TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የረመዳን ፆም ነገ ይጀምራል።

1443ኛው የረመዳን ፆም ነገ መጋቢት 24  ይጀምራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን በመታየቷ ፆሙ ነገ ቅዳሜ እንደሚጀምር አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#KonssoZone📍

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ የወረዳው የገቢዎች ኃላፊ ምግብ ቤት ውስጥ በጥይት መገደሉ ከተገለጸ በኋላ በተከታታይ 4 ሰዎች መሞታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ህይወታቸው ያለፈው የ ' ሰገን ገነት ቀበሌ ' ሊቀመንበር አቶ ኩሴ ጦኔ እንዲሁም አንድ የሚሊሻ አባል እና 2 ነዋሪዎች ናቸው።

የወረዳው የመንግስት ተጠሪ አቶ ገመይዳ ጉዴኖ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት መጋቢት 18 ቀን 2014 የአከባቢው ሚሊሻ ከደራሼ ልዩ ወረዳ ሀይቤና ቀበሌ በኩል የመጡ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመውበት መገደሉን ገልጸዋል። አቶ ገመይዳ ፥ " ጥቃቱ ሲፈጸምም ሽፋን የሰጠ አካል የለም " ሲሉ ነው የገለጹት።

በመቀጠልም ፤ መጋቢት 22 በግምት ከቀኑ 8:30 አከባቢ የሰገን ገነት ቀበሌ ሊቀመንበር ኩሴ ጦኔ በታጣቂዎቹ ታፍኖ መሳሪያውን ተቀምቶ ተገድሏል ብለዋል። ''ትላንት ማታ ነው ሬሳ ያወጣነው'' ሲሉም ተናግረዋል።

በዚያው ቀን 5:30 አከባቢም በመጓዝ ላይ በነበሩ 3 ሰዎች ላይ በተከፈተ ጥቃት ሁለቱ ህይወታቸው ሲያልፍ አንደኛው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት መረጃ ይድረስንልን ያሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ፤ ጥቃቱን የሚፈጽሙት " በትጥቅ የተደራጁና መሳሪያ የታጠቁ አካላት " መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከአካካቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያሰባሰብነው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ የክልሉ ልዩ ኃይል ከነበረበት ካንፕ ለቆ በወጣበት ቅጽበት የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ኮሴ ጡኔ በታጣቂዎቹ መገደላቸውን ይጠቁማል።

አቶ ገመይዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሉት የጸጥታ መዋቅሩ ከየቀጠናው ተሰብስቦ በመውጣቱ ጥቃቱን ሚሊሻ ብቻውን መከላከል እንዳልቻለ ጠቁመዋል።

የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በርሻ ኦላታ ፤ " ፅንፈኛው " ሲሉ የጠሩት ኃይል እየፈጠረ ባለው ሁከትና ብጥብጥ ህዝቡ ዳግም መፈናቀሉንና ለእንግልት መዳረጉን ገልፀዋል።

አቶ በርሻ ፤ የመለጋ እና ዱጋያ ቀበሌ ህብረተሰብ መንግስት የሰጣቸውን ጊዜያዊ መጠለያ ሸራ ቤት በመወጠር ቤት ንብረቱ በተቃጠለበት ቦታ ቀልሰው መኖር በጀመሩበት ወቅት ጥቃት መፈጸሙን አንስተዋል። በዱጋያ ትም/ት ቤት እና ለሰራዊት ማረፊያ የተገነባው ሁለት ካምፕ ላይም ጥቃት ደርሷል ሲሉ ነው የገለፁት።

በተመሳሳይ ከትላንትና መጋቢት 22 ቀን 2014 ማታ ጀምሮ " ጋርጨ " በሚባል ቀበሌ ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው ሸራ ወጥረው በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መከፈቱን የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን መልዕክት ጠቁመዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ሸራውን ሙሉ ለሙሉ ማቃጠላቸውን እና ለመቋቋሚያ የተሰጣቸውን ቆርቆሮም መዘረፉ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች በ7ቱ ላይ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን አምስቱ ሙሉ ለሙሉ መቃጠላቸውን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡ ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት የአካባቢው ቤተሰቦቻችን ሶስት አመት ሙሉ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ መሰቃየታቸውን ይናገራሉ።

ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ የክልልና የፌደራል መንግስት አካላት እንዲያውቁት ቢደረግም እዚህ ግባ የሚባል ምላሽ እንዳላገኙና ይበልጡኑ ይህ ችግር ባለበት ሁኔታ ያሉትን የጸጥታ ኃይሎች ማንቀሳቀስ ለችግሩ መስፋፋት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🤲 ረመዳን 🤲

ነገ ቅድሜ ታላቁ የረመዳን ፆም አንድ ብሎ ይጀምራል።

ቤተሰቦቻችን እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳችሁ።

ረመዳን የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የሰላም ፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር ነው።

በዚህ ታላቁ ወራችን በስቃይና መከራ ፣ በሰላም እጦት ፣ በግጭት እና በጦርነት ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ወድቀው የሚገኙ፣ በረሃብ እና ጥማት የሚሰቃዩ፣ በድርቅ የተጎዱ ፣ በህመም እና በጭንቀት፣ በተለያየ የኑሮ ፈተና ላይ ያሉትን ወገኖቻችን ሁሉ እድናስብ አደራ እንላለን።

እንዲሁም ለዓለም፣ ለሰው ልጅ ሁሉ ሰላም እና ደህንነት ፈጣሪያችንን አጥብቀን የምንማፀንበት ፤ ፈጣሪያችንም ተማጽኗችንን የሚሰማበት እንዲሆንልን እንመኛለን።

رمضان مبارك
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
#ZOnlineShopping

የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
ሙሉ የጀርባ አና የወገብ ቀበቶ  950 ብር
የትከሻ ቀበቶ  650 ብር
የመቀመጫ  (Cushion)   850 ብር
የጀርባ መደገፊያ (Pillow)  750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣ የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ
ስልክ ፦ 0989055551 ፡ ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን።
አድራሻ ፦ ቦሌ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Afar #WFP ወደ ትግራይ ጉዞ እንደጀመሩ የተገለፀላቸው የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት መጀመራቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) አስታውቋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ኢሬብቲ ደርሰው ወደ ትግራይ ማቋረጥ መጀመራቸውን የገለጸው ድርጅቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መቐለ ይገባሉ ብሏል፡፡ ከ500 ሜትሪክ ቶን በላይ የተመጣጠነ ምግብ በርሃብ አፋፍ ላይ ለሚገኙ የእርዳታው…
ፎቶ ፦ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 ተሸከርካሪዎች በሰላም የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በፎቶ አስደግፎ አስታውቋል።

ይህ ከታህሳስ 2014 ዓ.ም. አጋማሽ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በየብስ ትግራይ ክልል የደረሰ የሰብዓዊ ድጋፍ ነው።

እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ ተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ ዛሬ ይገባል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትላንትና ከወራት በኋላ የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ ማድረሱን "እጅግ አስፈላጊ የሆነ መልካም እርምጃ ነው" ብሎታል።

ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑት ተሽከርካሪዎች የደህንነት ስጋት ሳያጋጥማቸው በሰላም ትግራይ መድረስ በመቻላቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና አጋሮቹ የፌደራል መንግስትን ፣ የአፋር ክልል መንግሥት እንዲሁም የአፋር ማሕብረሰብ አባላትን አመስግነዋል።

የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 5 ሚሊዮን ሰዎች ለመድረስ የእርዳታ መጠኑን እና ፍጥነቱን በመጨመር የአቅርቦት ስራውን ማስቀጠል አለብንም ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 ተሸከርካሪዎች በሰላም የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በፎቶ አስደግፎ አስታውቋል። ይህ ከታህሳስ 2014 ዓ.ም. አጋማሽ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በየብስ ትግራይ ክልል የደረሰ የሰብዓዊ ድጋፍ ነው። እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ ተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ ዛሬ ይገባል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትላንትና…
#USA

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ የድርጅታቸው አጋር የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኮንቮይ ከመቶ ሺህ በላይ ለሆኑ የትግራይ እና አፋር ነዋሪዎች ሰብዓዊ እርድታ ማጓጓዙን ገልፀዋል።

በየብስ ወደ ትግራይ የገባው ሰብዓዊ እርዳታ ከ3 ወር በላይ ከሆነ ጊዜ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ እና አፋር ላሉ ዜጎች በቅርብ ቀናት የተደረገው ሰብአዊ እርዳታ በአወንታ የሚታይ ነው ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ፤ አስተማማኝ፣ የተረጋጋችና የበለፀገች ኢትዮጵያ ሂደትን ለማረጋገጥ ሁሉም ወገኖች ባሳዩት አውንታዊ እርምጃ እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ተጨማሪ " 30.3 ሜትሪክ ቶን " የምግብ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል ላከች። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ 5,700 ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ከ7,100 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 30.3 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦትን የጫነ አምስተኛ አይሮፕላን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ ከተማ ልካለች። ሀገሪቱ ድጋፉ እየጨመረ የመጣውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ፍላጎት…
#UAE

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ተጨማሪ የ30 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦት ወደትግራይ ክልል መዲና መቐለ ልካለች።

ከጥቂት ቀናት በፊት ሀገሪቱ ፤ 30.3 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦትን የጫነ አምስተኛ አይሮፕላን ወደ ትግራይ መላኳ ይታወሳል።

መረጃው በዱባይ በእግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው Khaleej Times ነው።

@tikvahethiopia
#የዩኒቨርሲቲ_መውጫ_ፈተና

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከሁሉም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ተማሪዎች በሰለጠኑባቸው ሙያዎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንዲወስዱ የሚጠበቀውን የመውጫ ፈተና ወደ ተግባር እንዲገባ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።

የመውጫ ፈተናውን በተመለከተ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ ባዘጋጀው ውይይት የመውጫ ፈተናው አስፈላጊነት፤ የፈተናው አወጣጥና አፈታተን እንዲሁም በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እየተደረገበት ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ መንግስት በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ጠንካራ ትግበራ እና ርምጃዎችን እንደሚወስድ አንስተዋል።

በቀጣይ አምስት ዓመታት አዲስ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደማይኖር የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይልቁንም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቅም እና ጥራት ማሻሻል ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተመራቂ ተማራዎች ፈተናዉን እንዲወስዱ በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

የመውጫ ፈተናው በእያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ በየሙያው እና ትምህርት ዘርፍ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ትግበራ ፖሊሲና ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በህግና በህክምና ሙያ የሚሰጠው የመውጫ ፈተናና የብቃት ማረጋገጫ ፍተሻ እንደ ልምድ ይወሰዳል ተብሏል።

ምንጭ፦ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሶሴትድ ፕሬስ (AP) ዘጋቢ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖላቸዋል። ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኞቹ ከአገር እንዳይወጡ የጉዞ እገዳም አስተላልፎባቸዋል። ጋዜጠኞቹ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብለ የተፈረጀውን "ሸኔ"…
ጋዜጠኞቹ ከእስር ተፈተዋል።

የአሶሴትድ ፕረስ (AP) ጋዜጠኛው አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ከእስር መፈታታቸው መረጋገጡን ኢትዮ ኒውስ ፍላሽ ዘግቧል።

ከህዳር 19 ጀምሮ ፤ " የአሸባሪውን ሸኔ ቡድንን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነበር " በሚል ጥርጣሬ ተይዘው የነበሩት ጋዜጠኞች ትላንትና በዋስ እንደተለቀቁ ተረጋግጧል።

ከቀናት በፊት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ60 ሺህ ብር ዋስትና (እያንዳንዳቸው) ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖላቸው እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bichena📍 2 ታዳጊዎችን አግተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን በቀን 19/07/2014 ዓ/ም ወደ ብቸና ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ቀርበው የማያውቁት ሰው ስልክ እየደወለ " ልጅሽን አግተነዋልና ዛሬውኑ 400,000 ብር ካላመጣሽ እንገለዋለን " እያለኝ ነው የሚል መረጃ ለፖሊስ ይሰጣሉ።…
#ተፈርዶባቸዋል

ከቀናት በፊት መጋቢት 19 ላይ በብቸና ከተማ 2 ታዳጊዎችን አግተው ከቤተሰቦቻቸው 400 ሺ ብር የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑን መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

[ https://t.iss.one/tikvahethiopia/69002?single ]

ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ በተገኘው መረጀ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።

የእነማይ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ የተጣራውን ምርመራ መዝገብ የተመለከተ ሲሆን 2ቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸውን በቀረቡ ማስረጃዎች አረጋግጧል።

መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎትም 1ኛ ተከሳሽ ተሾመ ሀብቴ በ7 ዓመት ከ6 ወር ፤ 2ኛ ተከሳሽ በሀይሉ ይዘንጋው በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

መረጃው የብቸና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia
#Alert

የጤና ሚኒስቴር የትዊተር አካውንት ተጠለፈ።

ከ204 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የሚኒስቴሩ የትዊተር አካውንት ተጠልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር ይፋዊ የትዊተር አካውንቱ #FMoHealth ዛሬ መጋቢት 24 መጠለፉን (ሃክ መደረጉን) አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በትዊተር ገጹ ላይ የሚለቀቁ ማንኛውም መረጃዎች እንደማይወክሉት ገልጿል።

@tikvahethiopia