TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ” - የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።

በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው።

በአማራ ክልል በ “ፋኖ” ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በየወቅቱ እያገረሸ የሚስተዋለውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚስተዋለው ሞት እየጨመረ መሆኑን፣ ሴቶችም ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች እየተበራከቱ መሆኑን የክልሉ ሴቶች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የክልሉን ሴቶች ማኀበር ወክለው የመጡ ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው  ምን አሉ ?

ከጤና ጋር ተያይዞ የእናቶች ሞት፣ የሕጻናት ሞት ከበፊቱ በጣም እየጨመረ መጥቷል።

በጣም በርካታ ሴቶች ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። አንደኛ ፍትህ የሚያገኙበት አጋጣሚም የለም። ሁለተኛ ደግሞ ከጦርነቱ ዘለው ወደ IDP center እንኳን ሲገቡ እዚያው ውስጥም መልሶ ጥቃት የሚያጋጥምበት ሁኔታ አለ።

ሰላም አስካልተጠበቀ ድረስ ሴቶች ነገም፣ ከነገ በኋላም የጥቃቱ ሰለባ ናቸው። በአጠቃላይ እንደ አገራችን፣ እንደ አማራ ክልልም ሴቶች ጥቃት እየደረሰባቸው ያለው ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ነውና የሴቶች አደረጃጀቶች ሰላምን ከማስጠበቅ አንጻር ጎልተው መውጣት አለባቸው።

አማራ ክልል ራሱ የበፊቱን እንኳን ትተነው አሁን በሚስተዋለው ግጭት ብቻ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል። ስለዚህ በዋናነት ይህን ጥቃት ለማስቆም መስራት ያለብን ሰላሙ ላይ ነውና በተለይ የሴቶች አደረጃጀት ደግሞ በጋራ ሆነው መንግሥትን፣ ሌላውንም አካል በማወያየት ሰላሙ ላይ ብንሰራ የሴቶችን ጥቃት መቀነስ ይቻላል.

በትላንቱ መርሀ ግብር የተለያዩ ተቋማትን ወክለው የተገኙ ኃላፊዎች በበኩላቸው ማኀበራቱ ሁሉ በጸጥታ ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ቅንጅት በሠፍጠር ልዩ ትኩረት እንዲሰጥበት በውይይታቸው አንስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታታይ የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በሞተር ብስክሌት ላይ እስከ ሰኞ ገደብ ተጣለ።

በአዲስ አበባ ከነገ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 25/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 12:00 ሰአት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም  የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ክልከላው ለምን እንደተጣለ በግልፅ ያሳወቀው ነገር የለም።

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ተብሏል።

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አሳስቦ ይህን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

ባለፈው ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጋር በተያያዘ ለቀናት የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎባቸው እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Infinix_Hot40

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ማራኪ ዲዛይንን በማጣመር የተመረተው አዲሱ 'Hot 40 pro' ስልክ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርገዋል!

#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries
" የአድዋ ሩጫ እንዳይካሔድ ተከልክለናል " - አዘጋጆቹ

' አድዋ ሩጫ ' የተሰኘ ድርጅት በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረው ሩጫ መከልከሉን አስታወቀ።

ድርጅቱ ዛሬ ጥዋት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ የሚመለከታቸው እና ፍቃድ መስጠት ያለባቸው የመንግሥት አካላት ሩጫው እንዲካሄድ ፍቃድ ሰጥተው እንደነበር ገልጿል።

ነገር ግን በቀን 05/06/2016 የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሩጫው መካሄድ እንደማይችል እንዳሳወቀው አመልክቷል።

ድርጅቱ ይህንንም ሊያስቀይር ይችላል ያልነውን " ምናልባት በፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከሆነ የምከለክሉን የዚህን አመት ብቻ በፕሮፌሽናል አትሌቶች ብቻ ማካሔድ እንችላለን " የሚል አማራጭ ሃሳብ በቃል ማቅረቡን ገልጿል።

ነገር የድርጅቱ ሰዎች ከቢሮ ውጪ እንድንቆዩ ተደርጎ ከደቂቃዎች የስልክ ውይይት በኃላ ዳግም ተጠርተው " አድዋን ተዉት " የሚል ትዕዛዝ አዘል የክልከላ መልስ እንደተሰጣቸው አሳውቋል።

ድርጅቱ ህገወጥ ነው ባለው በዚህ ክልከላ የሞራልና የገንዘብ ኪሳራ እንዳጋጠመው አመልክቶ " ከምንም በላይ ደግሞ አኩሪ ታሪካችን የሆነውን የአድዋ ድል በአል እንደዜጋ ማክበር አለመቻሉ ክፉኛ አሳዝኖናል " ብሏል።

በተጨማሪም " ይህንንም ክልከላ ለአንዳንድ ሚዲያዎች ለጉዳዩ ሽፋን ሰጥተው ለህዝብ እንዲያሳውቁልን ብንጠይቅም ሽፋን ሊሰጡት ፍቃዳቸው እንዳልነበር ህዝብ " ይወቅልን ብሏል።

(ድርጅቱ የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" ክረምቱ ይገባል በኛ በኩል ጊዜውን ከዚህ በላይ መግፋት አንችልም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

" ምርጫው የሚደረግባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታ፣ የበጀት እና ድምፅ የሚሰጥበት ቀን እና ጊዜ ይታሰብበት " - ተፎካካሪ ፖርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፀጥታ ችግር ምክንያት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያልተደረገባቸው እና ቀሪ ምርጫ የሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ አራት ክልሎች  በሰኔ 6 2016 ዓ/ም ምርጫ የሚደረግ መሆኑን አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ ከጥር 22 ፥ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቢሮዎችን የመክፈት እንቅስቃሴ በመጀመር ፣ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ምልመላ እያከናወነ ሲሆን የመራጮች ምዝገባ ከሚያዚያ 7 እስከ ሚያዚያ 21 / 2016 ዓ/ም ለማድረግ አቅዷል።

ምርጫ ያልተደረገባቸው እና ቀሪ ምርጫ የሚደረግባቸው ፦
👉 4 ክልሎችን ፣
👉 29 የምርጫ ክልሎችን ፤
👉 1146 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎችን፣
👉 በ34 የሀገር ውስጥ የተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ወደ 5730 የሚሆኑ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ባካተተ መልኩ ለ9 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እና ለ26 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምርጫ ይደርጋል።

የሲቪክ ማህበራት እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምን አሉ ?

- የምርጫ ጊዜው ክረምት መሆኑ አብዛኛው መራጭ አራሽ ገበሬ መሆኑን ያላገናዘበ መሆኑ ፤ በተጨማሪም የምርጫው ቀን ሰኔ 6 2016 ዓ/ም ቀን ሐሙስ የሚውል መሆኑን ተከትሎ ቀኑ እንዲሻሻልና በእረፍት ቀናት እንዲደረግ ሀሳብ አላቸው።

- ለመራጮች ምዝገባ የተሰጠው ቀን ከሚያዚያ 7 እስከ 21 መሆኑ እና የእጩዎች ምዝገባና ከሚያዚያ 7 እስከ ሚያዚያ 16 ፥ 2016 ዓ/ም መሆኑ የሚያንስ ስለሆነ ቀኑ እንዲጨመር ጠይቀዋል።

- ምርጫ ከሚደረግባቸው ክልሎች አንዱ በሆነው ቤንሻንጉል ክልል መተከል እና ካማሺ እና ሌሎች አካባቢዎች ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት ምርጫውን ለማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ ቦርዱ አራቱ ክልሎች ያሉበትን የፀጥታ ሁኔታን የሚለይ ግምገማ አድርጎ ከሆነ ጥያቄ ቀርቦለታል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወ/ሮ ሜላተ ወርቅ ሀይሉ ለጥያቄዎቹ ምን ምላሽ ሰጡ ?

የምርጫ ቀኑ #ሐሙስ እንዲሆን የተወሰነው ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት እና የገበያ ቀናት በመሆናቸው ምክንያት ያን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

ቦርዱ ጥያቄውን #የሚቀበለው መሆኑን እና ቀኑ ወደ እረፍት ቀናት ሊቀየር የሚችልበትን ሁኔታ እንዳለ ፍንጭ ተሰጥተል።

ቀኑ አጠረ ስለተባሉት የምዝገባ ቀናት ከጊዜ እጥረት አኳያ መሆኑን ገልጸዋል።

ቦርዱ ምርጫ በሚደረግባቸው ክልሎች ያሉበትን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከተው አካል መረጃ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ነው።

ቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፀጥታ ሁኔታ ግምገማ ስብሰባ እንደሚኖር በመግለፅ የፀጥታ ሁኔታውን ለባለድርሻ አካላት ይፋ የሚያደርግ መሆኑን አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

ይህ ተከትሎ መንገዶች ይዘጋሉ።

በዚህም መሰረት፡-

- ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ

- ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ

- ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ

- ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ

- ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት

- ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ

- ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
እነሆ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ይበልጥ የሚያደምቅ ልዩ አድዋ የሞባይል ጥቅል አሰናድተን እስከ 20% በሚደርስ ቅናሽ በአርዲ ቻትቦት፣ በማይ ኢትዮቴል እና *999# እንዲሁም በቴሌብር https://onelink.to/fpgu4m ከተጨማሪ 10% ቅናሽ ጋር አቅርበናል።

ጥቅሉን ለራስዎ በመግዛትና በስጦታ በማበርከት በዓሉን በደስታ ያሳልፉ!

መልካም የድል በዓል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#Adwa128

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ስነስርዓቶች እንደሚከበር አሳውቋል።

በዓሉ በአ/አ ፒያሳ በሚገኘው የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም " እንደሚከበር ገልጿል።

የዓድዋ ጀግኖችን የሚዘክር የ34 ደቂቃ ዶክመንታሪ ፊልም፣ ቢል ቦርድ፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ሎጎ፣ መሪ ቃል እና ሠራዊቱ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ሆኖ የሚወያይበት ፅሁፍ ተዘጋጅቷል ተብሏል።

በዕለቱ የካቲት 23 ቀን ወታደራዊ የሰልፍ ትርኢት እና ድሉን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ትርኢቶች ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይቀርባል ተብሏል።

@tikvahethiopia