TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቴክኖ_ሞባይል

ቴክኖ ሞባይል እጅግ የተራቀቀውን እና የአለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊውን  ካሞን 20 የሰልክ ሞዴል በኢትዮጵያ የማስተዋወቅ ዝግጅት አካሄደ።

በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ተወዳጅ ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል በዛሬው እለት እጅግ በጣም የተራቀቀውን፣ የአለም አቀፍ ሽልማት የተጎናፀፈበትን ብሎም ጊዜው የደረሰበትን የስልክ ቴክኖሎጂ የያዘውን ካሞን 20 የሰልክ ሞዴል የቴክኖሎጂን እና የፋሽንን ጥምረት የሚያሳዩ ዝግጅቶች በደመቀ ልዩ ስነስርዓት አስተዋወቀ።

በ108 ሜጋ ፒክስል ካሜራ ፎቶ እና ቪዲዮ በጥራት በየትኛውም የእንቅስቃሴ ሳይረብሸው የማንሳት የሚያስችል የኤስ.ኤል,አር (SLR) ሲስተም የሚታገዝ ባለ ሁለት ሌንስ ካሜራ፣ በምሽት ጥራት ያለው 50 ሜጋ ፒክስል ምሰል ያለ እለ እንክን ለማንሳት ያሚያስችለው አርጂቢደብሊው (RGBW) ሴንሰር ባለቤት የሆነው ሞዴል ካሞን 20 ቴክኖ ሞባይል ለአለም ዙሪያ እያስተዋወቀ ይገኛል።

ካሞን 20 ለዩ የሆነውን ሲስተም የሚተገብር ካሜራ በመጠቀም እጅግ ከፍተኛ ጥራት (ultra-HD) የሆኑ ምስሎችን የማንሳት አቅም አለው።

#CamonSeries #TecnoMobile #TecnoEthiopia

(ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ)
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሪሜዲያል ፈተና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ላለፉት አራት ቀናት የተሰጠው መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ።

የሪሚዲያል ፈተናው ዛሬ ከሰዓት በተሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ማጠናቀቂያውን አጊኝቷል፡፡

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የማጠናከሪያ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የሪሚዲያል ተማሪዎች፣ የፈተናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ከነገ ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከነበሩበት ተቋም እንደሚወጡ ይጠበቃል።

ይህም ከሰኞ ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመዘጋጀት እና የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሆነ ተገልጿል።

የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን የተሰጡ ፈተናዎች እንዲሰረዙና ተማሪዎች ከዛ በኋላ በተሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ የትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ይታወቃል።

ከዚህ ባለፈ፤ ሚኒስቴሩ ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደውን እቅድ አሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት  በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ መወሰኑ የሚዘናጋ አይደለም።

ፈተናው ወደ መስከረም ወር 2016 የተራዘመባቸው ተማሪዎች እና የተማሪዎቹ ወላጆች ውሳኔውን ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ የተፈታኝ ተማሪዎችን ዝግጅት እና ልፋት እንዲሁም እየጠፋ ያለውን ጊዜ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈተናው እንዲሰጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ቅሬታ መግለፃቸው ይታወሳል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
ሀገረ አቀፍ ፈተናዎች . . .

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ :

የሬሜዲያል ፈተና ፦

- በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ሰኔ 30/ 2015 ዓ/ም ተጠናቋል።

(አሁን ላይ ያልተፈተኑ የግል ተማሪዎች ወደፊት በሚገለፅ ጊዜ በመስከረም 2016 ዓ/ም እንደሚፈቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል)

- በ2016 ዓ/ም ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የሚገኙ በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ይሆናሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመንግስት እና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ፦

- መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። ውጤት ሐምሌ 10 ይገለፃል። (የጤና ተማሪዎች መውጫ ፈተና ዛሬ ተካሂዷል)

- በዘንድሮው ዓመት 169 ሺህ በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

- ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች ተዘጋጅቷል።

- ሃምሳ (50) በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ያልፋሉ።

- ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ። የመጀመሪያው ዙር ፈተና መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ሲሆን ከዛ በኃላ ግን ልክ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በግል እንደሚፈተኑት መውጫ ፈተና ላይም ተፈታኞች ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት / በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ #ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

- የመውጫ ፈተና ሙሉ በሙሉ #በኦንላይን ይሰጣል።

- የተፈታኝ ተመራቂ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል ገብቷል።

- ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተከናውኖ ፤ የሞዴል ፈተና እየወሰዱ ነው።

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ፦

- ብሔራዊ ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ድረሰ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

- ለብሔራዊ ፈተናው የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ ይሆናሉ።

- የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

- ፈተናው ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን ተመዝግበዋል።

- ለፈተናው የተመዘገቡት 503,812 የሶሻል ሳይንስ እንዲሁም 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

- የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውኗል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ብርሃን ባንክ የ’ኤም ፖስ’ ማሽንን በከተማችን ውስጥ ለሚገኙ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት የኪሎሜትር ክፍያ ለሚያከናውኑ የታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች አሰራጭቷል።

ባንካችን ያስጀመረው የአገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ የሆነው ይህ የብርሃን ’ኤም ፖስ’ (M-POS) ማሽን የዲጂታል ደረሰኝ ለሚፈልጉ ለተለያዩ አነስተኛ ቢዝነሶች መዋል የሚችል ሲሆን በሆቴሎች እና በንግድ ማእከላትም ይገኛል፡፡

እነዚህ ማሽኖች ለአጠቃቀም እና ለአያያዝ እጅግ ቀላል ሲሆኑ የኔትወርክ ፍጥነታቸው ቀድሞ በገበያ ላይ ካሉት የፖስ ማሽኖች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ስለሆነ ተመራጭ ያደርገናል፡፡

(ብርሃን ባንክ)
#ልዩ_ዕቃ

GRINDER Machine (የቡና እና የቅመማ ቅመም መፍጫ)
🚩እጅግ በጣም ጠንካራ
🚩ለደረቅ ቅመማ ቅመሞች የሚሆን
🚩ሙሉ ለሙሉ ብረት (Stainless steel)
🚩የራሱ መለዋወጫ ጥርስ ያለው
100 ግ = 2800 ብር
200 ግ = 3999 ብር
400 ግ = 5800 ብር
500 ግ = 6800 ብር
1000ግ= 9600 ብር

 ቴሌግራም ቻናል👉 @LeyuEka

ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን 0944109295 @Le_Mazez
0933334444 @LeMazez_z
0946242424 @Le_Mazez
የኬንያ መንግሥት የኮንጎ ብራዛቪል ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ኬንያ መግባት እንደሚችሉ ውሳኔ አሳለፈ።

የጎረቤት ሀገር ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊልያም ሩቶ ከትላንት ጀምሮ በኮንጎ ብራዛቪል ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደርጉ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንት ሩቶ በጉብኝንታቸው ለሀገሪቱ ፓርላማ ንግግር አድርገዋል።

ሩቶ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ከዛሬ ጀምሮ የኮንጎ ብራዛቪል ዜጎች ኬንያ ለመግባት ቪዛ እንደማያስፈልጋቸው አሳውቀዋል።

ይህን ውሳኔ መተላለፉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ንግድ፣ ቢዝነስ ፣  የሃሳብ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚረዳና ግኝኑነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልጻዋል።

ፕሬዝዳንቱ ፤ የአፍሪካ አገሮች በመሠረተ ልማት አውታሮች መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ፣ የንግድ እንቅፋቶችን እና የቪዛ ገደቦችን #በማስወገድ ነፃ የንግድ አቅምን ማጎልበት አለባቸው ብለዋል።

በ " ትሬድስ " ይቀላቀሉን ፦ threads.net/tikvahethiopia

@tikvahethiopia
" የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይጠየቅልን " - ተፈናቃይ ወገኖች

ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት የተፈናቀሉ ዜጎች ፤ የክልሉ መንግሥት እንዲጠየቅ እንደሚፈልጉ ተናግሩ።

" የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንዲጠይቀን እንፈልጋለን " ያሉት ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች ናቸው።

ተፈናቃዮቹ ይህን የጠየቁት ፤ ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት በዞኑ ተገኝቶ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ነው።

ተፈናቃዮች ምን አሉ ?

