TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰራዊቱ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየተቀየረ መሆኑ ተነግሯል።

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ በማዘጋጀት በአገልግሎት ላይ እያዋለ መሆኑን አሳውቋል።

ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ ሠሌዳ የቀየረ ሲሆን ከነሃሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሸከርካሪዎች ላይ በመለጠፍ አገልግሎት መጀመሩ ተገልጿል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አዲስ ሰሌዳ እንደሚደርስ ይፋ ሆናል።

የሰሌዳ / ታርጋ ቅያሪ የተደረገው በተለያየ ምክንያት የተቋሙ በርካታ ሰሌዳዎች ከተቋሙ እውቅና ወጪ በሌሎች እጅ በመገኘቱ ነው ተብሏል።

በመሆንም እነዚህ ከተቋሙ እውቅና ውጭ በሌሎች እጅ የገቡ ሰሌዳዎች ለህገ-ወጥ ተግባር እንዳይውሉ ለመከላከል ታሳቢ ተደርጎ ሰሌዳው መቀሩን ሚኒስቴሩ አስረድቷል።

የተቀየሩት ሰሌዳዎች የሠራዊቱን ተልዕኮ እና ግዳጅ መነሻ አድርጎ በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት #በኮድ ተለይተው የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል። #EPA

@tikvahethiopia
#ICS

የሕዝብ ተ/ም/ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ9 ወር አፈጻጸም ትላንት ገምግሟል።

ኮሚቴው ከዚህ ግምገማ በፊት ማለትም ሚያዚያ 3/2016 ላይ #ድንገተኛ ምልከታ አድርጎ ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

- ምንም እንኳ የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና የተገልጋይን ቅሬታ መፍታት አልተቻለም።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ብለው በሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ምክንያት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ በድንገተኛ ምልከታ መመልከት ተችሏል።

- በዋና መ/ ቤቱ ተገልጋይ በተቋሙ ሠራተኞች ፦
➡️ #መሰደብ
➡️ #መመናጨቅ
➡️ #መገፍተር_ጭምር የሚደርስበት በመሆኑ ተገልጋይ በሥነ ምግባር መስተናገድ አለበት።

- በአዲስ አበባ " ካሳንቺስ አካባቢ " የሚገኘዉ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ምቹ ያልሆነ እና የንጽህና ጉድለት ያለው ነው። ይህ መታረም አለበት።

- ዋናው መስሪያ ቤት ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ፣ ሕንፃው የቆየ እና አስፈላጊዉን የማሻሻያ ጥገና ያላገኘ ነው። ሕንፃው ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስሪት ያለው ነው።

- በዋና መስሪያ ቤት ያለው መጨናነቅ እንዲቀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ከአምስት ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ የመፍትሔ ሃሳብ ቢሰጥም አልተፈጸመም። በተለይ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማስፋፋት ሥራዎች መሠራት አለበት።

- የደላላ ሰንሰለት በመለየት ማቋረጥ ያስፈልጋል።

- አሁንም ከደላሎች ጋር የሚመሳጠሩ የተቋሙ #ሠራተኞች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት።

- የሠራተኛ ባጅ አለመኖሩም ሊታሰብበት ይገባል።

በምክር ቤቱ የተገኙት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/EPA-04-27-2 #EPA

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹

" ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት ትከታተላለች አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ተገቢውን ምላሽ ትሰጣለች " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ልዩ ትኩረት ይሰጣል " ሲሉ ጠቁመዋል።

" ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ በበጎ መንፈስ የተቃኘ ዘላቂ ዲፕሎማሲ ላይ አተኩራ ትሰራለች "ም ብለዋል።

" የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴም ሊቆም ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።

አምባሳደር ነቢያት ፥
➡️ ከአውሮፓ ህብረት፣
➡️ ከአሜሪካ
➡️ ከተመድ ልዩ መልዕክተኞች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቁመዋል።

" ለሁሉም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ሆኖ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል " ብለዋል። #EPA

@tikvahethiopia