#እንድታውቁት
ወባ (Malaria)
" በኢትዮጵያ ተከታታይ በሆኑ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እንዲሁም ሌሎች ወረርሽኞች ሳቢያ በባለፉት 2 ዓመታት ላይ ተመስርቶ በወጣ ሪፖርት የወባ በሽታ ቁጥር ከ150%-120% ጭማሪ አሳይቷል " - #WHO Ethiopia
ወባ ተላላፊ በሽታዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ ሲሆን የሚተላለፈውም Plasmodium በሚባል የፕሮተዞአ ዓይነት በሴቷ አኖፊለስ የወባ ትንኝ አማካኝነት ነው።
- የወባ ትንኝ ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታ ላይ በብዛት ትራባለች።
- የወባ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ብዙ በመሆናቸው የሚያስከትሉት ችግር አንዱ ከአንዱ ይለያያል። ለሞት የሚዳርጉ አሉ፤ቀለል ያለ ህመም የሚያስከትሉም አሉ። በኛ ሀገር ሁለቱም ይገኛሉ። በዋናነት የከፋ ችግር የሚያስከትሉት P.falciparum እና p.vaivax ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
▫️P.falciparum የተባለው በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች ላይ በስፋትም በገዳይነትም ብዙውን ድርሻ ይወስዳል፡፡
-ለወባ በሽታ ማንኛውም ሊጋለጥ ይችላል::የወባ በሽታ ከተላላፊ በሽታዎች በገዳይነቱ ወደር የሌለው ነው።በተለይ በህፃናት፣ ነብሰ ጡር እናቶችና አረጋዊያን ላይ ሲከሰት የገዳይነት ጉልበት ያገኛል።
ምልክቶቹ ፦
▪️ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ፣ ማንቀጥቀጥ
▪️ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
▪️ሆድ ህመም፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ
▪️ራስ ምታት፣ሰውነትን ጥምቅ ሚያደርግ ላብ
- ወባ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል ያጠቃል። የከፋ ከሚሆንባቸው አንዱ አንጎልን ሲያጠቃ ነው። በተለምዶ የጭንቅላት ወባ (Cerebral malaria) ተብሎ ይጠራል።
- ሌላው ወባ የኩላሊት መድከምን ሲያስከትል ነው። አንዳንዴ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ደረጃም ላይ ይደርሳል።
- የልብና የሳንብ ችግር በማስከተል ለሞት የመዳረግ አቅም አለው። በተጨማሪም የደም ማነስ ያስከትላል።
* መከላከያ መንገዶች
የወባ ትንኝ ንክሻን በመከላከል፤ የመራባት አቅሟን በማስቆም፣ ቅድመ መከላከል መድሐኒት በመውሰድ መከላከል ይቻላል።
- በወባ በሽታ በብዛት ተጠቂ በሆኑ ቦታዎች ላይ የቤት ውስጥ ፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ማድረግ እንዱሁም ደግሞ በፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል የተነከረ አጎበርን በአግባቡና በትክክል መጠቀም፤ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታን በማፋሰስ የወባ ትንኝ እንዳትራባ ማድረግ እና ወባ በብዛት ያለበት ቦታ ልንሄድ ከሆነ ሃኪም በማማከር ቀድመን ፀረ-ወባ መድሃኒት መውሰድ ናቸው፡፡
▪️ከላይ የተባሉትን ምልክቶች ብዙ ጊዜ በሽታውን በያዘችው ትንኝ ከተነከስን ከጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ልናይ እንችላለን፤አንዳንድ የወባ በሽታ አይነቶች ግን እስከ አመት ድረስ ምልክት ሳያሳዩ በሰዉነታችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።
▫️ምልክቶቹን ካየን ግን በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብናል።
#WHO, #EthioDemographyAndHealth
@tikvahethiopia

ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና ፦
- የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው።
- በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል::
አጋላጮች ፦
▫️የአቻ ግፊት
▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች
▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል
▫️የማንነት ጥያቄ
▫️የሚዲያ ተጽዕኖ
▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው።
- በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው።
ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች ፦
* ከልክ በላይ ጭንቀት
* የስሜት መዋዠቅ
* ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም #በህይወት_መቆየት_አለመፈልግ
የባህሪ ችግሮች ፦
° ትኩረት ማጣት፣
° ለነገሮች መቸኮል፣
° የፀባይ ለውጥ መኖር
የአመጋገብ ችግር ፦
➡ ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር ነው።
የስነ-ልቦና ቀውስ ፦
• ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል።
• ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ።
• ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድርበታል።
- ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ ?
▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት።
▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።።
#WHO #የዓለምጤናድርጅት
#TikvahEthiopia

አልኮል ፦
- አልኮል በዓለም ላይ 3 ሚለዮን ለሚሆኑ ሞቶች አስተዋፅኦ ያደርጋል፤ እንዲሁም ደግሞ ከ200 በላይ ላሉ አካላዊ እና አዕምሮአዊ የጤና ችግሮች መንስኤ ነው፡፡
- ምንም እንኳን እንደሚወሰደው መጠንና የጊዜ ብዛት ቢለያይም የትኛውም አልኮል መጠን ጤና ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡
ከሚያስከትለው የጤና ችግር በጥቂቱ ፦
➡ አዕምሮን ነገሮችን የሚመለከትበትን መንገድ በመቀየር የባህሪ ችግር እንዲኖርና ነገሮችን በትክክል ማሰብ እንዳይችል ያደርጋል፤ አልፎም ተርፎም ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ በማወክ ለአዕምሮ ቀውስ ይዳርጋል።
➡ የልብ አመታት ችግር
➡ የልብ ጡንቻዎች መድከም
➡ ስትሮክ
➡ የደም ግፊት
➡ የጉበት ህመም ፤ ጉበትን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ስራውን እንዲያቆም ብሎም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡
➡ የተለያዩ ንጥረ ቅመሞችን የሚያመርተው ቆሽት መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን እንዲያመርት፤ በዚህም ምክንያት ለራሱም እንዲሁም ሌሎች አካላትን እንዲጎዱ ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ ለስኳር እና ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
➡ በቀን ውስጥ 1 የአልኮል መጠጥ የምትጠጣ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከ 5-9% ያህል ከማይጠጡት ይልቅ ይጨምራል፡፡
➡ የአንጀት ካንሰርን ጨምሮ አልኮል የብዙ ካንሰር ዓይነቶች መንስኤ ነው፡፡
➡ ብዙ አልኮል መጠቀም የበሽታ መከላከል አቅምን በመቀነስ ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
➡ ትምህርት ላይ ባለው ተፅዕኖ፤ የጤና እክልን በማምጣትና ያለዕድሜ ህይወት እንዲያልፍ በማድረግ ምርታማነትን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
በየቀኑ ወይም ደግሞ በአንድ ጊዜ ብዙ የአልኮል መጠን መውሰድ በየቀኑ ለምንሰራቸው ስራዎች እንቅፋት ይሆናል፤ በአካልም በስነልቦናም የአልኮሉ ጥገኛ ሆነን ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን፤ ይህን ችግር ራሳችን ላይ ካየነው እርዳታ በመፈለግ ህክምና ማግኘት ይኖርብናል፡፡
በቅርብ ያሉ ቤተሰቦቻችን ወይም ጓደኞቻችን ላይ ይህን ችግር ካየን ለአዕምሮቸውም እንዲሁም ለአካላቸው ጤና ስንል ከማግለል ይልቅ ተገቢውን እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
#PAHO #WHO

#WHO🚨
በግብረ ስጋ ግኝኑነት የሚተላለፉ ሽታዎች ወይም የአባላዘር በሽታዎች በዓለም ዙሪያ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) አዲስ ሪፖርት አሳይቷል።
ሪፖርቱ ፥ በየዓመቱ በመላው ዓለም 2.5 ሚሊዮን ሰዎች በግብረ ስጋ ግኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ፣ በኤችአይቪ እንዲሁም ሄፓታይተስ እየሞቱ ናቸው ብሏል።
በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉት እና ሊታከሙ የሚችሉ በሽታዎች እጅግ በፍጥነት እየተስፋፉ ሲሆን ሁኔታው አሳሳቢ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።
ሪፖርቱ ፦ https://www.who.int/news/item/21-05-2024-new-report-flags-major-increase-in-sexually-transmitted-infections---amidst-challenges-in-hiv-and-hepatitis
በዓለም ላይ በየዕለቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ የተለያዩ የሽታ አይነቶች ይያዛሉ።
ዲኤንኤ ዊክሊ የተሰኘ የጤና ድረገጽ እንደሚለው ፤ ዛሬም ድረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ስለሚመጡ በሽታዎች መነጋገር ' እንደ ሚያሳፍር እና እንደ ተከለከለ ' አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ ናቸው።
ከጤና ባለሞያዎች ጋር መመካከር ፣ ስለጉዳዩ ማወቅ ፣ ሲታመሙ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ የሚያፍሩ ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።
ነገር ግን በበሽታዎቹ በየዕለቱ ሚሊዮኖች የሚያዙ ሲሆን በየአመቱም ሚሊዮኖች የሞታሉ።
በመሆኑ ስለ ጉዳዩ አሳስቢነት ሳያፍሩ መነጋገር ፣ የመተላለፊያ የመከላከያ መንገዶች ማወቅ ፣ የጤና ባለሞያዎችን ማማከር ምክራቸውንም መስማት ይገባል።