" ኦሮሚያ ክልል፤ ተወልደን ያደግንበት፣ ትዳር መስርተን ልጆች የወለድንበት፣ ኃብትና ንብረት ያፈራንበት ክልላችን ሆኖ ሳለ ከክልላችን ስንፈናቀል የክልሉ መንግስት የት እንደወደቅን መጠየቅ አለመቻሉ አሳዝኖናል።

ከክልላችን ስንፈናቀል ከ60 ዓመታት በላይ ያፈራነውን ኃብትና ንብረት ይዘን መውጣት አልቻልንም።

ድጋፍ ከመንግስት መጠበቅ ሰልችቶናል መንግስት የጸጥታውን ጉዳይ በፍጥነት ይፍታልንና ወደ ክልላችን መመለስ እንፈልጋለን።

የዕለት ደራሽ ምግብ እጥረት ገጥሞናል ፤ እጥረቱ በተለይም በሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ የሚመለከተው አካል በፍጥነት ይድረስልን። " ብለዋል።

ተፈናቃዮችን ሄዶ የተመለከተው ቡድን ለተፈናቃዮቹ በተለይም ደግሞ ሕፃናት፣ ሴቶችና አረጋዊያን በዕለት ደራሽ የምግብ አቅርቦት እጥረት ምክንያት ከመጎዳታቸው በፊት የሚመለከታቸው አካላት የተሟላ የዕለት ደራሽ ምግብ ሊያቀርቡላቸው ይገባል ሲል አሳስቧል።

በመጠለያ ጣቢያዎቹ የመፀዳጃ እና ሻወር ቤቶችን ተዘዋውሮ በተመለከተበት ወቅትም መፀዳጃና ሻወር ቤቶች  ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ቢሆኑም፤ በመጠለያ ጣቢያዎቹ ያለው የተፈናቃይ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ተጨማሪ መፀዳጃና ሻወር ቤቶች መገንባት እንዳለበት አሳስቧል።

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ በዞኑ ከ44 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ አሳውቋል።

ያጋጠመውን የዕለት ደራሽ ምግብ እጥረት ለመፍታት ዞኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የከፋ ችግር እንዳይደርስ እየሰራ መሆን ገልጿል።

አስተዳደሩ ፤ የችግሩን ስፋትና ክፋት ለማስረዳት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቢነጋገርም ለችግሩ እልባት እንዳልተሰጠው አሳውቋል።

ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋምና ወደ ቀያቸው ለመመለስ ቋሚ ኮሚቴው ሚናውን እንዲወጣ ተጠይቋል።

Via HoPR

@tikvahethiopia
#ቴክኖ

የላቁ ፈጠራዎችን እጅግ ከዳበሩ ግልጋሎቶች ጋር የያዘው አዲሱ Tecno Camon 20 Series ለተጠቃሚዎች እጅጉን የላቀ አገልግሎትን ዘመኑ ከድረሰበት ዲዛይን ጋር ይዞ ቀርቧል !

ዘመኑ ያፈራውና ከፍተኛ አቅም እንዳለው የሚነገርለትን ፕሮሰሰር የያዘው ካሞን 20 Series ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ በፍጥነት እና ያለ እንከን በመስራቱ በሞባይል ስልክ በመጠቀም ብዙ ስራዎችን ለሚሰሩ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ያደርገዋል።

45ዋት የፍጥነት ቻርጅ የማድረግ አቅም ያለው ባለ5000 ሚሊአሚፒር ባትሪ የያዘው ይህ ሞዴል አገልግሎትን ያለ ማቋረጥ እየሰጠ ቀኑን ሙሉ ያለ ስጋት እንድንጠቀም ያስቸለናል።

#CamonSeries #TecnoMobile #TecnoEthiopia

(ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ)