TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎ በማንኛውም ዓይነት ስልኮች ያለኢንተርኔት መገልግል የሚችሉበት የUSSD አማራጭ ይዞ መጥቷል ። አገልግሎቱን ለማስጀመር የአፖሎ መተግበሪያ ላይ በመግባት USSD የሚለውን አማራጭ በመመረጥ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ። *685# በመደወል አገልግሎቱን ይጠቀሙ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apolloussd #ussd #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#ለጥንቃቄ

" በምዕራብ ኦሞ ዞን ባለፉት ሦስት ወራት 9,000 #ህፃናት በኩፍኝ ተጠቅተዋል። 11 ሞት ተመዝግቧል " - የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፦
° 65 በመቶ የሚሆን #ገዳይ የወባ ዝርያ እንዳለ፣
° በአንድ ዓመት ውስጥ 101 ሰዎች በወባ እንደሞቱ፣
° ማኅበረሰቡ ወደ ሕክምና ተቋማት እንዲሄድና አጎበር የመጠቀም ልምዱን እንዲያዳብር የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ተስፋፅዮን ተረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኩፍኝ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

* ምዕራብ ኦሞ ዞን ባለፉት 3 ወራት 9,000 #ህፃናት በኩፍኝ ተጠቅተዋል። 11 ሞት ተመዝግቧል። በክልሉ በአንድ ዓመት ውስጥ 12,700 የኩፍኝ ኬዞች ተገኝተዋል። 

* ከሌሎች ቦታዎች በተለዬ መልኩ በምዕራብ ኦሞ ዞን አሁንም ከፍተኛ ሥራ የሚጠይቅ የኩፍኝ ወረርሽኝ ስርጭት አለ። በመቀጠልም በቤንቺ ሸኮና ከፋ ዞኖች በተወሰኑ ወረዳዎች ይስተዋላል።

* አርሶ አደሮች በሚኖሩባቸው ( #በተለይም ምዕራብ ኦሞ)፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የክትባት አሰጣጡን አፌክት ያደርገዋል።

* #አርሶ_አደሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ ችግሩ እንዲቀረፍ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በአካባቢው ተንቀሳቀሰው ሕክምና እንዲሰጡ እየተደረገ ነው።
 
* የኩፍኝ ኬዞች ያሉባቸው አራት ዞኖች ናቸው። ቤንቺ ሸኮ ዞን ላይ ወደ 3,000፣ ከፋ ዞን ከ1,000 በላይ ኬዞች ነበሩ ፤ አሁን መቆጣጠር ተችሏል።

* ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ለማድረግ ጤና ሚኒስቴር ፈቅዷል። ከአምስት ዓመት በታች ለሚሆኑ ሕፃናት ክትባት ይደረጋል።
 
ወባ በምን ደረጃ ይገኛል?

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃልፊ አቶ ኢብራሄም ተማሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦

- ለሁለት ዓመታት #የወባ_ወረርሽኝ በክልሉ ተከስቶ ቆይቷል። የኩፍኝ ወረርሽኝም በተለይ በምዕራብ ኦሞ ዞን ልዩ ትኩረት ይሻል። ከእስከዛሬው ጋር ሲነጻጸር ግን ኬዞቹ እየቀነሱ ነው። ግን አሁንም ሥራ ይጠይቃል።

- የወባ ወረርሽኝ ቆዬ ስንል በርካታ ሥራዎችን ሰርተናል ከወባ ጋር ተያይዞ ወደ 1.2 ሚሊዮን የአጎበር ስርጭት ተካሂዷል። ከ6,000 ኪ.ግ በላይ እርጭት ተካሂዷል።

- አሁንም ውሃ ያቆሩ ቦታዎች ላይ እርጭት እያካሄድን ነው ፤ በጣም በተለየ መንገድ ምዕራብ ኦሞ ላይ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያለው ግብዓት አሰራጭተን የመከላከሉን ሥራ እየሰራን ነው።

አቶ ተስፋፅዮ በበኩላቸው ስለ ወባ ምን አሉ ?

* የተወሰኑ ወረዳዎችን ላያካትት ይችል ይሆናል እንጂ ሁሉም  ዞኖች በጣም ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው ናቸው።

* በአመት ውስጥ #በ6_ዞኖች በወባ ወደ 101 ሞት ተመዝግቧል። አሁን ግን ማኅበረሰቡ  በአቅራቢያቸው ህክምና እያገኙ ስለሆነ የህመም (የኬዝ)፣ የሞት መጠኑ በዛው ልክ ቀንሷል።

* ላለፉት ሁለት ዓመት ለዚህ መንስኤ የሆኑ ጥናቶች ለማድረግ ሞክረናል፣ የምላሽ ሥራው ተሰርቷል።

* እስካሁን ባለው በአጠቃላይ ወደ 400,054 ሰዎች በአንድ ዓመት የወባ አይነቶች ተለይተው ህክምና ያገኙ ናቸው።

* በተሰሩ ሥራዎች በተለይ ከአራት ወራት በፊት እስከ 15,000 ሰዎች በወባ ይጠቁ ነበር። አሁን ባለንበት በሳምንት በወባ የመጠቃቱ ሁኔታ ከ7,000 እስከ 6,000 ሰዎች ዝቅ ለማድረግ ተችላል።

* በመከላከል ላይ ያለ ክፍተት ነው የወባ ቁጥር ከፍ ብሎ እዲታይ እያደረገ ያለው። ምዕራብ ኦሞ ፣ ካፋ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች ላይ አርብቶ አደሮች ናቸው በተለይ ተጋላጭ የሆኑት።

* ከጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ሆስፒታል ድረስ የወባ ህክምና አለ።

* ሞት እያስከተለ ያለው ቆይተው ስለሚመጡ ነው። ቆይተው ሲመጡ ደግሞ በክልላችን #ከ65 ፐርሰት በላይ ፋልሲፋረም የሚባል በባህሪው #ገዳይ የሆነ ዝርያ ነው ያለው።

* በእኛ ክልል ላይ የሚበዛው ያ " ፋልሲፋረም " ነው። ሰዎች ወዳውኑ ምልክቱን እንዳዩ የመወሳሰብ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ወደ ጤና ተቋማት ሂደው መታከም አለባቸው። ችግሩ ሲወሳሰብ ደም ሊፈልግ ይችላል፣ #ነፍሰ ጡሮችን በተለይ ወዲያው የመግደል ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

ለ2ቱም ወረርሽኞች ለሞት አደጋው መከሰት ምክንያቱ ፦

° የሕሙማን ወደ ሕክምና #ዘግይቶ መምጣት፣

° #የጤና_ኤክስቴንሽኖች ወረርሽኝ አካባቢዎች ላይ አክቲቭ አለመሆንና በወቅቱ ለይቶ አለመላክ ነበር።

* በዘላቂነት ችግሮቹን ለማስወገድ ክልሉ የንቅናቄ መድረክ እንያዘጋጀ ነው። አሁንም ዝናብ ወጣ እየገባ እያለ ስለሆነ ለወባ መራባት እጅግ በጣም ምቹ አጋጣሚ ስለሚፈጥር ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ሊያደግ ይገባል።

ጥንቅሩ በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
እንዲህም አለና ተጠንቀቁ . . .

ከመቐለ ከተማ መኪና ሰርቆ ሲጠፋ የነበረው ተጠርጣሪ ግለሰብ አፋር ኤሬብቲ ከተማ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ መኪናዋን ይዞ ሲጠፋ የነበረው የሃሰት ሊብሬና የሰሌዳ ቁጥር በማዘጋጀት ነበር።

የወንጀል አፈፃፀሙ እንዴት ነበር ?

ወንጀሉ የተፈፀመው በመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ነው።

ተጠርጣሪው ፤ ህዳር 26/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 1:30 ለሰረቃት መኪና ህጋዊ ያልሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) እና የሰሌዳ ቁጥር አዘጋጅቶ በመጠቀም መኪናዋን ይዞ  ይሰወራል። 

የመቐለ ከተማ የፓሊስ ምርምራ መረጃ እንደሚያመለክተው የመኪናዋ ቁልፍ በመስበር ነው የቀድሞን የሰሌዳ ቁጥር በመቀየር እና የሃሰት የባለቤትነት ማረጋገጫ በማዘጋጀት ተጠርጣሪ ግለሰቡ ከግብረ አበሮቹ በመሆን ነው ከመቐለ የተሰወረው።

