የተረክ በM-PESA የዕጣ ሽልማት ሊያልቅ 1 ወር ብቻ ቀርቶታል! አልሰማንም የሚልን እንዳይኖር!
የመጨረሻዋ መኪና ሌሎች ዕጣዎችን ጨምሮ እናንተን እየጠበቀ ነው። ውሰዱት እንጂ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ @SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!
#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA

TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በተለያዩ ጊዜያት የጅምላ እስር እና አፈሳ ይደረጋል በሚል ቅሬታዎች ሲነሱ ቆይተዋል። የመንግስት ምላሽ ደግሞ " በከተማው እንዲህ ያለው ነገር የለም " የሚል እንደነበር አይዘነጋም። ይኸው የአፈሳ ነገር ሰሞኑን ከነበረው በዓል ጋር ተያያዞ ቀጥሎ በርካታ ወጣቶች " በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየታፈሱ ታስረዋል " በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታዎች ደርሶት ተመልክቷል።…
" በከተራ በዓል የታሰሩ 32 ሰዎች ተፈትተዋል " -የታሳሪ ቤተሰብ
በ2016 በተለይ ከከተራ በዓላት ጀምሮ ወጣቶች በአፈሳ መልኩ ታሰሩ የሚሉ ቅሬታዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰውት ነበር።
ለአብነትም በ2016 ዓ/ም የከተራ በዓል ዕለት አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ " 32 የአማራ ተወላጆች በፓሊስ ተይዘው " ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 12 መታሰራቸውን፣ እነዚህ ሰዎች ሥራ ሰርተው ልጅ የሚያሳድጉ፣ ቤተሰብ የሚረዱ ሰዎች እንደሆኑ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች መግለጻቸው አይዘነጋም።
እኚሁ ግለሰብ በወቅቱ ታሳሪዎቹን ሂደው ጠይቀው እንደነበርና የታሰሩበትን ምክንያት ምን እንደሆነ ሲጠይቁ አንዱ ታሳሪ፣ " እነሱ የከሰሱን ሁላችንንም ‘ ፋኖ በሚል ነው' " ሲሉ እንደመለሱላቸው፣ " ፖሊስም ብናናግር ‘እኛ መፍትሄ አንሰጥም’ ነው የሚሉት" የሚል ቅሬታ ለቲክቫህ አቅርበው በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።
ሰዎቹ መታሰራቸውን በወቅቱ ገልጸው የነበሩት እኚሁ የመረጃ ምንጭ የጉዳዩን ሂደት በተመለከተ ድጋሚ በሰጡን ቃል፣ " በከተራ በዓል የታሰሩ 32 ሰዎች ተፈትተዋል " ብለዋል።
መቼ ከእስራት እንደተፈቱ በገለጹበት አውድም ፣ " በጥር 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከእስር ቤት እንዲወጡ ነበር የተፈረደላቸው፣ በጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ነው ጠቅለው የወጡት (ግን 29ም የወጡ አሉ) " ሲሉ ተናግረዋል።
" አሁንም ባጃጅ ነው የሚሰሩት " ያሉት እኚሁ ቤተሰቦቻቸው ታስረውባቸው የነበሩ የመረጃ ምንጩ፣ ሰዎቹ ታስረው ሲወጡ የሥነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ በአካላቸው ላይ ግን ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አስረድተዋል።
በተያያዘ ዜና ፤ በ2016 የጥምቀት በዓል ወቅት በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በበዓለ ንግሱ እንዲሁ በፓሊስ አባላት የታሰሩ ወጣቶች እንደነበሩ በወቅቱ ሲገለጽ የነበረ ሲሆን፣ ሁሉም ስለመፈታታቸውና አለመፈታታቸው ለጊዜው ማወቅ ባይቻልም የተወሰኑት ከእስር እንደተለቀቁ ተሰምቷል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

#OROMIA
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።
ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።
ኢሰመኮ ፦
➡ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣
➡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)
➡ ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ #በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።
በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦
* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።
* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።
* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

#CentralEthiopia
ትላንትና እሁድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ ይጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ 7 ሰዎችን ከጫነ " ባጃጅ " ጋር በመጋጨቱ ነው የደረሰው።
የ5ቱ ተጓዦች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ፤ በሁለቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ ነበር። ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ከተላኩት መካከል አንደኛው ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ አልፏል።

#Oromia
ዛሬ ሌሊት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ፤ ዱከም ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
አደጋው አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በተከሰተው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በተጨማሪም 11 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።
መረጃው የቢሾፍቱ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።