TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የኬንያንው ፕሬዜዳንት ተማፅኖ ....

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት መቋጫ ያገኝ ዘንድ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ከሚነገርላቸው ሀገራት ጎረቤታችን ኬንያ አንዷ ናት።

የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዚህ በፊት ለግጭቱ መቆሚያ መፍትሄ እንደመጣ ጥሪ ሲያቀርቡ እንደበር አይዘነጋም።

ትላንት ለሊት የተ.መ.ድ ዋና ፀሀፊት አንቶኒዮ ጉተሬዝን መልዕክት ተንተርሰው በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ተማፅነዋል።

ኬንያታ ምን አሉ ?

- የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚጋሩ አስታውቀዋል።

- በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ውስጥ የሚሳተፉ አካላት ሁሉ ጦርነቱን እንዲያቆሙም ተማፅነዋል።

- የቀጠለው ግጭት የኢትዮጵያን ህዝብ እየዘረፈ እና የዚህ ታላቅ ህዝብ ባህልና ስልጣኔ ውስጥ ያለውን ክብር እያሳጣ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

- አስተማማኝ ሰላም የሚሰፍነው እንዲሁም የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን የምትሆነው ሁሉም የኢትዮጵያ አካላት ዘላቂ በሆነና በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ባለው መንገድ ፈተናዎችን ማለፍ ሲችሉ ብቻ ነው ብለዋል።

- ሁሉንም ያሳተፈና በመስማማት መንፈስ የሚካሄደው ሀገራዊ ውይይት፤ በግጭቱ ምክንያት ለተጎዱ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ማህበረሰቦች ያለውን ሸክም ከማቅልለ አንጻር ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

- የኢትዮጵያ፣ የቀጠናውና የአህጉሪቱ ብልፅግና፤ ዘላቂ በሆነ ሰላም እና ደህንነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። አንድ ላይ ሆነን የተሻለ ዓለም መፍጠር እንችላለን ብለዋል።

ምንጭ፦ State House Kenya

@tikvahethiopia
#Borana

የኢትዮጵያጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስጣናት በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ጉብኝቱ ፥ " በድርቅ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለመገምገም " እንደሆነው ገልጿል።

ፅ/ቤቱ የዝናብ ውሀ እጥረት መከሰቱ የእንስሳት መኖ እጥረት እና የውሃ አቅርቦት ውስንነትን ጨምሮ በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችን ማስከተሉን አሳውቋል።

በሌላ መረጃ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ያቤሎ ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መጎብኘታቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#GamoZone

በጋሞ ዞን የሰዓት እላፊ ማሻሻያ ተደረገበት።

የጋሞ ዞን ኮማንድ ፖስት #ለተሽከርካሪዎች የሠዓት ማሻሻያ ማድረጉን ትላንት ምሽት አሳውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ የዞኑ ሠላም እንዲጠበቅ ለማድረግ በቂ የሆነ የሕዝባዊ ሠራዊት በመሠልጠኑ እንዲሁም የህብረተሰቡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዳይገደብ የሠዓት ማሻሻያ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልጿል።

በዚሁ መሠረት፦

- ለባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል እስከ ምሽቱ 3:00 ሠዓት

- ለባለሦስት እግር ባጃጅ እስከ ምሽቱ 4:00 ሠዓት ማሻሻያ ማድረጉን የዞኑ ኮማንድ ፖስት ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle 📍 የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በመቐለ ከተማ ለሚገኙ ሆስፒታሎች ወሳኝ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ማከፋፈል መጀመሩን ትላንት አሳውቋል። ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያዎቹን አምስት በረራዎች ማጠናቀቁን ገልፆ በነበሩት በረራዎች ኢንሱሊንን ጨምሮ እጅግ አስቸኳይና አስፈላጊ መድሃኒቶችን ማጓጓዙን ገልጿል። ይኸው ተግባር በዚህ ሳምንትም እንደሚቀጥል አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle📍

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በዚህ ሳምንት 2 በረራዎችን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በማድረግ የህክምና ቁሳቁሶችን አድርሷል።

ባለፈው ሳምንት በ5 በረራዎች እጅግ አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ማጓጓዙና ማከፋፈል መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል።

በዚህ ሳምንት ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና ከቀይ መስቀል የቀረቡ መድሃኒቶችና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶችን በመያዝ 2 ተጨማሪ በረራዎች ወደ ትግራይ ክልል ተደርገዋል።

በዚህ ሳምንት በቀሩት ቀናት እና በሚቀጥሉት ሳምንታት ተመሳሳይ በረራዎች እንደሚደረጉ እና ይህም ቀጣይነት ያለው እርዳታ እንደሚሆን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ላለፉት ወራት የህክምና አቅርቦት ማድረግ እንዳልቻለ ገልፆ አሁን እየተደረጉ ያሉት እጅግ በጣም አስቸኳይ ለሰዎች ህይወት አድን የሚሆኑ አቅርቦቶች ናቸው ብሏል።

ከዚህ በተሻለ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች እና መድሃኒቶችን ለማድረስ ከአየር ላይ በረራ በተጨማሪ በየብስ ለማጓጓዝ መታሰቡን ይህን ተግባራዊ ለማድረግም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአፋር ክልል እና አማራ ክልል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ገልጿል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን በመጠቀም ካሉበት ሆነው የቪዛ ካርድዎን ማዘዝ የሚችሉ ሲሆን፣ ካርድዎ ሲደርስ በአቅራቢያዎ ከሚገኙት የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎቻችን መውሰድ ይችላሉ።

ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ የሚያገኙበትን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን በመጠቀም ህይዎትዎን ያቅልሉ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU2022Summit እስካሁን የየት ሀገር ሚኒስትሮች ገቡ ? ነገ ለሚጀምረው የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ናቸው። እስካሁን የገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፦ 🇿🇼 ፍሬድሪክ ሻቫ (ዝምባብዌ) 🇸🇹 ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ (የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ) 🇨🇲 ሌዡን ቤላ ቤላ (ካሜሩን) 🇹🇩 ማህማት ዜኑ…
#AU2022Summit

የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ40ኛዉ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።

እስካሁን የገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፦

🇿🇼 ፍሬድሪክ ሻቫ (ዝምባብዌ)
🇸🇹 ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ (የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ)
🇨🇲 ሌዡን ቤላ ቤላ (ካሜሩን)
🇹🇩 ማህማት ዜኑ ሸሪፍ (ቻድ)
🇨🇮 ካንዲያ ካሚስኮ ካማራ (ኮትዲቯር)
🇸🇴 አብዲሳድ ሙሴ አሊ (ሶማሊያ)
🇨🇬 ዢያን ክላውዴ ጋኮሶ (የሪፐብሊክ ኮንጎ)
🇳🇪 ሀሱሚ ማሹዱ (ኒጀር ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)
🇿🇦 ዶ/ር ናለዲ ፓንዶር (ደቡብ አፍሪካ)
🇸🇳 አሲታ ቶል ሳል (ሴኔጋል)
🇲🇷 እስማኤል ኡልድ ሼክ አህመድ (ሞሪታኒያ)
🇩🇯 ሙሀሙድ አሊ የሱፍ (ጂቡቲ)
🇱🇾 ናጅላ አልማንጉሽ (ሊቢያ)
🇳🇬 ጃፍሬ ኦኖማ (ናይጄሪያ)
🇦🇴 ቲቴአን ቶኒያ (አንጎላ)
🇺🇬 ኦሪም ሄነሪ ኦክሎ (ዩጋንዳ - የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ)
🇲🇼 ናይሲ ቴምቦ (ማላዊ)
🇩🇿 አምባሳደር ራምታን ላማምራ (አልጀሪያ)
🇬🇦 ሙበሌት ቡቤያ (ጋቦን)
🇲🇦 ቦሪታ ናስር (ሞሮኮ)
🇹🇳 ኦተማን ጃርዲ (ቱኒዚያ)
🇲🇬 ፖትሪክ ራአጆልንት (ማዳጋስካር)
🇨🇻 ማሪያና ዳጃምላ (ኬፕ ቨርዲ)
🇧🇮 አልበርት ሻንግሮ (ቡሩንዲ)
🇬🇶 ሲሞኔ ኦዮኖ ኢሶኔ (ኢኳቶሪያል ጊኒ)
🇰🇲 ዶህር ዶል ከማል (ኮሞሮስ)
🇸🇿 ቱሊሲሌ ድላድላ (ስዋህቲኒ)
🇰🇪 ረይሼል ኦማሞ (ኬኒያ)
🇲🇿 ቬሮኒካ ማካሞ ንዶቮ (ሞዛምቢክ)
🇹🇬 ኮምላን ኢዱ ሮበርት (ቶጎ)
🇿🇲 ስታንሌይ ካኩቦ (ዛምቢያ)
🇧🇼 ሌሞሀንግ ኪዌፔ (ቦትስዋና)
🇬🇲 ሳፊ ሳንካሬ (ጋምቢያ)
🇳🇦 ኔቱምቦ ናንዲ ንዳይትዋህ (ናሚቢያ - ም/ ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)
🇪🇷 ኦስማን ሳሌህ (ኤርትራ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፅጌሬዳ_ግርማይ የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን ግድያ በተመለከተ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ መረጃ ሰጥቷል። ሰኞ ዕለት ህይወቷ ያለፈው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተጠረጠረ ተማሪ ትላንት ከሰዓት ፍርድ ቤት ቀርቧል። ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት የሰጡ የተጠርጣሪው #ሁለት_ጓደኞቹ የሚከተለውን ብለዋል :- "ተማሪ ፅጌሬዳ ከተጠርጣሪ ወንጀለኛው ጋር ግንኙነት…
#Update

የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

በምትማርበት ተቋም አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ውስጥ በሰው እጅ በአሳዛኝ ሁኔታ የተገደለችው የ20 ዓመቷ ወጣት ፅጌሬዳ ግርማይ ስርዓተ ቀብሯ ተፈፅሟል።

የፅጌሬዳ ስርዓተ ቀብር የተፈፀመው በዳንሻ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነው።

ሰኞ ጥር 23 /2014 ምሽት ላይ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተገደለችው ፅጌሬዳ ግርማይ የሁለተኛ ዓመት የሆቴል እና ቱሪዝም ማኔጅመት ተማሪ ነበረች።

የወጣቷን ህይወት እንደቀጠፈ የተጠረጠረው ተማሪ ከትላንት በስቲያ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ቀጣይ ቀጠሮ መስጠቱን መግለፃችን ይታወሳል።

ውድ ቤተሰቦቻችን @tikvahuniversity (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን የፍርድ ሂደት እስከመጨረሻው ድረስ ተከታትሎ ለማሳወቅ ጥረት ያደርጋል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የሄኖክ ታደለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሳምሶን ተ/ሚካኤል የት ነው ያለው ? ከቀናት በፊት በኬንያ ናይሮቢ የታፈነው ኢትዮጵያዊ ሳምሶን ተ/ሚካኤል ጉዳይ እጅጉን እንዳሳሰባቸው ባለቤታቸው ሚለን ሃለፎም አሳወቀች። ሚለን ይህን ያሳወቀችው ለቢቢሲ በሰጠችው ቃል ነው። ሚለን ባለቤቷ ሕዳር 10 ነዋሪ በሆኑባት ናይሮቢ ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከመንገድ ላይ በኃይል ከተወሰደ በኋላ አድራሻው አለመታወቁን ተናግራለች። መንገደኛ ቀርጾት በማሕበራዊ…
ሳምሶን ተክለሚካኤል እስካሁን ያለበት አልታወቀም፤ የት ነው ያለው ?

ኢትዮጵያ የኬንያ ባለስልጣናትን ናይሮቢ ውስጥ መሀል መንገድ ላይ ስለታገተው ሳምሶን ተክለሚካኤል ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቃለች።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ አለም ኬንያ ለሚገኝ የሃገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ የኬንያ የህግ አስከባሪ አካላት በንግድ ስራ ላይ የተሰማራው ሳምሶን ተክለሚካኤል የት እንዳለ እንዲሁም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እንዲያብራሩ መጠየቃቸውን ገልፀዋል።

አምባሳደር መለስ ኢትዮጵያ የኬንያ ባለስልጣናት እና የህግ አስከባሪ አካላትን በማነጋገር ስለ ዜጋዋ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጣት መጠየቋን አስረድተዋል።

ሳምሶን በመጥፋቱ ቤተሰቦቹ አሁንም ድረስ ከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሆኑ የገለፁት አምባሳደሩ ክስተቱ የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያንም እንደጎዳው ገልፀዋል።

አምባሳደሩ፥ " በህዳር ወር የተከሰተው ክስተት ኢትዮጵያን አስደንግጧል። በኪሊሌሽዋ በጠራራ ፀሀይ፣ በህዝብ በፊትና ፖሊስ ባለበት ነው የተከሰተው፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሳምሶን ተክለሚካኤልን አላየንም" ብለዋል።

" የኬንያ ባለስልጣናትን ቀርበን ስለ ዜጋችን ደህንነት መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀን ምርመራዎች እስኪጠናቀቁ ድረስ እየጠበቅን ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ አለም " ባለፉት 3 ወራት ቤተሰቦቹ እና ልጆቹ በጭንቀት ውስጥ ናቸው ሰፊው የኢትዮጵያ ማህበረሰብም እንዲሁ፤ ህዝባችን ከዚህ ሁኔታ እንዲወጣ እንፈልጋለን። በእኛ በኩል ዜጋችን ሳምሶን ያለበትን እስክናውቅ ድረስ አንመለስም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ምርመራው ረዘም ያለ ጊዜ መውሰዱን የሚገልፁት አምባሳደሩ፤ " 3 ወር አጭር አይደለም፤ እኛ ጉዳዩ በእጅጉ ያሳስበናል፤ ይህንም የኤምባሲው ተልዕኮ ይጋራል" ሲሉ ገልፀዋል።

ሳምሶን የት ነው ያለው ?

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና አቡበክር አል ባግዳዲ መገደሉ ተረጋገጠ! የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአይኤስ-አይኤስ (ISIS) መሪው አቡበክር አልባግዳዲ አሜሪካ በወሰደችው የጥቃት መገደሉን አረጋግጠዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ የሀገሪቱ ወታደሮች በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባካሄዱት የፀረ ሽብር ዘመቻ የአይ ኤስ መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ መገደሉን አስታውቀዋል።…
#NewsAlert

አሜሪካ አቡ ኢብራሂም አል-ሃሺሚ አል-ቁራይሺ መሞቱን አስታወቀች።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባይደን የISIS መሪ አቡ ኢብራሂም አል-ሃሺሚ አል-ቁራይሺ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ አሜሪካ ያካሄደችውን ወታደራዊ ኦፕሬሽንን ተከትሎ መሞቱን ተናግረዋል።

ባይደን፤ “ ሁሉም አሜሪካውያን ከኦፕሬሽኑ በደህና ተመልሰዋል ” ሲሉም ገልፀዋል። የፀረ ሽብር ኦፕሬሽኑ የአሜሪካን ህዝብና አጋሮቻችንን ለመጠበቅ እንዲሁም ዓለምን የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ለማድረግ ነውም ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን ዛሬ እንደተናገሩት የአሜሪካ ልዩ ኦፕሬሽን ኮማንዶዎች ባኬሄዱት ኦፕሬሽን የISIS መሪ ተገድሏል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች እንዳሉት ደግሞ በጥቃቱ ከተገደሉት ቢያንስ 13 ሰዎች መካከል ሴቶች እና ህጻናት (6 ህፃናት እና 4 ሴቶች) ይገኙበታል።

አንድ ከፍተኛ የአስተዳደር ባለስልጣን ደግሞ አል-ቁራይሺ በኦፕሬሽኑ መጀመሪያ ላይ ቦንብ አፈንድቶ ህይወቱ እንዳለፈ እና ከሱ በተጨማሪ ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ የገዛ ቤተሰቦቹ አባላት ህይወት እንዳለፈ ለኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

ፔንታጎን በበኩሉ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ የተሳካ ኦፕሬሽን መካሄዱን በመግለፅ በአሜሪካ በኩል ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጿል። ስለሲቪል ሰዎች መሞት ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia