TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ይሄ ' የአማራ አዋሳኝ ' የሚባለው ቀልድ መቆም ያለበት ነው " - አቶ ረዳዒ ኃለፎም
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳዒ ሀለፎም ሰሞኑን ስለነበረው የተኩስ ልውውጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ረዳዒ ሀለፎም ምን አሉ ?
- ግጭቱ ራያ አላማጣ ሳይሆን ጨርጨር አካባቢ ነው። ይሄ የአማራ አዋሳኝ የሚባለው #ቀልድ ደግሞ መቆም ያለበት ነው።
- የትግራይ መሬት ነው ጨርጨር። ጨርጨር ትግራይ እንጂ አማራ ሆኖ አያውቅም። አሁንም አይደለም። እዚያው የአማራ ታጣቂዎች አሉ። እነዛ የአማራ ታጣቂዎች በእኛ ሚሊሻዎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት ነው። የአጭር ጊዜ ተኩስ ልውውጥ ነበር ቁሟል አሁን ግጭቱ የለም።
* ጉዳዩን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ለቀረበ ጥያቄ ፦ " በእኛ በኩል (በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርም) ከላይ ከሚመለከታቸው የፌደራሉ መንግሥትም የተወሰነ ንግግር እየተደረበት ነው " ብለዋል።
* የመፍትሄ ሀሳብን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ፦
" የመጀመሪያው ነገር ሕገ መንግሥቱን ማክበር ነው። የአዋሳኝ ጉዳይ አይደለም መሀል ትግራይ ላይ ነው ችግሩ እየተፈጠረ ያለው። ወረው በኃይል ከያዙት መሬት ላይ ነው አሁን ደግሞ መልሰው ጥቃት እየፈጸሙ ያለት። ይሄ ትክክል አይደለም። ለማናችንም የሚጠቅም ነገር አይደለም።
መሆን ያለበት ጥያቄ ያለው አካልም በሕጉ መሠረት ካልሆነ በቀር የሆነ አጋጣሚ ተጠቅሞ ‘ጉልበት አለኝ፣ ይጠቅመኛል’ ብሎ ባሰበ ጊዜ የኃይል አማራጭ የሚወስድ ከሆነ፣ ቢያንስ የሕዝቦች ዘላቂ ወዳጅነትና መቀራረብ የሚያረጋግጥ አይደለም። ከዚህ መቆጠብ ነው ያለብን " ብለዋል።
- የፌደራል መንግሥት ሲቪሊያንን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ድሮም ቢሆን በውሉም በተመሳሳይ ፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖም ከመከላከያ ሰራዊት ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ውሉም ያስገድዳል። አለመውጣታቸውም ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የአማራ ታጣቂዎች ባሉበት አካባቢ ሴቶች እየተደፈሩ ናቸው። ሰብዓዊ መብቶች እየተረገጡ ናቸው። ብዙ ጥፋቶች እየተፈጸሙ ናቸው። ስለዚህ ውሉን በአግባቡ ተግባሪዊ ማድረግና በቁጥጥር ሥር መስራት ከተቻለ ብቻ ነው ወደ ሰላም ማምራት የምንችለው።
- በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ያሉት ትክክል ስላልሆኑ አደብ መያዝ ያስፈልጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 8/2016 ዓ/ም
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia

" የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣንም ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገው ሌላው የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል ! " - ነዋሪዎች (ከሰሞኑን በሚዛን አማን በነበረ ህዝባዊ ውይይት ላይ የተነሳ)
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ዕድል
በቅርብ ቀን - በዲኤስቲቪ በአቦል ቲቪ 465
📣 አዲስ ነገር ይዘን መጥተናል!
👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 የሜዳ ደንበኛ ከሆኑ ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ሲያሳድጉ... እኛም ቀጣዩን የፕሪምየም ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #አቦልቲቪ #DStvSelfService #AnEdil #አንድዕድል

#Sidama
" #አፊኒ " የተሰኘውና በሲዳማ ባህላዊ የእርቅ ስነስርአትና የግጭት አፈታት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተሰራው ፊልም ትላንት በሀዋሳ ከተማ ተመርቋል።
ፊልሙ የሲዳማ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ነው የተመረቀው።
የፊልሙ ባለቤትና ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ኃላፊነቱን ወስዶ ሲሰራዉ የነበረው የሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ነው ተብሏል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ፤ " አፊኒ ፊልም የሲዳማን ባህል ወግና ትውፊት የሚያንጸባርቅ ተንቀሳቃሽ ሙዚየም ነው " ብለውታል።
" አፊኒ " ፊልም የሲዳማን ባህል የማስተዋወቅ ዓላማ ያለዉና በኢንተርናሽናል ስታንዳርድ የተሰራ መሆኑ ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት " አፊኒ " ፊልም ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ መሰራቱን መግለጹን ተከትሎ ከፊልሙ አሰሪ ኮሚቴ " ትክክል አይደለም !! " የሚል ቅሬታ ቀርቦ ነበር።
ይሁንና ትክክለኛ የፊልሙ ወጭ ስንት እንደሆነና ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተጨማሪ ፊልሙን በገንዘብ ስላገዙ አካላት መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ሊሳካ አልቻለም።
ሌላው ከምርቃት ስርዓቱ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወጥቷል እየተባለ ስለሚነገረው በሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ መጠን ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም።
በቀጣይ ከሚመለከተው አካል መረጃ የምናገኝ ከሆነ እናቀርባለን።
መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#AU : ዛሬ የታንዛንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኜሬሬ መታሰቢያ ሐውልት ተመርቋል።
ሐውልቱ የተገነባው በአዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ፊትለፊት ነው።
በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia
ሐውልቱ የተገነባው በአዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ፊትለፊት ነው።
በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም " - መንግሥት 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ " ወደ ስብሰባው እንዳልገባ የመከልከል ሙከራ ተደርጎብኛል " የሚል ክስ አሰምተዋል። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ከስብሰባው…
#ኢትዮጵያ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም መግለጫቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ትላንት አዲስ አበባ ሆነው ስለሰጡት መግለጫ ምላሽ ሰጥተዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሰጡት መግለጫ ፤ " ካረፍኩበት ሆቴል እንዳልወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መንገድ ዘጉብኝ ፤ በኃላም ከሌላ ፕሬዜዳንት ጋር (ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢሳማኤል ኦማር ጌሌህ) ጋር ሆነን ወደ ጉባኤው ልንገባ ስንል የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ክልከላ አደረጉብን " የሚል ክስ አሰምተው ነበር።
የሶማልያው ፕሬዜዳንት ለሰጡት መግለጫ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?
" እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታቸው ደኅንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባት።
ይሁን እንጂ የሶማሊያ ፕሬዚዳት በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም።
ይህ አሠራር (የአዘጋጅ ሀገር የእንግዶችን ደህንነት ማስጠበቅ) በመላው ዓለም የተለመደ ነው። በሶማሊያ ልዑክ በኩል የሆነው ከዚህ በተቃራኒ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታት መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንትም አድርጓል።
ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደኅንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት ተከልክለዋል።
ይህም የሕብረቱን የፀጥታ አካላት የሚመለከት እንጂ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም።
የኢትዮጵያ መንግስትም ከሕብረቱ ቅጥር ግቢ ደሕነታቸውን ከማስጠበቅ ውጭ በሕብረቱ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡም የመከልከል ኃላፊነት የለውም።
በሶማሊያ በኩል የተሰጠው መግለጫ በሌሎች የሕብረቱ ተሳታፊ ሀገራት መሪዎች ጭምር ተቀባይነት ያለገኘ እና የተሳሳተ ነው። " #ኤፍቢሲ

#AU #ETHIOPIA
ትላንትና ምሽት ላይ ለ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመጡ መሪዎች በብሄራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር።
ዛሬ የጠ/ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባሰራጫቸው ምስሎች የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ፣ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በእራት ግብዣው ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የጎረቤት ሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ አልታዩም።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ትላንት እዚሁ አ/አ ሆነው በሰጡት መግለጫ " የኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች ከሆቴል እንዳልወጣ እንዲሁም ከጅቡቲ ፕሬዜዳንት ጋር ሆነን ወደ ጉባኤው እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብናል " የሚል ክስ አሰምተው ነበር።
በትላንት ምሽቱ የብሔራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ላይ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ ከሌሎች ፕሬዜዳንቶች ጋር በመሆን ከፊት መስመር ከፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጎን ተቀምጠው ታይተዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ግን በስፍራው አልታዩም።
ዛሬ እሁድ " አናዱሉ " የዜና ወኪል ባሰራጨው መረጃ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቀውን የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ አቋርጠው ወደ ሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።