TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara
በነገው ዕለት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ይጀመራል።
በአማራ ክልል ውስጥ የተፈታኞች ቁጥር ከታቀደው በግማሽ እንደሚያንስ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።
ቢሮው በዚህ ዓመት ከ200 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀመጡ አቅዶ ነበር።
ነገር ግን አሁን ፈተና ላይ ይቀመጣሉ የተባሉት 96 ሺህ 408 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
ቀሪ 106 ሺህ ያክል ተማሪዎች ፈተና አይወስዱም።
አሁን ላይ ፈተናውን የማይወስዱ ተማሪዎች ተምረው በመስከረም 2017 ዓ/ም በሁለተኛ ዙር ለመፈተን እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።
በነገ ዕለት ፈተና የሚጀምሩት ተማሪዎች ለፈተናው መቀመጥ የሚያስችላቸውን ትምህርት የተከታተሉ እንደሆኑ ቢሮው አሳውቋል።
ባለፉት በርካታ ዓመታት የሀገሪቱ ከፍተኛው ውጤት የሚመዘገብበት እና እጅግ በጣም ጎበዝ ተማሪዎች የሚገኙበት አማራ ክልል ዘንድሮ የሚጠበቅበትን ያክል ተማሪ ባለማስተማሩ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዙር ፈተና ላይ መቀምጥ አልቻሉም።
በሌላ በኩል በአማራ ክልል ዘንድሮ ትምህርታቸውን መማር ከነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል መማር የቻሉት 3.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው።
ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት አልተማሩም።
ይኸው እስከ ዛሬ ትምህርት ያልጀመሩ ዞኖች እና ወረዳዎች አሉ።
በቅርቡ ቢሮው ዓመቱን ሙሉ በሙሉ ጭራሽ ምንም ያልተማሩ ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።
ተማሪዎች ካልተማሩባቸው መካከል ሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ዋነኞቹ ሲሆኑ ምንም አይነት ተማሪ / አንድም እንኳን ተማሪ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደማያስፈትኑ መግለጹ ይታወሳል።
#AmharaEducationBureau
#NationalExam
#DeutscheWelle
@tikvahethiopia

አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡
ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው።
የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።
ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጀመራቸው ይታወሳል።
Via @tikvahuniversity

የተፈጥሮ ሳይንስ የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀመረ።
ፈተናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ነው በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው።
@tikvahuniversity

#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።
የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።
ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።
በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበል።
በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።
ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።
የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

" ፈተናው ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት እየተዘጋጀ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ፤ " የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ብሏል።
" ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ሲል ገልጿል።
በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ እንዳሉም ጠቁሟል።
በዚህም " የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።
የፈተና ዝግጅቱ፡-
1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ እንደሆነ ተገልጿል።
ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ እንደሆነ ተመላክቷል።
በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎት መ/ቤቱ አሳስቧል።
ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል።
የዘንድሮ ሀገር አቀፉ የ12ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም።