TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SpecialForce

" የሁሉንም የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማደራጀው ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ነው " - ፌዴራል መንግሥት

የፌዴራሉ መንግሥት ፤ በሁሉም ክልል ያለውን የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንደገና የማደራጀቱ ስራ  " ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት " ሲባል የሚደረግ ነው ብሏል።

መንግሥት ፤ የዚህ ተግባር ዓላማ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም ያለ ሲሆን ስራውን ከሁሉም የክልል መዋቅር ጋር በመወያየት እና በመግባባት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ሲባል የሚሰራው ስራ በጥንቃቄ እንደሚመራው ፌዴራል መንግሥት ህዝቡ እንዲያውቀው ብሏል።

ከዚህ ቀደም የክልል ልዩ ኃይሎች በሀገሪቱ ወዳሉት ሌሎች መዋቅሮች እንዲገቡ ህዝብም ጭምር ሲጠይቅ ነበር ያለው የፌደራል መንግሥት በዚህ መሰረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደጀመረ አመልክቷል።

በልዩ ኃይል ውስጥ ያሉ አባላት እንደምርጫቸው / እንደ ፍላጎታቸው ፦
- በሀገር መከላከያ ሰራዊት
- በፌዴራል ፖሊስ
- በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ። ወደነዚህ የፀጥታ መዋቅሮች የሚቀላቀሉት ትጥቃቸውን እንደያዙ ነው ተብሏል።

በዚህ ውስጥ መካተት የማይፈልጉ የልዩ ኃይል አባላት መብታቸው እንደሚጠበቅ እና ወደ መደበኛ ሲቪል ህይወት እንደሚገቡ መንግሥት የማቋቋም ስራ እና ድጋፍም እንደሚያደርግ የፌዴራል መንግሥት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢፍጣራችን ለወገናችን " ሶስተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የፊታችን ቅዳሜ ዕለት / ረመዳን 17 ይከናወናል ተብሏል። የዘንድሮው ኢፍጧል " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። የቅዳሜው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት ጉዳት ያደረሰባቸዉና የተቸገሩ ወገኖቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ በሰጡት መግለጫ…
#ረመዷን

" ኢፍጣራችን ለወገናችን "

ምዕመናን ነገ መጋቢት 30 በአዲስ አበባ በሚካሄደው " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ' ሲመጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ደንቦች አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል።

1. የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ፍተሻ ትብብር ማድረግ፤

2. የሰላት መስገጃ ይዘው ይምጡ፤

3. ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ተደርጓል። ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲያሳውቁ።

5. የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅር እና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበው ህብር ብሄራዊ አንድነነቱን በማሳየት ለሃገር ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

6. በዕለቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ ለተቸገሩ ወገኖች የሚሆን ፦
- እንደ ፉርኖ ዱቄት፣
- ሩዝ ፣
- ፓስታ፣
- መኮረኒ፣
- ዘይት፣
- የበቆሎ እህል፣
- ምስር፣
- የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች፣
- የሕፃናት አልሚ ምግቦች
- የንጽህና መጠበቂያ፣
- አልባሳት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይዞ መምጣት ይቻላል።

(ከአዘጋጆቹ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የክልል ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር ነው " - መንግስት መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ የሚያስችል አንድ ጠንካራ የተማከለ ሠራዊት ለመገንባት አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። በዚህ መሠረት የየክልሉን ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ…
#SpecialForce

" የክልል ልዩ ኃይሎች ከስመው በህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መጠቃለላቸውን እንደግፋለን " - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ፌደራልና የክልል ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ የማስገባት በጎ ጅምር አላስፈላጊ ውዥንብር ፈጥሮ ሌላ ሀገራዊ አደጋ እንዳይጋብዝ ጥንቃቄ ይፈልጋል ሲል አሳሰበ።

ፓርቲው ይህ ውሳኔ ከመዘግየቱ በስተቀር ተገቢነቱ ላይ ጥያቄ ሊነሳበት አይገባም ብሏል።

ባለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ከሕጋዊ አሠራር ውጪ እንዲቋቋሙ የተደረጉ የክልል ልዩ ኃይሎች በፌደራል መንግሥት የፀጥታ ዕዝ ሥር እንዲገቡ መደረጉ ተገቢም ልክም ሲል አቋሙን ገልጿል።

ፓርቲው የዘውግ ፖለቲካ ነፀብራቅ የኾኑ የክልል ልዩ ኃይሎች እየፈጠሩ ከነበረው ሀገራዊ አደጋ አንፃር ከስመው ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ እንዲገቡ ከዚህ በፊህ አቋሙን በተለያዩ ሁኔታዎች እና መድረኮች ላይ ሲያሳውቅ እንደነበር አስታውሷል።

የዚህ አቋሙ እና ስጋቱ ትክክለኛነት የትግራይ ክልል ልዩ ኃይሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ በከፈቱት ጦርነት በገሃድ ተረጋግጧል ብሏል።

ለአንድ ዘውግ ወይም ክልል ብቻ ጠባቂ ሆኖ የሚቋቋም ልዩ ኃይል ሀገር እና ሕዝብ ላይ አደጋ እንደሚፈጥር የታየው በትግራይ ክልል ታጣቂዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተመሳሳይ ዝንባሌ እየተስተዋለ ነው ሲል ገልጿል።

" በአስተዳደር ወሰን ይገባናል ጥያቄ መነሻ የኦሮሚያ ፣ የሶማሌ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የአፋር እና የቤንሻንጉል ልዩ ኃይሎች አንዳቸው ከሌላኛው ጋር መጋጨታቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው " ያለው ኢዜማ " ይህ ሁኔታ አሁንም ድረስ በአንዳንድ ክልሎች መካከል እየቀጠለ ነው፡፡ ይህም ንፁሀን ዜጎችን ከመጉዳቱም ባሻገር የሀገር ሉዓላዊነት ላይ አደጋ ደቅኗል፡፡ " ብሏል።

በመሆኑም፤ ከሕግ አግባብ ውጪ በአንድ ክልል ወይም ዘውግ ጠባቂነት የተቋቋሙ የክልል ልዩ ኃይሎች ከስመው በህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መጠቃለላቸውን የምንደግፈው ተገቢ ውሳኔ ነው ሲል አቋሙን ገልጿል።

ፓርቲው ምንም እንኳን የክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መግባታቸውን ከልቡ የሚደግፈው ውሳኔ ቢሆንም አተገባበሩ ፈንጅ የማምከን ያህል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚፈልግ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ሁሉ አሳስቧል።

በተለይም በሀገሪቱ ሥር ከሰደደው የዘውግ ፖለቲካ ጡዘት አኳያ አፈጻጻሙ በተጠና መልኩ መሆን አለበት ብሏል።

ለአብነት " በቅርቡ ከአሸባሪነት መዝገብ እንዲፋቅ የተደረገው የህወሓት ቡድን በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን በኩል በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ሥር ያሉ አካባቢዎችን ስለማስመለስ እንደሚሠራ በስፋት እያስተጋባ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ይህንን ውሳኔ በጥድፊያ እና በድብቅ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር አደገኛ ውጤት እንደሚያመጣ የፌደራል መንግሥት ሊገነዘበው ይገባል " ብሏል።

" ህወሓት የታጠቃቸውን መሣሪያዎች መፍታቱ በግልጽ ባልታወቀበት ሁኔታ የትግራይ አዋሳኝ ክልሎች ዳግም የመወረር ስጋት ቢያድረባቸው የሚያስወቅስ አይደለም " ያለው ኢዜማ የውሳኔውን አፈጻጸም ቅደም ተከተል በተመለከተ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አስገንዝቧል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል። ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል። ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን…
#ነዳጅ

" ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ #በኤሌክትሮኒክስ_የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ገልጾ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም አሳውቋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ #ከሐምሌ_አንድ ጀምሮ #በአስገዳጅነት እንደሚተገበር ተጠቁሟል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በ " ቴሌ ብር " ውጤታማ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በ " ቴሌ ብር " ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አመልክቷል።

የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገንባቱንም አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር ደግሞ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያለ ሲሆን በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን ይፈታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ሲል አሳውቋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SpecialForce " የሁሉንም የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማደራጀው ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ነው " - ፌዴራል መንግሥት የፌዴራሉ መንግሥት ፤ በሁሉም ክልል ያለውን የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንደገና የማደራጀቱ ስራ  " ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት " ሲባል የሚደረግ ነው ብሏል። መንግሥት ፤ የዚህ ተግባር ዓላማ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም ያለ ሲሆን ስራውን ከሁሉም የክልል…
#SpecialForce

" ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " - ወ/ሮ ሰለማዊት ካሳ

መንግሥት እያካሄደ ያለው የልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀት መርሃ ግብር ትጥቅ ከማያስፈታት ጋር እንደማይገናኝ አሳወቀ።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " የሁሉንም ክልል ልዩ ኃይል አባላት መልሶ የማደራጀት ስራ ነው የሚሰራው እንጂ ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " ብለዋል።

የተጀመረው መልሶ የማደራጀት ሂደት የሀገር ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ፣ ከሀገር ውስጥ ሆነ ከውጭ የሚሰነዘርን ማንኛውም አይነት ጥቃት ከመከላከል አንፃር ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ለመገንባት የሚያስችል ዕድል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

" ህወሓትን በተመለከተ ፤ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ የመፍታት ሂደቱ ያለማወላወል የሚፈፀም ነው " ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት " ሂደቱ ከሌሎች ሀገራዊ እቅዶች ጋር የሚገናኝ አይደለም / የሚጣረስም አይደለም እራሱን ችሎ በራሱ መርሀግብር የሚከናወን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ይህንን ሂደት ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እየተከታተሉት መሆኑ መታወቅ አለበት ሲሉ አክለዋል።

ወ/ሮ ሰላማዊት የክልል ልዩ ኃይል አባላትን መልሶ ማደራጀት " በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ወቅት እየተተገበረ ያለ ነው " ያሉ ሲሆን ሂደቱ በጥንቃቄ እና በጋራ መግባባት እየተመራ ያለ ነው ሲሉ አሳውቀዋል።

በሂደቱ በሁሉም ክልሎች ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ በተለይ የፀጥታ ስጋት / የማህበረሰብ ጥያቄ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ሀገር መከለከያ ሰራዊት ሁሉም ቦታዎች ስምሪት ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ነው በዚህ ረገድ ክፍተት አይፈጠርም ብለዋል።

እየተካሄደ ባለው የመልሶ ማደራጀት ስራ በልዩ ኃይል ውስጥ ያሉ አባላት እንደምርጫቸው / እንደ ፍላጎታቸው ፦
- በሀገር መከላከያ ሰራዊት
- በፌዴራል ፖሊስ
- በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ ተብሏል።

ወደነዚህ የፀጥታ መዋቅሮች የሚቀላቀሉት ትጥቃቸውን እንደያዙ መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህ ውስጥ መካተት የማይፈልጉ የልዩ ኃይል አባላት መብታቸው እንደሚጠበቅ እና ወደ መደበኛ ሲቪል ህይወት እንደሚገቡ መንግሥት የማቋቋም ስራ እና ድጋፍም እንደሚያደርግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#አቢሲያን_ባንክ

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮዽያ ክልሎች አገልግሎት የሚሰጡ ወደ 20 የሚጠጉትን የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን በመጠቀም ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት ፦
- ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ፤
- ቼክ መመንዘርና ተቀማጭ ማድረግ፤
- የሃገር ውስጥ ሓዋላ፤
- ገንዘብ ማስተላለፍ እና እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ካርድ ባንኪንግና ሞባይል ዋሌት (ጊዜፔይ) ያሉ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላሉ፡፡

እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን ያማከለ ከወለድ ነጻ የቨርቹዋል ባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከሎቻችንም፣ በቅርንጫፎች የሚሰጡትን የተሟላ አገልግሎቶች ማግኘት ያስችላሉ፡፡

#BankofAbyssinia #Banking #BanksinEthiopia #VirtualBanking #ITM #MoneyTransfer #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ethiotelecom

በቴሌብር ሱፐርአፕ በአንድ ጊዜ ለበርካታ ሰዎች ገንዘብ መላክ ተችሏል !

በቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ገንዘብ ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ለመላክ የተቀባይ ቡድን በመፍጠር ለቡድኑ አባላት ተመሳሳይ ወይም የተለያየ የገንዘብ መጠን በአንድ ትዕዛዝ ለሁሉም እኩል ይልካሉ ጊዜዎን ድካምዎን ይቀንሳሉ!
ለሰራተኞችዎ ደሞዝ ክፍያ፣ ለወዳጅ ዘመድ ገንዘብ ሲልኩ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮችዎ ይጠቀሙበት ይወዱታል!

አዲሱን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ።

#ኢትዮቴሌኮም #ቴሌብር
#Tigray

በትግራይ ላሉ ዩኒቨርሲቲዎች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች አድርጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት በመቐለ አድርገዋል።

በትግራይ ክልል የሚገኙት አራት ዩኒቨርሲዎች ፕሬዝዳንቶች ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ የሚያሳይ ሪፓርት በመድረኩ አቅርበዋል፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ተቋርጦ የቆየውን የዩኒቨርሲቲዎች እና አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር የመምህራንና የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የትብብር መድረክ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሀና "በጦርነቱ የተጎዱ የወሎ፣ ወልድያ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የታየው ትብብር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚደገም" ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም ለጊዜው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች አድርጓል፡፡

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ድረስ መንገዶች ይዘጋሉ።

" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ፕሮግሙ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በሚካሄድበት ወቅት  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-  

- ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአራተኛ ክፍለ  ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከጎማ ቁጠባ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከአራት ኪሎ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia