TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል። የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል። ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል። …
ነዳጅ 📈
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ፦
- ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ማስተከከያ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ማለትም የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ ባሉበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።
በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።
ሚኒስቴሩ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ፦
- ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር
- ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ብሏል።
ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኢብኮ
@tikvahethiopia

#ProfMesfinWoldemariam
የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መታሰቢያ እና ዓመታዊ ኮንፈረንስ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ/ም ሊካሄድ ነው።
የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን በላከልን መልዕክት ፤ መስከረም 22 ቀን 205፣ ከ7፡30 አንስቶ ለግማሽ ቀን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ " እሸቱ ጮሌ አዳራሽ " በርካታ እንግዶች በተገኙበት ታላቅ ጉባዔ ይካሄዳል ብሏል።
" የተመራማሪ፣ መምህር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ እና የፍትሕ ተቆርቋሪ በሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ስም የተመሰረተው ፋውንዴሽን በሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተመዝግቦ በሕጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል " ሲል ፋውንዴሽኑ አስታውሷል።
የድርጅቱ ዋና ዓላማ ከችግርና ድህነት የተላቀቀች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ብሏል።
ፋውንዴሽኑ ዓላማውን ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሰብዓዊ መብትና ማሕበራዊ ፍትሕ፣ አገራችን ከድህነትና ችጋር ልትላቀቅ ስለምትችልበት መንገዶች፣ ቅራኔን በሰላማዊ መንገድ ስለመፍታት፣ በመስኩ ሰፊ የሆነን ልምድ እና እውቀት ባካባቱ ሰዎች ጥናታዊ ወረቀት በማቅረብ ሰፋ ያለን ውይይት በዓመታዊው ጉባኤ ማካሄድ ዋነኛው ነው ሲል ገልጿል።

#Bishoftu #Mojo #Debrebrihan ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መጀመሩን አሳውቋል። ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር #ስምንት የሚያደርሰው ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር እና አዳማ ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል። ደንበኞች…
#Awaday #Gondar
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እያካሄደ የሚገኘውን የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል።
ዛሬ በተላከልን መልዕክት ፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች አስጀምሯል።
ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር 10 አድርሶታል። ከዚህ በፊት በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ላይ ሙከራ መጀመሩ ይታወቃል።
የአወዳይ እና ጎንደር ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
በአወዳይ አንድ በቀበሌ ዐ1 የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር እና በጎንደር አራት (በፒያሳ፣ አራዳ፣ አዘዞ እና ኮሌጅ) የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው ሲል በላከልን መልዕክት አሳውቋል።

#ጥቆማ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ፦
- በኮምፒውተር ሳይንስ፣
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣
- ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም እና ተዛማጅ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ተማሪዎች #በልዩ_ሁኔታ የስራ ቅጥር ለመፈፀም ማስታወቂያ አውጥቷል።
በሶፍትዌር ልማት ላይ ልዩ ተሰጥኦ ወይም አቅም ያላቸሁ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን መሰረታዊ መረጃችሁን የያዘ ሲቪ (CV) ከሁለት /2/ ገፅ ያልበለጠ እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም እንድታያይዙ ተቋሙ ጠይቋል።
https://www.insa.gov.et/web/guest/vacancy
@tikvahethmagazine

#MadingoAfework የተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ይፈፀማል። ስርዓተ ቀብሩ 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ነው የተነገረው። የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ሲሆን የኮሚቴው ቃል አቀባይ ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን " የቀብር ሥነ ስርዓቱ ሐሙስ ዕለት በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል። ከቀብር…
#ተፈፀመ
የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥተ ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።
ከሥርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ዘመድ ወዳጆች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በመኖሪያ ቤቱ እና በወዳጅነት ዐደባባይ የአስከሬን ሽኝት ተካሂዷል፡፡
በመንበረ ጸባኦት ቅድሥተ ሥላሴ ካቴድራል በነበረው የቀብር ስነሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ፣ የድምፃዊው ቤተሰቦች ፤ የስራ ባልደረቦች ፣ ጓደኞች ፣ ወዳጆች ፣ አድናቂዎች ተገኝተው ነበር።
መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ/ም ህመም ተሰምቶት ወደ አንድ ክሊኒክ ከሄደ በኃላ ህይወቱ ያለፈው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የአንዲት የ17 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር።
ከድምፃዊ ማዲንጎ አፈወትቅ ህልፈት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ መግለፁ አይዘነጋም።

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ አርብ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እሁድ መስከረም 22/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ ተከልክሏል።
የሞተር እንቅስቃሴ የተከለከለው ከነገ ወዲያ ቅደሜ መስከረም 21/2015 ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ ነው።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማነጅመንት ኤጀንሲ ፤ " ለኢሬቻ በዓል በሁሉም የከተማድ መግቢያ በሮች የሚገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች ስለሚኖሩ ለጋራ ደህንነት፣ ሰላም እና ጸጥታ ሲባል ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴን መገደብ አስፈልጓል " ብሏል።
የተጣለውን ገደብ ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ የእርምት ርምጃ ይወሰዳል ሲልም አሳስቧል።