TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
A_HRC_54_55_AdvanceUneditedVersion.docx
79.2 KB
#ETHIOPIA #UN

ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት እንዲቆም ስምምነት ከተፈረመ አንድ አመት ሊሞላው ቢቃረብም አሁንም ግፍ፣ የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው ሲል በተመድ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አሳወቀ።

ኮሚሽኑ የሰላሙ ሁኔታ አሁንም ያልተረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ባወጣው ባለ 21 ገጽ ሪፖርቱ ከህዳር 3 ቀን 2020 ጀምሮ በግጭቱ ውስጥ በተሳተፉ #ሁሉም_አካላት የተፈፀሙ መጠነ ሰፊ አሰቃቂ ድርጊቶችን አስፍሯል።

ከእነዚህም ውስጥ ፦
- የጅምላ ግድያ፣
- አስገድዶ መድፈር፣
- ረሃብ፣
- የትምህርት ቤቶች እና የህክምና ተቋማት ውድመት፣
- የግዳጅ / በኃይል ማፈናቀል እና የዘፈቀደ እስራት ይገኙበታል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሀመድ ቻንዴ ኦትማን ፤ " የሰላም ስምምነቱ መፈረሙ በአብዛኛው የመሳሪያ ድምፅ ጸጥ ያሰኘው ቢሆንም ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በትግራይ ያለውን ግጭት አልፈታም ወይም ምንም አይነት አጠቃላይ የተሟላ ሰላም አላመጣም " ብለዋል።

" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ የመብት ጥሰት እና በትግራይ እየተፈጸመ ያለ ግፍን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንዳሉት ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ያፋ ባደረገው ሪፖርት፤ የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ጥሰቶችን መፈፀም መቀጠላቸውን አመልክቷል። ይህም ስልታዊ የሆኑ አስገድዶ መድፈር፣ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃቶችን እንደሚያካትት አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት ሃይሎች ይፈፀማል ስላለው የሰላማዊ ዜጎች እስራት እና የማሰቃየት ድርጊትን በተመለከተ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።

በተጨማሪም ፤ በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ተወላጅ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶችን እንዳገኘ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እና ለጭካኔ ወንጀሎች የሚያጋልጡ ሁኔታዎች መኖራቸው በእጅጉ እንደሚያሳስበው አመልክቷል።

ይህ ሁኔት በኢትዮጵያ እንዲሁም በሰፊው ቀጣና መረጋጋት ላይ እንዲሁም በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ህፃናት ላይ እንድምታ እንዳለው ገልጿል።

https://www.ohchr.org/en/press-releases/2023/09/ethiopia-nearly-one-year-after-ceasefire-un-experts-warn-ongoing-atrocities

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሩስያ

ሩስያ ላልተወሰነ ጊዜ ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ወደ ውጭ መላክ አቆመች ፤ ይህ ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ይኖራል ተብሎ ተሰግቷል።

ሩስያ ፤ " የሀገር ውስጥ ገበያን ለማረጋጋት እንዲሁም የሀገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎትን ለማሻሻል " በሚል ከአራት የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት አባላት ውጭ ወደ #ሁሉም_ሀገራት የነዳጅ ምርቶችን ቤንዚን እና ናፍጣ መላክን ለጊዜው አግዳለች።

እገዳው ፦
- ቤላሩስ ፣
- ካዛኪስታን ፣
- አርሜኒያ እና ኪርጊስታን #አይመለከትም ተብሏል።

እገዳው " ጊዜያዊ ነው " የተባለ ሲሆን እስከመቼ እንደሚቆይ ሩስያ ያለችው ነገር የለም።

ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከው የናፍጣ ነዳጅ በቀን ወደ 900,000 በርሜል እንደሚገመት እና ሀገሪቱ በየቀኑ ከ60,000 እስከ 100,000 በርሜል ቤንዚን ወደ ውጭ እንደምትልክ የመንግስት የዜና ወኪሉ " ታስ " ዘግቧል።

የሩስያ የነዳጅ እገዳን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ #ሰላም

#ሰላም_ከሌለ_ሁሉ_ነገር_የለም!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" ... በምድር ላይ ሰላም ካልነገሰ በቀርን መቼም ምንም ነገር ሊሆን አይችልም። ሰላም ዓለምን የሚገዛ ነው ፤ ሰላም ከሌለ ሁሉ ነገር የለም። ሰላም ካለ ሁሉ ነገር አለ።

ለሰላም የሚሆን ዋጋ በዓለም ላይ አይገኝም። ብርም ይሁን ፣ ወርቅም ይሁን አልማዝም ይሁን #አይመጥነውም። ለሰላም የሚሆን ዋጋ አይመጥነውም ይሄ ሁሉ።

ሰላሙን የምናመጣው እኛው ነን ፣ የምናባርረውም እኛው ነን።

ሰላም በምድር መንገስ አለበት። ሰላም በምድር ካለ ሁሉም ነገር አለ ፦
- ሀብት አለ
- ትምህርት አለ
- ስልጣኔ አለ
- ድሃ በጉልበቱ፣ ሃብታም በሀብቱ ፣ የተማረም በእውቀቱ ሀገርን ያቀናል እራሱም ይኖራል።

ሰላም ከሌለ ሁሉም ነገር እንደሌለ የታወቀ ነው።

ስለ ሰላም #መጸለይ ምንጊዜም አስፈላጊ ነው። ሰላም በሶስት ፊደል የተወሰነች ብትሆንም ዓለምን #የምትገዛ ሰላም ናት። ሰላም ዓለምን ይገዛል ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚስተካከለው በሰላም ስለሆነ።

ስለ ሰላም ምንጊዜም ቢሆን #ሁሉም_ኢትዮጵያዊ በያለበት ጸሎት ማድረግ አለበት፤ በጸሎት ሁሉም ነገር ይገኛልና። "

የፎቶ ባለቤት፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው + ኢጃት (አዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል - ' የአእላፋት ዝማሬ ' - በኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ)

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡

በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።

#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡

የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡

Credit - Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበው 236.7 ቢሊዮን  ብር ነው። አጠቃላይ የ2017 በጀት (971.2 ቢሊዮን) በ2016 በጀት ዓመት ከጸደቀው የወጪ በጀት አንጻር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው  ተገልጿል። ዛሬ ከሰዓት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ምክር…
#Ethiopia

የደቡብ ክልል ፈርሶ እንደ አዲስ የተዋቀሩት #ሁሉም አዳዲስ ክልሎች በጀት የሚደለደልላቸው በነበረው የድሮ ቀመር እንደሆነ ተገልጿል።

ገንዘብ ሚኒስቴር #አዲስ_ቀመር የማዘጋጀት ምንም ስልጣን እንደሌለው ይህ ስልጣን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሆነ አመልክቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2017 በጀት ረቂቅን ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባብራሩበት ወቅት ስለ አዳዲሶቹ ክልሎች የበጀት ድልድል ቀመር ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

" ከደቡብ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ #የትኛው_ቀመር ነው ? የሚለው የምክር ቤቱ ስልጣን እንጂ የገንዘብ ሚኒስቴር ስልጣን አይደላም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

" አዲስ ቀመር በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የነበረው ቀመርና በፌዴሬሽን ም/ቤት በፀደቀው መሰረት ነው ገንዘብ ሚኒስቴር ድልድል የሚያደርገው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፥ ሁሌም የፌዴራል መንግሥት #ለክልሎች አጠቃላይ ምን ያህል በጀት ይመደብ ? በሚል ካለው አቅም አንጻር እንደሚያስቀምጥ አስረድተዋል።

አሁን የተበተኑት ክልሎች በደቡብ ክልል ስር አንድ ላይ በነበሩበት ጊዜ የወጣ ቀመር እንዳለ አስታውሰዋል።

አሁን እየተሰራበት ያለው ያ የቀድሞው ቀመር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ቀመሩ ምንድነው ?

አሁን እየተገበረ ያለው ቀመር የቀድሞው ደቡብ ክልል የነበረው በጀት ለአራቱ ክልሎች #ይከፋፈላል

መጀመሪያ ሲዳማ ሲወጣ ratio ተሰርቶ በዛ መንገድ ነው የተሰራው።

ደቡብ ምዕራብ ሲወጣም ratio ተሰርቷል።

ሌሎቹ ሁለቱም ሲወጡ ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ratio ተሰርቶ በዛ መንገድ ነው ድልድል የሚደረገው።

ይህ ደግሞ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት ነው የተካሄደው።

የነበረው ቀመር ማለት በአጭሩ ደቡብ ክልል በአንድ ላይ በነበረበት ወቅት ይመደብለት የነበረው በጀት በ ratio ለአዳዲሶቹ እንዲከፋፈል ይደረጋል።

አቶ አመህድ ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ቀመር ተገዛጅቶ ተግባር ላይ እስካልዋለ ይህኑን ተፈጻሚ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

" በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ህዝብ ቆጠራ አልቆ ፣ አጠቃላይ የeconomic census እና survey በሚገባ ተጠናቆ ፤ አዲስ ቀመር በሚዘጋጅበት ጊዜ እና የተሟላ ቀመር ሲኖር አዲሱን ቀመር መሰረት በማድረግ ተግባራዊ   ይደረጋል (የበጀት ድልድሉ) " ብለዋል።

አዲስ ቀመር #የማዘጋጀት_ስልጣን ደግሞ የገንዘብ ሚኒስቴር ሳይሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣን እንደሆነ ተናግረዋል።

በአዳዲሶቹ ክልሎች ከበጀት ጋር በተያያዘ ፤ " የበጀት እጥረት " የሚሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ ይታወቃል።

የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ መዘግየትና በአግባቡ አለመክፈልም በስፋትም ከአዳዲሶቹ ክልሎች የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia