TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Russia

ምንም እንኳን ምዕራባውያን ሀገራት ዩክሬን ገብተው ከሩስያ ጋር ጦርነት ባይገጥሙን እጅግ ከፍተኛ የሆነ ትጥቅ ለዩክሬን ኃይሎች እያቀረቡ ዩክሬንን እያገዙ ይገኛሉ።

በየዕለቱ ለዩክሬን ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የሚቀርቡ ሀገራት እና የሚደረግው የወታደራዊ ድጋፍ መጠንም እያደገ መጥቷል።

ሩስያ በበኩሏ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬን የሚልኩ ሀገራት በሩሲያ ኃይሎች ላይ ጥቅም ላይ ከዋሉ ተጠያቂ ይሆናሉ ስትል አስፈራርታለች።

በዩክሬን እና በሩስያ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዛሬ 6ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያሳድረው ተፅእኖ እየተበረታ ነው።

@tikvahethiopia
#USA #RUSSIA

አሜሪካ #ኒውዮርክ መቀመጫው ባደረገው የተመድ ዋና መስሪያ ቤት ይሰሩ የነበሩትን 12 ሩሲያውያን ዲፕሎማቶች አባራለች።

በተመድ የአሜሪካ ሚስዮን እንዳስታወቀው ከሆነ የሩስያ ዲፕሎማቶቹ "ለሀገራዊ ደህንነታችን ጠንቅ የሆኑ የስለላ ስራዎችን ሲሰሩ የነበሩ የመረጃ ሰዎች" ናቸው ሲል ገልጿል። እርምጃ ለበርካታ ወራት የተደረገውን ጥናት መሰረት በማድረግ የተወሰደ ነው ብሏል።

እርምጃው የተወሰደው በተመድ ዋና መ/ቤት ስምምነትና አሰራር መሰረት እንደሆነ ተነግሯል።

በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዝያ ዲፕሎማቶቹ እስከ መጋቢት7/22 ድረስ አሜሪካን ለቀው እንዲወጡ መጠየቃቸውን አረጋግጧል፡፡ አሜሪካ በዲፕሎማቶቹ ላይ ለወሰደችው እርምጃ “ሩሲያ ተገቢውን ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ትሰጣለች” ብለዋል።

መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ያሰራጨው አል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጠ/ሚ ፅ/ቤት🔝 የአስተዳደር #ወሰን እና #የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንና የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመት ፀድቋል የአባላት ዝርዝር ከላይ ባለው ምስል ተገልጿል። #PMOEthiopia @tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ፈረሰ።

ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠው የስልጣን ዘመን መገባደጃ ላይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የስልጣን ጊዜ እንዲራዘምለት ጠይቆ ነበር። እስካሁን በህ/ም/ቤት በኩል የኮሚሽኑን የስራ ጊዜ ለማራዘም ዝግጁነት እንደሌለ ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ቢሮውን በቅርቡ ለተቋቋመው ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያስረከበ መሆኑ ተገልጿል።

ቢሮውን ብቻ ሳይሆን መንግስት የመደበለትን በጀት እንዲያስረክብ በህ/ተ/ም/ቤት የቃል ትዕዛዝ ደርሶታል።

ኮሚሽኑ በስራ በቆየበት 3 ዓመት መንግስት በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲመድብለት የነበረ ሲሆን በስራ ዘመኑ መጠናቀቂያ 2014 በጀት ዓመት ከ21.4 ሚሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ በጀት ተይዞለት ነበር።

ከሃምሌ ወር 2013 ጀምሮ የስራ ዘመኑ እስካበቃበት ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ኮሚሽኑ ከተመደበለት በጀት ከ4 ሚሊዮን ብር በላዩን የተጠቀመ ሲሆን ቀሪውን ለምክክር ኮሚሽን እንዲያስረክብ ታዟል።

በያዝነው የካቲት ወር የህ/ተ/ም/ቤት ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ኮሚሽኑ የስራ ዘመኑ መጠናቀቁን ገልጾ ባለፉት 3 ዓመታት የከወናቸውን ስራዎች በተመለከተ የተጠቃለለ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርብ አሳስቧል።

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ግጭትና ቁርሾን በሀገራዊ እርቅ ደምድሞ ሰላም የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ይፈጥራል ፤ ለዘመናት የዘለቁ ግጭቶችን መንስኤ ከመሰረቱ በማጥናት መፍትሄ ለማምጣት ያግዛል ተብሎ የተቋቋመ ነበር።

በተጨማሪ በዳይና ተበዳዮችን የመለየት ስራ ሰርቶ ይቅር ያባብላል፣ ሌሎችም በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነትና ግዴታ ተወጥቶ ኢትዮጵያን ሰላም ያደርጋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ቢሆንም ፍሬውን ሳያሳይ የስራ ዘመኑ አብቅቷል።

