TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Empowering Africa, One Venture at a Time. Jasiri Talent Investor strives to remove barriers that hinder the success of new businesses. The program guides the Fellows from ideation to venture creation, by providing funding, coaching, strategic advisory, and guidance in the complex innovation space.

Application for Cohort 6 is ongoing, submit your application via https://jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
#MertEka

እነዚህ የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ  ይሄንን👉  t.iss.one/MerttEka 👈 ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376
PHOTO ፦ የመጀመሪያው ምሽት ተራዊህ ሶላት በሳዑዲ አረቢያ - #RAMADAN #ረመዷን ☪️

Photo Credit : Haramain

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ስትራቴጂካዊ ግምገማ ተጀምሯል።

እነማን ተገኙ ?

- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት
- የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዛዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
- የቀድሞው የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ይገኙበታል።

የፌደራል መንግስትን ከወከሉት መካከል ፦

* የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣
* የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣
* የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ ይገኙበታል።

ህወሓትን ከወከሉት መካከል ፦

° ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ሊቀመንበር)
° አቶ ጌታቸው ረዳ (ም/ሊቀመንበር እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት)
° ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ (የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት)
° ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ (በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ) ይገኙበታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ "...መግለጫው የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ ያመላከተ ነው " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም የትግራይ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ የኤርትራ ጦር  የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን መሬቱን ለቆ እንዳልወጣ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደርን ጨምሮ ሀገራትና ተቋም በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል። በቅርቡ እንግሊዝ የሚገኘው…
#Tigray

" የኤርትራ ሰራዊት በራሱ ግዛት ነው ያለው የሚለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ ራስን ከማሞኘት ያለፈ ትርጉም የለውም " - አኒና የኢሮብ  ማህበረሰብ መብት ጠባቂ ማህበር

አኒና የተባለው የኢሮብ ሲቪክ ማህበረሰብ  ማህበር መጋቢት 1/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ኢትዮጵያ በሚገኙ 3 ዞኖች የሚገኙ በርካታ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ነዋሪዎች እያንገላታና ግፍ እየፈፀመ ይገኛል ብሏል።

ስቪክ ተቋሙ የኤርትራ መንግስት የካቲት 28/2024 ያወጣው መግለጫን በተመለከተ " የኤርትራ መንግስት የትግራይ ኢትዮጵያ መሬቶች መያዙ በዚህ በሰለጠነ የመረጃ ዘመን ፈፅሞ መካድ አይቻልም " ብሎታል።

የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ ከእውነት የራቀና በፍፁም መወገዝ ያለበትን ነውም ብሏል።

የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፦
- የዛላኣንበሳ ከተማ
- በጉሎመኸዳ ወረዳ ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ፣ ሸዊት ለምለምና ሰበያ
- በኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ፣ ወርዓትለ ዓገረ ሎኽማና ዓሊቴና የተባሉ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል ሲል ገልጿል።

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በታሕታይ ኣድያቦ የኩናማ ማህበረሰብና ሌሎች የሚኖሩባቸው ገማህሎ ፣ አደመይቲ ፣ የባድመ ከተማና አከባቢው ፣ ዓዲ ፀፀር ፣ ለምለም ሸዊት ፣ ሸምበሊና ፣ መንጠብጠብ ፣ ዓዲ ኣሰር ፣ ሰየምቲ አድያቦ በኤርትራ ስራዊት ስር እንደሚገኙ ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው ሲልም አክሏል።

የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ማእከላዊ ዞን የእገላና ራማ አከባቢዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቆጣጥሮ የአከባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ ለበርካታ ችግሮች እንዳጋለጠው  ያመለከተው አኒና የኢሮብ ስቪክ ማህበረሰብ መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ህዝቡ ከእንግልትና መከራ እንዲታደገው ጥሪ አቅርቧል።

አኒና የኢሮብ ሲቪክ ማሕበረሰብ ያወጣውን መግለጫ የተከታተሉ የመቐለ ነዋሪዎች ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት አስተያየት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች የፌደራል መንግስትና ህወሓት ፣ የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ ፣ ኢጋድና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተዛቢዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውል አተገባበርና አፈፃፀም አስመልክቶ በሚካሄደው ግምገማ በኤርትራ ሰራዊት ስር ስላሉ የትግራይ ኢትዮጵያ ግዛቶች ጉዳይ የውይይቱ አካል ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                           
@tikvahethiopia            
 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጥንታዊውና ታሪካዊው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች መገደላቸው አንድ አባት ደግሞ አምልጠው ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ መነገሩ ይወሳል። ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ መላከሰላም ቀሲስ ዳዊት ያሬድ በሰጡት ቃል ፤ " ከተገደሉት አባቶች መካከል ያልተገኙ አንደኛው…
" ገዳሙ የ2016 ዓ/ም የማህበር ቀለብ መሸመት እስከማይችል ድረስ ኢኮኖሚያዊው ተጎድቷል " - ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም

በመላው ዓለም የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ቀረበ።

ጥሪውን ያቀረበው ገዳሙ ነው።

ይህ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም ከቅብር አመታት ወዲህ የመነኮሳትን ህይወት መስእዋትነት እስከማስከፈል የደረሰ ለዘርፈ ብዙ ጥቃት መጋለጡን ገልጿል።

ገዳሙ ከዚህ ቀደም በገንዘብ ከተፈፀመበት ዝርፊያ ባለፈ በቅርቡ ለገዳሙ አይን የሆኑ 4 መነኮሳት አባቶች አሰቃቂ በሆነ መንገድ መገደላቸውን ይህም የመነኮሳትን ልብ የሰበረ እንደሆነ አመላክቷል።

በ2012 የተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ በየትኛው ተቋም ላይ ያደረሰው አሉታዊ ተፅእኖ በገዳሙም ላይ እንዲሁ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን አሁን ላለበት እጅግ ዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጥ የጀመረው ግን ህገወጥ ታጣቂዎች አካባቢው ላይ መንቀሳቀስ ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ ነው ብሏል።

ገዳሙ ፤ ህገወጥ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ወደ ገዳሙ በመግባት የጥበቃ ትጥቅ በመንጠቅ ገዳሙን በመዝረፍ አራቁተውታል ሲል ገልጿል።

ይህ ሁኔታ የ2016 ዓ/ም የማህበር ቀለብ መሸመት እስከማይችል ድረስ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እንደጎዳው አስረድቷል።

በተለያዩ መስኮች እና አገልግሎቶች መንፈሳዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጸው ገዳሙ አሁን እየደረሰበት ያለው ጥቃት ሁለንተናዊ ችግር ላይ ስለጣለው የህዝበ ክርስቲያኑን ትብብር ግድ የሚልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በይፋ አሳውቋል።

በመሆኑን በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች አቅማቸው በፈቀደ በገንዘብም ፣ በቁሳቁስ፣ በሞያ፣ በሃሳብ የእርዳታ እጃቸውን ለገዳሙ እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርቧል።

የገዳሙ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000011282222 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ወይም 31905877 (አቢሲንያ ባንክ) መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውጭ ገዳሙ የመደበውም ሰው ይሁን ማህበር ስለሌለ ከተጠቀሰው አካውንት ውጭ #እንዳታስገቡ ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገዳሙ አስተዳደር ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia