TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ምንም አይነት የቴሌግራም ገፅ የለንም " - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ምንም አይነት የቴሌግራም ገፅ እንደሌለው አሳውቋል።

ሳፋሪኮም በቅርቡ የተለያዩ የቴሌግራም ገጾች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስም ተከፍተው መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተረድተናል ብሏል።

ድርጅቱ እስከአሁን ምንም የቴሌግራም ገጽ እንደሌለው እያስታወቀው ሳፋሪኮም በገጾቹ የሚተላለፉት መረጃዎች በድርጅቱ እውቅና እንደሌላቸው አረጋግጦልናል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በፌስቡክ፣ ትዊተር ፣ ሊንክድኢን እና ቲክቶክ ላይ ይፋዊ ገፆች ያሉት ሲሆን በፌስቡክ፣ ትዊተር እና ቲክቶክ አድራሻው #SafaricomET እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የLinkedIn አድራሻው Safaricom Telecommunication Ethiopia PLC. እንደሆነም ገልጿል።

@tikvahethiopia
#FireAlert🚨

በአዲስ አበባ ከዑራኤል ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ የእሳት አደጋ መከሰቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት አድርገዋል።

ፎቶ እና ቪድዮ : Rebka F. & Israel Taye (Tikvah-Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ኑሆ ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አርቲስት ኑሆ ጎበና ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ አርቲስት ኑሆ ጎበና በአፋን ኦሮሞና በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ ዜማዎችን ለአድማጭ አበርክቷል፡፡ አርቲስት ኑሆ ፤ ከአባቱ አቶ መሃመድ ጎበና እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ አደም በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡ #ኤፍቢሲ/#ኦቢኤን @tikvahethiopia
#Adama

የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በአዳማ ከተማ ተፈፅሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ቤተስቦቹ፣ አርቲስቶች፣ ወዳጆቹ ፣ አድናቂዎቹ እንሲሁም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

አርቲስት ኑሆ ጎበና በድሬደዋ ቀፊራ ገንደጋራ በ1940 ዓ.ም ነበር የተወለዱት ፤ ለረጅም አመታት ለኦሮሞ ኪነ ጥበብና ለአፋን ኦሮሞ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አንጋፋ አርቲስት ነበሩ።

ፎቶ ፦ ኦቢኤን

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን በመጠቀም የካናል ፕላስ ወርሃዊ ክፍያና የተለያዪ አይነት የአገልግሎት ክፍያዎችን ካሉበት ሆነው ይፈፅሙ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#FireAlert🚨 በአዲስ አበባ ከዑራኤል ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ የእሳት አደጋ መከሰቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት አድርገዋል። ፎቶ እና ቪድዮ : Rebka F. & Israel Taye (Tikvah-Family) @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

📍ቦሌ አትላስ አካባቢ የደረሰው አደጋ 9:20 አካባቢ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ዛሬ ከሰዓት 8 ሰዓት አካባቢ ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኙት የግንባታ ዕቃዎች መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋው በቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስትያን እና በአትላስ እንዲሁም በፀጋ ሆስፒታል መሃል ላይ በሚገኙት የንግድ ሱቆች መጋዘኖች ላይ የደረሰው።

የአደጋው መነሻ እስካሁን አልታወቀም።

ቁጥራቸው 7 የሚደርስ የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን እሳት አደጋ መከላከል ተሸከርካሪዎች የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች አንዳይዛመት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

እሳቱ 9፡20 አካባቢ ማጥፋት ተችሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደርጉት የነበረው ርብርብ የሚደነቅ እንደነበር ተገልጿል።

Credit : ETHIO FM 107.8
ቪድዮ : አቤል

@tikvahethiopia
#GeneralAbebawTadesse

ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተቃረብኩኝ ባለበት ወቅት የውጭ ሀገር ኃይሎች አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ኃይል አዘጋጅተው እንደነበር የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጄነራል አበባው ታደሰ በፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ተናግረዋል።

ጄነራል አበባው፤ " ጣርማ በር ... ሲገባ እኮ ሰላም አስከባሪ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ፣ እገሌ አገር እገሌ አገር ልል እችላለሁ ፥ ሚሲነሪ ወታደር እየተዘጋጀ እነሱን የሚያግዝ ፣ ሽግግር መንግስት እየቆመ፣ ሽግግር መንግስት ለማቋቋም ሰነድ ተዘጋጅቶ የስልጣን ክፍፍል እየተጀመረ፣ ሸኔም የኦሮሞን የመገንጠል እንዲያነሳ ጥያቄ እየተስተካከል ሀገር ነው እኮ የነበረው " ብለዋል።

ነገር ግን በተካሄደው የ " ዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት " ሀገርን ከብተና ማዳን እንደተቻለና ሀገር እንደዳነ ጄነራሉ ተናግረዋል።

ጄነራል አበባው ፥ " የመጀመሪያው ውጤት ሀገር ነው የዳነው ፣ ሀገር ከብተና ነው የዳነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲገቡ የእኔ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከሀገር በላይ አይደለም፤ ምንም ማለት አይደለም ነው፤ ይሄን ሁሉ ጉድ ስለሚያውቁ ስለዚህ ሀገር ከማውቀው ወንድሞቼ ጋር ሆኜ ደረቴን ሰጥቼ መዋጋት አለብኝ ብለው ነው የሄዱት። ያን ያክል የሚያስኬድ ነገር ነበራቸው ወይ ? ተብሎ ከተጠየቀ ግን ኢትዮጵያን ሊያፈርሷት ጫፍ ደርሰው ነበር " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GeneralAbebawTadesse ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ተቃረብኩኝ ባለበት ወቅት የውጭ ሀገር ኃይሎች አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ኃይል አዘጋጅተው እንደነበር የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጄነራል አበባው ታደሰ በፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ተናግረዋል። ጄነራል አበባው፤ " ጣርማ በር ... ሲገባ እኮ ሰላም አስከባሪ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ፣ እገሌ አገር እገሌ አገር ልል…
#GeneralAbebawTadesse

ጄነራል አበባው ታደሰ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ዘልቆ ያልገባበትን ምክንያትም ከፋና ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጠይቀው መልሰዋል።

ጄነራል አበባው ታደሰ ምን አሉ ?

" ... ለምንድነው የቆምነው ? የሚለው በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። ... ለምን ቆምን የሚለው ሲገለፅ ምዕራፍ አንድን ጨርሰናል ነው የሚለው ስለዚህ ምዕራፍ አንድን ጨርሰናል ማለት ቃል በቃል ምዕራፍ ሁለት አለ ማለት ነው።

መቐለና ትግራይ ግን የኢትዮጵያ ግዛት ነው ፤ ማንም እኛን አያቆመንም ፤ እንገባለን ጠላት እናጠፋለን ፤ ይሄ ምንም የሚያሻማ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ ህዝብም እንዳለቀ አድርጎ አይደለም እራሱ መውሰድ ያለበት ፤ አላለቀም።

በዚህ በኩል ሸኔ ነኝ፣ እንደዚህ ቅማንት ነኝ ፣ በዚህ ምናምን ነኝ የሚባል ነገር ከዚህ በኃላ እየሰራም፤ የጊዜ ጉዳይ ነው፤ አሁን አንድ ትልቅ ግዳጅ ስላለን ጠላት ስላለን ነው እንጂ ይሄ የጊዜ ጉዳይ ነው መጥፋት አለበት።

መጥፋት ማለት ምን ማለት ነው ? ይሄ ትጥቅ አንስቶ በሀገር ውስጥ መዋጋት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ስልጣኔ አይደለም ፤ ስልጣኔው በሀሳብ ነው ሀሳቡን ይሽጥ " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
ቪኪ ፎርድ ኢትዮጵያ ናቸው።

የዩናይትድ ኪንግደም (UK) የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ እዚህ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ቪኪ ፎርድ ዛሬ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተገናኙበት ወቅት ዩናይትድ ኪንግደም የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እንደሚያሳስባት ገልፀው ነገር ግን ዘላቂ ሰላም በኢትዮጵያ እንደሚሰፍን ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በቅርቡ የተካሄደውን የእስረኞች መፈታት እና የብሔራዊ ውይይቱን በደስታ እንደሚቀበሉ አሳውቀዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም እና ኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ አጋርነት እና መልሶን ግንባታን በተመለከተ የዩናይትድ ኪንግደምን ድጋፍ በተመለከተ መነገራቸውን ቪኪ ፎርድ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ቪኪ ፎርድ ከገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጋር መገናኘታቸውን ገልፀዋል።

እንዲሁም ደግሞ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ሰላም አስፈላጊነት እና ስለ ዩናትድ ኪንግደም እና ኢትዮጵያ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 5,028
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 643
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 22
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 760
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 379

ዛሬ ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ አጠቃላይ 2,399 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 50 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሞሊ ፊ እና ሳተር ፊልድ በሱዳን ውይይት አድርገዋል። በቀናት በፊት ሳዑዲ አረቢያ የነበሩት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ሱዳን ገብተው በሱዳን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ በአዲስ አበባ ተገኝተው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ…
#Update

📍ሱዳን

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ዛሬ በሱዳን ከሉዓላዊው ምክር ቤር ወታደራዊ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ሀገራቸው አሜሪካ ለሱዳን ህዝብ ነፃነት፣ ሰላም እና ፍትህ ቁርጠኛ መሆኗል ግልፀው ፤ ብጥብጥ እና ሁከት ሳይቆም የፖለቲካ ሂደቱ ሊቀጥል እንደማይችል ግልጽ አድርገዋል።

በተጨማሪም ባለስልጣናቱ ከዶክተር ኤል ሃዲ ኢድሪስ ጋር በቅርቡ በካርቱም እና በዳርፉር ስለተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ እንዱሁም ሱዳን አሁን ካለችበት የፖለቲካ ችግር እንዴት ልትወጣ እንደምትችል ተነጋግረዋል።

ሞሊ ፊ እና ዴቪድ ሳተርፊልድ ባወጡት መግለጫ የሱዳን ጦር በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስደውን የኃይል እርምጃ ያወገዙ ሲሆን ግጭት ካልቆመና የሱዳንን ህዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ በሲቪል የሚመራ መንግስት ወደቦታው ካልተመለሰ የቆመው የአሜሪካ እርዳታ እንደማይቀጥል አሳውቀዋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

በቀጣይ በአዲስ አበባ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉ።

@tikvahethiopia
#Balderas

" ጉዳት ያደረሱት የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እንጠይቃለን " - ባልደራስ ፓርቲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ ዛሬ ጥር 12/2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የወይብላ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለጥምቀት የወጣ ታቦታ እና አጅበውት በነበሩት ህዝበ ክርስቲያን ላይ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ተኩስ በመክፈት ታቦቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገባ ባደረጉት ክልከላ እና ይህን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ምዕመናን ለጉዳት መዳረጋቸውን አሳውቋል።

ፓርቲው፥ " በዚህ ግጭት ከልጅ እስከ አዛውንት የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት በምዕመናኑ ላይ መድረሱን ተገንዝቤያለሁ " ብሏል።

በርካታ ምዕመናን በህክምና መስጫ ተቋማት ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በመግለጫው ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ገልፆ ፥ " የኦህዴድ/ብልፅግና ’መንግስት’ አሁንም ህግ የማስከበር ተቀዳሚ ተግባሩን አለመወጣቱን ባልደራስ አበክሮ ያወግዛል " ብሏል።

አክሎም ፥ " አሁንም እየደረሰ ላለው ውጥረት እና ግጭት ’መንግስት’ ህግ እንዲያስከብር እንጠይቃለን። ጉዳት ያደረሱትን የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑም ባልደራስ ይጠይቃል " ብሏል በመግለጫው።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ወይም ከኢኦተቤ መገናኛ ብዙሀን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት በኩል የወጣ ተጨማሪ መረጃ ለመፈለግ ጥረት ብናደርግም ለጊዜው ማግኘት አልቻልንም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አደጋውን ያደረሱት የሠራዊቱ አባላት አይቀጡም " - ፔንታገን ባለፈው ነሃሴ ወር በአፍጋኒስታን በአሜሪካ ድሮን ለተገደሉ 10 ሰላማዊ ሰዎች የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ፔንታገን አደጋውን ያደረሱትን የሠራዊቱን አባላት እንደማይቀጣ አስታወቀ፡፡ ከዚህ ውሳኔ የተደረሰው የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን ከሁለት የበላይ አዛዦች የቀረበላቸውን አስተያየት ካጸደቁ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የፔንታገን ቃል…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Video : የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን በነሃሴ 29 (እ.ኤ.አ.) በካቡል ከተማ 10 ሰዎች የተገደሉበትን የድሮን ድብደባ የሚያሳይ ቪዲዮ ዛሬ ሀሙስ አውጥቷል።

በዚህ የድሮን ድብደባ 7 ህፃናትን ጨምሮ 10 የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸው ይታወሳል።

በድሮን ለተገደሉት 10 ሰላማዊ ሰዎች የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፣ ፔንታገን አደጋውን ያደረሱትን የሠራዊቱን አባላት እንደማይቀጣ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናበተች። ሀገራችን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆናለች። ብሄራዊ ቡድናችን ዛሬ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ እኩል ቢለያይም በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል። በዛሬው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምት ለሀገራችን ብቸኛዋን ጎል በ52ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ @tikvahethiopia
ፎቶ : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ደርሷል።

ብሄራዊ ቡድኑ አዲስ አበባ ሲደርስ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፣ ከፌዴሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች እና ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ አካላት አቀባበል አድርገዋል።

የብሄራዊ ቡድኑ አባላት ከቦሌ አየር ማረፍያ ወደ ጁፒተር ሆቴል ያመሩ ሲሆን በሆቴሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸው የተዘጋጀላቸውን ኬክ ቆርሰዋል ተብሏል።

More : @tikvahethsport