TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በ2 ጎን ፅንፍ ተይዞ እየተደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት በጣም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው " - የቆቦ ነዋሪ

በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎችና ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች መሬት ላይ ያለውን እና ቀጥተኛ የጦርነት ገፈጥ ቀማሽ የሆነውን ማህበረሰብ እየጎዳ ነው።

አንድ ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ ከቆቦ ደሴ ተፈናቅለው የገቡ የቆቦ ነዋሪ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚሰራጨው መረጃ መሬት ላይ ካለው ሀቅ እንደማይገናኝ ገልፀዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው የፉክክር ጉዳይ ነው የሚመስለው " ያሉ ሲሆን ለአብነት ቆቦ ተለቀቀች ተብሎ የሚሰራጨው ሀሰት እንደሆነና የህወሓት ታጣቂዎች በከተማው እንዳሉ ይህን እዛው ካሉ ቤተሰቦቻቸው እንደተገለፀላቸው አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ወቅትም የፉክክር እና የውድድር ነገር ነው ያለው በሰው ሀብት፣ በሰው ነፍስ፣ በሰው ንብረት ጨዋታ የተያዘ ነው የሚመስለው ሲሉ የማህበራዊ ሚዲያውን ሁኔታ ገልፀዋል።

እኚሁ የቆቦ ነዋሪ በ2 ጎን ፅንፍ ተይዞ እየተደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት በጣም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ፤ ለአብነት ቆቦ በመንግስት ኃይል ስር ገብታለች ተብሎ ከተነገረበት ሰዓት ጀምሮ ብዙ ተፈናቃይ ወገኖች እንመለስ የሚል የእግር ጉዞ ጀምሮ ነበር ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ትክክለኛ መረጃ እንዳይገኝ እና ህዝቡ እራሱን እንዳያደራጅ እያደረገው ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ፤ " ያልተያዘውን ተይዟል፤ በዚህ ገቡ፣ በዚህ ወጡ " በሚል ህዝብ ተሸብሮ ንብረቱን ጥሎ እንዲፈናቀል ፣ ከተሞች እንዳይረጋጉ የሚያደርጉ አካላትም ቀጥተኛ የጦርነት ገፈጥ ቀማሽ ወገኖችን እየጎዱ በመሆናቸው ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ሲሉ አንድ የቤተሰባችን አባል መልዕክታቸውን ልከዋል።

@tikvahethiopia
" ገንዘብ ያለወጠው ህሊና "

በስህተት ወደ ሌላ ሂሳብ የገባ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለባለቤቱ መመልሱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገለፀ።

አቶ ሲሳይ ተስፋዬ በስልካቸው አንድ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡ በወቅቱ ሀሰተኛ መልእክት ስለመሰላቸው ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፡፡

በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ሲሳይ ዘመድም ወዳጅም ይህን ያደርጋል ብለው የሚጠብቁት ነገር ስላልሆነ በሂሳባቸው ብር 501,840.00 መግባቱን የሚናገረውን መልእክት ሀሰተኛ ነው ብለው አምነዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ሂሳባቸውን በኤ.ቲ.ኤም ሲያዩ ግን እውነትም ብር 501,840.00 ወደ ሂሳባቸው ገብቷል፡፡

አቶ ሲሳይ በጡረታ ዘመኔ ያገኘሁት ሲሳይ ነው ብለው አልተደሰቱም፡፡ ይልቁንስ በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑ ስለገባቸው የገንዘቡን ባለቤት ማፈላለግ ጀመሩ እንጂ፡፡

ወደ ባንክ በመሄድ የሂሳብ ዝርዝር አስወጥተው ገንዘቡን ወደ ሂሳባቸው ያስገባውን ሰው ስም አገኙ፣ የውጭ ሀገር ዜጋ  ነው፡፡

ስልኩን ከባንኩ ተቀብለው ደወሉለት፡፡ እውነትም በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑን አረጋገጡ፡፡ አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት መሆኑን ሲያረጋግጡም ገንዘቡን በታማኝነት መለሱ፡፡

ገንዘቡ ህይወታቸውን ሊለውጥ ቢችልም ህሊናቸውን ግን ሊለውጥ እንደማይችል የተናገሩት አቶ ሲሳይ፣ ገንዘቡን ሲመልሱ የተሰማቸው ደስታ ወደር የለውም፡፡

የሰው ገንዘብ በፍፁም እንደማይፈልጉ እምነታቸው አድርገው የኖሩት አቶ ሲሳይ፣ አጋጣሚው የሚሉትን በተግባር ሆነው ያገኙበት ሆኖ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ገንዘቡ በስህተት ገቢ የተደረገበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ቅርንጫፍ ለአቶ ሲሳይ ተስፋዬ ታማኝነት እና አራያነት ያለው ተግባር የምስጋናና የአድናቆት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡

#CBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION

ሰቆጣ !

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ  ሁኔታ በማስመልከት ውሳኔዎችን አሳልፏል።

- ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- ከጸጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- ማህበረሰቡን የሚያውኩ የሃሰት አሉባልታዎች / የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ተከልክሏል።

- ተፈናቃዮች ከተሰጣቸው የመጠለያ ካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ በብቅ ተከልክሏል።

- ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴል እና መስል የመንግስትና የግል ድርጅቶችን መዝጋት በጥብቅ ተከልክሏል።

- በከተማው የሚገኙ የመንግስትና የግል ታጣቂዎች መንግስት በሚያሰማራው የፀጥታ ስራ ላይ ተሳታፊ የመሆን ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

- ማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ  ተጠቃሚ ግለሰብ ሆነ ድርጅት የትኛውንም  ሚዲያ ተጠቅሞ የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፣ በተለይ ስለጦርነቱ አሉቧልታ መዘገብ ሆነ መግለጫ መስጠት በጥብቅ ተከልክሏል።

- ማንኛውም የቤት አከራይ ወይም አልጋ ቤቶች ተከራዮቻቸውን የመለየትና የገለሰቦቹን ማንነት የሚለይ ህጋዊ መታወቂያ ስለመያዛቸው የማረጋገጥ ግደታ አለባቸው።

- ማንኛውም የከተማው ማህበረሰብ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር የመቀናጀትና የመተባበር  ግዴታ አለበት።

እንዚህ በማይከብር ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ታዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ሰቆጣ ! የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ  ሁኔታ በማስመልከት ውሳኔዎችን አሳልፏል። - ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል። - ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።…
#ATTENTION

ኮምቦልቻ !

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የከተማድን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

- በከተማው አሉባልታ ማናፈስ በህብረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር የሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።

- በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የሚሰጡ  ታክሲዎች እስከ 11 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ተወስኗል።

- ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እረምጃ  እንዲወሰድ ታዟል።

- በምግብ ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎችና ግረሶሪዎች ከ11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት ተከልክሏል።

- DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

- የአልጋ አከራ ሆቴሎች፣ የመኖሪያ እና መደብ አከራዮችን አገልግሎት ሲሰጡ የተገልጋዩን ማንነት የሚገልፅ መረጃ በመያዝ አገልግሎት እንዲሰጡና መታወቂያ ኮፒ ማድረግ እንዳይዘነጉ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ለመረጃ እና ጥቆማ፦ በስልክ ቁጥሮች 0335510005
0335510945
0921038804 ላይ መደወል ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ኮምቦልቻ ! የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የከተማድን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ከውሳኔዎቹ መካከል ፦ - ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። - በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።…
#ATTENTION

ደብረ ብርሃን !

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

- በከተማው አስተዳደር በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ከምሽቱ 12:00  ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ተከልክሏል።

- ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- መጠጥ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 2:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

- የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ ተከልክሏል።

- ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ ተከልክሏል።

- ከመንግስት ዕውቅና ውጭ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ ተከልክሏል።

- አዳር የሚሰሩ በከተማው ያሉ ፋብሪካዎችና ድርጅቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ  መረጃ እና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዛ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላሉ።

- ህብረተሰቡን ለማሸብር አሉባልታ መንዛት፣ ወሬ ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ ነው ፤ መላው ማህበረሰብም አካባቢውን ቀንና ሌሊት በንቃት መጠበቅ አለበት።

- የሆቴል አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ገለሰብ በድርጅታቸው ውስጥ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንዲያሳውቁ ፤ በሌላ በኩል ፤ የቤት አከራዮች የሚያከራዩትን ግለሰብ መታወቂያ በመጠየቅ፣ ፎርምም በመሙላት ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ እንዲያሳውቁ ተብሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
* አስቸኳይ

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስ/ር የሰቆጣ ከተማ አስ/ር ምክር ቤት የመንግስት እና የግል ባንኮች አገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያሻሽሉ በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

ሰቆጣ በርካታ ህዝብ የሚኖርባት እና ከ70,000 ሺህ በላይ ወገኖች ተፈናቅለው የባንክ አገልግሎት እያገኙ የሚገኙባት ከተማ ናት።

ነገር ግን ከላይ በደብዳቤው ስማቸው የተገለፀው (የኢትዮጵያ ንግድ ፣ አባይ፣ ዳሽን፣ አቢሲንያ፣ አንበሳ፣ አዋሽ፣ ቡና፣ ህብረት፣ አማራ፣ ፀደይ ባንኮች) በበሬ ወለደ ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ የባንክ አገልግሎት በተገቢ መንገድ እየሰጡ እንዳልሆነ በምክር ቤቱ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በሚል ሰበብ ህዝብ እንዲረበሽና እንዲሰጋ እያደረጉ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአሉባልታና የሚመለከተው የፀጥታ ምክር ቤት መረጃ ሳይጠይቅ ሆን ተብሎ ጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዲፈጠር በማደረግም ቢሮ ዘግተው አገልግሎት ማቋረጣቸውን ም/ቤቱ አሳውቋል።

ምክ/ቤቱ ባንኮቹ ከዚህ ተግባራቸው እንዲወጡ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ታሪካዊ ስህተት የፈፀሙ እና ህዝብን የካዱ ፣ የህዝቡ እንግልትና ስቃይ ላይ ተባባሪ መሆናቸውን ሊያውቁት ይገባል ሲል አሳስቧል።

ይህንን በመረዳትም አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ደብዳቤው ፦ ከሰቆጣ ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ደብረ ብርሃን ! የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል። - በከተማው አስተዳደር በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ከምሽቱ 12:00  ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ተከልክሏል። - ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።…
#ATTENTION

ላሊበላ !

የላሊበላ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ውሳኔዎቹ ፦

- ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ወደ ከተማዋ መግባትም ሆነ መውጣት አይቻልም።

- ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12:00 ድረስ መንቀሳቀስ አይቻልም።

- ከተፈቀደለት አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- በመንግስት ዕውቅና ካለው የፀጥታ አካል ውጭ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ በፍፁም አይቻልም።

የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ህዝቡ በሀሰተኛ ወሬ እና አሉባልታ ሳይደናገር አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰሜን አሜሪካ ደርሰዋል ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓመተ ምሕረት በወሰነው መሠረት ለሕክምና ሐምሌ 18 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ሰሜን አሜሪካን የተጓዙት ብፁዕ ወቅዱስነታቸው በትናንትናው ዕለት…
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
" የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋል " - አቶ መሐመድ እድሪስ

የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ፍቅር እና ሰላምን መስበክ እንዲሁም የአብሮነት እሴቶችን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ገለፁ።

ይህን ያሉት ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

አቶ መሐመድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃኑ ትውልድን በሃይማኖት መርሆዎች በመቅረጽ ለሰላም ግንባታ ሚናቸው የላቀ ነው ያሉ ሲሆን የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በአንዳንድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የሌሎችን ሃይማኖት አለማክበርና ማንቋሸሽ ይስተዋላል፤ ይህ አካሄድ ሊታረም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በዘላቂነት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሃይማኖት ሚዲያ ካውንስልን ለማቋቋም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መደረሱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተሸረሸሩ የመጡ እሴቶች መበራከትና በየቦታው የሚፈጠሩ ችግሮች የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የቤት ስራዎቻቸውን ላለመስራታቸው ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

" በርካታ አማኞች ያሉባት አገሪቱ የሚገዳደል እና መንገድ የሚዘጋ ትውልድ ተበራክቶባታል " ያሉ ሲሆን መገናኛ ብዙሃኑ ከመነቃቀፍ ይልቅ መደጋጋፍን እኛ እና እነሱ ከሚል የጥላቻ ትርክት በላይ አብሮነትን መስበክ አለባቸው ብለዋል።

ተገቢ ባልሆነ አካሄድ ውስጥ እየተጓዙ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ሰላምን እንዲሰብኩ እንመክራለን ያሉ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን በሕግ የሚጠየቁበት ሁኔታ መኖሩን አስገዝበዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች " - ዶ/ር ሁሴን አደም የህወሓት ኃይሎች በአፋር ያሎ በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸውም ውስጥ ወደ ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል መጥተው ህክምና የተከታተሉ…
" የህፃናት ህይወት ተቀጥፏል " - UNICEF

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ፤" አሁንም በድጋሚ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት የህፃናትን ህይወት ቀጥፏል " ብሏል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነ #የአፋር_ክልል መንደር የተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ህፃናትን ገድሏል ፤ በርካቶችንም ቁስለኛ አድርጓል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል።

UNICEF በኢትዮጵያ ላሉ ህፃናትና ለወደፊት ህይወታቸው ሲባል ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉም ወገኖች እንዲስማሙ ተማፅኗል።

UNICEF በመግለጫው ላይ ጥቃት የደረሰበትን የአፋር ክልል መንደር በግልፅ ባይሳውቅም ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች በአፋር " ያሎ " በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።

በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ዱብቲ ሆስፒታሉ እንደገቡና ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia