TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። የፖሊስን የምርመራ…
#Update

ፍ/ቤት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ።

" የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ፤ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል " ተብለው የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱ ተሰማ።

የፌደራል መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ቡድን፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ማጣሪያ ስራ አጠናቆ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በችሎት ተሰይሞ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም መረከቡን ጠቅሶ፤ ማስረጃ ተመልክቶ ክስ ለማቅረብ እንዲያስችለው ክስ ለመመስረቻ ጊዜ 5 ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች " ዐቃቤ ህግ ምርመራውን ሲመራ ቆይቶ እንደአዲስ መዝገቡን ተመልክቼ ክስ ለመመስረት፣ ለመወሰን እንዲያስችለኝ የክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ " ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።

ጠበቆቻቸው ደንበኞቻቸው ተጨማሪ ጊዜ በእስር ሊቆዩ እንደማይገባ ገልጸው፤ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መፍቀድ ስነ ስርዓታዊ መሆኑን በማመን የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለዐቃቤ ህግ የ5 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በዚህም መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ/ም ክስ ይመሰረታል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ባጋጠመ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከ10 በላይ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ተቀጠፈ።

የትራፊክ አደጋው ዛሬ  ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት አከባቢ የተከሰተ ሲሆን የሰሌዳ ቁጥር TG - 04539 የሆነ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከዓድዋ ወደ መቐለ ሲጓዝ ወርዒ ልዩ ቦታ  እንዳፈላሲ ቁልቁለት ሲወርድ ወደ ገደል በመግባቱ ነው አደጋው ያጋጠመው።

በውስጥ ከተሳፈሩ ሰዎች ከ10 በላይ ወድያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ 5 ሰዎች በፅኑ ተጎድተዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመላክተው 48 ሰዎች የመጫን አቅም ያለው መለስተኛ አውቶቡስ በአጋጣሚ 20 ሰዎች ብቻ አሳፍሮ መጓዙ ለሟችና ቁስለኞች መቀነስ ምክንያት ሆኗል።

የአደጋው ምክንያት ገና በመጣራት ላይ ነው።

ይህ ወር በርካታ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ ይኖራል ፤ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አይለያችሁ።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል።

የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል።

ይጠብቁ !

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
Live stream scheduled for
Live stream started
TIKVAH-ETHIOPIA
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል። የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል። ይጠብቁ ! #TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba @tikvahethiopia
#ውጤት : የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ የፈተናው ውጤት ለሊት 6 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

መግለጫውን ከላይ በቀጥታ ይከታተሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አጠቃላይ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ናቸው። @tikvahethiopia
ዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች ናቸው ያለፉት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች ናቸው ያለፉት። @tikvahethiopia
አዲስ አበባ 10,690 ተማሪዎች በማሳለፍ ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል።

አዲስ አበባ ካስፈተናቸው ተማሪዎች 21.4 በመቶ አሳልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ አበባ 10,690 ተማሪዎች በማሳለፍ ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል። አዲስ አበባ ካስፈተናቸው ተማሪዎች 21.4 በመቶ አሳልፏል። @tikvahethiopia
ከፍተኛ ውጤት ስንት ተመዘገበ ?

በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በትግራይ ነው።

በትግራይ ፈተናው ከ700 ነው የተሰጠው።

ከቀላሚኖ 675 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ፤ በወንድ ተማሪ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል ከ700 ይሄን ያህል ውጤት ሲመዘገብ።

ሌላ በሀገር ደረጃ ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከፍተኛው ነው ከተፈጥሮ ሳይንስ ፤ የካቴድራል ተማሪ ናት።

ከማህበራዊ ሳይንስ 538 ተመዝግቧል። ከኢትዮ ፓረንትስ ትምህርት ቤት ናት።

በተፈጥሮም በማህበራዊ ሳይንስም ትልቅ ውጤት የመጣው በሴቶች ነው።

@tikvahethiopia
Live stream finished (55 minutes)
ሬሜዲያል ዘንድሮም ይኖራል።

" አምና ሰጥተናል። ዘንድሮ ከዓምናው የቀነሰ ቁጥር እንወስዳለን። የሬሜዲያል ፕሮግራም በሂደት እየቀነሰ ይሄዳል " ሲሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሬሜዲያል ዘንድሮም ይኖራል። " አምና ሰጥተናል። ዘንድሮ ከዓምናው የቀነሰ ቁጥር እንወስዳለን። የሬሜዲያል ፕሮግራም በሂደት እየቀነሰ ይሄዳል " ሲሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተግረዋል። @tikvahethiopia
#Amhara

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " ዘንድሮ ሁሉም
ክልሎች አምና ካሳለፉት ተማሪ በላይ አሳልፈዋል " ብሏል።

" በፐርሰንቴጅም በአክቹዋል ቁጥርም ካለፈው የተሻለ ነው " ተብሏል።

ከአክቹዋል ቁጥር ያነሰው አንድ ክልል ነው እሱም የአማራ ክልል እንደሆነ ተገልጿል።

ክልሉ ያነሰው ደግሞ የተፈተኑት ተማሪዎች ቁጥር ከግማሽ በታች ስለነበር ነው ተብሏል።

ክልሉ ፈተና ካስፈተናቸው ውስጥ ግን 6.6 በመቶ ተማሪዎች አልፈዋል።

አምና ከተመዘገበው 4.1 በመቶ ዘንድሮ በልጧል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ውጤቱ በጣም ዝቅተኛ ነው !

" በ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ የተሰጠው ፈተና ውጤት እንድምታው ሲታይ ከ2014 ዓ/ም 30,034 (3.3%) ፣ ከ2015 ዓ/ም 27,267 (3.2%) ... (ዘንድሮ 5.4%) መሆኑ እያሽቆለቆለ እየሄደ ያለው ጉዞ የተገታ እና መጠነኛ የመሻሻል አዝማሚያ ያሳየ ቢሆንም አሁንም 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተፈታኞች ቁጥር በጣም #ዝቅተኛ ነው። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር)

@tikvahethiopia