TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሶማሊ ክልል በሚገኙ 78 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ146 ሺ በላይ ከብት፣ ግመልና ፍየሎች መሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ አስታውቋል። በክልሉ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና በሲቲ ዞን ውስጥ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ወደ…
#Update

" በድርቅ ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል " - የሶማሊ ክልል መንግስት

በሶማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ ዜጎችን ለሞት እየዳረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በጥቅምት መዝነብ የነበረበት ዝናብ ባለመዝነቡ በክልሉ የሚገኙ 9 ዞኖች ለድርቅ ተጋልጠው የነበረ ሲሆን አሁን ድርቁ ወደ 10ኛው ዞን መሸጋገሩን ኃላፊው ተናግረዋል።

በዚህም በተለይም በክልሉ 4 ዞኖች በዳዋ ፣ አፍዴራ፣ ሸበሌ እና ቆራሔ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 1 መቶ 46 ሺሕ 8 መቶ 6 እንስሳት መሞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በድርቁ የሚሞቱ እንስሳት ቁጥር በቅርብ ቀናት ሊጨምር እንደሚችል ስጋት መኖሩንም ጠቅሰው ፤ በድርቁ የተነሳ በክልሉ የሚገኙ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕዝብ ለችግር መጋለጡን አስረድተዋል፡፡

ሚያዚያ ወር ላይ የሚጠበቅ ዝናብ እንዳለ የገለፁ ሲሆን ዝናብ ካልዘነበ ድርቁ ከዚህም በላይ የከፋ እንደሚሆንና በርካታ ዜጎችን ሊያሳጣ እንደሚችል ስጋት መኖሩን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በሚኖሩበት ሀገር አሜሪካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። በታጠቅ ጦር ሰፈር፣ ህፃናት አምባ ፣ ጀግኖች አምባ መቋቋም ላይ ድርሻ እንደነበራቸውና በኢሰፓ ውስጥ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል። አምባሳደር ዶ/ር ካሳ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደር…
#Update

የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈፀማል።

የአምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ አስከሬን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን የቀብር ስነስርዓታቸው ከሰዓታት በኃላ በቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ኢዜአ ዘግቧል።

አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን በታጠቅ ጦር ሰፈር፣ ህፃናት አምባ ፣ ጀግኖች አምባ መቋቋም ላይ ድርሻ እንደነበራቸው እንዲሁም በኢሰፓ ውስጥ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል።

በተለያዩ ሀገራትም የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን አገልግለዋል።

በ80 ዓመታቸው በአሜሪካ ሀገር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ የአንድ ወንድ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
2 ዓለም አቀፍ የእርዳታ ቡድኖች የኢትዮጵያ መንግስት በከፊል / በሙሉ ስራቸውን እንዳቋረጠባቸው እና የስራ ፍቃዳቸውን እንደነጠቃቸው ትላንት አሳወቁ። ቡድኖቹ የDoctors Without Borders - MSF (የደች ቅርንጫፍ) እና Norwegian Refugee Council (NRC) ሲሆኑ ሐምሌ 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ መንግስት ስራ እንዳያከናውኑ እንዳገዳቸው ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት…
#Update

የኖርዌይ የስደተኞች ካውስል እገዳው እንደተነሳለት አሳወቀ።

የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል / NRC / በሰብአዊ ድጋፍ ስራው ላይ ለ5 ወራት ተጥሎበት የነበረው እገዳ እንደተነሳለት በኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደተገለፀለት አሳውቋል።

እግዱ የተነሳለት ከታህሳስ 22/2014 ጀምሮ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን አስመልክቶ ድርጅቱ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፥ የመከለከያ ኃይል የያዘቸዉን አካባቢዎች አፅንቶ እንዲቆይ በታዘዘዉ መሠረት ይዞታዉን በማጠናከር በነበረበት ምሽጉን ይዞ ቆሟል ብለዋል።

"መንግስት ወደ ትግራይ ክልል የመከላከያ ሠራዊቱ እንዳይገባ የወሰነዉ የትግራይ ህዝብ በመጀመሪያዉ ዙር ያባከነዉን የማስተዋል ጊዜ ዳግም እንዲያጤናዉና ራሱን ከአሸበሪዉ ሃይል ነጥሎ ለጥቅሞቹና መብቶቹ መከበር እንዲቆም ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል ነዉ" ብለዋል።

ሚኒስትሩ፥ "በአሁኑ ወቅት የትግራይ ህዝብ በርካታ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዉስጥ እንደሉ መንግስት መገንዘብ ብቻ ሳይሆን የህዝባችን አንዱ አካል በመሆኑ እነዚህ ችግሮቹ እንዲፈቱለት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነዉ" ሲሉም ተናግረዋል።

"እነዚህ ጥቅሞቹና መብቶቹ እንዲከበሩ ከተፈለገ በጦርነት ብቻ የመኖር ፍላጎትና ጥማት ያለዉን አሸባሪው የጥፋት ሃይል ዳግም የትግራይን ህፃናት በጦርነት እንዳይማግድ የሽብር ቡድኑን የጦርነትና የግጭት አባዜን ማስቆም ይኖርበታል" ብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ፥ "ለጥቂት የሽብር ቡድኑ አባላት ፍላጎትና የስልጣን ጥማት ሲባል ምንም አይነት ጥቅም ያላስገኘለትን ይልቁንም ልጆቹ የተማገዱበትንና ህይወቱ እንዲመሰቃቀል ያደረገዉን ቡድን ድርጊት ማውገዝ ብቻ ሳይሆን በጥብቅ መቃወም፤ መታገል መጀመር መቻል አለበትም" ሲሉም ተናግረዋል።

"በትግራይ ክልል በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እና በዉጭ ያለዉ የትግራይ ማህበረሰብም የትግራይ ክልልና ህዝብ ወደ ሰላማዊ ህይወቱ እንዲመለስ፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹ እንዲፈቱና ዘላቂ ጥቅሞቹ እንዲረጋገጡ የበኩለቸዉን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል" ብለዋል።

ያንብቡ - telegra.ph/UPDATE-01-05-2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዋንግ ዪ ኤርትራ ገቡ። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን ኤርትራ ገብተዋል። ዋንግ ዪን እና የልዑካን ቡድናቸው አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ዋንግ ዪ በኤርትራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከአቻቸው (ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ) ጋር ውይይት…
#Update

የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የተመራውን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ቻይና ባለፉት 100 ዓመታት በCPC መሪነት ያስመዘገበችውን ትልቅ እድገት አድንቀዋል። ዓለም አቀፍ ህግን በማክበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ የሆነ አለም አቀፋዊ ስርዓት እንዲመጣ ቻይና ላበረከተችው ጉልህ ሚናም አመስግነዋል።

ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ስለኤርትራ ልማታዊ ፕሮግራሞች፣ ስለቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን አመለካከቶችን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል።

ዋንግ ዪ በበኩላቸው ፥ ሀገራቸው ቻይና በኤርትራ ላይ የአንድ ወገን እና ህገወጥ ማዕቀብ እንደማትቀበለው አረጋግጠዋል።

ቻይና ለኤርትራ የምትሰጠውን ተጨማሪ የ100 ሚሊዮን ዩዋን ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።

ሁለቱም ወገኖች በሰው አቅም ግንባታ ፣ በመሰረተ ልማት፣ በማዕድን እንዲሁም በማሳዋ እና አሰብ ወደብ ልማት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።

ዋንግ ዪ ለፕሬዜዳንት ኢሳያስ ከቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል።

ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በሁለትዮሽ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ቻይናን እንዲጎበኙ ግብዣ አድርገውላቸዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ልዑካን ቡድናቸው በኤርትራ ያካሄዱትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ከሀገሪቱ የወጡ ሲሆን ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ኬንያ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

Photo Credit : Yemane G. Meskel

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ 5 ተከሳሾች በህመም ምክንያት ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። አሞናል በማለት ፦ - አቶ ስብሐት ነጋ ፣ - አቶ አባዲ ዘሙ፣ - አቶ ዘሚካኤል አንባዬ፣ - ዶ/ር ሙላት ይርጋ እና አቶ ቴድሮስ ሀጓስ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። የማረሚያ ቤት ተወካይ 5ቱ ተከሳሾች አሞናል በማለታቸው ምክንያት እንዳላመጣቸው አስረድቷል። ቀሪዎቹ ማለትም ፦ - ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም…
#Update

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ባለንበት ማረሚያ ቤት በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት እና በማረሚያ ቤት በተለያየ ቦታ ላይ የታሰርነው ተገናኝተን ለመወያየት ይፈቀድልን ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር አስተያየት እንዲሰጥበት ታዘዘ።

አቶ ተክላይ አብርሐ ፖስፖርቴንና መንጃ ፍቃዴን ለማሳደስ ለዩንቨርስቲ መታወቂያ ላላቸው ቤተሰቦቼ ውክልና እንድሰጥ ይፈቀድልኝ ሲሉም ላቀረቡት አቤቱታ አስተያየት እንዲሰጥ ታዟል።

ፍርድ ቤት በወ/ሮ ኬርያ ፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ እና በአቶ ተክላይ አብርሐ በተጠየቁ አቤቱታዎች ላይ ጥር 5 ቀን የማረሚያቤት አስተዳደር አስተያየት እንዲሰጥበት ትዛዝ ሰቷል።

ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዛብሔርን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በጎፋ ገብርኤል ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ታስራብኛለች ያሏት ልጃቸውን በጥንቃቄ በአጃቢ እንዲጠይቋት ፈቅዷል።

ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዛብሔር ልጄን እንዲጠይቅ በፍርድ ቤቱ በተሰጠኝ ፈጣን ምላሽ ደስ ብሎኛል ሲሉ ምስጋና አቅርበዋል። 

ወ/ሮ ሙሉ ከዚህ በፊት በጽሁፍ አመልክቻለው ያሉትን በፓርላማ የተከፈተላቸው የደሞዝ መቀበያ የባንክ ሒሳባቸው እና የጋራ መኖሪያ ቤት ገንዘብ መቆጠቢያ የባንክ ሒሳብ እግድ እንዲነሳላቸው ጠይቀዋል።

በምርመራ ተይዞቦኛል ያሉት ኮምፒዩተር እንዲሁም ስልክ እንዲመለስላቸውም አመልክተዋል።

ከሳሽ ዓቃቢህግ በበኩሉ በፖሊስ ስለተያዘ ንብረት ለፖሊስ እንዲጻፍ አስተያየት የሰጠ ሲሆን የባንክ ሒሳብ እግድን በተመለከተ ግን አጣርተን ምላሽ እንሰጣለን ብሏል።

የቀድሞ የትግራይ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ለነበሩት ወ/ሮ አሰፉ ሊላይ ዓቃቢህግ የሰነድ ማስረጃ እንዲያደርሳቸው ታዞ የነበረ ሲሆን ትዛዙን የሚፈጽመው ሀላፊ በመታመሙ ምክንያት ማድረስ አለመቻሉን ጠቅሷል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ዓቃቢህግ በቀጣይ ቀጠሮ ማለትም ጥር 5 ቀን የሰነድ ማስረጃ ለ20 ኛ ተከሳሽ እንዲያደርስ ታዟል።

ዛሬ በችሎት የቀረቡት ወይዘሮ ኬርያ እና ዶክተር ሰለሞን ጨምሮ ስድስቱ ተከሳሾች ችሎቱ ትዛዝ ሲሰጥ ከወንበር ባለመነሳታቸው ምክንያት ትዛዝ :ብይን እና ፍርድ ሲሰጥ ከወንበራቸው ተነስተው መቆም እንዳለባቸው የችሎት ስርአትን እንዲረዱ ፍርድ ቤቱ አስገንዝቧቸዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tarik-Adugna-01-05

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
TIKVAH-ETHIOPIA
ፌልትማን ሀሙስ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ሀሙስ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተነግሯል። ፌልትማን ኢትዮጵያ የሚመጡት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሰላም ድርድር ጉዳይ ለመነጋገር እንደሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል። አምባሳደር ፌልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከከፍተኛ…
#EXCLUSIVE

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ ተብሏል።

ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሮይተርስ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከ9 ወራት የስልጣን ቆይታ በኋላ በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ መስማቱን ገልጿል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ይተኳቸዋል ተብለው የሚጠበቁት #በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደርነት ጊዜያቸውን የጨረሱት ዴቪድ ሰተርፊልድ መሆናቸውን ሮይተርስ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች መስማቱን ገልጿል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#GERD

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የታላቁ ህዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

በጉብኝት መርሀ ግብሩ የተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል፡፡

የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነችው ጉባ እየተካሄደ ነው፡፡

Credit : FBC

@tikvahethiopia