#USA
አምባሳደር ሳተርፊልድ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።
አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።
አምባሳደር ሳተርፊልድ እኤአ ከጥር 17-20 ባሉት ቀናት ነው ሃገራቱን የሚጎበኙት፡፡
በቅድሚያ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ የሚጠበቁት ልዩ መልዕክተኛው ቀጥሎ ካርቱምንና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ አብረዋቸው ወደ ሃገራቱ እንደሚጓዙ ተገልጿል።
አምባሳደር ሳተርፊልድ በሪያድ ቆይታቸው በሱዳን ያለውን ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁትን የለውጥ ኃይሎችን እንደሚያገኙና በመንግስታቱ ድርጅት አመቻችነት ለማካሄድ ስለታሰበው ሃገራዊ ውይይት እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል፡፡
ወደ ካርቱም ተጉዘው ከተለያዩ የለውጥና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር እንዲሁም ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር ይወያያሉ፡፡
በኢትዮጵያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
መንግስት የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል እንዲያጠናክር፣ የአየር ጥቃቶችን እንዲያቆም እና ሌሎችም መቃቃሮች እንዲያበቁ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩም ነው የተገለጸው፡፡
ተኩስ እንዲቆም፣ እስረኞች አሁንም እንዲለቀቁና ሰብዓዊ እርዳታዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲቀርቡ ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡
መረጃውን #አል_ዓይን_ኒውስ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ነው በድረገፁ ላይ ያስነበበው።
@tikvahethiopia

" ግጭቱ በባህላዊ እርቅ ተቋጭቷል "
በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌና ማረቆ የሰላም ጉባኤ በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ ኢንሴኖ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌና ማረቆ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በባህላዊ እርቅ ተቋጭቷል።
የእርቅ ስነ-ስርዓቱ ግጭቱ በተከሰተበት ቦታ ኢንሴኖ የተካሄደ ሲሆን የክልልና የዞን አመራሮች የአገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል፡፡
ግጭቱ የተነሳው ከአከላለል ጋር በተያያዘ ሲሆን ከግጭቱ ለማትረፍ ፍላጎት ያላቸው አካላት እንዲባባስ ያደረጉ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በዚህም የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ዜጎችም ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል።
ግጭቱም የግብርና እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ፈጥሮ መቆየቱ ነው የተገለጸው፡፡
ሁለቱ ወገኖች ልዮነታቸውን በባህላዊ የዕርቅ መንገድ መፍታታቸውን ተከትሎ የእርቅ ጉባኤ በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን መረዳ ኢንሴኖ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
#ENA

TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ : ድብድብ በኬንያ 🇰🇪 ፓርላማ ! ዛሬ ከሰአት #በኬንያ የፓርላማ አባላት አወዛጋቢ ነው በተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች (ማሻሻያ) ረቂቅ ህግ ላይ ሲያደርጉት የነበረው ጠንከር ያለ ክርክር ተካሮ የፓርላማው አባላት ሲደባደቡ ታይተዋል። ከሰሞኑን ብቻ ፓርላማ ውስጥ የተከሰቱ መሰል ክስተቶችን ስናጋራችሁ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ዛሬ ጥዋት የጆርንዳን ፓርላማ አባላት እንዲሁም ከቀናት በፊት በጋና የፓርላማ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ቡጢ የተሰናዘሩት የሶማሊላንድ ፓርላማ አባላት👊
ዛሬ ጥዋት የ2022 በጀት ላይ የጦፈ ክርክር ላይ የነበሩት የፓርላማ አባላቱ ቡጢ ሲሰናዘሩ እና ሲደባደቡ በቀጥታ ስርጭት ታይተዋል።
@tikvahethiopia
ዛሬ ጥዋት የ2022 በጀት ላይ የጦፈ ክርክር ላይ የነበሩት የፓርላማ አባላቱ ቡጢ ሲሰናዘሩ እና ሲደባደቡ በቀጥታ ስርጭት ታይተዋል።
@tikvahethiopia
#ሹመት
ከጥር 3/2014 ጀምሮ ለኢትዮጵያ ኢንተርፕራዝ ልማት አዲስ አመራሮች ተሹመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፤ አቶ ብሩ ወልዴን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አድርገው የሾሙ ሲሆን አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ደግሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል።

AFCON 🏆 ግጥሚያው ተጧጥፏል!
የዛሬ ጨዋታዎች
⚽️ ጋቦን VS ጋና ከምሽቱ 4:45 ሰዓት
ሁሉንም ጨዋታዎች በላቀ ጥራት በቀጥታ SS AFCON ቻናል 222 ይመልከቱ!
ሁሉንም ጨዋታዎች ከጎጆ (አክሰስ) ፓኬጅ ጀምሮ በሁሉም የዲኤስቲቪ ፖኬጆች ላይ ያገኙታል!
ፈጥነው ዲኮደሩን ይግዙ! ግምትዎን ያጋሩን!
የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ 699 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ፡፡
የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ👇
https://bit.ly/2WDuBLk

"በመካከለኛው ምስራቅ በእስር ቤቶች የሚማቅቁ ወገኖቻችን አፋጣኝ መፍትሄ ይሻሉ" - ነእፓ
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በውጭ ሀገር በችግር ላይ የወደቁ ወግኖቻችንን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
ነእፓ ባለፉት ዓመታት መንግስት በውጭ ሀገር በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ አንዳንድ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎችን ወደሀገር ቤት ለመመለስ ባደረገው እንቅስቃሴ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ማድረግ ቢቻልም አሁንም በርካታ ዜጎች እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ብሏል።
ፓርቲው ፥ በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ወገኖች ደረሱኝ ባለው መረጃ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያውያን፣ የዜጎቻችንን ክብር ብሎም ጤንነትና ደህንነት አደጋ ውስጥ በሚጥል ሁኔታ በተለያዩ እስር ቤቶች ታጉረው እንደሚገኙ ለመረዳት ችያለሁ ብሏል።
"በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቻችን ክብር የሀገራችን ክብር ነጸብራቅ ነው" ያለው ነእፓ በየትኛውም ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርስ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በሀገር ሉአላዊነት እና ክብር ላይ የሚደረግ ጥቃት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል ብሏል።
በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር የምናደርገው ጥረት በባእድ ሀገራት ለሚገኙ ወገኖቻችንም ጭምር ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝቧል።
ነእፓ በየትኛውም ሀገር፣ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ በወገኖቻችን ላይ የሚደርስን ጥቃት አጥብቆ እንደሚቃወም ገልጿል።
ነእፓ ውጭ ሀገር የሚገኙ ዜጎቻችን ሚያጋጥማቸውን አደጋ ለመከላከል መንግስት በተለይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና በየሀገሩ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ኃላፊነታቸው በሚገባ እንዲወጡ ያሳሰበ ሲሆን በአደጋ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቻችን አፋጣኝ ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

#Update የደሴ - ወልዲያ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተገባደደ ነው። ፍተሻው በስኬት ከተጠናቀቀ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች በሰዓታት ውስጥ ኤሌክትሪክ ሊያገኙ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል። ተቋሙ እስከዛሬ ድረስ በተከናወነው ጥገና ጉዳት የደረሰበት መስመርና ምሰሶ ከ97 በመቶ በላይ ተጠናቋል ብሏል። ቀሪ ሥራዎችን በርብርብ በማጠናቀቅ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች…
#Update
ከደሴ እስከ ወልዲያ ያሉት ከተሞች ኤሌክትሪክ አግኝተዋል።
ከደሴ እስከ ወልዲያ ሲከናወን የቆየው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መስመሮች የመጠገን ሥራ ትናንት ምሽት ተጠናቆ ከተሞቹ ከ 10:05 ጀምሮ ኃይል አግኝተዋል።
ጥገናው ትናንት ምሽት ቢጠናቀቅም መስመሩ በሚያልፍበት አካባቢ በደሴ እና በሀይቅ መካከል እንዲሁም መርሳ አካባቢ የበቀለ ዛፍ ከመስመሩ ጋር ተገናኝቶ ባለመቆረጡ የተነሳ ኤሌክትሪክ ማገናኘት አልተቻለም ነበር።
ይሁንና ዛሬ ዛፎቹ በመቆረጣቸውና ኃይል ለመስጠት የሚያግድ ነገር ባለመኖሩ ከተሞቹ ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።
በተጨማሪ ፥ ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ የተዘረፈው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት የሚተካ ዘላቂ ሥራ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጀምሯል።
የተጀመረው ሥራ በቀጣዮቹ ከ4 እስከ 5 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ከፍተኛ ኃይል ለመስጠት የሚያስችል ነው።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

