TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ራያ “ ሕወሓት /TPLF ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ” - አቶ ሀይሉ አበራ የትግራይ እና አማራ ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ አካቢዎች ሰሞኑን በተለይ ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአላማጣና አካባቢው ባለስልጣናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የአላማጣ ከተማ እና ዙሪያው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የትግራይ…
#Update

አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊትና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን ከንቲባው አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውንም ገልፀዋል።

አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ?

- " ከትላንት ሰኞ ጀምሮ ከተማው በመከላከያ ሠራዊት እና ፌዴራይል ፖሊስ ስር ይገኛል። "

- " አላማጣ ከተማው መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ነው ያለው። ዙሪያው የተያዘው ግን በትግራይ ታጣቂዎች ነው። "

- " የራያ አላማጣ ወረዳ እና የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከሰኞ ጀምሮ አካባቢውን ለቅቀው ወጥተዋል። በአሁኑ ሰዓት ቆቦ ነው የሚገኙት። "

- " አሁን እኛ እዚያ እየሠራን አይደለም። " 

አቶ ኃይሉ አበራ ፥ የራያ አላማጣ አካባቢዎች በአማራ ክልል ስር ከሆነ በኋላ በተመሠረው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የነበሩት ኃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማውን እያስተዳደሩ አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሞላ ደርበው እና ለሌችም ሰዎች በትናንትናው ዕለት መገደላቸውን አቶ ኃይሉ አበራ ተናግረዋል።

" አቶ ሞላ ሕይወታቸው ያለፈው ከህወሓት ጋር በተያያዘ አይደለም። ሕግ የያዘው ነገር ስለሆነ ተጣርቶ የሆነ ነገር እስከሚባል ድረስ ዝርዝሩን አልገልፅም " ብለዋል።

ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በርካታ የአላማጣ ነዋሪዎች ወረዳውን እና ከተማውን ለቀው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሸሻቸውን ተነግሯል።

ነዋሪዎች ሸሽተውባቸዋል ከተባሉ አጎራባች አካባቢዎች አንዱ ቆቦ ከተማ ሲሆን አንድ የቆቦ ከተማ ኃላፊ ከትናትን ጀምሮ በርካታ ወደ ከተማዋ እየገቡ መሆኑን ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ያሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን " በተለይም የአለማጣ ከተማ ከትላንት ጀምሮ ከማንም ታጣቂ ነፃ ናት " ብለዋል።

" የአማራ ይሁን የትግራይ ታጣቂዎች በቦታው አለመኖራቸውን " ገልጸው ስጋት ያደረበት ነዋሪው ወደ አጎራባች አካባቢ መሄዱን አስረድተዋል።

እስካሁን በራያ ጉዳይ በአማራ እና በትግራይ ክልል ደረጃ እንዲሁም በፌዴራሉ መንግሥት በኩል የተሰጠ ማብራሪያም ሆነ አስተያየት የለም።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች በክልሉ ለሚገኙ ሚድያዎች መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ " በፕሪቶሪያ ውል ያልተፈፀሙት እንዲተገበሩ እየሰራን እንቀጥላለን " ብለዋል። 

" የፕሪቶሪያ ውል የፈረምነው የተለያዩ የትግራይ ቦታዎች ከክልሉ አስተዳደር ውጭ በነበሩበት በርካታ ወገኖች ከቄያቸው በተፈናቅሉበት ጊዜ ነበር " ያሉት ጄነራሉ " የውሉ ተዋዋዮች በህገ-መንግስት መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ተስማምተዋል " ብለዋል። 

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውልን በጥንቃቄ መተግበር ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን በመታየት ያለው ውጤት የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግራይ በሃይል የተያዘባት መሬት ሙሉ በሙሉ መልሳ የተማላ ቁመናዋ መያዝ ፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ እንዲተገበሩ ያስገድዳል ይህ እንዲሆን ደግሞ በሃይል በተያዙ ቦታዎች ያሉ ታጣቂዎች መውጣትና ህጋዊ ያልሆነው አስተዳደር መፍረስ አለባቸው " ብለዋል።     

" ህጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮች ማፍረስና ታጣቂዎች ትጥቃቻውን ማስፈታት የፕሪቶሪያ ውል የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ቀጥሎ የሚደረገው ሁሉ #ሰላም ከተረጋገጠ በኋላ የሚሆን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ተፈናቃዮች ሲመለሱ ክብራቸው ተጠብቆ ፣ የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማት ሁሉ ተሟልቶ ሰብአዊ ድጋፍ ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ መሆን አለበት "  ያሉት ጀነራሉ  " አስተዳደርን በሚመለከት ቀበሌዎችና ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩ ጊዚያዊ  አስተዳደሮች ራሱ ህዝቡ ይመርጣል " ብለዋል።  

ዘላቂ መፍትሄ በሚመለከት ምን አሉ ?

" የፌደራል መንግስት ' አከባቢዎቹ በፌዴራል ስር ቆይተው #ሪፈረንደም ይካሄድ ' የሚል አቋም ያለው ሲሆን በእኛ በኩል ደግሞ በአከባቢው ጊዚያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ትግራይ ይመለሱ የሚል አቋም ነው ያለው፤ ይህ የአቋም ልዩነት እስካሁን አልተፈታም እንዲፈታ ደግሞ ቀጣይ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - Tigrai & DW TV
                                          
@tikvahethiopia            
ቴሌብር ኢንጌጅ ምንድነው ?

(ኢትዮ ቴሌኮም)

ኩባንያችን የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያስችለው " ቴሌብር ሱፐርአፕ " ደንበኞች ከመገበያየት እና ገንዘብ ከማስተላለፍ ባሻገር መረጃን በነጻ በመለዋወጥ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እና ቢዝነሳቸውን የሚያጠናክሩበት ቴሌብር ኢንጌጅ የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡ 

አዲሱ ቴሌብር ኢንጌጅ የቢዝነስ እና ግለሰብ ደንበኞች #ያለምንም_ተጨማሪ_የኢንተርኔት_ክፍያ ለተናጠል ወይም ለጋራ ፦
- የጽሁፍ፣
- የፎቶ፣
- ድምጽ፣
- ቪዲዮ እና ፋይሎችን ለማጋራት የሚያስችል ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለበዓል ወይም ለተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች የተናጠል ወይም የቡድን መልካም ምኞት መልእክት ከገንዘብ ስጦታ ጋር መላክ የሚያስችላቸውን አዲስ ገጽታ አካቷል፡፡

በተጨማሪም በጭውውቶች ወቅት ገንዘብ ለመጠየቅ፣ ለመላክ እና ለመቀበል፣ ቢል ለማጋራት እንዲሁም ጥቅል ወይም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን በአንድ መተግበሪያ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በማስተዋወቅ የቢዝነስ ተሞክሮአቸው እና የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ ተጨማሪ ምቾት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/3W3291x ይጠቀሙ፡፡

#telebirrEngage
#Ethiotelecom
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

የመጋቢት ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 26.2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳወቀ።

በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ፦

➡️ ምግብ ነክ ዕቃዎች (food items) 29 በመቶ ድርሻ ይዘዋል።

➡️ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) 22 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል።

በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ #በየካቲት_ወር ከነበረበት 28.2 በመቶ ወደ 26.2 በመቶ በመሆን መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አመላክቷል።

@tikvahethiopia
#Rwanda #UK

ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል።

የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በዚህ ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

‘ የሩዋንዳ ዕቅድ ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ምን አሉ ?

" የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል።

አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው። " ብለዋል።


በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን በዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት 2 ዓመታት አስቆጥሯል።

በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችል ቪኦኤ በዘገባው አስፍሯል። #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስረከም 19/2016 ዓ/ም ለስራ በወጡበት በታጣቂዎች ከታገቱ 6 የኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኞች ሁሉም እንዲለቀቁ 2.8 ሚሊዮን ብር ቢከፈልም 3ቱ ተለቀው የቀሩት 3ቱ እስካሁን ያልተለቀቁ ሲሆን ያሉበት ሁኔታም አይታወቅም። የታጋች ቤተሰቦች ዛሬም በሀዘን…
#Update

“ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት

ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ እንደሞከረ ከ2 ሳምንታት በፊት ገልጾልን ነበር።

በወቅቱ #እንባ እየተናነቃቸው ቃላቸውን የሰጡን የአንዱ ታጋች እህት ፣ “ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን። 2.8 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ አልተለቀቁም ” ማለታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም። በሰላም እንዲለቋቸው የሚል ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ ” ነበር ያለው።

አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ከ3ቱ ታጋቾች መካከል የሁለት ልጆቻቸው አባት የታገተባቸው ወ/ሮ ቤተልሄም ገዛኸኝ ፥ ታጋቾቹ አሁንም እንዳልተለቀቁ ገልጸዋል።

ከባለቤታቸው በተጨማሪ አንድ የሁለት ልጃቸው እናት የሞቱባቸው አባትና አንድ ሁለት ቤተሰቦቹን የሚያስተምር ሠራተኞች እንደሚገኙበትና ከታገቱ ከ6 ወራት በላይ ቢያስቆጥሩም ፣ አሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በንግግራቸው መሀል #የሚያለቅሱት ወይዘሮ ቤተልሄም በሰጡት ቃል ፣ “ በሕይወቱ ስለመኖሩም እየተጠራጠርኩ ነው። ሁለቱ ልጆቹ በትምህርታቸው ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ደርሶባቸዋል። አንዷ ተመራቂ፣ አንዱ ማትሪክ ተፈታኝ ናቸው። እኔም የስኳርና የደም ግፊት ሕመምተኛ ነኝ ” ብለዋል።

ለመንግሥት ጭምር ባስተላለፉት መልዕክትም፣ “ ሞቷልም፣ አለም ቢባል እኮ አንድ ነገር ነው። እንዲህ አድርጉ የሚሉን ነገር ካለም ቢጠቁሙን መፍትሄ ነው” ብለው፣ “እንደ ቀላል ነገር በሀገራቸው ላይ ታግተው በወጡበት ቅርት ሲሉ ዝም ማለት በጣም ይከብዳልና ሁሉም ርብርብ ያድርጉልን ” ሲሉ ጠይቀዋል።

