TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🔊 በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ / ከመደበኛ ፍሰቱ ወጥቶ ሞልቶ በመፍሰሱ ዜጎቻችን እየተጎዱ ነው። እንደ ዳሰነች ወረዳ አስተዳደር መረጃ ፦ - በ34 ቀበሌያትና በ7 ደሴቶች የሚኖሩ 79,828 ቤተሰብ አባላት በወንዙ ሙላት የተጎዱ ተጎድተዋል። - በወረዳው ካሉ 40 ቀበሌያቶች 34ቱ ቀበሌያት በውሃ የመዋጥና የመከበብ አደጋ ያጋጠማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ቀበሌያት ሙሉ…
#Update
" 10, 572 ሰዎች ደሴት ላይ ገና በውሃ ተከበው አልወጡም " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር
በዳሰነች ወረዳ ተከሰተ የተባለው የጎርፍ አደጋ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ፣ በአደጋው የሰውና የእንስሳት ሕይወት እንዳለፈና እንዳላለፈ፣ በንብረት ላይ ምን ያህል ውድመት እንደደረሰ ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ማልኮ እንደገለጹት ከሆነ፣ 10,572 ሰዎች ደሴት ላይ ገና በውሃ ተከበው አልወጡም። እንዲሁም በጎርፍ አደጋው 4.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
69,256 ቤተሰቦች ከወንዙ እንደወጡ ያስረዱት ያሉት አስተዳዳሪው፣ 79,828 ሰዎች በአጠቃላይ በጎርፉ ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም፣ እንስሳት የዳልጋ ከብት፣ በግና ፍየልን ጨምሮ 889,454 ከወንዙ እንደወጡ ገልጸው፣ "በጎረፍ አደጋ የሞተ የለም። እንስሳት ላይም ሞት የለም። ተቋማትና የአርብቶ አደር ቤቶች በጎርፍ እንደተያዙ ይገኛሉ" ብለዋል።
መፍትሄው ምን እንደሆነ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም፣ መንግሥት ማህበረሰቡን ወንዝ ወደማይደረስበት ማስፈረና ትልልቅ የመስኖ አውታር በማቋቋም ወደልማት ፊታቸውን እንድያዞሩ ማድረግ፣ አስፈላጊው መሰረተ ልማት በሰፈሩበት ቦታ ማሟላት አለበት ብለዋል።
ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia

Photo
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰሠረት ከኅዳር 15 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄደው የምኅላ ጸሎት በሁሉም አድባራትና ገዳማት በወጣለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በሀገሪቱ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት እንዲሰፍን በሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም መወሰኑ አይዘነጋም።
" የአሁኑ ጸሎተ ምኅላ የሚደረገው ፦
- አለመግባባት በምክክር፣ በውይይት፣ በመደማመጥ እንዲፈታ፤
- መከራን በመረዳዳት እንድንሻገር፣ እንደየ ኃላፊነታችን የሚጠበቅብንን ለመወጣትና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ እንድንችል፣ ችግራችን ሁሉ ተፈትቶ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሃሊው አምላክ እንዲያግዘን በአንድነት ለመጮኽ ነው " ማለቱም ይታወሳል።
አስቀድሞ የደረሰውንና፣ አሁንም እየደረሰ ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ሁሉም ምዕመን ከጸሎትና ምኅላው ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም ቤተክርስቲያን ማዘዟ አይዘነጋም።
Photo Credit - የኢኦተቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት / መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

#ሙስና📈
" ዛሬ እኮ አገልግሎት ተፈልጎ ክፍለ ከተማ ቢኬድ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ፣ ተደብቆ ነው ሲሰጥ የነበረው "
በኢትዮጵያ ውስጥ #ሙስና ከመቀነስ ይልቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ፣ የሚፈፀምበትም መንገድ እየተራቀቀ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ ... ሌሎችም አገልግሎት ለማግኘት ሲኬድ ከእጅ መንሻ ጋር እንደሆነ መረዳቱን ገልጿል።
✦ የተቋሙ ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ምን አሉ ?
- በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሙስና እንደሚፈፀም ተገልጋዮች ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ።
- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት የሚጠየቁት ጉቦ በድብቅ ሳይሆን በግልፅ ነው።
- ለሙስና ተጋላጭ ናቸው የተባሉ ተቋማት ተለይተዋል እየተባለ ቁጥጥሩ ለምን እንደላላ ግራ የሚያጋባ ነው።
- " ዛሬ አገልግሎት ፈልገህ ክፍለ ከተማ ብትሄድ እኮ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ምናምን ነው ሲሰጥ የነበረው፤ ዛሬ በካኪ ታሽጎ የሚሰጠውን ገንዘብ እዛው ፊትለፊት ላይ የሚቀዱ የመንግሥት ሰራተኞች ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው ፤ ምንም እንኳን የየስራ ባህሪያቸው ቢለይም። "
- የስርዓት ለውጥ ነው የሚያስፈልገው፤ ሙስናን መሸከም የማይችል፣ ሙስናን ማስተናገድ የማይችል ስርዓት ፣የህግና የተቋም ስርዓት ነው መዘርጋት ያለበት።
- የስነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሰጠው ኃላፊነት ሙስናን ለመከላከል በቂ አይደለም። ይህ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለአስፈፃሚው አካል ነው፤ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚያስችለው አይደለም። የተቋሙ ኃላፊዎች የሚሾሙት በአስፈፃሚው አካል ነው፤ ተጠሪናታቸውም ለዛ አካል ነው እንጂ ለምክር ቤት አይደለም። ሌላው እየሰራ ያለው መከላከል ላይ ነው፤ የህግ ማስከበሩን ለፍትህ ሚኒስቴር ነው የተሰጠው አሁን ካለው ከፍተኛ የሙስና ችግር አንፃር የህግ ማስከበሩንም የመከላከሉንም ስራ መስራት የሚችል ጠንካራ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋል።
- ጠንካራ ኮሚሽን ባልተቋቋመበት ሁኔታ ኮሚቴ እያቋቋሙ ሙስናን የመከላከል የሚቻልበት ሁኔታ የለም።
◾️የህግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን ይላሉ ?
- ሙሰኞች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ጠንካራ ስላልሆነ ሙስና ከመቀነስ ይልቅ እንዲጨምር ሆኗል።
- የፖለቲካ መዋቅሩ በራሱ አጥፊዎች እንዳይጠየቁ እድል የሚሰጥ ነው። ብሄርና ትውውቅን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በአጥፊውና በጠያቂው መካከል ልዩነት እንዳይኖር ሆኗል።
- " ሰዎች ሙስና ሰርተው ሲያጠፉ በግልፅ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጥፋተኛ መሆን ሲገባቸው እንደውም ከለላና ሽፋን ሲያገኙ ፣ ከበላበት ቦታ ወደሌላ ቦታ ዘወር ሲል ፣ ሃብትና ንብረት እንዲያገኙ ሲመቻችላቸው ይታያል። ይሄ ሁሉ የፖለቲካ ስሪቱ ነው። የፖለቲካ ስሪቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑነው። ይሄ ብሄርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት የሰላ ትግል እንዳይደረግና ተጠያቂነት እንዳይመጣ ያደርጋል። "
- የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን መክሰስም ሆነ የመመርመር ስልጣን ቢሰጠው አሁን ካለው ስራ የተሻለ ማድረግ አይችልም። ለ16 ዓመታት ይሄ ኃላፊነት ተሰጥቶት የሰራው ስራ ታይቷል።
- አሁን የሚበጀው አጥፊዎች የሚጠየቁበትን ህግ ማጠናከር ነው።
- " ሰው በዚህ ሰመን በካልኩሌሽን መታሰር ጀምሯል። ለምሳሌ አንድ የሙስና ወንጀል የፈፀመ ሰው 10 ሚሊዮን ብር ቢያገኝ በቀላሉ 10 ዓመት ቢታሰር / ቢወሰንበት ምን ብሎ ያስባል ' ይሄን 10 ሚሊዮን ብር በ10 ዓመት ላፈራው አልችልም ደግሞ ማንኛውም ታራሚ አመክሮ ስላለው በ7 ዓመት / በ6 ዓመት ብወጣ ይሄን 10 ሚሊዮን ብር መብላቱ / መመዝበሩ የተሻለ ነው ፤ ምክንያቱም በ6/7 ዓመት ውስጥ ላፈራው አልችም ' ብሎ ሰው በካልኩሌሽን መታሰር የጀመረበትና የደረሰበት ዘመንና ሁኔታ ላይ ደርሰናል "
- መፍትሄው ሙስና የሚፈፅሙ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ህጉን ጠንካራ ማድረግ ብቻ ነው።
🔹በስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን የጥቅም ግጭት መከላከል መሪ ስራ አስፈፃሚ መስፍን በላይነህ ምን ይላሉ ?
- የሙስና ጉዳይ በጣም እየጎላ መጥቷል።
- ሁሉም ዘርፍ ከሙስና ተግባር የፀዳ አይደለም ፤ ግን ደረጃው ይለያያል።
- የእኛ ኮሚሽን ሙስናን መከላከል እንጂ ከተፈፀመ በኃላ የመመርመር፣ የመክሰስና የማገድ ኃላፊነት አልተሰጠውም። ዋናው ተልዕኮ የስነምግባር ትምህርትን ማስተማር ነው።
- በአብዛኛው ዓለም ላይ ሶስቱንም ማለትም፦
• የማስተማር፣
• የመመርመር ፣
• የመክሰስ አውድ ይዞ ነው የሚኬደው ፤ እኛ ሀገርም ተሞክሯል ከ1993 - 2008 ተሞክሯል። ከ2008 በኃላ የሙስና ወንጀል ምርመራ ብሎም ክሱ ወደሌላ አካል ተለልፋል። ቅንጅት ከተፈጠረ ይህ መሆኑ ችግር የለውም። ፖሊስ ይመረምራል፣ አቃቤ ህግ ይከሳል፣ ፍርድ ቤት ፍርድ ይሰጣል። ህብረት ያስፈልጋል። ቅንጅቱ ግን ጠንካራ አይደለም።
- ብዙ ሀገራት ላይ ይህን ዘርፍ በአንድ ተቋም ነው የሚመሩት ፤ እኛ ሀገር በተለያየ ተቋም ነው የሚሰራው ይህንን የሚመሩ አካላት እንደ አንድ ተቋም ሊሰሩ ይገባል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ / ጋዜጠኛ ያሬድ እንዳሻው ነው።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia
የምንወዳቸውን ጨዋታዎች ባልተገደበ ፍጥነት ለመመልከት ዕለታዊ የሳፋሪኮም 1GB ኢንተርኔት ጥቅል እንግዛ፤ እንዝናና።
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#የልብሕሙማን
የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ፤ በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎች መሥራት የሚያስችል አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ እየሰራ ያለው አንድ ሶስተኛውን መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማዕከሉ ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምህረተዓብ ኤርሚያስ (ዶ/ር) ፤ " ማዕከሉ ባለው ሙሉ አቅም ሕክምና እንዳይሰጥ የሕክምና ግብዓቶች እጥረትና ሌሎች መሠል ምክንያቶች ፈተና ሆነዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
" በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎች መሥራት እንችላለን ግን አሁን እየሰራን ያለነው ግን አንድ ሦርተኛውን ነው " ብለዋል።
ወደ ማዕከሉ የሚያቀኑ ታካሚዎች " በወረፋቸው አገልግሎት አላገኘንም " የሚል ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣል፤ ለዚህ ችግር ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ምህረተዓብ (ዶ/ር)፣ " በሕመማቸው አይነትና ከወቅቱ ካለን ዕቃ አንፃር ውጪ ወረፋ የምናስቀድምበት ምንም ምክንያት የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለውም ፤ አንዳንድ የሕክምና ዕቃዎች ከ10 እስከ 20፣ ከ20 እስከ 40 ኪሎ ላሉ ሕፃናት ክብደት ተብለው እንደሚወሰኑ አስረድተው፣ ታካሚዎቹ ለሕክምና በሚሄዱበት ወቅት የሚገኙት የሕክምና ዕቃዎች በዛ ክብደት ሬንጅ ውስጥ ሳይሆን ሲቀር በኋላ የተመዘገበ ሰው ሊታከም ይችላል ብለዋል።
እንዲሁም፣ አምና በነበረው ቁጥር መሠረት ከ7,500 በላይ ህፃናት ታካሚዎች ወረፋ በመጠበቅ እንደሚገኙ፣ ነገር ግን ገና የታከሙትን ሲቀናንሱበት ቁጥሩ ከፍ ወይም ዝቅ ሊል እንደሚችል ምህረተዓብ (ዶ/ር) ገጸዋል።
የልብ ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ?
