TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PropertyTax

ኢትዮጵያ ውስጥ " ፕሮፐርቲ ታክስ " እስካሁን እንዳልተጀመረ ነገር ግን ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ይፋ አደረጉ።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ ፕሮፐርቲ ታክስ መላው ኢትዮጵያ ውስጥ በአዲስ አበባ ጨምሮ እንዳልተጀመረ ገልጸው በአ/አ እየተከናወነ ያለው ከዚህ ቀደም የነበረውን የጣሪያ እና ግርግዳ ግብር ህግ በማሻሻል እየተሰበሰበ ያለ ግብር ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

" ይህ የተሻሻለው የጣሪያ እና የግድግዳ ግብር ማለት ፕሮፐርቲ ታክስ ማለት አይደለም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ወደፊት የፕሮፐርቲ ታክስ አዋጅ በዝርዝር የሚታይ ጉዳይ ነው ብለዋል።

" ፕሮፐርቲ ታክስ " ካቢኔው አፅድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ አዋጁ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

ከጣሪያና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ ያለው የታክስ ምንጭ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አምጥቶ ያልተገባ ሀብት ወስዶ ከሆነ ቅሬታ የሚሰማበት ስርአት ስላለ በዚያው ስርአት ቅሬታ ቀርቦ ሊታይ እንደሚችልም አስገንዝበዋል።

በአዲስ አበባ እየተሰበሰበ ያለው የጣራ እና የግድግዳ ግብር መሆኑንና ይህም ከ1937ዓ.ም ጀምሮ የመጣ እና ማሻሻያ የተደረገበት ነው ብለዋል፡፡

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ቅዱስ ፓትርያርኩ የተመረጡትን አባቶችን አልሾምም አላሉም  ፤ ወደ ትግራይም በተያዘው መርሀግብር ይጓዛሉ " - ቤተክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በአንዳንድ ማኅበራዊ  ሚዲያዎች ላይ " ቅዱስ ፓትርያርኩ በቅዱስ ሲኖዶስ የተመረጡትን መነኮሳት አልሾምም ፤ ወደ ትግራይም አልሔድም " ብለዋል  ተብሎ እየተሰራጨ ያለው ዜና ፍጹም ሐሰት ነው አለች።

ቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ፓትርያርኩ " የተመረጡትን አባቶችንም አልሾምም አላሉም። በተያዘው መርሐ ግብር  መሠረትም ወደ ትግራይ ይጓዛሉ " ስትል አሳውቃላች።

ቤተክርስቲያንኗ " እንዲህ ዓይነቱ ሆን ተብሎ የሚሰራጭ የሐሰት ዘገባ ፤ #የእርቅ ሂደቱን የማደናቀፍ እና  የቅዱስ ፓትርያርኩንስም በሐስት የማጠልሽት የተለመደና ቀጣይ የሐሰተኞችና ስም አጥፊዎች ዘመቻ አካል ነው " ያለች ሲሆን " ይህን አይነቱን የሐሰትና የፈጠራ ወሬ በቅድስት እርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ላይ የሚነዙ  አካላትም ከዚህ ደርጊታቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን " ብላለች።

@tikvahethiopia
" የትኛው ፖሊስ ጋር ነው ያመለከቱት ? ፌክ ኒውስ በጣም በብዛት እያሰራጩ ነው " - የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በታጣቂዎች እገታዎች ተፈፅመው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚጠየቅ በተደጋጋሚ መገለፁ ይታወቃል።

በቅርቡ አንድ ሰዓሊ ከጓደኛው ጋር ሶደሬ አካባቢ ከታገተ በኃላ ቤተሰቦቹ ጋር ተደውሎ ገንዘብ ከተጠየቁ በኃላ ለመነጋገር ድጋሚ ሲደውሉ " በእሱ ጉዳይ አትደውሉልን አፈር አልብሰነዋል " የሚል መርዶ ተነግሯቸው ሀዘን ላይ እንደነበሩ ፤ ጓደኛው ግን 500 ሺህ ብር ከፍሎ ከእገታ መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህ ክስተት በፊትም የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸውን መግለፃችን ይታወሳል።

እኚህን ባለስልጣን ያገቷቸው ታጣቂዎች 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸው መነገሩም አይዘነጋም።

ወደ ጎጃም መስመር " ዓሊዶሮ " ላይም 30 ሹፌሮች እና ረዳቶች በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው መግለፃቸው ፤ ከታገቱት ውስጥም 500 ሺህ እና 1 ሚሊዮን ብር ቤተሰቦቻቸው ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው መግለፃችን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

እንደውም ከቀናት በፊት ልጃቸውን ከእገታ ለማስለቀቅ 1 ሚሊዮን ብር የከፈሉ አሳዛኝ መምህር ታሪክ መሰራጨቱ ይታወሳል።

ወራትን ወደኃላ ብንጓዝ በርካቶች እየታገቱ ገንዘብ ተጠይቆባቸው ለአጋቾች ተከፍሎ ተለቀዋል ፤ በርካታ ሚዲያ ላይ ያልቀረቡ መሰል ክስተቶች አሉ።

ከታጋች ቤተሰቦች እንደሚሰማው ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ቢወስዱት አጋቾች የያዙትን ሰው ህይወት ያጠፋሉ የሚል ስጋት አለ ፤ ከዛ ውጭ ግን ጉዳዩን ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ዛሬ በነበረው የፓርላማ ውሎም የምክር ቤት አባላት የእገታ ጉዳይን አንስተው አሳሳቢነቱን ገልጸዋል። ለጠ/ሚኒስትሩም ጥያቄ አቅርበዋል።

ይህንን የእገታ ጉዳይ በተመለከተ ዶቼ ቨለ ሬድዮ አንድ አጭር ዘገባ አሰራጭቶ የተመለከትን ሲሆን በዚሁ ዘገባ ላይ የነዋሪዎች / አሽከርካሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ ቃል ይገኝበታል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ አሽከርካሪ ፤ ጅቡቲ ኮሪደር ላይ እስካሁን ከነበረው አሁን ላይ መሻሻል እንዳለ፤ መንግሥት ከፍተኛ ሰራዊት መድቦ ከወለንጪቲ እስከ መተሃራ በፌዴራል እና መከላከያ የሚጠበቅ ቀጠና መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ትልቁ ችግር ያለው ከፍቼ - ጎሃ ፂዮን ያለው ቀጠና ነው ብለዋል።

አንድ የአ/አ ነዋሪ ደግሞ ከእገታ ጋር በተያያዘ 3 ዓይነት ሰዎች አሉ ፤ እራሳቸው ሳይታገቱ " ታግተናል " በሚል ለፖለቲካም ሆነ ለሌላ አላማ የሚጠቀሙ ፣ የገንዘብ ፍላጎት ኖሯቸው የሚንቀሳቀሱ አሉ እነዚህ ገንዘብ ያላቸውን ፣ ቢዝነስ ውስጥ ያሉ ሰዎችን አጥንተው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፤ በረሃ ላይ አሸከርካሪዎችን የሚያግቱም አሉ እነዚህም ገንዘብ ይጠይቃሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ልጅም " ታገትኩ " ብሎ አባቱን ገንዘብ የሚያስጠይቅም አለ እውነቱን ለማወቅ አቸጋሪ ጊዜ ነው ነገሩ ሁሉ ውስብስብ ነው ሲሉ አክለዋል።

የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ግን የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ መሆኑን ገልጸው አሽከርካሪዎችም ሆኑ ሌሎች ከታገቱ የት ፖሊስ ጣቢያ ሄደው እንዳመለከቱ መረጃ ሊጣራ ይገባል ብለዋል።

አቶ ጄይላን ፤ " የትኛው ፖሊስ ጋር ነው ያመለከቱት ? ፌክ ኒውስ በጣም በብዛት እያሰራጩ ነው ፤ ፌዴራል ፖሊስ መንገድ ላይ እዛው አመልክተዋል ወይ ? ሆን ተብሎ ፌክኒውስ ሀገሪቱ ላይ ሰላም እንደሌለ ለማስመሰል ፤ፌክኒውስ እየተሰራጨ ነው ያለው ሰው ታግቷል ተብሎ " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " - ባለስልጣን መ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ አስጠንቅቋል። የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል፡፡…
#ETA

ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በድጋሚ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ወደሚያስፈትኑበት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመሔድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያጠናቅቁ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በድጋሜ አሳስቧል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚያስፈትኗቸውን ተማሪዎች ፦

- ፎቶ፣
- የይለፍ ቃል፣
- የተጠቃሚ ሥም እና የትምህርት ቤት ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ ወደተመደቡበት ተቋም በመሔድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

ባለስሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፤ በአሁኑ ወቅት ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረሶኛል ባለው መረጃ መሰረት ከላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮችን በማሟላት ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አነስተኛ ናቸው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አላስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ባለማሟላታቸው ምክንያት ተማሪዎች ለፈተና የማይቀመጡበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ባለሥልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊነት የሚወስዱ መሆኑን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።

(ባለሥልጣኑ ዛሬ ያወጣው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

Via @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
ሹፌሩን እና ረዳቱን #በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን " FSR መኪና " ይዘው ከተሰወሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች አንዱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ።

እንደ ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መረጃ ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቅ ጎጃም ዞን  ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፤ አባጀምበር ቀበሌ ፤ " የጨረቃን ጎጥ " ነው።

ከ " ገንዳ ውሃ " ከተማ ወደ " አዲስ አበባ " አንድ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ  ሾፌርና ረዳቱን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሰኔ 28/2015 ዓ/ም ሰዓቱ በትክክል ባልታወቀበት ሁኔታ ገድለው በመጣል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ፡፡

የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው ክትትል ተጠርጣሪ ወንጀለኛቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ማሳደራቸው መረጃ ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹን ክትትል በማድረግ ላይ እያለ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ/ም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ አንዱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ #ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ሌሎች ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ ነው ሲል የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል።

የጎንቻ ሲሶ እነሴና ግንደወይን ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት ላደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ልዩ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በከተማችን አሉ በተባሉ ሬስቶራንቶች በልተው ጠጥተው እስከ 15% ድረስ ቅናሽ ያግኙ!
ለበለጠ መረጃ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡

https://apollo.bankofabyssinia.com/deals-discounts/

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
የመውጫ ፈተና ተጀመረ።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ያደረገው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን የመውጫ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል።

በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የመንግሥት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ፈተናቸውን በ " ኦንላይን " መውሰድ ጀምረዋል።

ዛሬ የመውጫ ፈተናቸውን መውሰድ የጀመሩት የጤና ተማሪዎች ናቸው።

በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ደግሞ ከጤና ተማሪዎች ውጭ የሆኑ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

ፎቶ ፦ ከዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራይ ከነገ ጀምሮ ከ60 ሺህ የማይበልጡ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና ይወስዳሉ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ #ከነገ_ጀምሮ በትግራይ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል። በ2012 ዓ/ም መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ ሲሆን በወቅቱ 120,000 ገደማ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ነበር። አሁን ከነገ ጀምሮ በሚጀምረው የ8ኛ ፈተና ከ60 ሺህ…
#Tigray

በትግራይ ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ዛሬ መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ፈተናው በክልሉ 75 ወረዳዎች ውስጥ በ1,007 ትምህርት ቤቶች የተሰጠ በ518 ትምህርት ቤቶች ፈተናውን መስጠት አለመቻሉ ታውቋል።

በ2012 ዓ/ም መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ ሲሆን በወቅቱ 120,000 ገደማ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ነበር።

አሁን ላይ ግን ከ60 ሺህ የማይበልጡ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ፈተናውን መውሰድ የቻሉት።

@tikvahethiopia
' ሕዝበ ውሳኔ '

የአማራ ክልል መንግሥት የማንነት እና የወሰን ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ሲል አሳወቀ።

የክልሉ መንግሥት ይህን ያሳወቀው ዛሬ በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ጥያቄ የሚያነሱባቸውን የማንነት እና የወሰን ጉዳዮችን በተመለከተ አንስተዋል።

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፤ " የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ቢያንስ ከ30 ዓመት በኃላ በ #ሕዝበ_ውሳኔ በሕጋዊ መንገድ እንዲያልቅ #ስራዎች_እየተሰሩ_ይገኛሉ " ብለዋል።

የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ አቶ ግዛቸው ገልጸዋል።

ትላንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፤ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ የሰጡት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል ስላለው የይገባኛል ጥያቄ ጉዳይ አንስተው ነበር።

ዶ/ር ዐቢይ " በአማራና ትግራይ መካከል ያሉ ባለፉት 30 ዓመታት ጥያቄያቸው ሲነሳ የነበሩ ቦታዎች አሉ ፤ ይሄ በተለይ ታላቁ የአማራ ህዝብ ፣ የትግራይ ህዝብ በሰከነ መንገድ እንዲያየው መክራለሁ " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ፤  " #በመሬት ምክንያት መባላት ፣ መገዳደል አያስፈልግም ፤ መሬት የፀብ ምንጭ መሆን የለበትም ፤ ህዝቦች ተወያይተው ተመካክረው በ ' win win approach ' ጊዜ ወስደው በሰከነ መንገድ የትኛው ክልል መኖር እንደሚፈልጉ መወሰን ይችላሉ ፤ ይህንን ሲዳማ ላይ አድርገነዋል፣ ደቡብ ምዕረብ ላይ አድርገነዋል፣ ትላንትም ወስነናል ስለዚህ በሰከነ መንገድ ሰዎች ወስነው ሰው ሳይሞት ማድረግ ይቻላል ፤ ከዛ ውጭ ያለው አማራጭ ጥሩ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" መነጣጠቅ ጥቅም የለውም፤ ዘላቂ ሰላም ማምጣት ያስፈልጋል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " #አማራን እንዳለ ቆርጦ #ከትግራይ ጉርብትና ማንሳት አይቻልም ትግራይንም እንዲሁ ፤ አብሮ የሚኖር ህዝብ ነው ፤ ዋናው አስፈላጊ ነገር ሰላም ነው ፤ ይሄን ታሳቢ በማድረግ ፦
- በሰከነ መንገድ በውይይት
- የተፈናቀለውን መልሰን፣
- የተጎዳውን ጠግነን
- የተጣላውን አስታርቀን በ #ህዝብ_ውሳኔ ነገሮች በህጋዊ መንገድ ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኙ በልበ ሰፊነት ካልሰራን በስተቀር ጥፋት ነው ፤ ብንዋጋም ዘላቂ ድል አናመጣም " ብለዋል።

በአማራና ትግራይ ክልሎች የማንነትና የወስነ ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የወልቃይት አካባቢ አሁን ላይ #በኃላፊነት_ደረጃ እያገለገሉ የሚገኙት ኮሎኔሌ ደመቀ ዘውዱ ፤ ከሳምንታት በፊት የህዝበ ውሳኔ ጉዳይን በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።

በወቅቱም ፤ ' ሕዝበ ውሳኔ ' ተገቢም እውነትም ነው ብለው እንደማያስቡና ወልቃይት ጠገዴ በጉልበት ወደ ትግራይ የተጠቃለለ በመሆኑ፣ በሕግም በታሪክም ተጣርቶ ሕጋዊ ምላሽ ይሰጠናል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረው ነበር።

ኮሎኔል ደመቀ ፤ " ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው የተፈጸሙ በደሎችን እና ታሪካዊ እውነታዎችን ታሳቢ ያደረገ ፖለቲካዊ ውሳኔ ሲሰጥ ነው " ያሉ ሲሆን " እኛ ሕግን መሠረት አድርገን ነው የጠየቅነው፣ ከሕግ አንጻር ጉዳዩ ተዘርዝሮ መታየት አለበት። እየጠየቅን ያለነው ፣ የማንነት ጥያቄያችን ምላሽ እንዲያገኝ ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን ለደረሰብን በደልም ካሳም ጭምር ነው " ሲሉ ገልጸው ነበር።

ከዚህ በተጫማሪ ፤ የወልቃይት እና አካባቢው ጉዳይ ከውይይት ውጭ በሆነ መንገድ ይፈታል ብለው እንደማያምኑ፤ ለአካባቢው ጦርነትና ግጭት መፍትሄ እንደማይሆንም አስገንዝበዋል።

በወልቃይት ጉዳይ ከትግራይ ክልል አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ያላቸው እንደሆነም ተጠይቀው ፤ " ጉዳያችን ሊያልቅ የሚችለው በመነጋገርና በመወያየት ብቻ ነው ፤ በጉልበት የሚያልቅ ነገር የለም። እኛ ብቻ አይደለንም መላው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ፣ መላው የአማራ ሕዝብ ሊነጋገር ይገባል እንዲሁም የትግራይ እና የአማራ ሕዝብም ተገናኝቶ መነጋገር ይገባዋል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

@tikvahethiopia
በአዳዲሶቹ የድሕረ-ክፍያ ሞባይል ጥቅሎቻችን ያለገደብ ይጠቀሙ!

በወርሃዊ፣ የ6 ወራት እና የ2 ዓመት አማራጮች እስከ 35% በሚደርስ ቅናሽ የቀረቡትን የድሕረ-ክፍያ የሞባይል ጥቅሎች አስቀድመው በቴሌብር ሱፐርአፕ ወይም በአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በመግዛት ብዙ ያተርፋሉ!

በሁሉም አቅጣጫ ተደራሽ የሆነ ኔትወርክ፤ ከተመጣጣኝ ዋጋ ጋር በማቅረብ ሁሌም በአብሮነት አለን!

(ኢትዮ ቴሌኮም)