“ ከታገቱ ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ/ም 7 ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ። እቃ እንኳን ሲጠፋ ዝም አይባልም እንኳን ሰው። እንደ ሰው ትኩረት ይሰጣቸው ” ሲሉም አክለው አሳስበዋል።

“ እንዲያው በእግዚአብሔር፣ በሁሉም ልጆች ባሏቸው አባቶች፣ እህት፣ ወንድም ባላቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሁሉም ሰዎች እንደራሳቸው አይተው የሚችሉትን ነገር ሁሉ ይተባበሩን። ያጣሩ። ከእግዚአብሔር በታች ሰዎችን ነው የምለምነው ” ነው ያሉት።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia

🎁 ልዩ ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎችን ከ M-PESA በመግዛት 50% ተጨማሪ ዳታ አግኝተን በነጻ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም እንደዋወል! 🤳
  
ዳታ እንግዛ! በነጻ እንደዋወል!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#Furtheraheadtogether
" 400 ሺህ ብር ክፈል ይሉኛል። እኔ ይሄን ያህል ገንዘብ ከየትም ላመጣ አልችልም። ... ልመና ወጥታችለሁ። " - አባት

ኤርትራዊው ስደተኛ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዶ ለማስለቀቂያ 400 ሺህ ብር እንደተጠየቀበት ተነገረ።

አባት ገንዘቡን ለማግኘት ልመና ወጥተዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በጭላ ቀበሌ በተቋቋመው የዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩት ኤርትራዊው ስደተኛ አቶ መሀመድ ኡስማን ባለፈው መጋቢት 26 ቀን 2016 ልጃቸው አማን መሀመድ መታገቱን ገልጸዋል።

ልጃቸው በአቅራቢያ ካለው የዳባት ትምህርት ቤት ቀን 10:00 እየተመለሰ እያለ ባልታወቁ ሰዎች መታገቱን አመልክተዋል።

አጋቾቹ በየሁለት ቀን በመደወል የማስለቀቂያ ገንዘብ እየጠየቋቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

አባት አቶ መሀመድ ፥ " እየደወሉ 400 ሺህ ብር ክፈል ብለውኛል። እኔ ይሄን ያህል ገንዘብ ከየትም ላመጣ አልችልም። እስከዚህች እለት ድረስ ይኸው በየአብያተክርስቲያናቱ እና በየመስጂዱ ለልጄ ማስለቀቂያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ ልመና ላይ ነኝ። ሌሎች ስደተኞችም በልመና ይተባበሩኛል እስካሁን የተገኘ ገንዘብ የለም " ብለዋል።

አጋቾቹ በየደወሉ ቁጥር ልጃቸው እያለቀሰ ድምፁን እንደሚያሰሟቸውም ገልጸዋል።

ልጃቸው በተለምዶ " ባጃጅ " በሚባለው ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ታግቶ መወሰዱን ገልጸው የሰሌዳ ቁጥሩን ለፖሊስ ቢያመለክቱም እስካሁን ውጤት የለም።

የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ " አንድ ልጅ የጠፋ አለ እገታ ሳይሆን አይቀርም የሚል መረጃ ስለመጣ እንደተቋም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " ብሏል።

የጭላ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ምናለ ግንብነህ በበኩላቸው ፥ ከህፃኑ ጋር ሌላ የአስተማሪ ልጅም መወሰዱን ጠቁመዋል።

" እንዴት ሄደ ? ወደየት ሄደ ? የሚለውን ፖሊስ እየሰራበት ነው " ያሉት አስታዳዳሪው " አንድ የታሰረ ልጅ አለ መረጃ ስጥ እየተባለ ነው ያለው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊትና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን ከንቲባው አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል። የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውንም ገልፀዋል። አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ? - " ከትላንት ሰኞ ጀምሮ…
#Update

የአማራ ክልል መንግሥት ምን አለ ?

ዛሬ የአማራ ክልል መንግሥት ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።

የክልሉ መንግሥት ፥ " ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ከሷል።

" ህወሓት የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል " ሲል አስታውሷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ህወሓትን " የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት " እንደሆነ ገልጾ " ባለፉት 3 ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል " ብሏል።

" የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ገልጿል።

" ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው ፦
- የራያ አላማጣ፣
- ራያ ባላ፣
- ኦፍላ፣
- ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች  ናቸው " ብሏል።

" ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ህወሓት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት በኃላ አካባቢዎቹ በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት እንደቻሉ " የአማራ ክልል መንግሥት ገልጿል።

በኃላም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ፤ ህወሓት ግን ስምምነቱን በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም እንደቆየ አመላክቷል።

" አሁንም እየፈጸመ ይገኛል " ብሏል።

የአማራ ክልል መንግሥት ፥ ህወሓት ደም አፋሳሽ የሆነ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲያከብር አሳስቧል።

" በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ " ሲል ጠይቋል።

" ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።

ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።

" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።

በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ #በስራ_ላይ_እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@tikvahethiopia