TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር መግለጫቸው ይበልጥ ትኩረቱን ያደረገው በሕገወጥ የሐዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በሚመለከት ነው። በመግለጫቸው ምን አሉ ? - 391 የሚደርሱ ሕገወጥ የሐዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው ተዘግቷል ፤ የግለሠቦቹን ስም ዝርዝር ለፍትሕ ሚኒስቴር በመላክ ክስ የመመስረት ሂደት ይጀመራል። …
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ፦

- ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ደረጃ ከ100 ሺህ ብር በላይ ለድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸወል።

- ገንዘብ በባንክ መቀመጥ አለበት ፤ የግብይት ስርዓትም በባንክ ማካሄድ ይቻላል።

- መመሪያው ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ አስቀምጦ የተገኘን አካል #የጠቆመ ግለሰብ 15 በመቶ የወረታ ክፍያ ይከፈለዋል።

- በውጭ አገራት ገንዘብ ግብይት መፈጸምም ሆነ በህገወጥ መንገድ ይዞ መገኘት አይቻልም።

- ወርቅን በህገወጥ መልኩ ቤት ውስጥ ማከማቸት የማይቻል ሲሆን በህገወጥ መልኩ ወርቅን ያከማቸ ግለሰብ ለጠቆመ ግለሰብ ባንኩ በወቅቱ ባለው ግብይት የ15 በመቶ ወረታ ይከፈለዋል።

- በህገወጥ የሃዋላ የውጭ አገራት የተሰማሩ አካላትን ለጠቆመም እስከ 25 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።

- በህገወጥ ገንዘብ ህትመት የተሰማሩ አካላትን ያጋለጠም ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።

- ጠቋሚዎች ወረታውና ሽልማቱ የሚበረከትላቸው #ደህንነታቸው እና #ሚስጥራዊነታቸው በተጠበቀ መልኩ ነው።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
እባካችሁ አሽከርካሪዎች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ !

ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ " አምቦ መስክ " ቀበሌ አቅጣጫውን ከባህር ዳር ወደ ማርቆስ ያደረገ ሰሌዳ ቁጥር " አማ 17492 " የሆነ ተሽከርካሪ ወይም ኮስትር ተሽከርካሪ እና መነሻውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ያደረገ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በተሳፋሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የሰሜን ሜጫ ወረዳ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ግጭቱ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት መፈጠሩን ገልጿል።

በዚህ ወቅት ከአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ ስላለ አሽከርካሪዎች በተገቢው ፍጥነት በማሽከርከር እራሳቸውን እና ተሳፋሪውን ከትራፊክ አደጋ እንዲታደጉ የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አሳስቧል።

ምንጭ፦ የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ ቤት እና የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA አምባሳደር ማይክ ሐመር ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ወደ ኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና #ኢትዮጵያ ጉዞ ያደርጋሉ። የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2022 ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ እንዘሚጓዙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አሳውቋል። ሐመር ወደ ቀጠናው የሚመለሱት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆምና…
#Update

አምባሳደር ማይክ ሐመር ኬንያ ይገኛሉ።

የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተነጋግረዋል።

ፕሬዜዳንት ሩቶ ከአሜሪካው አምባሳደር ሐመር ጋር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ " ሰላምና መረጋጋት ለአገሮች ልማትና ብልፅግና የግድ አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን ኬንያ ፤ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም እና ደህንነት የምታደርገውን ድጋፍና ቁርጠኝነት ታደንቃለች ብለዋል።

ከቀናት በፊት አሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሐመርን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆምና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ እንደላከች ማሳወቋ ይታወሳል።

በሌላ መረጃ አፍሪካ ህብረት በህብረቱ የሚመራና በደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለህወሓት ግብዣ አቅርቦ እንደነበርና በሁለቱም በኩል ግብዣው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል ፤ የሰላም ንግግሩን በተመለከተ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ሁለቱም ወገኖች ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበው፤ ንግግሩን የሚመሩት እነማን እንደሆኑ ይፋ አድርገዋል።

የሰላም ንግግሩ ፤ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ እንደሚመራ ገልፀዋል።

የሰላም ንግግሩን የሚመሩት አካላት ሰፊ ልምድና የአመራር አቅማቸውን በመጠቀም ሁሉን አሳታፊ የሆነ ገንቢ ውይይት ማድረግ እንደሚያስችሉ ሙሉ መተማመን እንዳላቸው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU

በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የሰላም ንግግር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙን ሮይተርስ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ቀጠሮ የተያዘለት የሰላም ንግግር መራዘሙ ከሎጂስቲክስ ዝግጅት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸው እስካሁን አዲስ ቀን እንዳልተቆረጠ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በአፍሪካ ህብረት የቀረበውን  የሰላም ንግግር ግብዣ መቀበላቸው እና የሰላም ንግግሩ ከነገ ጥቅምት 8/2022 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#GoE

የኢትዮጵያ መንግስት፤ የኢትዮጵያ ወዳጆች ወይም " የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ህገመንግስት እናከብራለን " የሚሉ ወገኖች ከሰላም ንግግሩ ጋር በተያያዘ የቃላት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረጉ አሳሰበ።

ፌዴራል መንግስት ማሳሰቢያውን ያወጣው በስሩ ባለው የ " ወቅታዊ ሁኔታዎች መረጃ ማጣሪያ " በኩል ነው።

የመረጃ ማጣሪያው እንደ " የትግራይ መንግስት (Government of / state of Tigray " ወይም ፣ " የትግራይ የውጭ አገልግሎት / Tigray External Service " የመሳሰሉ አገላለጾች ተራ ስህተቶች ሳይሆኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው ሊፈተሹ ይገባል ብሏል።

የኢትዮጵያ ወዳጆች ወይም " የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ሕገ መንግሥት  እናከብራለን " የሚሉ ወገኖች ሁሉ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት በቅርቡ በሚደረገው የሰላም ንግግር ሕገ-ወጥ ቃላትን / አገላለፅን ከመጠቀም ይቆጠቡ ሲል አስገንዝቧል።

" ከዚህ የሰላም ንግግር አንፃር ወዳጆቻችን እና አጋሮቻችን ማስታወስ ያለባቸው ሁለቱ ወገኖች በመሰረታዊነት ልዩነት ያላቸው መሆኑን ነው " ያለው ይኸው የመረጃ ማጣሪያ ፤ " አንዱ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ህጋዊ መንግስት እና ሌላኛው ' ህወሓት ' የታጠቀ ቡድን ነው " ብሏል።

እንደዚሁም እንደ " የትግራይ አስተዳደር / Tigray Administration " ወይም " የትግራይ ክልል መንግስት / Regional Government of Tigray " የመሳሰሉ አገላለፆችም ተቀባይነት የላቸውም ሲል አሳውቋል።

ምክንያት ያለውም ፤ " በትግራይ ክልል ውስጥ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠ አካል ስለሌለ ነው " ሲል አስረድቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እባካችሁ አሽከርካሪዎች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ! ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ " አምቦ መስክ " ቀበሌ አቅጣጫውን ከባህር ዳር ወደ ማርቆስ ያደረገ ሰሌዳ ቁጥር " አማ 17492 " የሆነ ተሽከርካሪ ወይም ኮስትር ተሽከርካሪ እና መነሻውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ያደረገ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በተሳፋሪዎች…
" ተማሪዎቹ በሰላም ገብተዋል "

ዛሬ " የሰሜን ሜጫ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን " እና " የመራዊ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት " ትላንት በአምቦ መስክ ቀበሌ ከባህር ዳር ወደ ደብረ ማርቆስ ያደረገ ኮስተር ተሽከርካሪ እና #ከሰከላ_ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዌችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ተጋጭተው " ከቀላል እስከ ከባድ " ጉዳት መድረሱን አሳውቀው ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መዝገቡ ስመኘው ለብስራት 101.1 ሬድዮ ጣቢያ በትራፊክ አደጋው የተጎዱ ሌሎች ሰዎች መኖራቸውን እና በተማሪዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት መካከል በ5 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱንና ፈተና ላይ ከመቀመጥ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

ዛሬ ከሰዓት ደግሞ  የሰከላ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ አድማስ  የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ በነበረው የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ፤ " የትራፊክ አደጋ የደረሰ ቢሆንም በተማሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም " ብለዋል።

ተማሪዎቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው ሌላ መኪና ተቀይሮላቸው በሰላም ወደተመደቡበት መግባታቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።

ወላጆች ክስተቱን በመስማት እንዳይደነግጡ እና ተማሪዎችን ለማግኘት በሚል አላስፈላጊ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ  መልዕክቱን የማዳረስ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።

በተጨማሪ ፤ የሰከላ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እሱባለው መንግስት ፤ በትራፊክ አደጋው ተማሪዎች ተጎዱ ተብሎ የተሰራጨው ስህተት ነው ብለዋል።

ተማሪዎችን ይዞ የነበረው ቅጥቅጥ አይሱዙ መንገድ ከመልቀቅ ፣ ፍሬቻና ስፖኪዮው ከመጎዳት ውጭ ጉዳት አልደረሰበትም ብለዋል። ተማሪዎች ላይ ቀላል የሚባልም ጉዳት እንዳልደረሰ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዛሬ ጥዋት መረጃውን ለህዝብ ያሰራጩት የሰሜን መጫ መንግስት ኮሚኒኬሽ እና የመራዊ ኮሚኒኬሽን ከማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ምንም ነገር ሳይሉ #መረጃውን_ማጥፋታቸውን ተመልክቷል።

ዋናው የተማሪዎቹ ሰላም መሆንን እና ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ነው ፤ የተለያዩ የኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ለህዝብ የሚያሰራጩትን መረጃ እንዲናበብ ማድረግ እንዲሁም ትክክለኛውን ሁኔታ በዝርዝር አረጋግጠው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

መሰል የመረጃዎች ስርጭት ቤተሰቦችንም የሚረብሽ በመሆኑ በመንግስት የኮሚኒኬሽን አካላት የሚሰጥ መረጃ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል።

ከዚህም ባለፈ ፤ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ተቋማት የማድረስ ስራ እየተሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የትራፊክ እንቅስቃሴው በእጅጉ ጨምሯልና አሽከርካሪዎች ከምን ጊዜው በላይ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘነጉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የሰላም ንግግር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙን ሮይተርስ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ቀጠሮ የተያዘለት የሰላም ንግግር መራዘሙ ከሎጂስቲክስ ዝግጅት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸው እስካሁን አዲስ ቀን እንዳልተቆረጠ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በአፍሪካ…
ኡሁሩ ኬንያታ ምንድነው ያሉት ?

በደቡብ አፍሪካ ነገ ሊጀመር የነበረው የሰላም ንግግር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙን የዲፕሎማቲክ ምንጮች መግለፃቸው ይታወቃል፤ ይህ ውይይት መቼ ይደረጋል የሚለው እስካሁን ቀን አልተቆረጠለትም።

የሰላም ንግግሩን እንደሚመሩ የተነገረላቸው አንዱ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ነገ ታስቦ ለነበረው የሰላም ንግግር ደ/አፍሪካ መገኘት እንደማይችሉ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ደብዳቤ ፅፈዋል።

(ይህ ደብደቤ ከመውጣቱ በፊት የሰላም ንግግሩ መራዘሙ ተነግሯል)

ኡሁሩ ኬንያታ ለሙሳ ፋኪ በፃፉት ደብዳቤ ፦

ነገ በደቡብ አፍሪካ ይጀመራል ተብሎ በነበረው የሰላም ንግግር መድረክ መገኘት አልችልም ብለዋል። በቦታው እንደማይገኙ የገለፁት ሌላ በተመሳሳይ ቀን የያዙት ሥራ ስለነበር መሆኑ አስረድተዋል።

ኬንያታ ፤ ሌላ የንግግር ቀን እስኪወሰን ድረስ ፣ ኅብረቱ ስለ ሰላም ንግግሩ ቅርጽ፣ አካሄድና አወያዮች መከተል ስላለባቸው ደንቦች ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ኡሁሩ በደብዳቤው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ ከንግግሩ ከአጀንዳዎች ሁሉ ቀዳሚው እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸው ፤ ይህም የሰዎችን ስቃይ በማስቆም ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ ከማስቻሉ ባሻገር ለንግግሩ ትክክለኛውን ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

ነገር ግን ፤ ኡሁሩ ኬንያታ በሰላም ንግግሩ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደማይሳተፉ / እራሳቸውን እንዳገለሉ ተደርጎ የሚሰራጩት መረጀዎች ስህተት ናቸው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ነገ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል መክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ዘጠኝ (9) ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎቹ በሰላም ገብተዋል " ዛሬ " የሰሜን ሜጫ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን " እና " የመራዊ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት " ትላንት በአምቦ መስክ ቀበሌ ከባህር ዳር ወደ ደብረ ማርቆስ ያደረገ ኮስተር ተሽከርካሪ እና #ከሰከላ_ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዌችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ተጋጭተው " ከቀላል እስከ ከባድ " ጉዳት መድረሱን አሳውቀው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ፤…
" ተማሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተርፈዋል ፤ ወላጆችም ተረጋጉ " - የሲግሞ ወረዳ

ዛሬ በጅማ ዞን ፤ ከሲግሞ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ስጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ነበር።

ነገር ግን ተማሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውን የወረዳው አስተዳደር አሳውቋል።

የተማሪ ወላጆችም ይህንን በማወቅ እንዲረጋጉ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የሲግሞ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን / ሱልጣን ኢብራሂም / ነው።

በዚህ አጋጣሚ ወቅቱ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ከማድረስ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በመኖሩ አስሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እና በእርጋታ እንዲያሽከረርክሩ በድጋሜ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#Gambella

" የአካባቢው ማህበረሰብ በተቻለው አቅም እራሱን እንዲጠብቅ አደራ እንላለን " - የጋምቤላ ክልል መንግስት

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ሲገድሉ ፤ አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ አፍነውን ወስደዋል።

የጋምቤላ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን እንዳሳወቀው በቀን 26/01/2015 ዓ/ም ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ ላይ በኑዌር ዞን ፤ በማኮይ ወረዳ በሎንጆክ ቀበሌ የሙርሌ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው 3 ሰዎችን ሲገድሉ፤ አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ አፍነው ወስደዋል።

ይህ ድርጊት የተፈፀመበት ቦታ " ጎርፍ ካጠቃቸው " ቦታዎች አንዱ ሲሆን ህብረተሰቡን የማረጋጋት እና ታጣቂዎች ለመያዝ እየተሰራ መሆኑን ክልሉ አሳውቋል።

የክልሉ መንግስት ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ በተቻለው አቅም እራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጊዜ ድንበር ጥሰው እየገቡ በኑዌር ዞን እና አኝዋሃ ዞን በሰው ህይወት ላይ አደጋ ሲያደርሱ እና በርካታ ከብቶችንም ዘርፈው ሲወስዱ ቆይተዋል።

@tikvahethiopia