#Balderas የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል የሚያደርጉትን ጉዞ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ጀመሩ። በፓርቲው ፕሬዜዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአመራሮች ቡድን ዛሬ ወደ አፋር ክልል ገብተዋል። ቡድኑ በአፋር የዛሬ ውሎው…
#BahirDar
በፕሬዜዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ቡድን ዛሬ ከሰዓት ወደ አማራ ክልል መዲና ባህር ዳር መግባቱን ፓርቲው አሳውቋል።
ቡድኑ ባህር ዳር ሲደርስ በከተማዋ ወጣቶችና የፋኖ አባላት አቀባበል እየተደረገለት ፓርቲው ገልጿል።
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመሩት የባልደራስ ፓርቲ አመራሮች ቡድን ትላንት አፋር ክልል በመግባት በዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ በግንባር የተጎዱ የጦር አባላትን መጠየቁ እንዲሁም በአዋሽ ወንዝ ላይ እየለማ ያለውን የስንዴ ምርት መጎብኘቱ መገለፁ ይታወሳል።

#Update ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጤና ችግር አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል። ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል። ቅዱስነታቸው ፥ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና…
#Update
ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።
በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ህክምናቸውን በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ታውቋል።
ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት የተላለፈውን መልዕክት ያንብቡ : https://telegra.ph/EOTC-01-15

#JustinTrudeau #OlusegunObasanjo የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ልዩ መልዕከተኛው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንዲያበቃ እና በሁሉም አካላት መካከል ውይይት እንዲፈጠር ለማበረታታት የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ ተቀብለዋል።…
#DrAbiyAhmed #JustinTrudeau
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።
ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እንደ ካናዳ ያሉ ወዳጅ ሀገራት የሚሰጧትን ድጋፍ እንደምታደንቅ ገልፀዋል።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ፥ ትላንት ከሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ጋር በተያያዘ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር መነጋገራቸው ይታወሳል።

#ENDF
በመከላከያ ሰራዊት የብሄራዊ ተዋፅኦን የማመጣጠን ጉዳይ በተመለከተ የመከላከያ ጀነራል ኢንስፔክተር ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ ምን አሉ ?
ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ (በኢቲቪ ቀርበው የተናገሩት) ፦
" ... ከሰሞኑ የማዕረግ ሹመት ጋር ሲታይ ትኩረቱ የተወሰኑ ብሄሮች ላይ ነው.. ሌሎች ተረስተዋል ... ምናምን የሚባሉ ነገሮች አሉ።
ውትድርና ከባድ ሞያ ነው ፤ የሰው ልጅ ያክል ጭንቅላት አሳምነህ ውጊያ ውስጥ አስገብተህ እንዲሞት አሳምነህ የምትመራበት ስራ ነው ፤ ቢቻል ሳይሞት እንዲወጣ አድርገህ የምትመራበት ስራ ነው ያ ልምድን ችሎታን፣ ብቃትን ይጠቃል እንጂ ዝም ብለህ የብሄር ተዋፅኦ ለመጠበቅ ብለህ ከግራም ከቀኝም ሰብስበህ መሾም ሀገርንም ተቋምንም ይገድላል።
ሰሞኑ በነበረው የማዕረግ ሹመት እንደ አንድ የካውንስል አባል ስለሚመለከተኝ የነበረውን ሂደት ስለማውቀው በተቻለ መጠን የብሄር ተዋፅኦ በጠበቀ መንገድ ለመስራት ተሞክሯል።
አንዳንዶቹ በጣም Junior ሳሉ የብሄር ተዋፅኦውን ለማምጣት ሲባል ከ Senior ዎች ጋር እንዲሾሙ የተደረጉ አሉ።
... መከላከያ የሚያስቀድመው አሁንም ስራን ማዕከል ያደረገ፣ የተቋሙን ተልዕኮ ሊያስፈፅም የሚችል፣ በሚመራው አሀዱ ተቀባይነት ያለው፤ በሚሰራው ስራ ብልጫ ላሳየ ኦፊሰር ቅድሚያ ይሰጣል። "
ያንብቡ : https://telegra.ph/ENDF-01-15

Telegraph
ENDF
#ENDF በሀገር መከላከያ ሰራዊት የብሄራዊ ተዋፅኦን የማመጣጠን ጉዳይ በተመለከተ የመከላከያ ጀነራል ኢንስፔክተር ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ ምን አሉ ? ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ (በኢቲቪ ቀርበው የተናገሩት) ፦ " ... የብሄራዊ ተዋፅኦን የማመጣጠን ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፤ ህገመንግስታዊ ነው። ህገ መንግስታዊ ስለሆነ በተቻለ መጠን የብሄራዊ ተዋፅኦን የማካተት ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ…
#Ethio_Sudan
በሱዳን ኃይሎች የተያዘው የአልፋሽቃ መሬት ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በኢትዮጵያ በኩል በኃይል የመፍታት እድል ይኖረው እንደሆነ ከጀርመን ሬድዮ የተጠየቁት የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ጄነራል ባጫ ደበሌ፥ "በእኛ በኩል መንግስታችን ከሱዳን ጋር ተዋጉ የሚል ትዕዛዝ አልሰጠንም" ብለዋል።
አክለውም፥ "እኛ የያዝነው ውጊያ አለ፤ ከእነዚህ ሰዎች (ከሱዳኖች) ጋር ድሮውንም እንዳልነው ነው በውይይት የምንፈታው ነገር ነው። እነሱ ከነበሩበት የቀጠሉት የለም። ስለዚህ ትኩረት የተነፈገው አይደለም። በሚገባ እየተከታተልን ነው ያለነው" ሲሉ ገልፀዋል።
ጄነራል ባጫ፥ " ሁሉንም ድስት ጥደህ አንዱንም ሳታማስል ሊያርብህ አይገባም። ሆኖም በየትኛውም አካባቢ በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የሚመጣ ችግር ካለ ግን ይሄን መመለስ የሚችል አቅሙ አለን " ብለዋል።
በሌላ በኩል ከአል ዓይን ኒውስ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ጀማል አል ሼክአምባሳደር ጀማል አል ሼክ፤ በሱዳን ቁጥጥር ስር ስለሚገኘውና የይገባኛል ጥያቄና ክርክር እየተነሳበት ስላለው ስፍራ የሱዳንን አቋም አንፀባርቀዋል።
አምባሳደሩ፥ "አሁን ክርክር እያስነሳ ያለው መሬት ሱዳን የኔ ነው ብላ ታምናለች" ያሉ ሲሆን " ሱዳን ጉዳዩ ከፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ውጭ በሌሎች አማራጮች ይፈታል ብላ አታምንም " ብለዋል።
አምባሳደሩ፥ " እነዛ ቦታዎች የሱዳን ናቸው፤ ለዚህ ማስረጃም እንደፈረንጆቹ 1902 በሁለቱም ሀገራት የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት እንዳለ ይታወቃል፤ ስለዚህም የድንበር ውዝግቡ የስምምነቱን ዋና ዋና ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ሊፈታ ይችላል የሚል እምነት አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል።
ሱዳን ጉዳዩን በዲፕሎማሲ እና ፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።