የተዘረፈው ግለሰብ መኪናው እንደጠፋችበት ለመቐለ ፓሊስ ያመለክታል። ፓሊስም የተበዳይ መረጃ በመያዝ ከዓፋር ክልል ፓሊስ በመተባበር በሰራው ስራ ዉጤት ተገኝተዋል።

በመኪና ስርቆት የተጠረጠረው ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ህዳር 27/2016 ዓ.ም በዓፋርዋ ኢሬብቲ ከተማ ከነኤግዚቢቱ እጅ ከፍፈንጅ ተይዟል።

የመቐለ ፓሊስ በወንጀል መከላከሉ ዙሪያ ልዩ ትብብር ላሳየው የዓፋርዋ ኢሬብቲ ከተማ ፓሊስ ምስጋና አቅርበዋል። 

የመቐለ ከተማ ፓሊስ ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩ በመቀያየር እየታየ ያለው የስርቆት ተግባር እንዲገታ ህዝቡ እንዲጠነቀቅና ከፓሊስ ጎን እንዲቆም ማሳሰቡን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                            
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama " ... እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻችሁን ከማስተማር ተቆጠቡ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በአብዛኛዉ ከደረጃ በታች መሆናቸዉ ተከትሎ 17 ኮሌጆች #መዘጋታቸዉ ተገለጸ። የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ባካሄደዉ…
በሲዳማ ክልል የተዘጉ ኮሌጆች ዉስጥ እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ዕጣፋንታ ምንድን ነዉ ?

በሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በኩል 17 ያክል ኮሌጆች መዘጋታቸዉን ተከትሎ በተማሪዎችና ወላጆች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል።

ወደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎች እና ወላጆች ከተላኩ ጥያቄዎች መካከል ዋነኛው " በኮሌጆች ዉስጥ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች እጣፋንታ ምንድን ነዉ ? " የሚል ነበር።

ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሀላፊው አቶ ፍስሀ ፍቶላ ፤ በነዚህ የተዘጉ ኮሌጆች የነበሩ ተማሪዎች መረጃ ተጠናቅሮ በቅርብ ወዳሉ ኮሌጆች እንደሚዘዋወሩ ገልጸዋል።

ለነዚህ ኮሌጆች ከ1 አመት በፊት #ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ መቆየቱን የገለፁት አቶ ፍስሀ ይህ ቆይታ የተማሪዎችን ጉዳይ ለመጨረስ እና ያለምንም ጉዳት ለማዘዋወር በቂ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ በክልሉ ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ዉሳኔ የተዘጉ  ኮሌጆች ቅሬታቸዉን እያቀረቡ ስለመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተረዳ ሲሆን ይህን ጉዳይ የምንከታተል ይሆናል።

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ፦
* በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በህገወጥ ስራ መሰማራታቸዉን፤
* 17 ኮሌጆች ስራ እንዲያቆሙ ሲወሰን ኮሌጆቹ በመላዉ ሲዳማ የጀመሯቸዉን የማስተማር ስራዎች አቁመዉ ፈቃዳቸዉን እንዲመልሱ እንደተናገራቸው፤
* ያላግባብ #ሳያስተምሩ_አስመርቀዉ ስራ ፈላጊና የሀገር ሸክም በማድረጋቸዉም በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ፤ ቢሮዉ እጁ ላይ ያለዉን መረጃ ባፋጣኝ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ እንደሚልክ፡
* ማህበረሰቡ እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቹን ከማስተማር እንዲቆጠብ፤
* ከዚህ በኋላ በመላዉ ሲዳማ ክልል ከገበያዉ በላይ የተማረ ሰዉ በመኖሩ የአካዉንቲንግ ማርኬቲንግና የሰዉ ሀይል አስተዳደር ትምህርቶችን መማርም ሆነ ማስተማር የተከለከለ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ በመሳተፍ ይሸለሙ!  https://www.facebook.com/globalbankethiopia

#Global_Bank_Ethiopia #Shared_Success #Bank_in_Ethiopia
#ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል

የካንሰር ህክምናዎች
በሙያቸው  የካበተ ልምድ ባላቸው በኦንኮሎጂስት ፣ በሄማቶሎጂስት፣ የሴቶች የመራቢያ አካላት ካንሰር ሰብስፔሻሊስቶች፣ እንዲሁም በፓቶሎጂስት በመታገዝ የሚከተሉትን ጥራቱን የጠበቁ አገልግሎቶች  እንሰጣለን ፡፡ 

የካንሰር ቀዶ ህክምና ፣  ኬሞቴራፒ፣ ኢሚኖቴራፒ ፣ የሆርሞን ህክምና ፣ የናሙና ምርመራዎች ፣የደም ህዋሳት ምርመራ /ሞርፎሎጂ/፣ የመቅኔ ምርመራ ፣  የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ (ፓፕ ስሚር) ፣ ዉጭ ሀገር ካሉ አጋር ዲያግኖስቲክ ላቦራቶሪዎች ጋር በመተባበር ኢሚዩኖሂስቶኬሚስትሪ ፣ባዮፕሲ

📞 8175 / 0940 33 33 33

Facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital
Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral

Telegram: https://t.iss.one/teklehaimanothospital1
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/teklehaimanot-general-hospital/

Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4
Website: www.teklehaimanothospital.com
E-mail: [email protected]
TIKVAH-ETHIOPIA
ውዝግብ የፈጠረው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ! " ' የጉምሩክ ኮሚሽን ' የገንዘብ ሚኒስቴርን ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን " - ከሰደት ተመላሾችና 10 የሚደርሱ የአገር ውስጥ አስመጪዎች " በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ በተከተለ መልኩ ነው። ' ህጋዊ ስርዓቱን አልተከተለም ' በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ፤ #ሀሰተኛ መረጃ…
#Update

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም ውዝግብ ፈጥሮ የነበረውን የ165 ተሽከርካሪዎች ግልፅ ጨረታ አሸናፊዎች ይፋ አድርጓል።

የጨረታው አሸናፊዎች በ5 ቀናት ውስጥ ቀሪ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን እንዲረከቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይህ ካልሆነ ያስያዘትን CPO ለመንግስት ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ መሆኑ ተገልጿል።

ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙር ሲፒኦ (CPO) ከቀን 01/04/2016 ጀምሮ እንዲወስዱ ተብሏል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የወጣው የተሽከርካሪዎች ጨረታ ህግን ያልተከተለና የገንዘብ ሚኒስቴርን ትዕዛዝ የጣሰ መሆኑን መንግስት ደክመው ያፈሩትን የላባቸውን ዋጋ አላግባብ በሌላ ሰው እጅ እንዳይሆን የሽያጭ ሂደቱን እንዲያስቆምና መፍትሄ እንዲሰጣቸው ከሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ደግሞ በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ የተከተለ መሆኑን ፤ ምንም አይነት የህግ ጥሰት አለመፈፀሙን መግለፁ ይታወሳል።

(የአሸናፊዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በሚሰራባቸው አካባቢዎች ምዝገባው እስኪጠናቀው ድረስ ምንም አይነት የስም  ዝውውር አይደረግም " - ኤጀንሲው

በአዲስ አበባ 7ተኛ ዙር የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ እና ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።

ማረጋገጥ እና ምዝገባው ለመጪዎቹ 5 ወራት ይቀጥላል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ ከዚህ በፊት በ6 ዙር ባደረገው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ምዝገባ ከ383,000 በላይ ይዞታዎች አረጋግጦ በካዳስተር ሲስተም መመዝገቡን አሳውቋል።

ኤጀንሲው ምዝገባው መካሄዱ አንድ ይዞታ በማን፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደተያዘ እና በይዞታው ላይ ለተፈጠረው መብት ህጋዊ ዋስትና አና ከለላ በመስጠት የመሬት ነክ ገበያውን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል ብሏል።

7ተኛ ዙር የይዞታ ማረጋገጡ ምዝገባ በ7 ክፍለ ከተሞች ይካሄዳል የተባለ ሲሆን 85 ቀጠናዎች እና 386 ሰፈሮችን ያካትታል።

ምዝገባው የማያካሄዱ ባለይዞታዎች ምንም አይነት ህጋዊ ዋስትና እና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቆ ባለይዞታዎች እና በይዞታዎች ላይ ጥቅም አለን የሚሉ ሁሉ በምዝገባው ላይ ሊሳተፉ ይገባል ብሏል።

ምዝገባው እስከ ሚያዝያ 28 ድረስ ባሉት 5 ወራት የሚካሄድ ሲሆን ከ15 ቀናት በኋላ ጀምሮ ባለይዞታዎች አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ የክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመሄድ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።

ለማመልከት ሲኬድ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድና አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ሲሆን የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ የክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት የከናወናል።

የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በሚሰራባቸው አካባቢዎች ምዝገባው እስኪጠናቀው ድረስ ምንም አይነት የስም  ዝውውር እንዳማይደረግ ተገልጿል።

7ተኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች፦

* ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣ 5፣ 8፣ እና 10

* የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ 5፣6፣7 ፣8 እና 9

* ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣5፣11፣12እና14

* አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣5 እና 8

* ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣3፣4፣5እና 6

* አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ11፣12፣13እና 14

* ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 እና 13 ናቸው ተብሏል።

የይዞታ ማረጋገጡ ስራ የሚከናዎነው በስልታዊ ዘዴ ወይም በመደዳ ሲሆን የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በታወጀባቸው በ7 ክፍለ ከተማዎች እና በ30 ወረዳዎች ውስጥ በ85 ቀጠናዎችና በ386 ሰፈሮች የይዞታ ማረጋገጥ ስራው ይካሄዳል።

በተጠቀሰው አካባቢ ባለይዞታ የሆኑ ሰዎች #በጊዜ እንዲያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
አትሌት ለተሰንበት ግደይ አሸናፊ ሆነች።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አትሌቲክስ ኢንተርናሽናል ፌርፕሌይ (ስፖርታዊ ጨዋነት) ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ የሽልማቱ አሸናፊ የሆነችው በቡዳፔሽቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ከትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር በነበራት ቅፅበት መሆኑ ተገልጿል።

አትሌት ሲፋን በውድድሩ ላይ መውደቋን ተከትሎ አትሌት ለተሰንበት #ስታፅናናት እንደነበር አይዘነጋም።

አትሌት ለተሰንበት ከሽልማቱ በኋላ ፤ " ሲፋን ሀሰን ስትወድቅ እኔም ከልቤ ተሰምቶኝ ነበር ምክንያቱም የውድቀትን ስሜት አውቀዋለሁ የ2023 ፌር ፕሌይ ሽልማት በማሸነፌ ተደስቻለሁ። "ብላለች።

Via @tikvahethsport    
ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ግብይት! የM-PESA መተግበሪያን ዛሬውኑ አውርደን እንጠቀም ፤ ህይወታችንን ቀለል እናድርግ!

ፕለይ ስቶር/ አፕ ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia     

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#EMA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፤ " የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ ያግዛቸዋል " ያለውን ስልጠና ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ከሚገ ኙ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ የሚኒ ሚዲያ አባላት ተማሪዎች መስጠቱን ገለጸ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ፤ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካታ መገናኛ ብዙኃን እየተበራከቱ መሆናቸውንና በዚህም በርካታ የተሳሳቱ፣ ሀገርን የሚያፈርሱ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ሐሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ሲሰራጩ እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል።

መ/ቤታቸው የሰጠው ስልጠናም ታዳጊዎች መገናኛ ብዙኃንን ሲጠቀሙ ፤ የትኛው መረጃ ትክክል እንደሆነ እና እንዳልሆነ እና የትኛው መረጃ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ነው የሚለውን በመለየት እና ባለማሰራጨት፣ ባለማጋራት እንዲሁም ተሰራጭቶ ሲያገኙ ለባለሥልጣኑ በመጠቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ፤ ስልጠናው ተማሪዎቹ ከወዲሁ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

" ወጣቶች ነገ የሚረከቧት ሀገር ከጥላቻ የፀዳች እንድትሆን ጥላቻን በመፀየፍ የሀገርን አንድነትና የህዝቦችን አብሮነት ለማፅናት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ዛሬ ላይ መወጣት ይኖርባቸዋል " ሲሉም አሳስበዋል።

ይህ ስልጠና የማስጀመሪያ ነው ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ወደፊት በአዲስአበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም 2ተኛ ደረጅ ት/ቤቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰል ስልጠና ለመስጠት ውጥን መኖሩን አመልክቷል።

@tikvahethiopia