TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ በቀላል ባቡር እና ቀለበት መንገዶች 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ሊገነቡ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በሚያልፍባቸውና ውስጠኛው ቀለበት መንገድ ተብለው በሚጠሩ ቦታዎች ላይ መሸጋገሪያ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ባለመኖራቸው እግረኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡና መንገድ ለማቋረጥ ረዥም ርቀት ለመጓዝ እንደሚገደዱ ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

በመሆኑም ፤ 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች እንደሚገነቡ ይፋ አድርጓል።

ተሻጋሪ ድልድዮቹና መተላለፊያ መስመሮቹ ከመሬት በላይ እንዲሁም በመሬት ውስጥ እንደሚገነቡ ጠቁሟል።

የእግረኛ ተሻጋሪ ድልድዮቹ ፦
- ሐና ማርያም፣
- ኃይሌ ጋርመንት፣
- ሳሪስ ሐኪም ማሞ ሰፈር፣
- አደይ አበባ፣
- ጉርድ ሾላ፣
- አውቶቡስ ተራና አብነት አካባቢ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ነው የሚገነቡት ብሏል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ፈተናው በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡

ከተማ አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በዚህ ዓመት በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በዚህም በአዲስ አበባ ለ6ኛ ክፍል 86,691 ተማሪዎች እንዲሁም ለ8ኛ ክፍል 88,028 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia