TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

በአዲስ አበባ ከተማ የላዳ  ታክሲዎችን በአዲስ ለመቀየር የሚያስችል ስምምነት በተሽከርካሪ አቅራቢና በባለንብረቶች መካከል በ2013 ዓ.ም ቢፈረምም ወደ ተግባር አለመግባቱ ብዙ ቅሬታ ሲያስነሳ ቆይቷል።

የመጀመሪያው ዙር የሚገጣጠሙ የላዳ ቅያሬ ተሽከርካሪዎች ግብዓቶች ወደ ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው የመገጣጠም ሥራው በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩ ተጠቁሟል።

በአጠቃላይ 10 ሺህ 500 መቶ የላዳ ቅያሬ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና ከአሽከርካሪ ማሕበራት ጋር ስምምነት መደረጉን የኤል አውቶ ኢንጂነሪንግና ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ አበበ አስታውሰዋል።

ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከሚገኘው ፋብሪካ በተጨማሪ የዱከሙ መገጣጠሚያ ፋብሪካም በቀጣይ ሳምንት መጀመሪያ ቀናት መኪናዎችን መገጣጠም እንደሚጀምርም ነው የገለጹት። ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅም ጥረት ይደረጋል ተብሏል።

አብዛኛዎቹ የላዳ ቅያሬ ተሽከርካሪዎች ባለ 7 ወንበር ያላቸው ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ገልጸው፤ የተወሰኑት ባለ 5 ወንበር ሲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎቹም አንድ ሺህ ሲሲ ጉልበት ያላቸው በመሆናቸው ለነዳጅ ቁጠባም አዋጭ ናቸው ብለዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተር አቶ ሙላይ ወልዱ በበኩላቸው ከቀረጥ ነጻ ዕድሉ መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችል የሕግ ዝግጅት በማስፈለጉ መመሪያው ተግባራዊ ሳይሆን ለተወሰኑ ወራት ዘግይቶ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ወደ ሚኒስቴሩም መጥተው የተመዘገቡ ከ200 በላይ የታክሲ ማሕበራት አሉ ያሉት ዳይሬክተሩ አስፈላጊውን መስፈርና ዶክመንት ያሟሉ ማኅበራት አገልግሎቱን እያገኙ ነውም ብለዋል።

Via EPA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት ዳግም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ድርጅቱ በላከልን አጭር መግለጫ ግጭቱ ዳግም መቀስቀሱን አውግዟል።

በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላት ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጡ አሳስቧል።

ከዚህም በተጨማሪ በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የንፀሐንን ዜጎች ህይወት እና ሰብዓዊ መብት በመጠበቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#NorthernEthiopia

በሰሜን ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል ዳግም ጦርነት ካጋረሸ በኃላ ሁኔታዎች ከመርገብ ይልቅ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ እንደሚገኙ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ።

ትግራይ ክልልን ከአማራ እና አፋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ አርብ በመቐለ የአየር ድብደባ እንደነበር እና በዚህም ሳቢያ ህፃናትን ጨምሮ እስካሁን አራት ሰዎች መሞታቸውን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሳውቋል።

ሆስፒታሉ ፤ የአየር ጥቃቱ ጉዳት ያደረሰው በህፃናት መጫወቻ ቦታ አካባቢ መሆኑን ገልጾ በጥቃቱ የተጎዱ እስከሁን 13 ሰዎች በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና ከነዚህ ውስጥ 4ቱ መሞታቸውን አመልክቷል። ከአራቱ 2ቱ ህፃናት መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት በመቐለ ከተማ የአየር ጥቃት ተፈፅሟል ይህን ተከትሎም ደርሷል ስለተባለው ጉዳት እስካሁን ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#Update

የፌዴራል መንግስት ፤ ዛሬ ከሰዓት ባስተላለፈው አስቸኳይ መልዕክት በትግራይ የሚኖሩ ወገኖች በተለይም የህወሓት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል።

የፌዴራል መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሬን ክፍት አድርጌ ብጠባበቅም ህወሓት ግን ጥቃቱን ቀጥሎበታል ብሏል።

የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ ለህወሓት የፀረ ሰላም እብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

በትግራይ የሚኖሩ ወገኖች ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፤ የፌዴራል መንግስት ከዚህ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ቀም ብሎ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ለሰላም የተከፈቱ በሮችን እየዘጋቸው ነው ብሏል።

የመከላከያ ኃይል ይዞ በቆየባቸው ቦታዎች አሁንም ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል ፤ መከላከያም የመንግስትን የሰላም አማራጭ በመያዝ በጥንቃቄ እየተከላከለ ነው ሲል ገልጿል።

በመግለጫው ፤ መንግስት ለሰላም ያደረገውን ጥረት በዝርዝር የገለፀ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ህወሓት ነዳጅ ዘራፊ ብቻ ሳይሆን ጠብ አጫሪ መሆኑን በመገንዘብ ሊያወግዘው ይገባል ብሏል።

" ሁለቱ ወገኖች " ከሚል ፍርደ ገምድል ጥሪ ተላቆ ህወሓት መንግስት ወደያዘው የሰላም አማራጭ እንዲመጣም ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ህወሓት ጥቃቱን የሚቀጥል ከሆነ መንግስት ማንኛውም እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Germany

• ጀርመን ከWFP መጋዘን ህወሓት የፈፀመውን በኃይል የነዳጅ ክምችት የመውሰድ ድርጊት " አፀያፊ " ስትል አወገዘች።

የጀርመን መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ለ5 ወራት የዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱና ጦርነቱ እንደገና መጀመሩ በእጅጉ እንዳሳዘነው ገልጿል።

በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት አሁኑኑ መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ተኩስ አቁም በፍጥነት መመለስ አለባቸው ብሏል።

" ግጭቱ ሊፈታ የሚችለው በድርድር ጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ ነው " ያለው የጀርመን መንግስት የአፍሪካ ህብረት የማሸማገል ጥረቶችን አሁንም መደገፉን እንደሚቀጥል እና ይህም ስራ አሁን መጠናከር እንዳለበት ገልጿል።

የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ህዝብ በቂ ስቃይ ደርሶበታል ያለው የጀርመን መንግስት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በጣም ብዙ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም ለከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰለባ ሆነዋል ብሏል።

ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል ፤ ሚሊዮኖችም በረሃብ እየተሰቃዩ ነው ሲል የጀመን መንግስት ገልጿል።

ከዚህም ዳራ አንፃር ህወሓት (TPLF) አስቸኳይ ህይወት አድን ሰብአዊ እርዳታን ለማከፋፈል የሚውልን ነዳጅ መውሰዱ " አስጸያፊ ነው " ስትል አውግዛለች።

@tikvahethiopia
#Tole

በምዕራብ ወለጋ " ቶሌ ቀበሌ " ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገላቸው።

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላ ፣ የቄለምና ምዕራብ ወለጋ ፣ የአሶሳና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምዕራብ ወለጋ በቶሌ ቀበሌ ተፈናቅለው የሚገኙ  ወገኖችን በሥፍራው በመገኘት የጎበኙ ሲሆን የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በቀበሌው ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖች መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያገኙበት የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ለመገንባትም ብፁዕነታቸው የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውም ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ቀናት ለምዕራብ ወለጋ ሰራተኞች፣ በሥሩ ለሚገኙ ሃያ ወረዳ  ሊቃነ ካህናት፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሥልጠና ይሰጣል ፤ የወረዳዎች ሪፖርትም በማድመጥ በስራ አፈፃፀማቸው ዙሪያ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።

ከዚሁ መርሐ ግብር መጠናቀቅ በኋላም ፤ በዞኑ #የዘላቂ_ሰላም_ውይይት እንደሚደረግ ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ : ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ በባህርዳር ገቡ።

ባህር ዳር ዩንቨርስቲ በነገው እለት በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ወቅት ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እንዲሁም ለኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ዛሬ በባህርዳር ገብተዋል።

ባህር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የባህርዳር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Photo Credit ፦ WMCC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NorthernEthiopia በሰሜን ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል ዳግም ጦርነት ካጋረሸ በኃላ ሁኔታዎች ከመርገብ ይልቅ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ እንደሚገኙ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ትግራይ ክልልን ከአማራ እና አፋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። በሌላ በኩል ፤ ዛሬ አርብ በመቐለ የአየር ድብደባ እንደነበር እና በዚህም ሳቢያ ህፃናትን ጨምሮ እስካሁን አራት…
#Update

ዛሬ በመቐለ የአየር ድብደባ መፈፀሙን በዚህም በህፃናት መጫወቻ ቦታ ላይ የሰው ህይወት የነጠቀ ጉዳት መድረሱን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መግለፁ ይታወቃል።

በደረሰው ጉዳት ቀን በነበረው መረጃ አጠቃላይ 13 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውን ፤ ከነዚህ ውስጥ አራቱ እንደሞቱ ከአራቱ 2ቱ ህፃናት እንደነበሩ ገልጾ ነበር።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ  ፤ የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለሮይተርስ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደስሯል የሚሉት ዜናዎች  " ውሸት እና የፈጠራ ድራማ ነው " ብለዋል ፤ ለዚህ የውሸት እና የፈጠራ ድራማ የትግራይ ባለስልጣናት " የሬሳ ማስቀመጫ ፕላስቲክ ይጥላሉ " ሲሉ ከሰዋል።

መንግስት ማንኛውም የሲቪል ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደማይፈፅም ገልፀው፤ ኢላማ የሚደረጉት የቡድኑ ወታደራዊ ቦታዎች ብቻ ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪ ቪኦኤ የእንግሊዝኛ ክፍል በኢሜል ከሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የኢሜል ምላሽ እንዳገኘ ገልጿል።

በዚህ የኢሜል ምላሽ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚፈፅም ገልፀዋል።

ህወሓት በሀሰት የሰው አስክሬን የያዘ ጥቁር ከረጢቶችን የሚመስሉ ነገሮች በሲቪል መኖሪያዎች አካባቢ በመጣል የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል የሚል ክስ ማሰማት ጀምሯል ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ አሜሪካ ዛሬ በመቐለ ከተሰማው የአየር ጥቃት ሪፖርት ጋር በተገናኘ ጉዳዩ እንደሚያሳስባት ገልጻለች።

ሁሉም የታጠቁ የግጭቱ ተዋናዮች ሁኔታዎችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ እና በአስቸኳይ ወደ ንግግር እንዲገቡ አሳስባለች።

በተጨማሪ UNICEF የመቐለውን የአየር ጥቃት አጥብቆ አውግዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkiye #UK ተርኪዬ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ማርች 24 /2022 በፌዴራል መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ከታወጀ በኃላ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶችን በሀዘን እና ስጋት ውስጥ ሆና እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልፃለች። ሁሉም ወገኖች ግጭት በዘላቂነት እንዲቆም ለማድረግ እና በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ወደ ንግግር እንዲመለሱ ጋብዛለች። ለዚህ አላማ ደግሞ ሁሉንም…
#UNHCR

ሚሼል ባሽሌት ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት በሰጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ ​​እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

" ሲቪሎች በቂ ጉዳት ደርሶባቸዋል " ያሉት ባሽሌት አሁን ዳግም ግጭት መቀስቀሱ አስፈላጊ የሆነ ድጋፍ የሚሹ የሰላማዊ ዜጎችን ስቃይ የሚያባብስ ብቻ ነው ብለዋል።

ባሽሌት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) አሁን ያለውን ሁኔታ ለማርገብ እንዲሰሩና ግጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ተማፅነዋል።

@tikvahethiopia