TIKVAH-ETHIOPIA
" በዓሉ #በሰላም ተጠናቋል " - ግብረ ኃይሉ የ2016 የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ #በሰላም መከበሩን የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል። ግብረ ኃይሉ ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል ያለድ የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ #መጠናቀቁን ገልጿል። የነገው የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓለም በተመሳሳይ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ…
#ኢሬቻ2016 : የ " ሆራ ፊንፊኔ " የኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች #እየተሸኙ ሲሆን ነገ የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓልን የምታስተናግደው ቢሾፍቱ ከተማ እንግዶቿን እየተቀበለች ትገኛለች።
ኢሬቻ " የምስጋና በዓል " እንደሆነ የማህበረሰቡ መሪዎች ይገልጻሉ።
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ምድርና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ዋቃ (ፈጣሪ) ምስጋናውን የሚያቀርብበት ፣ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።
ኢሬቻ የዘመን መለወጫ በዓልም ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በማለፉ በኢሬቻ ቀን ምስጋናውን ለፈጣሪ ያቀርባል።
የ2016 ኢሬቻ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተበረ ይገኛል።
@tikvahethiopia

Video
#Update
🗣 " ጦርነት ላይ ነን ፤ ጦርነቱንም እናሸንፋለን " - የእስራኤል ጠ/ሚ
🗣 " የከፈትነው ወታደራዊ ዘመቻ #ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ ነው " - ሃማስ
#በእስራኤል እና #ሃማስ መካከል ግጭቱ መባበሱ ተገልጿል።
- የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሕዝባቸው " የእስራኤል ህዝብ ሆይ ፤ ጦርነት ላይ ነን ፤ ይህን ጦርነትም እናሸንፋለን " ብለዋል።
- የእስራኤል ሀገር መከላከያ ሚንስቴር " ሃማስ ከባድ ስህተት ሰርቷል ፤ ለዚህም የከፋ ዋጋ እንደሚከፍል እና ለውጤቱም ሁሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል " ብሏል።
- ፈረንሳይ ፣ ዩኬ ፣ ጀርመን ፣ ጣሊያን ፣ አውሮፓ ህብረት ሃማስ የፈፀመውን ጥቃት አውግዘው ከእስራኤል ጎን እንቆማለን ፤ እራሷን የመከላከል መብት አላት ብለዋል።
- በሃማስ ጥቃት በትንሹ 22 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነግሯል።
- በምስራቅ እየሩሳሌም አካባቢ በእስራኤል ፖሊስ እና ፍልስጤማውያን መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል።
- ሃማስ ዛሬ ያለው ሁኔታ ከወራሪ ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው ብሏል። የከፈተው ወታደራዊ ዘመቻ ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ ነው ሲል ገልጿል።
- #ሂዝቦላህ ሃማስን #አወድሶ ቀጥተኛ ግንኙነት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
- ሃማስ እስካሁን 7000 ሮኬት ማስወንጨፉን ገልጿል።
- ሃማስ እስራኤል ላይ እያካሄድኩ ነው ባለው ኦፕሬሽን በርከት ያሉ #የእስራኤል_ወታደሮችን መያዙን አሳውቋል።

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ይጠቀሙ!!
ወደ ባንክ መሔድ ሳያስፈልግዎ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የኢንተርኔትና የሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ጊዜና ገንዘብዎን ይቆጥቡ ፡፡
መተግበሪያውን ከፕሌይስቶር ላይ ለማውረድ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ::
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ofss.dgbb
USSD *9335# በአማራጭነት መጠቀም ይችላሉ
ለተጨማሪ መረጃና አገልግሎት የባንካችንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ !! https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን !!

Photo
#National_GAT_Exam
የብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 1 /2016 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ፈተናው ቀድም ብሎ ከሰኞ መስከረም 28 ጀምሮ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።
ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች መመዝገብ ላልቻሉ ተፈታኞች የምዝገባው ቀን ለ2 ቀናት በመራዘሙ ፤ ፈተናው ከማክሰኞ መስከረም 29 እንደሚጀምር ታውቋል።
GAT ለመውሰድ የማመልከቻው ጊዜው እስከ ነገ እሑድ መስከረም 27/2016 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 የተራዘመ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች ሰኞ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ተጨማሪ የመለማመጃ ፈተና (GAT Mock Exam) ከሰጡ በኃላ ዋናው ፈተና ከመስከረም 29/2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል።
Via @tikvahuniversity

#ሲዳማ
- " እየታየ ያለው ከህግ ያፈነገጠ አካሄድ ሊቆም ይገባል " - ሲዴፓ
- " ተቃዋሚም ሆነ የገዥዉ ፓርቲ አባል ሁሉም ጥፋት ላይ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
በሲዳማ መንግስት ባለስልጣናት እየታዬ ያለዉ ከህግ ያፈነገጠ አካሄድ ሊቆም ይገባል ሲል የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ አሳሰበ።
ፖርቲዉ ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በክልሉ ባለስልጣናት የሚፈጸመዉ ህገወጥ እስርና ዉክቢያ እየከፋ መጥቷል ሲል ነዉ ክሱን ያቀረበዉ።
ለቲኪቫህ ኢትዮጽያ አስተያየታቸዉን የሰጡት የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ተሰማ ኤልያስ እንደሚገልጹት አሁን ላይ በርካታ ወጣቶች በክልሉ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተይዘዉ ራቅ ወዳለ ቦታ መታሰራቸዉን በመግለጽ እነዚህ ግለሰቦች በ48 ሰአት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸዉ መጣሱንም ገልጸዋል።
እስካሁን ከ10 በላይ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ለእስር ተዳርገዉብኛል የሚሉት ሀላፊዉ በቁጥጥር ስር የዋሉ አባሎቻችን ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ ሁሉ መከልከሉን ገልጸዉ እርሳቸዉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ዉክቢያ ዉስጥ መሆናቸዉን ገልጸዋል።
በዚህ ጉዳይ ለ ' አዲስ ስታንዳርድ ' ድረገፅ ከሰሞኑ ምላሽ የሰጡት የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በበኩላቸዉ ከህግ አግባብ ዉጭ የተያዘ ሰዉ አለመኖሩን በመግለጽ ተቃዋሚም ሆነ የገዥዉ ፓርቲ አባል ሁሉም ጥፋት ላይ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

#ለጥንቃቄ
" በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተበዳዮች ገልፀዋል።
የሚጠቀሙት የማጭበርበር ስልት ምንድነው ?
አጭበርባሪዎቹ በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይ በፌስቡክ እና በቴሌግራም ሌሎች ሰዎችን ለመሳብ " እኔ 10 ሺ ብር ኢንቨስት አድርጌ 180 ሺ ብር አግኝቻለሁ እናንተም ኢንቨስት አድርጉ " የሚል የምስክርነት ቪዲዮ አሰርተው ይለቃሉ።
መልዕክቶቹንም በፌስቡክ #Sponsored በማድረግ ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ እንዳደረጉት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን የሚቀርቡት ስማቸውን ፤ አድራሻቸውን ፤ ፎቶአቸውን የውጪ ሀገር ዜጋ አስመስለው ሲሆን በተጨማሪም የውጪ ሃገር የቢዝነስ አማካሪ እንደሆኑ ጭምር ያስመስላሉ።
አጭበርባሪዎቹ የውጪ ሃገር ሰው እንደሆኑ ያስመስሉ እንጂ ገንዘቡን የሚያስልኩት በሀገር ውስጥ ባንኮች መሆኑን ተበዳዮች ለቲክቫህ ከላኩት ማስረጃ ማየት ተችሏል።
በርካታ ተበዳዮች ስለ ፎሬክስ አሳሳች የቪዲዮ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎችን ተመልክተው 10ሺ ብር ለቡድኑ በመላክ መጭበርበራቸውን ገልፀዋል።
ተበዳዮች ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ ገንዘባቸው ኢንቨስት ስለተደረገ ገንዘቡን ለማስለቀቅ ተጨማሪ 36ሺ ብር ሲጠየቁ ሌሎች ተበዳዮችን ደግሞ "10 ሺ ኢንቨስት አድርጌ 180ሺ አትርፌአለሁ" የሚል የቪዲዮ ምስክርነት በኢንግሊዝኛና አማርኛ ቋንቋ ቀርፀው ከላኩ ገንዘቡን እንመልሳለን ብለው እንዳታለሏቸው አስረድተዋል።
ተበዳዮች ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ገፍተው መጠየቅ ሲጀምሩ ቡድኖቹ አድራሻቸውን አጥፍተው እንደሚሰወሩ ተበዳዮች ሲገልፁ ቀርፀው የላኩትን ቪዲዮ ሌሎችን ለማታለል እያዋሉት እንደሆነ በማየታቸው ሌሎች ሰዎች በእንደዚህ አይነት ማታለያ ከመጭበርበር እራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አስጠንቅቀው ፥ አጭበርባሪዎቹን የሚመለከተው የህግ አካል ሊከታተላቸው እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ ምንድነው ?
- ማኛውም ገንዘባችሁን አምጡ እያሉ በኦንላይን ለሚጠይቁ አካላት ፦
• ማንነታቸውን በትክክል የሚገልፅ መታወቂያ እንዲልኩ
• የሚሰሩበትን አድራሻ (ሀገር፣ ከተማ፣ አካባቢ) እና ከትክክለኛው አካል ህጋዊ ፍቃድ እንዳላቸውና እሱን እንዲልኩ መጠየቅ ይገባል።
- በተለይም በቴሌግራም ሆነ ፌስቡክ የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት (✅️ ) መግዛት ቀላል ስለሆነ ይህ ምልክት ያለበት ሰው እውነተኛ እና ታማኝ ነው በሚል የተሳሳተ አመለካከት እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ። ማንኛውም ሰው ይሄን ምልክት እየገዛ የተረጋገጠና እውነተኛ ታማኝ ሰው ለመምሰል ይሞክራል።
- " በትንሽ ብር ብቻ እጅግ ብዙ መቶ ሺዎች የሚገኝበት ነው " ስንባል እንዲህ የሚሉንን ሰዎች በበቂ ጥያቄ ማፋጠጥ፣ እያንዳንዱ አካሄዳቸውን መመርመር፣ በሌሎች በርካታ መንገዶች ሰዎቹን በጥያቄ መፈተሽ ይገባል።
ይወያዩ ፦ @BirlikEthiopia
Via👋 @TikvahethMagazine
" በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተበዳዮች ገልፀዋል።
የሚጠቀሙት የማጭበርበር ስልት ምንድነው ?
አጭበርባሪዎቹ በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይ በፌስቡክ እና በቴሌግራም ሌሎች ሰዎችን ለመሳብ " እኔ 10 ሺ ብር ኢንቨስት አድርጌ 180 ሺ ብር አግኝቻለሁ እናንተም ኢንቨስት አድርጉ " የሚል የምስክርነት ቪዲዮ አሰርተው ይለቃሉ።
መልዕክቶቹንም በፌስቡክ #Sponsored በማድረግ ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ እንዳደረጉት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን የሚቀርቡት ስማቸውን ፤ አድራሻቸውን ፤ ፎቶአቸውን የውጪ ሀገር ዜጋ አስመስለው ሲሆን በተጨማሪም የውጪ ሃገር የቢዝነስ አማካሪ እንደሆኑ ጭምር ያስመስላሉ።
አጭበርባሪዎቹ የውጪ ሃገር ሰው እንደሆኑ ያስመስሉ እንጂ ገንዘቡን የሚያስልኩት በሀገር ውስጥ ባንኮች መሆኑን ተበዳዮች ለቲክቫህ ከላኩት ማስረጃ ማየት ተችሏል።
በርካታ ተበዳዮች ስለ ፎሬክስ አሳሳች የቪዲዮ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎችን ተመልክተው 10ሺ ብር ለቡድኑ በመላክ መጭበርበራቸውን ገልፀዋል።
ተበዳዮች ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ ገንዘባቸው ኢንቨስት ስለተደረገ ገንዘቡን ለማስለቀቅ ተጨማሪ 36ሺ ብር ሲጠየቁ ሌሎች ተበዳዮችን ደግሞ "10 ሺ ኢንቨስት አድርጌ 180ሺ አትርፌአለሁ" የሚል የቪዲዮ ምስክርነት በኢንግሊዝኛና አማርኛ ቋንቋ ቀርፀው ከላኩ ገንዘቡን እንመልሳለን ብለው እንዳታለሏቸው አስረድተዋል።
ተበዳዮች ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ገፍተው መጠየቅ ሲጀምሩ ቡድኖቹ አድራሻቸውን አጥፍተው እንደሚሰወሩ ተበዳዮች ሲገልፁ ቀርፀው የላኩትን ቪዲዮ ሌሎችን ለማታለል እያዋሉት እንደሆነ በማየታቸው ሌሎች ሰዎች በእንደዚህ አይነት ማታለያ ከመጭበርበር እራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አስጠንቅቀው ፥ አጭበርባሪዎቹን የሚመለከተው የህግ አካል ሊከታተላቸው እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ ምንድነው ?
- ማኛውም ገንዘባችሁን አምጡ እያሉ በኦንላይን ለሚጠይቁ አካላት ፦
• ማንነታቸውን በትክክል የሚገልፅ መታወቂያ እንዲልኩ
• የሚሰሩበትን አድራሻ (ሀገር፣ ከተማ፣ አካባቢ) እና ከትክክለኛው አካል ህጋዊ ፍቃድ እንዳላቸውና እሱን እንዲልኩ መጠየቅ ይገባል።
- በተለይም በቴሌግራም ሆነ ፌስቡክ የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት (
- " በትንሽ ብር ብቻ እጅግ ብዙ መቶ ሺዎች የሚገኝበት ነው " ስንባል እንዲህ የሚሉንን ሰዎች በበቂ ጥያቄ ማፋጠጥ፣ እያንዳንዱ አካሄዳቸውን መመርመር፣ በሌሎች በርካታ መንገዶች ሰዎቹን በጥያቄ መፈተሽ ይገባል።
ይወያዩ ፦ @BirlikEthiopia
Via
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update
የእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ?
በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ መጥቷል።
ሀገራት የተለያዩ አቋማቸውን እያንፀባረቁ ይገኛሉ።
#ኢራን ፍልስጤም እና እየሩሳሌም ነፃ እስኪወጡ " ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን ነኝ " ብላለች። #አሜሪካ በበኩሏ ከእስራኤል ጎን እንደሆነች ገልጻ የማያወላዳ ድጋፏን እንደምታደርግ አሳውቃለች።
የሁለቱ ሀገራት ጎረቤቶች ሁኔታውን በእንክሮ እየተከታተሉ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ዓለም አቀፍ ይዞታን ሳይዝ እንደማይቀር ተሰግቷል።
ከመሸ የተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች ምንድናቸው ?
- እስራኤል ጋዛ ላይ እየወሰደች ባለው የአፀፋ እርምጃ 232 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ፣ 1697 ቆስለዋል ፤ በርካቶች ለህይወታቸውን የሚያሰጋ ጉዳት ላይ ናቸው።
- ሃማስ ባካሄደው ወታደራዊ ኦፕሬሽን የተገደሉ እስራኤላውያን ቁጥር ወደ 200 ማሻቀቡ ተሰምቷል።
- እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የኃይል አቅርቦት በማቋረጧ ሆስፒታሎች ተጎጂዎችን ለማከም እየተፈተኑ ይገኛሉ ተብሏል። በጋዛ ኤሌክትሪክ እንዲቋረጥ ያዘዘው የእስራኤል ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።
- ፍልስጤም ፤ አንድ የ13 ዓመት ልጅን ጨምሮ 4 ፍልስጤማውያን በ " ዌስት ባንክ ' በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን አሳውቃለች።
- የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ኻሚኒ አማካሪ ያህያ ራሂም ሳፋቪ " የፍልስጤም ተዋጊዎች በእስራኤል ላይ ከዓመታት በኋላ ትልቁን ጥቃት በማድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል። " የፍልስጤም ተዋጊዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። " ያሉት አማካሪው " ፍልስጤም እና እየሩሳሌም ነፃ እስኪወጡ ድረስ ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን እንቆማለን። " ብለዋል። ኢራን የሃማስን ኦፕሬሽን " የሚያኮራ " ብላለች።
- ሃማስ በእስራኤል ላይ ከፈትኩ ያለውን ኦፕሬሽን ተከትሎ ከኢራን፣ ቴህራን ከፍተኛ የሆነ ደስታን የሚገልጹ ቪድዮዎች ወጥተዋል። በቪድዮዎቹ ቴህራን ውስጥ ርችት ሲተኮስ እና ሰዎች ደስታቸውን ሲገልጹ ይታያል (ቪድዮ ከላይ ተያይዟል)።
- አሜሪካ በዚህ ወቅት ከእስራኤል መንግሥት እና ህዝብ ጋር መሆኗን በመግለፅ የማያወላዳ ድጋፏን እንደምታደርግ አሳውቃለች። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ተኩስ እንዲቆም ጠይቃለች። ቱርክ በንፁሃን ሞት ማዘኗን ገልጻ ግጭቱ ወደ ቀጠናው ሳይስፋፋ እንዲበርድ ድጋፏን እንደምታደርግ አሳውቃለች።
- NATO አጋሬ ናት ባለው እስራኤል ላይ የተፈፀመው የአሸባሪዎች ጥቃት መሆኑን ገልጾ ከተጎጂዎች ጋር እንደሚቆም እስራኤልን እራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ገልጿል።
- የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ የፍልስጤም ህዝብ ከ " ሰፋሪዎች እና ወራሪ ወታደሮች ሽብር " እራሱን የመከላከል መብት አለው ብለዋል።
- የእስራኤል ትምህርት ሚኒስቴር ነገ በመላው ሀገሪቱ ትምህርት እንዲዘጋ መወሰኑ ታውቋል።
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ወታደራዊ ግጭቱ የተነሳው ሃማስ ድንገተኛ እና ባለፉት በርካታ አመታት ታይቶ የማይታወቅ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እስራኤል ላይ ከጀመረ በኃላ ነው።
ሃማስ ጦርነቱ " ከወራሪ ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው " ብሏል። ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ ነው ሲልም ገልጿል።
የእስራኤል ሀገር መከላከያ ሚንስቴር " ሃማስ ከባድ ስህተት ሰርቷል ፤ ለዚህም የከፋ ዋጋ እንደሚከፍል እና ለውጤቱም ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል " ካለ በኃላ የአየር ጥቃቶችን ጨምሮ የአፀፋ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።