የመረጃው ባለቤት፦ ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
#ዓድዋ2014

የዘንድሮዉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ ዉስጥ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይን ጨምሮ በተለያዩ ሥፍራዎች እንደሚከበር የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር አረጋገጠ።

የባሕል ሚንስቴር ሥለ በዓሉ አከባበር አዉጥቶት በነበረዉ ዝርዝር ዉስጥ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ አልጠቀሰም መባሉ ቅሬታና ተቃዉሞ አስከትሎ ነበር።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር ትናንት ባወጣዉ መግለጫ በዓሉ ሌላ ሥፍራ ይከበራል መባሉን ተቃዉሞታል።

መግለጫዉ " የማክበሪያዉ ቦታዉ ወደ ሌላ ቦታ መዛወሩ የድሉን መታሰቢያነት ዝቅ ያደርገዋል የሚል ሥጋት አለን" ነበር ያለው።

የማሕበሩ ፕሬዝደንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ የበዓሉ ማክበሪያ ቦታ ወደሌላ ሥፍራ ተዛዉሯል የሚለዉ ዘገባ " በመናበብ ችግር የተፈጠረ ነዉ " ብለዉታል።

ልጅ ዳንኤል ጆቴ የዘንድሮዉ በዓል ከዚሕ ቀደም እንደሚከበረዉ ሁሉ በዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥና በሌሎች ዝግጅቶች ይከበራል ሲሉ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
"... በእኔ እይታ ዩክሬን በአሜሪካ የተቀነባበረ ቀውስ ሰለባ ነች " - አያቶላህ አሊ ካሜኒ

የኢራን ሐይማኖታዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በዩክሬን ያለው ጦርነት መቆም እንዳለበት ገለፁ።

ካሜኒ " ማፍያ መሰል መንግስት " ብለው የጠሯት አሜሪካን የዩክሬንን ቀውስ እየፈጠረች ያለችው እሷ ናት ሲሉ ከሰዋል።

" ... የዩክሬን ግጭት ሊቆም ይገባዋል ነገር ግን የግጭቱ ስር መሰረት እውቅና ሊሰጠው የግድ ነው ፤ የግጭቱ ስር መሰረት ደግሞ ምዕራባውያን እና የአሜሪካ ፖሊሲ ነው " ብለዋል። " ዩክሬንን እዚህ ያደረሰቻት አሜሪካ ናት ፥ አሜሪካ በአገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ትገባለች፤ በመንግስት ላይ ተቃውሞዎችን ታመቻቻለች...ሁሉም እንደዚህ ያበቃል " ሲሉ ተደምጠዋል።

ካሜኒ ፥ " አሜሪካ በችግር ውስጥ የምትኖር አገዛዝ ነች " ያሉ ሲሆን " በእኔ እይታ ዩክሬን በአሜሪካ የተቀነባበረ ቀውስ ሰለባ ነች " ሲሉ ተናግረዋል።

ካሜኒ አክለው ፥ " እዚህ ላይ ሁለት ትምህርቶችን መውሰድ አለብን። በአሜሪካ እና በምዕራባውያን ኃያላን ድጋፍ ላይ የተመሰረቱ መንግስታት እንደነዚህ ያሉትን ሀገሮች ማመን እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው። ዋናው ጉዳይ የህዝቡ ነው፤ ዩክሬናውያን መንግሥታቸውን ቢደግፉ ኖሮ ሁኔታው ​​አሁን ላይ ካለው ቀውስ የተለየ ይሆን ነበር " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ፈረሰ። ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠው የስልጣን ዘመን መገባደጃ ላይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የስልጣን ጊዜ እንዲራዘምለት ጠይቆ ነበር። እስካሁን በህ/ም/ቤት በኩል የኮሚሽኑን የስራ ጊዜ ለማራዘም ዝግጁነት እንደሌለ ተነግሯል። ይህንን ተከትሎ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ቢሮውን በቅርቡ ለተቋቋመው ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያስረከበ መሆኑ ተገልጿል። ቢሮውን ብቻ ሳይሆን መንግስት…
#ABIIC

ከሶስት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን በተቋቋመበት ተመሳሳይ ወቅት ተቋቁሞ የነበረው " የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን " የስራ ዘመኑ ተጠናቋል።

የዚህም ኮሚሽን ንብረት፣ ቢሮ እንዲሁም በጀት አዲስ ለተቋቋመው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲተላለፍ ተወስኗል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑት ፕ/ር መስፍን አርአያ አዲሱ ኮሚሽን ከፌደራል መንግስት ባገኘው ይሁንታ መሰረት ቢሮ የማደራጀት ስራውን መጀመሩን አረጋገጠዋል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚገለገልባቸው ቢሮዎች በማደራጀት ላይ የሚገኘው በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው የእርቀ ሰላም ኮሚሽን እና የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በሚገኙበት ቅጥር ግቢ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽኖች ለ2014 በጀት 25.7 ሚሊዮን ብር የተመደበለት ሲሆን የቀረውን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያስተላልፋል።

የሁለቱም ኮሚሽኖች (የዕርቀ ሰላም እና የአስተዳደር ወሰንና ማንነት) በጀት ወደ አዲሱ ኮሚሽን ከመተላለፉ በፊት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሂሳቡ ተመርምሮ መዘጋት እንዳለበት ተነግሯል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ በሁለቱ ኮሚሽኖች እና በአዲሱ ኮሚሽን መካከል የሚደረገው የርክክብ ሂደትን በተመለከተ ፥ " እኛ ዝም ብለን መውረስ አንፈልግም። መጀመሪያ ያላቸው ንብረት ኦዲት ተደርጎ ለመንግስት ርክክብ ካደረጉ በኋላ ወደ እኛ እንዲተላለፍ ጠይቀናል " ሲሉ መናገራቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እ.ኤ.አ ከጥር 2021 እስከ ጥር 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ ክልል ከቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ለተነጣጠሉ 41,326 ሰዎች ነጻ የስልክ ማስደወል አገልግሎት መስጠቱን ገልጿል።

#ICRC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የስያሜ ለውጥ አድርጓል ? ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ስያሜ ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል። በጉዳዩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት መኩሪያ ንጋቱ ለ @tikvahuniversity ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመቋቋሚያ አዋጁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ደረጃና ስያሜ የመስጠት…
#Update : የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የስያሜ ለውጥ አድርጓል።

ተቋሙ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ " የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት " የሚለውን ስያሜ መጠቀም ጀምሯል።

ባለፈው መስከረም የወጣው የተቋማትን አደረጃጀት የከለሰ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ መታወጁን ተከትሎ፤ በማህተም ጭምር "ኢንስቲትዩት" የሚለውን ስያሜ መጠቀም መጀመሩን የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኩሪያ ንጋቱ ለ @tikvahuniversity ተናግረዋል።

አዋጁ መስከረም ላይ ሲወጣ ከነበረው የተሻሻሉ ነገሮች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊው፤ ደንቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት ወደፊት እንደሚወጣ ገልጸዋል።

"ደንቡ ሲወጣ ምን ይዞ እንደሚወጣ ባይታወቅም፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት ከስያሜ ለውጥ ጋር ያነሱት ጥያቄ አሁንም እንደተጠበቀ ነው" ብለዋል።

ተቋሙ "የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ" የሚለውን ስያሜ ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ብቻ ተጠቅሟል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA #ETHIOPIA

አሜሪካ 840,060 ዶዝ የPfizer የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደረገች።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሜሪካ በ #COVAX በኩል ለኢትዮጵያ የለገሰችው ተጨማሪ 840,060 ዶዝ የPfizer የኮቪድ-19 ክትባት ዛሬ አዲስ አበባ መድረሱን ገልጿል።

ዛሬ አዲስ አበባ የደረሰው 840,060 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት አጠቃላይ እስካሁን ድረስ በአሜሪካ በኩል ለኢትዮጵያ የተደረገውን ልገሳ 7 ሚሊዮን እንዲጠጋ ማድረጉን ተገልጿል።

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

የዓድዋ ድል 126ኛ የድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 23 ቀን 2014 ዓ/ም ፒያሳ በሚገኘው ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ እና አዋሬ አካባቢ በሚገኘው አድዋ ድልድይ ዙሪያ በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ በምኒሊክ አደባባይ የሚካሄደው ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ

- በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት

- ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ

- ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር

- ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ

- ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት

- ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ

- ከእንቁላል ፋብሪካ በዮሃንስ ቤተክርስቲያን ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዮሃንስ መብራት ላይ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በተመሳሳይ አድዋ ድልድይ አካባቢ ለሚከናወነው ፕሮግራም

- ከመገናኛ በሲግናል ወደ አድዋ ድልድይ ድንበሯ ሆስፒታል መታጠፊያ

- ከካዛንቺ በመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ወደ ሴቶች አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ መታጠፊያ

- ከእንግሊዝ ኤምባሲ ባልደራስ ኮንደሚኒዬም ወደ አድዋ ድልድይ እንግሊዝ ኤምባሲ ጋር

- ከቀበና በአዋሬ ወደ አድዋ ድልድይ የሚወስደው ቤሌኤር መብራት

 - ከፓርላማ መብራት ወደ አዋሬ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት

- ከካዛንቺስ ወደ አድዋ ድልድይ የሚወስደው መንገድ እንደራሴ መታጠፊያ

- ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ የሚወስደው መንገድ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቃል፡፡

በዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚከናወነው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከንጋቱ 12፡00 በተመሳሳይ አድዋ ድልድይ አካባቢ ለሚካሄደው ፕሮግራም ከዛሬ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ክልክል ነው።

በዓሉን በሚከበርባቸው ስፍራዎች ላይ ፍተሻ ስለሚኖር ታዳሚያን ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት መዘዝ ፦ 📉 የሩሲያ ሩብል ወርዶ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ሆኗል። 📈 ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ7% ወደ 105 ዶላር ጨምሯል። 📈 የስንዴ ዋጋ በዘጠኝ ዓመት ውስጥ ሪከርድ በሆነ ሁኔታ ንሯል። 📈 ወርቅ በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋው ጨምሯል። 📈 የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በ1 ሺ ኪዩቢክ ሜትር 52 በመቶ ወደ 1,560 ዶላር በላይ ንሯል። 📉 ቢትኮይን ወደ 35,000 ዶላር…
ነዳጅ📈

ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በ10 % ወደ ' 107 ዶላር ' ከፍ ብሏል፤ ይህም እኤአ ከ2014 በኃላ ከፍተኛው እንደሆነ ነው የተነገረው።

ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ የምትገኘው ሩሲያ በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ የነዳጅ ዘይት አምራችና ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ ሀገር ነች።

አጠቃላይ ሩሲያ በዓለም የነዳጅ ምርት 10 % ድርሻ አላት። 

የዩክሬን እና የሩስያ ጦርነት፤ ጦርነቱን ተከትሎ ምዕራባውያን ሩስያ ላይ እያወረዱት ያለው ጠንካራ ማዕቀብ በዓለም ነዳጅ ዋጋ ላይ ከዚህም ከፍ ያለ ጭማሪ ሊያመጣ እንደሚችል ይሰጋል።

@tikvahethiopia
#UN #RUSSIA

ዛሬ በተካሄደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ መናገር ሲጀምሩ በምክር ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከነበሩ ተሳታፊዎች ብዙዎቹ ተነስተው ወጥተዋል።

ሰርጌይ ላቭሮቭ በምክር ቤቱ ፊት በአካል ከመገኘት ይልቅ በቪድዮ ኮንፈረንስ እንዲያደርጉ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በንዴት መንፈስ ሆነው ወደ ጄኔቫ ለመጓዝ በሰማዮቻቸው ላይ እንዳይበርሩ ሃገሮቹ መከልከላቸውን፣ በዚህ የአውሮፓ ኅብረት የመንቀሳቀስ ነፃነታቸውን መጋፋቱን ገልፀዋል።

ላቭሮቭ ለ8 ደቂቃ በቆየ ንግግራቸው " በዋሺንግተን ይመራል " ያሉትን " የምዕራቡን የጋራ ፖሊሲ " ሲያወግዙ ይህም " የኪየቭን አገዛዝ ላለፉት 14 ዓመታት በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት እንዲያካሂድ አድርጎታል " ብለዋል።

የዩክሬኑን አስተዳደርን በወንጀል አድራጎቶች የኮነኑት ሰርጌይ ላቭሮቭ " በሩሲያና ተገንጣዮቹ ዳኔትስክ እና ሉሃንስክ ውስጥ ባሉ ሩሲያኛ ተናጋሪ ዜጎቹ ላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጦርነት አውጆ ቆይቷል " ሲሉ ከስሰዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን " ዕጣ ፈንታቸውን በግድ የለሽነት እያዩ መቀጠል ባለመቻላቸው ለአካባቢዎቹ ነፃነት ዕውቅና ሰጥተው " ነዋሪዎቻቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከፍተዋል " ብለዋል።

ይህንን ቀደም ሲል በፑቲን በራሳቸው የተነገረ ምክንያት " ማሳሳቻ ሃሰተኛ መረጃ የማሠራጨት ዘመቻ" ሲሉ ያጣጣሉት ምዕራባዊያን መንግሥታት ሩስያ አካሂዳዋለች ላሉት ወረራ ታይቶ በማይታወቅ ስፋት ምላሽ ሰጥተዋል።

ላቭሮቭ በእነሱም ላይ ውግዘት ማሰማታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ቪድዮ - ተሳታፊዎች ተነስተው ሲወጡ (Elisabeth Tichy-Fisslberg)

@tikvahethiopia