ዶክተር ምህረተዓብ ኤርሚያስ ፦
" የታካሚዎች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም። ምክንያቱም የሚመጡ ታካሚዎች የታመሙ ብቻ አይደሉም። የታመሙና እዚህ አገልግሎቱ እንዳለ የሚያውቁ ናቸው። ታመው አገልግሎቱ እንዳለ የማያውቁ ሰዎች አሉ። ስለዚህ እነርሱ አይመጡም።
የታካሚ ቁጥር እንዳይጨምር ማድረግ አይቻልም። የሚቻለው እዚህ ላሉ ታካሚዎች የምንሰራበትን ፍጥነት መጨመር ነው።
በእኛ ተቋም በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎችን መስራት እንችላለን በተለያዩ ችግሮች ግን አሁን እየሰራን ያለነው አንድ ሦስተኛውን ነው። እንዲህ አይነት ተመሳሳይ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ማዕከላት ካልተከፈቱ የሕሙማኑን ቁጥር መቀነስ ያስቸግራል። "
* የልብ ህክምና ታካሚዎች በሌሎች ተቋማት ለአንድ ቀዶ ሕክምና እስከ 500,000 ብር የሚጠየቁ ሲሆን ከፍተኛ የግብዓት እጥረትም አለ። የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በቅርቡ ባስጀመረ ' ተስፋ ' በሚለው የድጋፍ ሲስተም ሰዎች የሕፃናትን የልብ ህክምና ወጪ በመሸፈን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።
ድጋፍ ማድረጊያ ፦ 6710 ላይ OK ብለው ያላኩ።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#የልብሕሙማን የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ፤ በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎች መሥራት የሚያስችል አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ እየሰራ ያለው አንድ ሶስተኛውን መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የማዕከሉ ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምህረተዓብ ኤርሚያስ (ዶ/ር) ፤ " ማዕከሉ ባለው ሙሉ አቅም ሕክምና እንዳይሰጥ የሕክምና ግብዓቶች እጥረትና ሌሎች መሠል ምክንያቶች ፈተና ሆነዋል " ሲሉ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት
በልጆች ላይ ሊስተዋሉ የሚችሉ #የልብ_ሕመም ምልክቶች ምንድናቸው ?
የልጆች የጤና የማያሳስበው ወላጅ የለም። እነዚህን የሕፃናት የልብ ሕመም ምልክቶችን በማወቅ የልጆችን ልብ "ያዳምጡ"።
- በጡት መጥባት ወቅት ማላብና የትንፋሽ ማቆራረጥ
- ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ፣ የትንፋሽ ማጠር እና የሰውነት እብጠት
- የክብደት እና የቁመት ውስንነት
እነዚህ የተዘረዘሩትን ምልክቶች በልጅዎ ላይ ካስተዋሉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።
ይህ መልዕክት የቀረበው ፤ በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ነው። ማዕከሉ በህዝብ እገዛ ለ34 ዓመታት ለ5,000 በላይ ሕፃናት መድረስ ችሏል። አሁንም ከ8000 በላይ ወረፋ የሚጠብቁ ሕፃናት ይጠብቁታል። 6710 ላይ OK ብለው SMS በመላክ በቀን 1 ብር ይለግሱ።

Register before all available spots are filled.
Training on Artificial Intelligence using Python Programming and Google Colab
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT), School of Electrical & Computer Engineering
Registration Deadline: 2nd December, 2023
Training Starts on: 4th December, 2023
Registration: Addis Ababa Institute of Technology (AAiT), School of Electrical and Computer Engineering, Main Building 1st Floor, Office Number: 124
Online Registration Link: https://forms.gle/bdR6GUWVEUNwGHCq7
Telephone: +251-940-182870 / +251-913-574525
Email: [email protected] / [email protected]
Telegram Channel: https://t.iss.one/TrainingAAiT

#ሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ #ኦዲት
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ / ም በጀት ዓመት ሲንከባለሉ የቆዩ የሒሳብ ጉድለት እንዳሉበት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተደደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
ይህንን ያስታወቀው የዩኒቨርሲቲውን የ2014 ዓ/ም በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ሕጋዊነትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።
የዩኒቨርሲቲው የሒሳብ የኦዲት ጉድለቶች ተብለው በቋሚ ኮሚቴው የቀረቡት ምንድናቸው ?
- ለዩኒቨርሲቲው ማስፋፊያ ቦታ ለባለ ይዞታዎች ካሳ ቢከፈልም እስካሁን ከቦታው አልተነሱም። ለባለ ይዞታዎቹ የካሳ ክፍያ ቢፈጸምላቸውም ምንም ዓይነት ሰነድ (ካርታ) አላቀረቡም ፤ ግለሰቦቹ በመሬቱ ላይ ያላቸው ሀብትና ንብረት በሚመለከተው አካል ሳይረጋገጥ ክፍያ ተፈፅሟል። ተነሺዎቹ በገቡት ውል መሠረት የካሳ ክፍያው በተፈጸመ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ይዞታቸውን እንዲለቁ ቢጠበቅም፣ አንድም ግለሰብ ቦታውን አለቀቀም።
- ከተጋባዥ መምህራን ያልተሰበሰበ ቅድመ ግብር ፣ ለአካዴሚክ የሕክም እና ባለሙያዎች ከደንብና ከመመርያው ውጪ " ቶፕ አፕ " ተብሎ በድምሩ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ቢጠየቅም እስካሁን ድረስ ግን አልተስተካከለም።
- በሥራ ገበታቸው እያሉ #ስብሰባ (ኮንፈረንስ) ለ2 ቀናት ለተሳተፉ ሠራተኞች የ18 ቀናት የውሎ አበል በቀን 171 ብር ተሠልቶ ያላግባብ ተከፍሏቸዋል።
- የተሟላ መረጃ ሳይቀርብ በወጪ መመዝገብ፣ ቀኑን በመጨመር ያላግባብ የውሎ አበል መክፈል፣ ከቀረበ ማስረጃ በላይ አስበልጦ መክፈልና የተሽከርካሪ ዕቃዎች ግዥ ሲፈጸም ያለ ደረሰኝ (በዱቤ) ሽያጭ ደረሰኝ 3,259,439 ብር ክፍያ ተፈፅሟል።
- በግባንታ ላይ ያሉ ' 12 ፕሮጀክቶች ' በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለአገልግሎት አልዋሉም። ተቋራጮቹ በገቡት ውል መሠረት መሥራታቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ ከግንባታ ክፍል በተገኘው መረጃ መሠረት በርካታ ክፍተቶች ተገኝተዋል።
ከዚህ ውስጥ ፦
* ሉሲ ኮንስትራክሽን የተሰኘ የኮንስትራክሽን ኩባንያ 233,432,359.95 ብር ለቴፒ ካምፓስ የመማሪያ ሕንፃ ግንባታና ለመምህራን አዳራሽ ሚያዝያ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲያጠናቀቅ በውሉ ቢገለጽም፣ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ግንባታው 56 በመቶ ላይ ብቻ ይገኛል።
* ኮንስትራክሽን ተቋራጩ (ሉሲ) በ73,652,906.05 ሳንቲም ለጂምናዚየም ግንባታ ሐምሌ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 15 ቀን 2012 ማጠናቀቅ እንደሚገባው፣ ተቋራጩ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ሳይጨርስ ሌላ ፕሮጀክት ተሰጥቶታል።
* የውኃ አቅርቦት ግንባታ በ 300,283,120.83 ብር በጀት ሉሲ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ግንባታውን እንዲያጠናቅቅ ፕሮጀክቱ ቢሰጠውም፣ ግንባታው እስካሁን አሥር በመቶ ላይ ይገኛል።
- ለግንባታና ለጥገና ለተደራጁ ማኅበራት ቅድመ ክፍያ ሲሰጥ ካደራጇቸው የመንግሥት ተቋማት የዋስትና ደብዳቤ ሳያቀርቡ 4,918,356.18 ብር ተከፍሏል።
በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት ዕርምጃ ያልወሰደበት #ከ46_ሚሊዮን_ብር_በላይ የሚሆን የበጀት ጉደለት ቢኖርም ማስተካከያ የተደረገበት የበጀት ጉድለት አንድ በመቶ/1% አይሆንም ተብሏል።
ቋሚ ኮሚቴው ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኦዲት ግኝት አስተያየቶችን ለማረም እያደረገ ያለው ጥረት በቂ አለመሆኑን ከዚህ በኋላ ኃላፊነታቸውን በማይወጡ ኃላፊዎች ላይ ተገቢው ዕርምጃ መወሰድ እንዳለበት፣ ሕጎችንና መመርያዎችን ማክበር እንደሚገባ አሳስቧል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤ ምን አለ ?
- በዩኒቨርሲቲው ሕጋዊ ሒደትን ያልተከተለ የግንባታ ፕሮጀክቶች ውል፣ ተገቢ ያለሆነ የአበል ክፍያ፣ ለባለ ይዞታዎች ያለ በቂ መረጃ የተከፈለ የቦታ ካሳ ክፍያና ያለ በቂ የአዋጭነት ጥናት የተጀመሩ የገቢ ማመንጫ ሥራዎች በኦዲት ግኝት ተረጋግጧል።
- በተያዘላቸው ጊዜ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መኖር፣ በማዕቀፍ መከናወን የነበረባቸው ግዥዎች በግለሰብ መፈጸማቸው፣ ሕጋዊ ደረሰኝ ያልተገኘላቸው ግዥዎች መኖራቸውን ጨምሮ፣ በዩኒቨርሲቲው ዕርምጃ ያልተወሰደበት የኦዲት ግኝት ከ59 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲደርስ አድርጎታል።
- ዩኒቨርሲቲው የውስጥ ቁጥጥርና የኦዲት ሥርዓት ደካማ በመሆኑ፣ ከ200 ሺሕ ብር በላይ ወደ ግለሰብ ኪስ እንደገባና ሕጋዊ ሒደቱን ባልተከተለ ግዥ መንግሥት ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ አጥቷል።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ ምን አሉ ?
- የኦዲት ግኝቶችን ለማረም ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው።
- በዩኒቨርሲቲው የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ የበጀት እጥረት፣ የፀጥታ ችግርና የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናር ምክንያቶችች ናቸው።
- የበጀት እና የንብረት አጠቃቀምን ለማስተካከል የዕውቀት ክፍተት አለ፤ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን የሰው ኃይል የማብቃት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።
- የካሳ ክፍያ የተከፈለባቸው ከ60 በላይ ይዞታዎች ውስጥ 46 ያህሉን ዩኒቨርሲቲው ተረክቧል። ሕግና ሥርዓትን በጣሱ ግለሰቦች ላይ የዕርምት ዕርምጃ እየተወሰደባቸው ነው።
መረጃው ከሪፖርተር ጋዜጣ የተገኘ ነው።

" የምንበላው አጥተናል ፤ የምንሄድበትም ጠፍቶን ጨልሞብናል። "
በባለፉት የክረምት ወራት ባጋጠመ የዝናብ እጥረት በተለያዩ #የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ጉዳት እየደረሰ ነው።
በተለይ አበርገለ ጭላ ወረዳ የበረታ ድርቅ በመከሰቱ የሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት እንደሆነ በርካቶችም ከቄያቸው ወጥተው ወደልመና እንዲገቡ እንዳደረገ ተነግሯል።
አንዲት እናት ፦
" በየአካባቢያችን ድርቅ ስላጋጠመን ወደጭላና ሌሎች ቦታዎች ሄደን እየለመንን ነው።
በየአካባቢያችን ምንም እህል የለም። የተወስኑ አካባቢዎች ብቻ ነው የተወሰነ ዝናብ የዘነበው እንጂ አብዛኛው አካባቢ እህል የሚያበቅል በቂ ዝናብ አልዘነበም።
አብዛኛው ሰው ወደ ልመና ተሰማርቶ ነው ያለው።
እርዳታ እንኳን ከተቀበልን 1 ዓመት ሆኖናል ከዛ በኃላ ተሰጥቶን አያውቅም። አጠቃላይ የዚህ አካባቢ ማህበረሰብ ተጎድቷል። ሁሉም እየተቸገረ ስለሆነ አንዳንዴ ለምነንም አናገኝም። በርካታ ሰዎችም በረሃብ እየሞቱ ነው። መንግሥት እርዳታ ያድርግልን ልጆቻችንም ትምህርታቸውን ይቀጥሉ። "
ሌላ አንዲት እናት ደግሞ ፦
" ከልጆቼ ጋር በጣም ስለተራብኩ ነው ወደ ጭላ ከተማ የመጣሁት። እዚህም ምንም የለም። ልጆቼን ይዤ በጣም ተቸግሪያለሁ።
አምስት ልጆች አሉኝ ሲጨንቀኝ ጊዜ 3ቱን ልጆች ሰው ቤት አስጠግቼያቸዋለሁ። ሁለቱ ከእኔ ጋር ናቸው ግን የማበላቸው የለኝም። ከዚህም ከዚያም እየለመንን እየዋልን እያደርን ያለነው።
በጣም ከፍቶናል፤ እርዳታ ካቆመ ቆይቷል። አንዳንዴ ሲጨንቀኝ የቀን ስራ እየሰራሁ የልጆቼን እራት አገኝ ነበር አሁን ግን የቀን ስራም የለም የምንሄድበት ጠፍቶን ጨልሞብናል። "
አንዲት ልጅ ደግሞ ፦ በመራቧ ምክንያት ትምህርት ማቋረጧንና ወደ ጭላ የሚበላ ፍለጋ መምጣቷን ገልጻ ፤ በየቀኑ እየለመንን ነው የምንበላው ብላለች። እርዳታ ይሰጠን ስትል ተማፅናለች።
የድርቁ ተጎጂዎች አስከፊው ድርቅ እንዳለ ሆነ ለነፍስ ማቆያ የሚሆነው እርዳታ ተቋርጦ በመቆየቱ ህይወት ጨልሞብናል ፤ መንግሥት ህይወታችንን ይታደግ ብለዋል።
የወረዳው አስተዳደር ምን ይላል ?
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሃጎስ ሃደራ ፦
" ህብረተሰቡ በችግር ላይ ችግር ወድቆ አደጋ ላይ ነው ያለው። የክረምት ወቅቱ በጣም የዝናብ እጥረት ነበረበት ፣ተባይም እንዲሁ የማዳበሪያ አቅርቦቶም ችግር ነበር ሌሎችም ምክንያቶች ነበሩ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ህዝቡ ላይ የደረሰው አደጋ አስከፊ ነው።
ከ7 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። እስከ 5000 ሺህ የሚያህል ተማሪ ተበቷል። ተመዝግቦ ነበር አሁን የለም።
አስከፊ ረሃብ አለ፣ ሞትም አለ፤ እስካሁን ከ210 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ ከመድሃኒት እጥረት፣ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው።
ችግሩን ለመፍታት የፌዴራል መንግሥት በማስተባበር ተግባራዊ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል። የተፈናቀሉ ሰዎችም ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለበት፤ እስኪመለሱ ደግሞ እርዳታ መምጣት አለበት። ህዝቡ አደጋ ላይ ነው ያለው ህዝቡ ሳያልቅ መድረስ አለበት። "
መረጃው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ለድምፂወያነ ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃለመጠየቅ የተወሰደ ነው።

ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ!
=====================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስምና አርማ በመጠቀም በሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሌብነት ተግባር የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች አሉ፡፡
በመሆኑም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ!
የባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• YouTube፡- https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
• LinkedIn፡- https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
• Twitter፡- https://twitter.com/combankethiopia
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
• Instagram፡- https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/
• tiktok:- https://www.tiktok.com/@commercialbankofethiopia