TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DireDawa

የድሬዳዋ ፖሊስ ማንኛውም ድሬዳዋ ከተማና ገጠር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ፍቃድ ቢኖረውም ባይኖረውም በአቅራቢያው በሚገኝ የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በግንባር በመሄድ ማስመዝገብ እንዳለበት በጥብቅ አሳስቧል።

ድሬዳዋ ፖሊስ ፥ ከህዳር 2 ቀንእስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት 2 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ሳያስመዘግብ የቀረ ከሆነ በህግ አግባብ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል፡፡

@tikvahethiopia
#AWI

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጫት ቤቶች እንዲዘጉ ተወሰነ።

ብሔረሰብ አስተዳደሩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል የመጀመሪያው ጫት ቤቶች እንዲዘጉ የሚል ነው።

በተጨማሪም ከየትኛውም ከተማ ከምሽቱ 2:00 በኋላ መንቀሳቀስ እንደማፈቀድ (በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት) ተገልጿል።

የመንግሥት እና የግል መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ተወስኗል።

መኝታ ቤት የሚያከራዩ ሰዎች ማንነትን እንዲያረጋግጡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተከራይ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ማንም ሰው ተኩስ ከተኮሰ መሳሪያውን እንደሚቀማ ውሳኔ ተላልፏል።

ማንኛውም ግለሰብ በየአካባቢው ተደራጅቶ በሮንድ አካባቢውን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት የማይተባበር ከሆነ በህግ እንደሚጠየቅ ተወስኗል።

ከመንግስት በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት ድጋፍ ያላደረጉ አካላት እንዲደግፍ ፣ እንዲከፍሉ ካልከፈሉ ድርጅታቸው ታሽጎ አገልግሎት እንዳያገኙ እንዲደረግ ተወስኗል።

(አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጧል)

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጉዳይ ! የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል። ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል። ፈተናው መሰጠት በጀመረበት ሰኞ ኅዳር 29/2024 ዓ.ም ፈተናው ተሰርቋል የሚሉ ወሬዎች ቢናፈሱም፤ ፈተናው አለመሰረቁን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም። "ተማሪዎች ተረጋግተው ይፈተኑ" በሚል ይመስላል መንግስት የማህበራዊ ሚዲያዎችን…
#ተጨማሪ

ትላንት የተሰጡት የታሪክ ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ከፈተናው በፊት ቀድሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መሰራጨቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቂ ማስረጃ ማረጋገጡ ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጠውም የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር (ሲቪክ) ትምህርት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ እንደነበርና ዛሬ የተሰጠው የፈተና ወረቀትም ትላንት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጨው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በበቂ ማስረጃ አረጋግጠናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቢዘጉም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አገልግሎቶቹ ቀጥለዋል።

ይህ ትውልድና እና ኢትዮጵያን የመግደል ተግባር በማን እና እንዴት እንደተፈፀመ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልግ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጠያቂው አካል መታወቅ ይኖርበታል።

ለዓመታት የለፉ ተማሪዎችን ድካም በሚያደናቅፍ ተግባር ላይ የተሳተፉ፣ ሲተባበሩ የነበሩ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ የነበሩ ሁሉ ሌላው ቢቀር ከሞራል ተጠያቂነት አይተርፉም።

በውጭ ያሉ የማህበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ አካላትም ሆነ የፖለቲካ ሰዎች ከምንም ጋር ግንኙነት የሌላቸው ተማሪዎችን የግል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ብቻ ሲሉ ኢ-ስነምግባራዊ በሆነ ትውልድን የመጉዳት ተግባር ላይ መሳተፋቸው እጅጉን የሚያሳዝን ነው።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ትምህርት ሚኒስቴር ስለጉዳዩ የሚለው ነገር ካለና ማብራሪያ ከሰጠ ተከታትሎ ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መከላከያ አርማውን ቀየረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ተቋማዊ አርማ መቀየሩን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ አስተወቁ።

ጄነራል መኮንኑ ፣ ተቋሙ ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ የቀየረው አዲስ ከፈጠረው አደረጃጀትና እየተገበረ ካለው ሪፎርም አኳያ ገላጭ ባለመሆኑ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

እንደ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ ገለፃ ፣ ተቋሙ አዲስ ይፋ ያደረገው አርማ ከተቋሙ ተልዕኮና ባህርይ አንፃር ልዩ ልዩ ትርጓሜዎችን የያዘ ነው።

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
#Somali

በሶማሊ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ 200 ሚሊዮን ብር ፀደቀ።

የሶማሊ ክልል መንግሥት ካቢኔ ዛሬ 7ተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል።

ስብሰባው በጎዴ ከተማ ነው የተካሄደው።

ካቢኔው በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ በተለይ ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች አስቸኳይ መልስ መስጠት የሚችልበት ሁኔታ ላይ በስፋት መክሯል።

በዚህም ድርቅ የተከሰተባቸውን አከባቢዎች ፈጣን መልስ ለመስጠት እና አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረስ 200 ሚልየን ብር ካቢኔው አፅድቋል።

#SRMMA

@tikvahethiopia
#GONDAR : ፖሊስ በጎንደር ከተማ ለእኩይ/ለሽብር ተግባር ሊውል ነበረ ያለውን ገጀራ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

ገጀራው በከተማው ቀበሌ 16 በተለምዶ ግሩፕ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግለሰብ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተገኘ ነው ተብሏል።

ማህበረሰቡ ባደረሰው ጥቆማ ከአንዲት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገወጥ ገጀራው መገኘቱን ያስረዳው የከተማው ፖሊስ ጥቆማ የተሰጠባት ግለሰብ ቤት ፖሊስ ሄዶ ህገወጥ ገጀራ መኖሩን ሲጠይቅ ምንም ነገር እንደሌለ መግለጿ ተመላክቷል።

ነገር ግን በተደረገው ፍተሻ በአልጋ ስር በከፍተኛ ሁኔታ የተደበቁ ገጀራዎች መገኘቱን እና ገጀራው ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ያልዋለና ለእኩይ አላማ ሊውል እንደታሰበ ያመለክታል ብሏል ፖሊስ።

የጎንደር ፖሊስ አሁን ላይ ነባራዊ ሁኔታውን መሰረት ባደረገ ሁኔታ በሮችን ከሁሉም የፀጥታ ኀይል ጋር በመሆን 24 ሰዓት እየጠበቀ መሆኑን ወንጀልንና ወንጀለኞችን መከላከልና መቆጣጠር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በቀጣይም ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን መሰል ህገወጦችን በቁጥጥር ስር እያዋልነ ወደ ህግ የማቅረብ ተግባሩ እንደሚቀጥል አሳቋል።

ምንጭ ፦ የጎንደር ከተማ 4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጫ ሰጥቷል።

ኤጀንሲው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል ብሏል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ ነው ያሳወቁት።

በ2 ሺ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው በዚህ ፈተና፣ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617 ሺ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565ሺ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ዘርፉ ሰራተኞችና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ፈተናዎች ተሰርቀው ወጥተዋል የሚባለው ጉዳይ እውነት ነወይ" ተበለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ምርምርራዎችና ትንተናዎች ተደርገው አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ምንም የሚያስጋ ነገር የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#SUDAN : የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት አቋቋሙ፡፡

ቡርሃን ምክር ቤቱን ያቋቋሙት በመፈንቅለ መንግስቱ የፈረሰውን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ለመተካት ነው፡፡

አዲስ የተመሰረተው ምክር ቤት 15 አባላት ያሉት ሲሆን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን ሲመሩት የነበሩት ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ም/ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል፡፡

ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን በምክትልነት ሲመሩ የነበሩት ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳገሎ (ሄሚቴ)ም በአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪነት እንደሚቀጥሉ ቡርሃን አስታውቀዋል፡፡

ከ15ቱ የምክር ቤቱ አባላት መካከልም 5ቱ የሃገሪቱ ጦር መሪ ጄነራሎች ናቸው፡፡

የሱዳን ጦር ከ20 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሚመራው የሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎም የሲቪል አስተዳድሩ ወደ ቀድሞ ስልጣኑ እንዲመለስ የሱዳን ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከታላቁ የኅዳሴ ግድብ በዓመት 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የኢትዮጵያ የኢኖቬስን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ደኤታ ሁሪያ አሊ ማህዲ አስታወቁ።

ኢትዮጵያ በዚሁ ከመጀመሪያ ዙር እንደምታመነጭ ከሚጠበቀው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በ14 ከመቶ እንደሚያሳድገው ገልፀዋል።

ሚኒስትር ደኤታዋ ሁሪያ አሊ ይህን ያሳወቁት ዛሬ በይነ መረብ በተካሄደ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ኢትዮጵያን በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለማሳደግ በርካታ ፕሮጄክቶችን እያከናወነች ነው ያሉት ምኒስትር ዴኤታዋ ፥ ከዋነኞቹ ፕሮጀክቶች ግንባር ቀደሙ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከጥቂት ወራት በኃላ 700 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይጀምራል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጫ ሰጥቷል። ኤጀንሲው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል ብሏል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ ነው…
#ተጨማሪ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና #በማህበራዊ_ሚዲያ ላይ ወጥቷል የሚል ጥቆማ እንደደረሰውና በቀጣይ ታይቶ በማስረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ እርምጃ ወይም ማስተካከያ እንደሚወሰድ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳውቋል።

የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ የ4 ቀኑ ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ፤ በማህበራዊ ሚዲያ ፈተናው ወጥቷል የሚል ጥቆማ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።

ይህ ጥቆማም በቀጣይ ታይቶ በማስረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ እርምጃ ወይም ማስተካከያ የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል።

በማስረጃ ተረጋግጦ ትክክል ከሆነ በትምህርት ቤት ደረጃ፣ በተማሪ እና በትምህርት ዓይነት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን መጠቆማቸውን ኤዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#CentralStatisticsAgencyኢትዮጵያ

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ምጣኔ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ34.2 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል።

የምግብ የዋጋ ግሽበት በ40.7 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ደግሞ በ25.2 በመቶ ከአምናው ጭማሪ ማሳየቱን ኤጀንሲው አመልክቷል።

በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በመጠኑ የተረጋጋ ሲሆን፤ ሩዝ፣ ጤፍ እና ስንዴ አነስተኛ የዋጋ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የበቆሎ ዋጋ በመጠኑ መጨመሩን የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል፡፡

ሥጋ፣ ወተት፣ አይብ እና እንቁላል፣ ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨው እና በርበሬ) መጠነኛ ቅናሽ ማሳየታቸውም ተጠቅሷል፡፡

ይህም ከመስከረም ወር ጋር ሲነጻጸር የምግብ የዋጋ ግሽበት በ1.3 በመቶ ቅናሽ እንዲያሳይ አድርጎታል ተብሏል፡፡

ከውጭ የሚገባው የምግብ ዘይት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ዋጋው የጨመረ ሲኾን፤ በአገር ውስጥ የሚመረተው ዘይትና ቅቤ ዋጋ ትንሽ እንደቀነሰ የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል፡፡

በሌላ በኩል የቡና ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

የጥቅምት ወር 2014 ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ25.2 በመቶ ጭማሪ እንደሚያሳይ ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል፡፡

የዋጋ ግሽበቱ ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ ጫት፣ ማገዶ እና ከሰል፣ የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶ፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ የግንባታ እቃዎች እና ወርቅን ጨምሮ በጌጣጌጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል፡፡

Credit : Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለ1 ሳምንት ተራዘመ።

በደቡብ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ በቀጣይ አንድ ሳምንት ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚካሄድ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት ለ5 ተከታታይ ቀናት የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦችና ተቋማት እንዲያስመዘግቡ ዉሳኔ መተላለፉን ገልፀው በነዚህ ቀናት መዝግቦ ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ከነገ 03/03/2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ለመጨረሻ ጊዜ ይካሄዳል ብለዋል።

በመሆኑም እስከአሁን የጦር መሳሪያ ያላስመዘገቡ ግለሰቦችና ተቋማት በቀጣይ አንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ በቅርበት ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርበዋል ።

ባለ ሁለት እግር ሞተርና አሽከርካሪዎች፣ የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡና የአከራይ ተከራይ ምዝገባ ለቀጣይ 7 ቀናት መራዘሙን ሃላፊዉ ገልጸዋል ።

በተራዘሙት የምዝገባ ቀናት የማያስመዘግቡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ኃላፊው ማሳወቃቸውን ከክልሉ ኮሚኒካሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ባለፉት ቀናት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት #ቴሌግራም እና #ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ትላንት ፈተናው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopia