TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ። የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንትና ለሊት በመቂ ከተማ መገደላቸው ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል። " ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው ተገድለው ነው አስክሬናቸው መንገድ ላይ የተገኘው " ተብሏል። አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት…
" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ?
" የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል አሁን ?
በቴን ቢያንስ አውቀዋለሁ ጠንካራ የሆነ የፖለቲካ አቋም ቢኖረውም ለማንም ሆነ ለየትኛውም ቡድን ክፉ የሚያስብ ሰው አልነበረም።
እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ተይዞ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበት ሞተ ተብሎ ለረጅም ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ ቆይቷል።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስርና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም። ይህ ለበቴ አይገባም ነበር። " ሲሉ የአቶ በቴን ግድያ አውግዘዋል።
የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉትበት ሆቴል ተውስደው ተገድለው መንገድ ላይ ተጥለው ተገኝተዋል።
ወደ መቂ ያቀኑት የእርሻ ስራቸውን ለመመልከት እንደነበር ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የቅርብ ጓደኛቸውን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።
እስካሁን ድረስ ፓርቲያቸው ኦነግ በይፋ መግለጫ አልሰጠም። በመንግስት በኩልም የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopia

" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ? " የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል…
#Update
በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ፣ #ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።
አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

#Update በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ፣ #ገለልተኛ እና…
#Update
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ።
ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
" በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረገው ግድያ ቀጥሏል " ያለው ኦነግ የታወቂውና ተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሳይረሳ እና ቤተሰቦቹ እስካሁን ፍትህ ሳያገኙ የበቴን ኡርጌሳን ግድያ መስማት እጅግ አሳዛኝ ነው ብሏል።
ጃል በቴ በተወለዱበት መቂ ከተማ #በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን በመግለጫው ላይ አመልክቷል።
" ምንም እንኳን ሁኔታው ለሁላችን እጅግ በጣም ከባድ ቢሆንም በግድያው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረግን ነው " ሲል ገልጿል።
" ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እና ሰላም ወዳድ ህዝቦች አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ " ጥሪ አቅርቧል።

Photo
#Update
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፥ ዛሬ በባሕር ዳር ስታዲየም በነበረ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ወቅት ፥ ከቀናት በፊት በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል።
ህዝበ ሙስሊሙ ጉዳዩን እጅግ በሰከነ መንገድ ፣ በአስተውሎት ተመልክቶ ችግሩ እንዳይባባስ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርቧል።
ግድያው የዒድ አልፈጥር በዓል በሀዘን ስሜት እንዲከበር እንዳደረገውም ገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ፤ በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የተፈፀመውን ግድያ " አረመኔያዊ ነው " ያለ ሲሆን " ግድያው በዓሉን #በሀዘን ውስጥ ሆነን እንድናከብረው አስገድዶናል " ብሏል።
ግድያውን " የሽብር ድርጊት ነው " ሲልም ጠርቶ " ሁሉም ሰው በአንድ ቃል ማወገዝ አለበት " ሲል ገልጿል።
ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላው ወገኖቹ ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ ፣ አካባቢውን ፣ ከተማውን እንዲሁም ክልሉን የእልቂትና ውድመት ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ግድያ ነው ሲልም አስረድቷል።
የሙስሊም ማህበረሰብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ በመመልከት የግድያው ፈጻሚዎች በህግ አግባብ ብቻ እንዲዳኙ እንጂ " እሾህን በእሾህ መንቀል " ተገቢ አይደለም በማለት ላደረገው አስተዋጽኦ ፣ መረጋጋትና ስክነት የከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርቧል።
ከቀናት በፊት በባህር ዳር ቀበሌ 14 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም 1 ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸው ይታወሳል።
እስካሁን ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ አካል ስለመኖሩ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

#Update የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። " በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና…
#Update #MNO
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ በፅኑ #እንደሚያወግዝ ገለጸ።
በወንጀሉ ዙሪያ ተገቢው ምርመራ እንደሚደረግና ውጤቱ ለህዝብ እንደሚገለጽ አሳውቋል።
የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ የኦነግ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ #ባልታወቁ_ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን ገልጿል።
" ይህ በማንኛውም መንገድ በየትኛው አካል ይፈፀም ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ያለው የክልሉ መንግሥት ግድያውንም " በፅኑ አወግዛለሁኝ " ሲል አሳውቋል።
" ምንም እንኳን መንግሥት ከአቶ በቴ ኡርጌሳ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረውም ከግድያው ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር የለም " ሲል ገልጿል።
ምርመራ ባልተደረገበት ሁኔታና ወንጀል ፈጻሚው ገና ባልታወቀበት ሁኔታ ክስተቱን ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ የሚጠቀሙ ኃይሎች መኖራቸውን በማመልከት አጥብቆ አውግዟቸዋል።
" ከመንግስት ጋር የአቋም ልዩነት ስላላቸውና የፖለቲካ አቋማቸው ስለሚለይ ብቻ ግድያው በመንግሥት አካል እንደተፈፀመ ተደርጎ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፥ " የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን ለግድያው ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሁኔታ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው " ሲል ወቅሷል።
መንግሥት በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ባወጣው መግለጫ ቃል ገብቷል።
የፀጥታ ኃይሎች የግድያውን ፈፃሚ በህግ አግባብ መርምረውና አጣርተው እስካላሳወቁ ድረስ " ይህ አካል ነው ኃላፊነት የሚወስደው " ብሎ መናገር እንደማይቻል ጠቁሟል።
ማህበረሰቡ ገና ውጤቱ ሳይታወቅ እየተካሄዱ ካሉት " እከሌ ነው የገደለው " ከሚሉ ፕሮፖጋንዳዎች ራሱን መጠበቅ አለበትም ብሏል።

#AddisAbaba
➡ " እስሮች እንዳሉ መረጃዎች እየደረሱን ነው " - ኢሰመኮ
➡ " ምናልባት ወንጀል ፈጽመው ሊሆን ይችላል " - የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምክንያቱ በትክክል ባልታወቀ ጉዳይ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት አማካኝነት አፈሳና እስር እየተከናወነ መሆኑ እየተነገረ ነው።
ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰዎች እየታፈሱ ወደ ፖሊስ ጣቢዎች እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን እንዲሁም የታሰሩትን ለመልቀቀ የገንዘብ ድርድር የሚያደርጉ የፀጥታ አካላት እንዳሉ እና በገንዘብ ተደራድረው የተፈቱ ስለመኖራቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ተነግሯል።
ስልክ አስከፍተው የሚበረብሩ እና ውስጡ ባሉት የተለያዩ ይዘቶች " እናተ ተልዕኮ አላችሁ " በሚል የሚታሰሩ እንዳሉም ተገልጿል።
የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትም ለእስር እየተዳረጉ ነው ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም እየተፈጸመነ ነው የተባለውን የአፈሳና እስር ጉዳይ ሰምቶ እንደሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን የጠየቀ ሲሆን ፣ አንድ የኮሚሽኑ አካል በሰጡት ቃል ፤ " በከተማው እስሮች እንዳሉ መረጃዎች እየደረሱን ነው " ብለዋል።
አክለውም " ሰዎቹ የታሰሩበትን ጉዳይ ለማጣራት አዲስ አበባ ላይ ከሚሰራው የእኛ ቲም ጋር እየተነጋገርን ነው። አሁን ላይ የተረጋገጠ መረጃ የለም። በተለመደው ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ሲኖሩ ክትትል ነው የምናደርገው ፣ አሁንም እሱን ነው የምናደርገው " የሚል ቃል ሰጥተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንንም ጠይቋል።
የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " ምናልባት ወንጀል ሰርተው ሊሆን ይችላል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
" የታሳሪ ቤተሰቦች በርካቶች ሰዎች ታሰሩባቸው በተባሉ ጣቢያዎች፣ ገብተው የሥራ ኃላፊዎችን ያነጋግሯቸው። የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ የሚሰጡ ይሆናልም " ብለዋል።
ኮማንደር ማርቆስ፣ " ምናልባት ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ ወደ ኮሚሽኑም (አዲስ አበባ ፓሊስ) መምጣት ይችላሉ። " ሲሉ ጠቁመዋል።
አክለውም ፣ " ምንድን ነው ? የሚለውን ነገር ቼክ ማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ቢሯችን ሁሌም በማንኛውም ሰዓት ክፍት ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
(ጉዳዩን በተመለከተ ከፓሊስም ሆነ ከኢሰመኮ የሚሰጥ ተጨማሪ ምላሽ ካለ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)
#TikvahethiopiaFamilyAA

#አውሮፓ
የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን #የስደተኞች እና #የጥገኝነት ደንቦችን የሚያጠናክር ትልቅ ማሻሻያ አጽድቋል።
የአውሮፓ ህብረት የጥገኝነትና ፍልሰት ስምምነት ከ2015 ጀምሮ ሲመከርበት የቆየ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
አዲሱ ሕግ ምን ይዟል ?
➡️ የጥገኝነት ሂደት ጥያቄ #ያፋጥናል ፤ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ #ያስገድዳል።
➡️ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ኃላፊነት እንዲጋሩ ያደርጋል።
➡️ የአውሮፓ ህብረት 27 አባል አገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን ካሉ " #የድንበር " አገራት እንዲወስዱ ወይም በምትኩ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያደርጋል።
➡️ ዝቅተኛ ተቀባይነት የማግኘት እድል ያላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት ሳያስገቡ ጉዳያቸው በፍጥነት መታየት አለበት ይላል።
➡️ የጥገኝነት ጥያቄዎች ቢበዛ በ12 ሳምንታት ውስጥ እንዲያልቁ ይላል።
➡️ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ #በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው ይላል።
➡️ ስደተኞች ከመግባታቸው በፊት ባሉ በ7 ቀናት ውስጥ ጠንከር ያለ የማጣራት ሂደት ይደረግላቸዋል። የጤና እና የደህንነት ፍተሻዎችን ይጨምራል።
➡️ ከ6 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ስደተኞች የባዮሜትሪክ መረጃ ይሰበሰባል። ስደተኞች ቁጥር በአጋጣሚ ካሻቀበም ምላሽ የሚሰጥበት አሠራር ተዘርግቷል።
ምንም እንኳን አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አገራት የተወሰኑ የስምምነቱን ክፍሎችን ቢቃወሙም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሚደረግ ድምጽ አሰጣጥ የአብዛኛውን ይሁኝታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ℹ ባለፈው አመት 380 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአውሮፓ ህብረትን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ አቋርጠዋል። ይህም እ.አ.አ ከ 2016 ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው።
ስለ ሕጉ ምን ተባለ ?
#ጀርመን፦ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ ታሪካዊና አስፈላጊ እርምጃ ” ብለውታል።
#የአውሮፓ_ፓርላማ፦ የፓርላማው ፕሬዝዳንት ሮቤታ ሜሶላ “ በአብሮነት እና በኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቋል ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ባይፈታም ግን 10 ግዙፍ እርምጃ የተጓዘ ነው " ብለዋል።
#ሀንጋሪ ፦ ምንም አይነት የስደት ስምምነት ቢደረስ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን አልወስድም ብላለች።
#ፖላንድ ፦ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መውሰድ አልያም ለድንበር አገራት ገንዘብ መክፈል የሚለውን ሃሳብ " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።
#ስሎቫንያ፦ “ ልንሰራበት የምንችለው ስምምነት ነው ” ስትል ደግፋለች።
#ቤልጂየም፦ “ ፍፁም አይደለም (ሕጉን) ግን እንደግፈዋልን ” ስትል አሳውቃለች።
#ፈረንሳይ ፦ ፕ/ት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ ሰጥተዋል። የፈረንሣዩ ቀኝ አክራሪ ናሽናል ራሊ አባል ጆርዳን ባርዴላ ስምምነቱ “ #አስፈሪ ” ነው ሲሉ ተቃውመዋል።
#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል ፦ ስምምነቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ “ከፍተኛ ስቃይ” የሚመራ ነው ሲል አስጠንቅቋል።
ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚነሳው አንዱ ተቃውሞ ዝቅተኛ ተቀባይነት የሚኖራቸው #ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው በድንበር #መግቢያዎች ላይ ወይም #በማቆያ_ስፍራዎች እንዲስተናገዱ በማድረግ ፍትሃዊ ዕድል የማግኘት ተስፋቸውን ያመነምነዋል የሚል ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ መሆኑን ይገልጻል።

#ወጋገን_ባንክ
አጓጊው ቀን ደረሰ ‼️
ወጋገን ባንክ ባዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር ጠቀም ባሉ አጓጊ ሽልማቶች ሊያንበሸብሽዎ ነው!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ!! አሁኑኑ ከስር የተቀመጡትን የወጋገን ባንክ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል እና የፌስቡክ ገፅ ሊንኮች ተጭነው በመቀላቀል እና ጥያቄዎችን አስቀድመው በመመለስ አጓጊ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ!
👉ቴሌግራም https://t.iss.one/WegagenBanksc
👉ፌስቡክ https://m.facebook.com/bankwegagen/
ልብ ይበሉ ይፋዊ የባንካችንን ገፆች በመቀላቀል እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ ለወራት በሚቆየው የጥያቄ እና መልስ ውድድር በመሳተፍ አሸናፊ ሲሆኑ አጓጊ እና ጠቀም ያሉ ሽልማቶችን ከባንካችን ይረከባሉ ‼️