TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የነዳጅ ክፍያዎን በሲቢኢ ብር በቀላሉ ይፈፅሙ!
**********
አዲስ በተሻሻለው የሲቢኢ ብር መተግበሪያ የነዳጅ ክፍያን መፈፀም እጅግ ቀሏል፡፡

የነዳጅ ቀጂውን ስልክ ቁጥር፣ የሚገዙትን የነዳጅ መጠን እና አይነት እንዲሁም ታርጋ ቁጥርዎን በማስገባት ብቻ ክፍያውን በቀላሉ መፈፀም ይችላሉ!
**********
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለማውረድ/ለማዘመን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

#CBE #cbebirr #fuel #payment
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrDessalegnChane በ2013 ዓ/ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መታሰራቸውን ቤተሰባቸውን ዋቢ በማድረግ አል አይን አማርኛው አገልግሎት ዘግቧል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ቤተሰብ አባል ፤ " ትናንት ጥር 22 ቀን…
#NewsAlert

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ እንደተወሰነላቸው ጠበቃቸው ተናግሩ።

በ2013 በተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ታስረው ቆይተዋል።

ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ፤ ደንበኛቸው ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በዛሬው ዕለት በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ እንደተነገራቸው ለአል አይን ኒውስ ተናግረዋል።

ይሁንና እስካሁን ድረስ ከእስር ስለመለቀቃቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ከሰዓት ከእስር መለቀቃቸውን የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ  ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ከዚህ ባለፈው ድርገፁ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ)፣ የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው " በምህረት " ከእስር እንደሚፈቱ ከታመኑ ምንጮች መስማቱን ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአል ዓይን ኒውስ እና የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

" የአየር መንገዳችንን ሰራተኛ ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ አሳዝኖናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትናንት ጀምሮ የአየር መንገዱን ዩኒፎርም የለበሰ ሰራተኛን የራሱን ሻንጣ በማስተካከል ላይ ሳለ የሚያሳይ ምስል ከተሳሳተ መረጃ ጋር በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በመዘዋወር ላይ እንዳለ ገለጸ።

ይህን ተከትሎ ፦
* በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ባልደረባ (Ethiopian Aircraft Technician) መሆኑን

* የአየር መንገዱ ዓርማ የታተመበት ሻንጣም የሰራተኛው መሆኑን፤

* በምስሉ ላይ የሚታየው ቦታ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ሰራተኞች የግል ንብረቶቻቸውን እና ለስራ የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች የሚያስተካክሉበት አካባቢ መሆኑን ግልጿል።

ሌሎቹ ቦርሳዎችም በምስሉ ላይ ያልተካተቱ የሌሎች ሰራተኞች ቦርሳዎች ናቸው ብሏክ።

" ይህ ስፍራ የመንገደኞች ሻንጣ ሊገኝበት የማይችል ለሰራተኞቻችን ብቻ የተከለለ ቦታ ነው " ያለው አየር መንገዱ በተጨማሪም ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት በደህንነት የካሜራ ዕይታ ውስጥ የሚገኝ እንደሆነ አመላክቷል።

በስራ ገበታው ላይ የሚገኝ የአየር መንገዱን ሰራተኛ ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ አሳዝኖኛል ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ በምስሉ ላይ የሚታየው የአየር መንገዱ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ባልደረባና የሚያስተካክለው ሻንጣም የራሱ መሆኑን አስገንዝቧል።

ደንበኞቹም ከሚዘዋወረው ምስል ጋር ተያይዞ ምንም ስጋት እንዳያድርባቸው አሳስቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች ሆነ ለንብረቶቻቸው ደህንነት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሰራኞቻችንም ደረጃውን የጠበቀ የደንበኛ አገልግሎት ለመስጠት ትጉህ መሆናቸውን አመልክቷል።

በተሳሳተ መረጃ የብሔራዊ አየር መንገዱን ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎች እንድትጠበቁ ሲልም መክሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ እንደተወሰነላቸው ጠበቃቸው ተናግሩ። በ2013 በተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ታስረው ቆይተዋል።…
አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ።

ከ6 ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ገልጸዋል።

ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ ፤ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክሳቸው ተነስቶ የተለቀቁት ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል።

ከአቶ አብዲ በተጨማሪም በተመሳሳይ በእሳቸው የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ የሌሎችም ተከሳሾች ክስ ተቋርጦ መለቀቃቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው ከዓመታት በፊት ጀምሮ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ሲመሩ የነበሩት አቶ አብዲ፣ በክልሉ ውስጥ ከተፈጸሙ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎች እና የመንግሥት ሀብት ብክነት ጋር በተያያዘ ክስ ይቀርብባቸዋል።

በቀድሞው ርዕሰ መስተዳደር ላይ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከልም በ2010 ሰኔ እና ሐምሌ ወራት ውስጥ “በሶማሌ ክልል የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በማሰብ ‘ሄጎ’ በሚል ስያሜ የሚታወቅ ወጣቶች ቡድን አደራጅተዋል” የሚል ይገኝበታል።

በወቅቱ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው፣ ንብረት እና አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

ዐቃቤ ሕግም ባቀረበው የክስ ዝርዝር በተከሰተው ግጭት ምክንያት ፦
* 59 ሰዎች #መገደላቸውን
* ከ250 በላይ መቁሰላቸውን
* በመንግሥት፣ በግል እና በሃይማኖት ተቋማት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልጾ ነበር።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ። የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ከ6 ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ገልጸዋል። ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ…
#Update

በእነ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘውና በእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች እንዲቋረጡ ተወሰነ።

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና በእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) መዝገቦች ቀርበው የነበሩ ክሶች እንዲቋረጡ መወሰኑን አሳውቋል።

ክሶቹ እንዲቋረጡ የተወሰነው " ለህዝብ ጥቅም " ነው ብሏል።

በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ስር ያሉ ተከሳሾች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ወንጀል ክስ ክርክር ሲካሄድ ነበር።

በሌላ በኩል የእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የክስ መዝገብ በ1ኛ የህገመንግስትና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት የክርክር ሂደት ላይ ቆይቷል።

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር እነዚህ የክስ ሂደቶች " ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም " ሲባል እንዲቋረጡ ተወስኗል ብሏል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ወርሃዊ ክፍያዎችን በፍጥነት ባሉበት ሆነው ለመፈጸም የአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ መተግበርያን ይገልገሉ። 

ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://

play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
ፎቶ ፦ ከትግራይ ተጉዘው አዲስ አበባ የተገኙ ከትግራይ ክልል ከተለያየ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መከሩ።

በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አሳውቀዋል።

" በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ፅኑ ነው " ያሉት ጠ/ሚስትሩ " የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ አላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነው “ ብለዋል።

ዛሬ በተካሄደው የውይይት መድረክ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የመከላከያው ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ተገኝተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑን ከሁሉም ክልል ተወካዮች ጋር እንዲሁም ከሃይማኖት አባቶች ጋር ምክክር ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ የትግራይ ተወካዮቹ ከሁሉም የትግራይ ዞኖች የተውጣጡ ሲሆኑ ብዛታቸው 200 ይጠጋል።

በቻርተር  አውሮፕላን እንዲጓዙ ተደርጎ ነው አዲስ አበባ የመጡት። አዲስ አበባ ከመጡ በኃላ ትላንት የዓድዋ መታሰቢያንን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል። ዛሬ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia
#ICS #Ethiopia

" በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል " - ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት በትግራይ ተቋርጦ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን አገልግሎት ለማስጀምር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

አገልግሎቱ ትላንት በሰጠው መግለጫ ነው ይህን ያለው።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት 6 ወራት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌቶችን ከውጭ ሀገር በማስገባት 640 ሺህ ፓስፓርት ፐርሰናላይዜሽን ህትመት በመስራት ለተጠቃሚዎች ማድረሱን አሳውቋል።

• ለአዲስ አበባ 260,371፣
• በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣
• በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 እንደሆነ አመላክቷል።

የውስጥ ህትመት አቅምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በቀን 2 ሺህ ይታተም የነበረው አሁን ወደ 10 ሺህ በላይ ወደማተም ደረጃ መደረሱን ገልጿል።

መ/ቤቱ በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ በይፋ አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ በእጁ ላይ 80 ሺህ ፓስፖርት ስላለ ያመለከቱና ተራው የደረሳቸው በስልክ በሚደርሳቸው መልዕክት መሰረት እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ፓስፖርት ለማውጣት ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረው የአንድ አመት ጊዜ ከመጋቢት 16 /2016 በኃላ እንደሚቀረፍ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት ገልጿል።

ከዚህ በባለፈ ፤ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ፦
➡️ከዋና ቢሮ፣
➡️ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣
➡️ ከቦሌ፣
➡️ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ #ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው ለህግ አካላት እንዲቀርቡ እንደየጥፋታቸውም ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድቷል።

ህብረተሰቡ ፦

* ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ
* በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣
* ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣
* ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣
* አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት  መስተናገድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

@tikvahethiopia