወቀም " በተባሉ ኃይሎች መፈጸሙን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትን ዋቢ በማድረግ ያመለከተው ጠቅላይ ቤተክህነት ግድያው በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመ ነው ብሏል።

ጠቅላይ ቤተክህነት በዚህ አሰቃቂ ግድያ ሕይወታቸውን ባጡ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

" ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደረሰውን አስደንጋጭ ሀዘን ከሰሙ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እየተከታተሉት ይገኛሉ " ብሏል።

ዝርዝር ሁኔታውን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገርና እስከ መጨረሻው ጫፍ በመድረስ ሕጋዊ እልባት  እንዲያገኝ እንደሚደረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia