TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡

ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡

‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡

አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡

ፑቲን ከዚህ በፊት በለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ወቅት ነው።

በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት አድርገው ነበር።

በዚህ ጉብኝታቸው ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡

በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#UNICEF #ETHIOPIA

ትላንት ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዩኒሴፍ ኤግዜኩቲቭ ዳይሬክትር የሆኑትን ካትሪን ራስል በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ በአገራችን በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ በርካታ ሕጻናትን ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ለማየትና ለመርዳት የሚያስችላቸውን የዓለም አቀፍ ከፍተኛ ድጋፍ ለማስገኘት ነው ተብሏል።

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የመስክ ሥራ ልምድ ያለው ሲሆን ግንኙነቱን በማሻሻልና በመጠናከር መሠራት እንዳለበት ፕሬዚደንቷ ገልጸዋል።

ካትሪን ራስል ከሶስት ወር በፊት ነው የዩኒሴፍ ኤግዜኩቲቭ ዳይሬክትር የሆነው የተሾሙት።

ምንጭ፦ የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በዚህ ሩጫ በበዛበት ዘመን የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ካሉበት ሆነው ለመክፈል የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ አይነተኛ አማራጭ ነው። በአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ የዲኤስ ቲቪ፣ የኢትዮ ቴሌኮም፣ የዌብ ስፕሪክስ ኢንተርኔት ክፍያ፣ የትምህርት ቤት እና የተለያዩ አይነት የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ ይክፈሉ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
" ትውልዱ የፊቼ ጨምበላላን ትርጓሜና እሴቶቹን መገንዘብ ያስፈልገዋል " - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል ለሆነው ለፊቼ ጨምበላላ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በሲዳምኛ ቋንቋ /Sidaamu Afoo/ ባስተላለፉት መልእክት ፤ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ የፊቼ ጨምበላላን ትርጓሜና እሴቶቹ ሰላም ፤ ፍቅር እና አንድነት መሆኑን ትምህርት መውሰድ ወይንም መገንዘብ እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ፊቼ_ጨምበላላ

የሲዳማ የዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምባላላ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

ዛሬ በዓሉ በሲምፖዚየምና ሌሎች ዝግጅቶች በሀዋሳ ተከብሯል።

በሲዳማ ባህል አዳራሽ በተካሄደው ሲምፖዚየም ላይ የፊቼ ጫምባላላ ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርቧል።

በዛሬው የበዓሉ ዋዜማ  የ ”ሻፌታ” ሥነ-ሥርዓትን ጨምሮ ሌሎችም  ዝግጅቶች  ነበሩ።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎና የዞን አመራሮች ተገኝተው ነበር።

በተጨማሪ የመጀመሪያው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባተ ኪሾ፣ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤና አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች ታድመው እንደነበር ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION📣

የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ከቀብር ስፍራ ጋር በተያያዘ በክርስትና እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተቀሰቀሰውን ግጭት መነሻ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አስታወቋል፡፡

በጎንደር በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ሁከቱን ለማባባስ የተንቀሳቀሱ 280 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን አመልክቷል፡፡

በጎንደር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎች በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር የሚጋብዙ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ ሲል ጠቁሟል።

በአንዳንድ አካባቢዎችም የእምነት ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግጭቱ ሃገራዊ ቅርጽ እንዲኖረው ሙከራ እየተደረገ ነው ብሏል።

የፌደራል የደህንትና የጸጥታ መዋቅር በድርጊቱ በሚሳተፉት ላይ ብቻ ሳይሆን ከኋላ በመሆን በሚዘውሩት ላይ በቂ መረጃና ማስረጃ ያለው በመሆኑ ተከታታይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እንዲስፋፋ በየትኛውም የመገናኛ ዘዴ የሚቀሰቅሱ፤ በተለይ ደግሞ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም ሃሰተኛና የጥላቻ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን የጋራ ግብረ ኃይሉ የጠቆመ ሲሆን በዚህ ህግወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ትኩረት📣

" በእምነት ተቋማት ላይና በንፁሀን ላይ የሚፈጸመው ሕገ ወጥ ድርጊት በአስቸኳይ ይቆም ዘንድ ሁሉም የሚመለከተው አካል ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል " - የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት

ዛሬ የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ላይ ምዝበራና ውድመት መፈፀሙን የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት አስታውቋል።

ድርጊቱ የተፈፀመው በአክራሪዎች እና ፅንፈኛ ኃይሎች ነው ብሏል።

እኚሁ ኃይሎች የደብሩን በር እንዲሁም ደግሞ መስኮት መሰባበራቸውን እና የጉልላት መንበሩን እንደገለበጡ ሀገረ ስብከቱ አሳውቋል።

የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ቃል ፤ " አክራሪና ጽንፈኛ ቡድኖች የደብሩን የጀነሬተር ቤትና የጥበቃ ቤት አቃጥለዋል " ብለዋል ።

አገልጋዮች እና የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ድብደባ የተፈፀመ ሲሆን ፤ የክርስቲያን ሆቴሎች ላይም ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በስልጤ ዞን ሳንኩራ ቅ/ ገብርኤል ቤተክርስቲያ ሙሉ በሙሉ ቃጠሎ መውደሙ ተገልጿል።

ሀገረ ስብከቱ ፤ ይህ ሁሉ ጥፋት ሲደርስ የሚያስቆም የዞን ኃይል ባለመኖሩ እጅግ እዳዘነ ገልጿል።

መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ፤ ከርዕሰ ከተማው ወራቤ ውጪ በሳንኩራ፣ ቂልጡ፣ ቅበት፣ ሌራ፣ ዳሎቻ፣ ቄራ በተባሉ አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ምእመናንንና አብያተክርስቲያናትን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በጎንደር ከተማ ላይ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ ችግሩን ለማስፋትና አጋጣሚውን ለሌላ ሁከት መጠቀም በእምነት ተቋማት ላይና በንፁሀን ላይ የሚፈጸመው ሕገ ወጥ ድርጊት በአስቸኳይ ይቆም ዘንድ ሁሉም የሚመለከተው አካል ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ሚያዚያ 21 ፤ በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡

ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቅዱስ ኡራኤል አካባቢ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ እና በዙሪያዋ የሚገኙ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት፦

🛣 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሀያ ሁለት ወይም ዘሪሁን ህንፃ አካባቢ ዝግ ይደረጋል፣

🛣 ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ኦሎምፒያ፤

🛣 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ፤

🛣 ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ እና ከሜኪሲኮ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚጓዙ ሜክሲኮ አደባባይ፤

🛣 ከጌጃ ሰፈርና ከጎማ ቁጠባ በሰንጋ ተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ የቀድሞው ደሳለኝ ሆቴል መስቀለኛ ላይ፤

🛣 ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ለሚጓዙ ጎማ ቁጠባ ላይ እና ከሜክሲኮ ወደ ፖስታ ቤት ለሚሄዱ ሚትሮሎጂ አካባቢ እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር አካባቢ፤

🛣 ከተክለኃይማኖት በጎላ ሚካኤል ለሚመጡ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ እና ከተክለኃይማኖት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ለሚመጡ ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከተክለ ኃይማኖት በሶማሌ ተራ ወደ ባንኮ ዲሮማ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሸዋ ሱፐር ማርኬት ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

🛣 ከቀድሞ አትክልት ተራ አካባቢ በአሮጌው ፖስታ ቤት ወደ ቸርችል ጎዳና የሚወስደው መንገድ አሮጌው ፖስታ ቤት፤

🛣 ከደጎል አደባባይ ወደ እሪ በከንቱ ደጎል አደባባይ ላይ እና ከአራት ኪሎ በፓርላማ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ሸራተን ሆቴል መውረጃ ላይ፤

🛣 ከ4 ኪሎ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ ይዘጋል።

🛣 ከካዛንቺስ ሼል ወደ ፍል ውሀ እና ወደ ባምቢስ የሚወስዱት መንገዶች ካዛንስ ሼል ላይ ከቀኑ7፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የጸጥታ ኃይሉ ኃይል መድቤያለው ቢልም ለሊቱን ከዚህ በፊት ተቃጥላ ዳግም የተሠራችውን የቂልጡ ማርያም ገዳምን አቃጥለዋል " - መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ

በትላንትናው ዕለት የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ላይ ምዝበራና ውድመት መድረሱ እንዲሁም የሳንኩራ ቅ/ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መቃጠሉ መገለፁ ይታወሳል።

የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ድርጊቱን የፈፀሙት አክራሪና ፅንፈኛ ኃይሎች ናቸው ማለቱ አይዘነጋም።

ዛሬ ጥዋት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ቃል ፤ ምዝበራ የተፈፀመበት የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን መቃጠሉን አሳውቀዋል።

ለክልሉ ልዩ ኃይል ቂልጡ፣ ቅበት፣ ሌራ፣ ዳሎቻ፣ ቄራ በተባሉ አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ምእመናንንና አብያተክርስቲያናትን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦ እንደነበር አስታውሰዋል።

" የጸጥታ ኃይሉ ኃይል መድቤያለው ቢልም ለሊቱን ከዚህ በፊት ተቃጥላ ዳግም የተሠራችውን የቂልጡ ማርያም ገዳምን አቃጥለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከእኩለ ለሌት በኋላ የጸጥታ ኃይሉን የሚመሩት አባላት ስልካቸውን ማጥፋታቸውን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ ምእመናን ተደራጅተው ቀሪ አብያተክርስቲያናትን እንዲጠብቁ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

አንዳንድ የወረዳ ፖሊሶች በማቃጠል በድርጊቱ ተባባሪ ናቸው ያሉ ሲሆን አንዳንድ የእስልምና ተከታዮች በገጠር ያሉ አብያተክርስቲያናትን ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

መንግሥት በመሀል ሀገር ተቀምጠው ድርጊቱን በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያነሳሱና መመሪያ የሚሰጡ አሻባሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባል መባሉን የኢኦተቤ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopia