TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሁንዳኦል ተማሪ እንጂ ፖለቲካኛ አልነበረም " - ፍራኦል ቤኛ

ባለፈው አርብ በነቀምቴ ከተማ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆኑት ለሚ ቤኛ ወንድም የሆነ ሁንዳኦል ቤኛ ተገድሏል።

የሁንዳኦል ቤኛ አስከሬን ለ3 ቀናት ያህል ከተከለከለ በኋላ የቀብር ስነስርዓቱ ሰኞ መፈጸሙን ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ አስነብቧል።

አሁን በእስር ላይ የሚገኘው የኦነግ አመራር ለሚ ቤኛ ወንድም የሆነው ሁንዳኦል ቤኛ የተገደለው ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲዘጋጅ ነው ሲል ወንድሙን ፍራኦል ቤኛ ገልጿል።

ሁንዳአኦል ቤኛ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በነቀምቴ ከተማ ነበር ትምህርቱን ሲከታተል የነበረው አርብ ማምሻውን ግን ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ተገድሏል።

ወንድሙ ፍራኦል ቤኛ ፥ " ባለፈው አርብ በነቀምቴ ከተማ የተኩስ ልውውጥ ነበር ፤ በማግስቱ በጥይት አንድ ሰው መሞቱን ሰምተናል፤ ከዚያም ሰዎች የወንድሜን ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ ነው ያየሁት " ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

" ምስሉን ባየሁ ጊዜ እውነት መሆኑን በመመርመር አረጋገጥኩ " ሲል ፍራኦል አክሏል።

ወንድሙ ሲገደል አብሮት እንዳልነበር የተናገረው ፍራኦል ስለሁኔታው በአካባቢው ያሉትን ሰዎች መጠየቅ እንደጀመራና ወንድሙ ከሌሎች ልጆች ጋር እቤት ውስጥ እያጠኑ ከቆዩ በኃላ ምሽት ላይ " ሪፍት ቫሊ " አካባቢ ለሻይ እንደወጡ በኃላም ትእዛዛቸውን ሲጠብቁ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ ከፍተውባቸው ሁንዳኦል ስገደል ፣ ጓደኞቹ ደግሞ መያዛቸውን ገልጿል።

አብረው ከነበሩ ውስጥ የቆሰሉ መኖራቸውን አመልክቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Nekemte-06-21

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲሚንቶ አከፋፍላለሁ በሚል ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ያጭበረበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ።

ፖሊስ ፤ ሲሚንቶ አከፋፍላለሁ በማለት ከተለያዩ ግለሰቦች ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብሯል ያለውን ተጠርጣሪ ግለሰብ ዛሬ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ግለሰቡ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ ሁለት የሩዋንዳ አካባቢ ነዋሪ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ የ ' ሲሚንቶ አከፋፋይነት ' ሕጋዊ ፍቃድ አለኝ በማለት ከተለያዩ ግለሰቦች ሲሚንቶ አቀርባለሁ በማለት የቅድመ እና ሙሉ ክፍያ ቼክ እየሰጣቸው ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስቦ መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል።

Via Addis Ababa Police

@tikvahethiopia
#Mali 🇲🇱

በአፍሪካዊቷ #ማሊ የታጠቁ አማፂያን በፈጸሙት ጥቃት ከ100 በላይ ንፁሀን ዜጎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ጥቃቱ ማዕከላዊ ማሊ ውስጥ መፈፀሙ ነው የተነገረው።

ጥቃቱን ' Katiba Macina ' የተባለው የታጠቀ ቡድን አባላት ቅዳሜ ለሊት ለእሁድ አጥቢያ የፈፀሙ ሲሆን ፤ ሞፕቲ ክልል ውስጥ በሚገኘው ባንካስ የገጠር ማህበረሰብ ውስጥ ቢያንስ በሶስት መንደሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 132 ንፁሃን ሰዎች በግፍ መደገላቸውን የሀገሪቱ መንግስት ገልጿል።

ጥቃቱን ተከትሎ የማሊ መንግስት ዛሬ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሀዘን አውጇል።

@tikvahethiopia
ፎቶ / ቪድዮ ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ፈረንሳይ 41 እየሱስ አካባቢ በፎቶው እና በቪድዮው የምትመለከቱትን ይመስል ነበር። ከዚህ አካባቢ በተጨማሪ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ከ1 ሰዓት በላይ በረዶን የቀለቀለ ዝናብ ጥሎ ነበር።

ወቅቱ ክረምት በመሆኑ በሚቻለው አቅም ጥንቃቄ እናድርግ ፤ በተለይ ደግሞ አሽከርካራዎች ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ ጥንቃቄያችንን ከምን ጊዜውም በላይ እናጠናክር።

(ዧ - Tikvah Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መቆሚያው የት ነው ? ባለፉት ዓመት ንፁሃን ዜጎች በተለይ ህፃናት እና ሴቶች እጅግ በጣም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ሲጨፈጨፉ ፣ ሲሳደዱ፣ ከገዛ ቤታቸው ሲፈናቀሉ አይተናል። ይህን ተከትሎም በርካቶች ሀዘናቸውን እና ቁጣቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ ያጋራሉ ፤ ከልባቸው ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይወተውታሉ። መንግስት ተቀዳሚ ስራው የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሆነ ደጋግመው ያሳስባሉ። በአንፃሩ…
" የትኛውም ቦታ የሚፈፀም የንፁሃን ግድያ ለሁለት እና ሶስት ቀን አጀንዳ ሆኖ ሊያልፍ አይገም " Tikvah Family

ባለፉት ዓመታት በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫ በርካታ ከግጭ ነፃ የሆኑ፣ ስለ ፖለቲካ ሆነ በሀገሪቱ ስላለው ነገር በቅጡ መረጃው የሌላቸው ንፁሃን ገበሬዎች፣ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ ታዳጊዎች ፣ ነገ የተሻለ ህይወት ለመኖር የሚያስቡ በርካታ ወጣቶች ሲገደሉ፣ ከቤታቸው ሲፈናቀሉ፣ ሲሳደዱ ተመልክተናል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ ለየትኛው ጉዳይ #በሰብዓዊትነት መርህ አንድ ላይ ተቁሞ እንደተወገዘ ፤ ለተጠናቂነት እና ለመፍትሄ ሁሉም እንደጮኸ ለማስተወስ ይከብዳል።

ለአብነት አንድ ቦታ ላይ ችግር ሲፈጠር ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር በማወዳደር ፤ ያኔ እናተ መቼ አወገዛችሁ ይባላል ፤ በዚህኛው በኩል ችግር ሲፈጠር እናተስ ባለፈው መቼ አወገዛችሁ ፤ መቼ ስለኛ ተናገራችሁ ይባላል ፤ ሌላም ቦታ እንዲሁም ያለፈውን በማወዳደር አጀንዳ ሲሆን ይከርምና የንፁሃን ደም ከንቱ ሆኖ ይቀራል።

በእጅ አዙር ጥፋተኛው እንዳይጣየቅ ሽፋን ይሰጣል (ለምን ? ምክንያቱም የአንዱ ወገን ስለሆነ፤ ከሰውነት ብሄር ስለገነነ) ፣ ስልጣን ላይ የተቀመጠውም ደጋፊ ስላለው ስለተጠናቂነት ቢናሳ ሊከላከልለት ብቅ የሚለውም ብዙ ነው። ይሄ መቼ ነው የማቆመው ?

" ተቀዳሚ ስራህ የዜጎችን ደህንነት ማስጠቅ ነው ፣ ሰላም ማረጋገጥ " ነው የተባለው መንግስት በየጊዜው ተመሳሳይ ነገር ይናገራል ግድያ እና ሞት ግን ይኸው ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።

በተለይም በታጣቂዎች የሚፈፀም ጥቃት በሚገርም ሁኔታ አሁን ድረስ ቀጥሏል፤ በመጀመሪያ ለውጥ በተባለ ሰሞን መንግስት አልተረጋጋም ጊዜ ይፈልጋል ሲባል ከረመ ፤ አመታት አለፉ ሁኔታዎች አልተቀየሩም ዛሬም ሰው በወጣበት ይቀራል ፤ ቤቱ በተቀመጠበት ይገደላል።

በዚህ ሁሉ ሁኔታ ምን ያህል እንባ እንደታበሰ ፣ ምን ያህል ዜጋ ፍትህ እንዳጋኘ በቅጡም አይታወቅም።

ይበልጥ ችግሩን እያባባሰው ያለው መርጦ የማዘኑ ፤ የኔ ወገን ፣ ሃይማኖት ተናካ ሲባል ብቻ ወጥቶ መናገሩ ፣ ግፍን ማወዳደሩ፣ ያለፈውን ስላልተናገራችሁ አሁን ይበላችሁ የሚል አዙሪት ውስጥ መገባቱ ነው።

ስለንፁሃን ሲነገር እርግማን መብዛቱ፣ ስም መለጠፉ፣ ማሸማቀቁ እስካልቆመ ድረስ ፤ ሁሌም ግፎችም እያወዳደሩ ከሰውነት ተራ መውጣቱ እስካልቆመ ፣ ሁሉም ነግ በእኔ ነው ብሎ ስለፍትህ ካልጠየቀ ፤ እንዴት ችግር ይፈታል ?

ግድያ እና ግፍ የንፁሃን ሞት የሁለት እና የሶስት ቀን አጀንዳ ሆኖ መቅረት የለበትም። ዛሬ መፍትሄ ካላገኘ ነገ መቀጠሉ አይቀርም ፤ በእርግጥ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው ሌላ ነው ዛሬ ይጮሃል ነገር ይረሳል።

ቤተሰቦቹን በግፍ ያጣ ፣ የሚወደን ከጎኑ የተነጠቅ ፣ የተገደለበት፤ የነገ ተስፋው የጨለመበት እንዲሁ የሚረሳው ይመስለናል ? እነዚህ ወገኖች ስለሀገራቸው ምን ይሰማቸዋል ? ብለን መጠየቅ አለብን።

ትላንት የሆነውን እኛ ብንረሳው ፤ ዘለለማዊ ጠባሳን በህይወታቸው ላይ ጥሎ የሚያልፍ ሰዎች በየጊዜው ቁጥራቸው እየበዛ ነው።

ከዚህ በፊት በታሪክ ፣ በፅሁፍ ነበር ግፍ እና በደልን ሲሰማ የነበረ አሁን ግን በቪድዮ/በፎቶ እየተቀረፀ ሰው በግፍ እየተረሸነ፣ የሰው ልጅ በቁሙ እየተቃጠለ በቪድዮ እየተቀረፀ፣ እጁ ላይ አንዳች ነገር ያልያዘ ሰው በጥይት ተደብድቦ እየተገደለ በቪድዮ የተቀረፀ ቀጣዩ ትውልድ ይህን እያየ እንዲያድግ ከተፈረደበት ነገ ከዛሬውም እጅግ በጣም የከፋ እንደሚሆን አያጠራጥርም።

ያለንበትን ሁኔታዎች በፍጥነት ማስተካከል ለዚህም መረባረብ እና ሌላ ለትውልድ #ጥላቻን እና #ቂምን ሊያወርስ የሚችል ተጨማሪ ችግር ከመደራረቡ በፊት ያሉትን መፍታት፣ የተበደሉትን እምባ ማበስ፣ ፍትህ ማስፈን ይጋባል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቴሌግራም ፕሪሚየም " ቴሌግራም በነፃ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በክፍያ አገልግሎት የሚሰጥበትን " ቴሌግራም ፕሪሚየም " ትላንት ለሊት ይፋ አድርጓል። የቴሌግራም ፕሪሚየም ወራዊ ክፍያ 5.99 የአሜሪካ ዶላር መሆኑም ታውቋል። አሁን ላይ የIOS (አይፎን) ተጠቃሚዎች መተግበሪያቸውን Update ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ፤ ዛሬ አልያም በቀጣይ ቀናት ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።…
#Update #Android

ከአንድ ቀን በፊት ቴሌግራም ለIOS (አይፎን ስልክ) ተጠቃሚዎች ' ቴሌግራም ፕሪሚየም ' የተካተተበትን መተግበሪያ #Update ማድረጉ ይተወሳል።

ትላንት ለሊት የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ እንዲደርሳቸው ሆኗል።

ዋናውን በድርጅቱ በኩል የሚቀርበው የቴሌግራም መተግበሪያ (ባለ ሰማያዊ ምልክቱ) ይጠቀሙ። #Update ለማድረግ ሊንክ ይኸው https://play.google.com/store/search?q=telegram&c=apps

" ቴሌግራም ፕሪሚያም " አሁን በነፃ እየተሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ አዳዲስ አገልግሎቶች የተካተቱበት ሲሆን በወር 5.99 ዶላር ያስከፍላል።

በአዲሱ #Update በነፃ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ከዚህ በፊት ከነበረው ማሻሻያ እና የነበሩትን ችግሮች የመቅረፍ ስራ መሰራቱ ድርጅቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፍትህ እንፈልጋለን፣ ጥፋተኞች በጠቅላላ ይጠየቁ " - የምዕራብ ወለጋ ቲክቫህ አባላት ከቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ ሲገልፁ የነበሩ የቤተሰባችን አባላት ህዝብ እና ሀገር አስተዳደራለሁ የሚል አካል ካለ ጥፋተኞች እንዲጠየቁ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ቤተሰቦቻቸውን በግፍ የተነጠቁ የቲክቫህ አባላት በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። ፍትህ…
ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ወገኖች ችግር ላይ ናቸው !

በምዕራብ ወለጋ ዞን በጊምቢ ወረዳ ፣ ቶሌ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን የምግብ እርዳታ ስላላገኙ ችግር ላይ ይገኛሉ።

ነዋሪዎቹ ቤት ንብረታቸው ከመውደሙ ባሻገር ንግዳቸው እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸው ስለተዘረፉ የምግብ ችግር እንደገጠማቸው እየተናገሩ ነው።

ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች ዘመዶቻቸው ጋር ተጠልለው እንደሚውሉና የተወሰኑት ምሽት ላይ በመስጅዶች ውስጥ እንደሚጠለሉ ገልፀዋል።

በቶሌ ቀበሌ በሚገኙት ፦
- ጉቱ፣
- ጨቆርሳ፣
- ስልሳው፣
- በገኔ፣
- ጫካ ሰፈር እና ሀያው በተባሉ መንደሮች (ጎጦች) ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ. ም. በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከ300 የሚልቁ ንጹሀን ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል፤ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ይገለፃል።

“ እየራበን እየጠማን ተቀምጠናል ”

የሰባት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ፎዚያ * ወንድማቸው ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የአራት ዓመቱ የመጨረሻ ልጃቸውን ጨምሮ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ቤተሰብ እየኖረ ነው።

በግብርና ይተዳደሩ የነበሩት ወ/ሮ ፎዚያ በጥቃቱ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ስልሳው በሚባለው መንደር ይኖሩ የነበረ ሲሆን፣ ሁለት ጥማድ በሬ፣ ሦስት ላሞች እና አንድ ጎተራ እህል ወድሞባቸዋል።

ዛሬ ለልጆቻቸው ንፍሮ ቢያበሉም፣ ነገ እና ከዚያ ወዲያ ያሉት ቀናት እንደሚያሰጓቸው ገልጸዋል።

“ ቤተሰቦቻችን አልቀው ብቻችንን እያለቀስን፣ እየራበን እየጠማን ተቀምጠናል” ብለዋል ወ/ሮ ፎዚያ።

" ያንን ሁሉ ሬሳ አይተን ልቦናችን ወደ ሥራ አይመራንም "

የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አሕመድ " ወደ 10 ይሁን 20 ኩንታል የሚጠጋ ስንዴ መጥቷል። ስድስት ካርቶን ኮቾሮ ነበር ልጆች በልተውታል። ስኳርም የተወሰነ ከረጢት መጥቷል። ሰው እናክማለን ብለውም ቦታ እየያዙ ነው " ብለዋል።

በግብርና የሚተዳደሩት አቶ አሕመድ እንደሚሉት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ እርሻቸው ለመመለስ ቸግሯቸዋል።

“. . . ያንን ሁሉ ሬሳ አይተን ልቦናችን ወደ ሥራ አይመራንም። ሰው ዝም ብሎ ሐዘኑን እየተካፈለ ነው። ቅዳሜ ከሞተው ሰው መካከል የተቀበረ፣ አሞራ የጎተተውም አለ” ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ማሳ ውስጥ ተደብቀው ሕይታቸውን እንዳተረፉ ተናግረዋል።

አሁን መከላከያ ሠራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በመኖሩ መረጋጋት ቢመለሰም፣ ሙሉ በሙሉ ከስጋት እንዳልተላቀቁ ገልጸዋል።

" ይሄ ማስጠንቀቂያ ነው፣ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ አገራችሁ ግቡ፣ እዚህ እንዳትቀመጡ፣ መጨረሻ ላይ ስንመጣ የሚተርፍ ሰው የለም ብለውናል። መንግሥት ከዚህ ያንሳን " ሲሉ ተማጽነዋል።

“ ሰባት ልጆቼን ምን ላብላቸው ? ”

በቶሌ ቀበሌ፣ ጨቆርሳ መንደር የሚኖሩት የሰባት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አብዱ* አሁን በአካባቢው የመከላከያ ሠራዊት እና ልዩ ኃይል በመግባቱ ሰላም ቢመለስም፣ ልጆቻቸውን የሚያበሉት ምግብ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ አቶ አብዱ በጥቃቱ የአጎቶቻቸውን ልጆች አጥተዋል። ቤት ንብረታቸውም ተዘርፏል።

ከመጋዘናቸው 110 ኩንታል በቆሎ እና 15 ኩንታል ሩዝ እንዲሁም አምስት በሬን ጨምሮ በግ እና ፍየል እንደተዘረፉ ተናግረዋል።

“የተፈጸመው አሰቃቂ፣ ዘግናኝ ጥቃት ነው። ትላንትም ሰው ቀብረናል። ሳይቀበር ጫካ የቀረም አለ። አንድ ጉድጓድ ውስጥ 63 ሰው የተቀበረበት ቦታ አለ። ከእነዚህ 40 የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው” ይላሉ።

ጨምረውም “. . . አሁን እኮ አንድ ኪሎ ምግብም የለንም። ልብስም ጫማም የለንም። መንግሥትም አልረዳንም። ከዝርፊያ የተረፈውን እህል ቀቅለን ንፍሮ ነው የምንበላው። ተጨፈጨፍን አሁን ደግሞ የረሃብ ጦር እየወጋን ነው ” ብለዋል።

አቶ አብዱ፣ ልጆቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉና በአካባቢው የተሰማሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለሕጻናት ብስኩት እየሰጧቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

“መከላከያዎች የተወሰነ ኮቾሮ እየሰጧቸው ነው እንጂ ሰባት ልጅ እንዴት ይደረጋል? ገና ዓመት ያልሞላት ልጅ አለችኝ. . . ረሃቡ አሳሳቢ ነው።”

ጥቃቱ የተፈጸመ ዕለት እሳቸው ከቀበሌው ወጥተው እንደነበርና ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው ማሳ ተደብቀው እንደተረፉ ተናግረዋል።

አቶ አብዱ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሰው ቤት ተጠልለው እንዳሉና እናቷ የተገደለችባት የ15 ቀን ልጅን ጨምሮ በአንድ ቤት ውስጥ በርካቶች እንደሚገኙ ገልጸዋል።

“አሁን እኮ አባ ወራ ብቻውን፣ እማወራ ብቻዋን ቀርተዋል። ምን ተረፍን ይባላል? ከዚያም ብሶ ረሃብ ሊጨርሰን ነው” በማለት እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጽነዋል።

“ ለምን እናርሳለን ? ”

ስልሳው የተባለ መንደር ውስጥ ተወልዶ ያደገው ከማል* በጥቃቱ ወንድሙን አጥቷል።

የሸቀጥ ሱቁ እንደተዘረፈ እና ዘመድ ቤት ተጠልሎ እንደሚገኝ ተናግሯል።

“ዘመድ ቤት፣ ጓደኛ ቤት፣ በየበረንዳው፣ በየመስጆዱ ነው ተጠልለን ያለው” ብሏል።

ከማል ያሳርሰው የነበረው መሬት እንደነበረው፣ ከጥቃቱ ወዲህ ግን ወደ እርሻ የተመለሰ ሰው በመንደራቸው እንደሌለ ገልጿል።

“ለምን እናርሳለን? ወቅቱ እኮ ታርሶ፣ ነጭ ማዳበሪያ የሚደረግበት ነበር። ግን ስንት ንብረት ቀለጠ! 4 ሄክታር በቆሎ እና አንድ ሄክታር ሩዝ አዘርቼ ነበር። ያው ቀልጦ ቀረ።

እና ለምን ብዬ ነው ሁለተኛ ወጪ አውጥቼ ማዳበሪያ የማስረጨው ? ለምን አስኮተኩታለሁ። ላስኮትኩት ብልስ መቼ ገንዘብ አለን? ገንዘባችን፣ ንብረታችን ተወስዷል። ሰው እንዲሁ እየተንቀዋለለ ነው።”

ከማል እንደሚለው ከሆነ ፣ ከየትኛውም የመንግሥት አካል የምግብ እርዳታ እስካሁን አልደረሳቸውም። የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለሕጻናት ብስኩት ሲሰጡ መመልከቱን ጠቅሷል።

“የተራረፈ በቆሎ እየቀቀልን ተካፍለን ነው የምበላው። ጨው እንኳን የለንም። መከላከያዎች ከቀለባቸው አዋጥተው ለሕጻናት እና ለእናቶች ጠዋት አንድ፣ ማታ አንድ ብስኩት ሲሰጡ አይቻለሁ። ግን ይሄ እስከ መቼ ያዘልቃል?” ይላል።

የሰኔ ወር ሰብል የሚኮተኮትበት እንደነበረ፣ በጥቃቱ ሳቢያ ሥራ በመስተጓጎሉ ግን አዝመራው በአረም እየተበላ መሆኑን ተናግሯል።

“. . .ሰብል መኮትኮቱ ቀርቶ እኛ ሰው አጥተናል። ስለ በቆሎ አዝመራ ማን ያስባለል? ነፍስ ይቀድማል። የሞተው ሰው ወደ 500 ደርሷል እየተባለ ነው።”

ማኅበረሰቡ አሁን ያለውን ምግብ ተካፍሎ ቢበላም፣ ከጥቂት ቀናት በላይ እንደማያልፍ ይናገራል። እርዳታ በአፋጣኝ እንዲሰጣላቸውም ይጠይቃል።

“መከላከያ ስላለ አሁን ሰላም ነን። መከላከያ ከወጣ ግን ራሱን መከላከል የሚችል ሰው የለም። አሁንም ፈርተን ግማሻችን ስንተኛ፣ ግማሻችን እንጠብቃለን። አንድ ሸንኮራ ‘በሥነ ሥርዓት ተጠቀሙ’ ተብሎ ለሁለት ተካፍለን እንበላለን። በቋፍ ነው ያለነው” ሲል አክሏል።

* ቃላቸውን የሰጡ ግለሰቦች ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው ተቀይሯል።

Credit : ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት

@tikvahethiopia
#DoubleA

የ “Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

መተግበርያውን ለማውረድ:
Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or
https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
" ፏን ኋን ሲሚንቶን እንዳትጠቀሙ " - ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ፏን ኋን ኃ/ተ/የግ/ማህበር ፏን ኋን ሲሚንቶ CEM II 32.5N እና CEM I 42.5N የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ CES 28: 2013 ያላሟላ በመሆኑ ማስተካከያ እስኪያደርግ ድረስ ከሐምሌ 09/2013 ዓ ም ጀምሮ የብሔራዊ ደረጃ ምልክት እና ምርት ጥራት ሰርተፍኬት የመጠቀም ፈቃዱ ታግዶ ነበር።

ነገር ግን የብሔራዊ ደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ እና ምርት ጥራት ሰርተፍኬት ላይኖራቸው CEM II 32.5 N ሲሚንቶ ምርት በገበያ ላይ በመገኘቱ እና ከምርቱ ጥራት ጋር ተያይዞ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሰኔ 10/2014 ዓ.ም በፋብሪካው በአካል በመገኘት ምርት ማምርቱና እና አለማምርቱን ማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

በመሆኑም የብሔራዊ ደረጃ ምልከት የመጠቀም ፈቃድ እና ምርት ጥራት ሰርተፍኬት ታግዶ እያለ ጥራቱና ድህንነቱ ያልተረጋገጠ ምርት በተጭበረበር መልኩ በማምርት የህብረተሰብ ድህንነት እና ኢኮኖሚ የሚጎዳ ፏን ኋን ሲሚንቶ ወደ ገበያ ያሰራጨ በመሆኑ በድርጅቱ ላይ ውሳኔ መተላለፉን ገልጿል።

የተላለፈው ውሳኔ ፦

1. በራሱ ወጭ ፏን ኋን ሲሚንቶ ምርቱን ከሰራጨበት የሀገሪቱ የገበያ ቦታዎች ላይ እንዲሰበስብ

2. ፏን ኋን ሲሚንቶ ምርት ጥራት ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ ከማዋል እንዲቆጠብ ተወስኗል ሲል ሚኒስቴሩ ዛሬ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

የነዳጅ ማደያ በሌለባቸው ከተሞችና አከባቢዎች በሕገወጥ ንግድ ለሚከናወነው የነዳጅ ችርቻሮ ሽያጭ የወጣ አዲስ መመርያ፣ የነዳጅ ማደያ ካለበት በ20 ኪሎ ሜትር በሚርቁ አካባቢዎች የነዳጅ ውጤቶች በቸርቻሪዎች እንዲሸጡ መፈቀዱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

አዲሱ መመርያ ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች የነዳጅ ውጤቶች የሚሸጡበትን የዋጋ ተመን የሚሰላበትን መንገድ ያስቀመጠ ሲሆን ቸርቻሪዎች የትርፍ ህዳጋቸው 5 በመቶ እንደሚሆን ወስኗል፡፡

ይህ የትርፍ ህዳግ መንግሥት ለመደበኛ የነዳጅ ማደያዎች ካወጣው የ0.23 በመቶ ትርፍ ህዳግ አንፃር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

መመሪያውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን በጋራ እንዳወጡት የተገለፀ ሲሆን በችርቻሮ የሚቀርበው ነዳጅ ተገቢ ባልሆነ ዋጋና በሕገወጥ ንግድ መልክ የሚከናወን በመሆኑ ይህንኑ የአሠራር ክፍተት ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መመርያው የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ የሚመራበት የነዳጅ ዋጋ የሚወሰንበት፣ ቁጥጥር የሚደረግበትና የአካባቢ ደኅንነት የሚጠበቅበት የአሠራር ሥርዓት የሚዘረጋ ነው፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-06-22-2

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#AddisAbabaUniversity

የፀጥታ ችግር ካለባቸው ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ መደበኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የክረምት እረፍት ጊዚያቸውን በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠበቅ ላይ ናቸው።

ቲክቫህ በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ማቲዎስ እንሰርሙ (ዶ/ር) ጠይቋል።

"የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ጥያቂያቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት በማመልከቻ በማቅረብ ምላሽ እንደሚሰጣቸው" ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

"ከተማሪዎች ዲን ጋር በመሆን እያንዳንዱን ጥያቄ ኬዝ በኬዝ በማየት እና አመልካቾቹን ቃለመጠይቅ በማድረግ ምላሽ ይሰጣል" ብለዋል።

በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ የሆኑ እና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎችንም በመለየት ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በግቢው ስለሚቆዩ እና የክረምት ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስለሚገቡ የዶርም እጥረት መኖሩን በመግለጽ የተማሪዎቹ ጥያቄ ኬዝ በኬዝ እንደሚታይ ተናግረዋል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia