TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
" Genocide ተካሂዷል ለማለት መረጃ የለም" - ሚሼል ባሽሌት

ጄኔቫ ላይ መግለጫ የሰጡት የተመድ (UN ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት በተለያየ ደረጃ በሁሉም አካላት የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መኖራቸውን ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት እጅግ በተደጋጋሚ ምርመራው ጭብጦች (Facts) ላይ ተመስርቶ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሁሉም አካላት ቢፈፀሙም #Genocide ዘር ላይ ያተኮረ የጅምላ ፍጅት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ተካሂዷል ለማለት በቂ መረጃ የለም ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
#ሪፖርት

በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ፦

• ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣
• ማሰቃየት፣
• ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣
• በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።

በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ ፦

በማይካድራ "ሳምረ" በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ፤ ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለው በጅምላ መቃብሮች መቀበራቸውን ተመላክቷል።

የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን በተቆጣጠሩባቸው ቀጣይ ቀናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የበቀል ግድያዎች መፈጸማቸውን እና የፋኖ ሚሊሺያዎችም በግድያው መሳተፋቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል።

በአክሱም ከተማ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከ100 በላይ ሲቪሎችን መግደላቸውን፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያዎቹ ሲፈጸሙ ጣልቃ ሳይገቡ መቅረታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

በቦራ አምደውሃ ፣ በቦራ ጫማላ እና ማኢ ሊሃም ከተሞች ከ70 በላይ ሲቪሎች በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸውን የጋራ ሪፖርቱ ገልጿል።

እነዚህን እና ሌሎች የግድያ ማስረጃዎችን በመያዝ የሕግ ትንታኔ የሰጠው የምርመራ ቡድኑ በዚህ ጦርነት ውስጥ "የጦር ወንጀሎች" ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

#EHRC #OHCHR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ !

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የወጣውን የጋራ ሪፖርት በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል።

TPLF በትግራይ ክልል በቀሰቀሰው ግጭት ወቅት የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል በሚል ያናፈሰው የሐሰት ውንጀላ ተጨባጭ መሠረት እንደሌለው በቡድኑ የጋራ ምርመራ በግልፅ ተረጋግጧል ብለዋል።

ቡድኑ ባወጣው ሪፖርት መሰረትም መንግስት ረሃብን 'የጦርነት መሳሪያ' አድርጎ ይጠቀምበታል የሚለውን ተደጋጋሚ ክስ በአሳማኝ ማስረጃ ላይ ያልተመሰረተ ሲል መደምደሙ ይፋ ባደረገው መግለጫ ተመላክቷል ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በትግራይ ውስጥ ሆን ተብሎ መንግስት ለህዝቡ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደርስ ከልክሏል በሚል የቀረበውን ክስ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዳላገኘ በሪፖርቱ እንደማለከተ አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ''እነዚህ ውንጀላዎች ውሸት መሆናቸውን እናውቃለን፣ ነገር ግን ጠላቶቻችን አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰርተዋል'' ብለዋል።

በሪፖርቱ ላይ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ቢኖሩንም ሪፖርቱን እንደ ጠቃሚ ሰነድ ተቀብለነዋል፤ ለተጎጂዎች መፍትሄ ለመስጠት፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

አክለውም የሁለቱ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ሙያዊና ተዓማኒ የሆነ የሰብአዊ መብት ምርመራ ለማካሄድ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

* ሙሉ ምላሻቸው ከላይ ተያይዟል።

#ENA

@tikvahethiopia
#US : በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ ግሌን ዮንከን አሸነፉ።

ግሌን ዮንከን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ቀድም ብሎ በዚህ ግዛት ላይ ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ሲናገሩ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት አሸንፈው ነበር።

ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው።

ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ ፦
- የዋጋ ግሽበት መባባስ፣
- የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት - ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

መረጃው ከኤኤፍፒ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማከሄድ ጀምሯል። በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በፌዴረሽን ምክር ቤት 11ኛ ክልል ሆኖ ለጸደቀው ደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የስልጣን ርክክብ ያደርጋል። @tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ክልል ም/ቤት በዛሬው እለት 6ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ከአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር የስልጣን ርክክብ አድርጓል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ሆኖ በፌዴሬሽን ም/ቤት መፅደቁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት ቆሟል፡፡

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፥ " ለህዝቡን ድህንነት ሲባል በተለያዩ መንገዶች ወደ ከተማው የሚገቡ ጸጉረ ልውጦችን እና ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል ሲባል የከተማ አስተዳደሩ ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም ወረዳ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት መስጠት ቆሟል " ብሏል።

የሀገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ከከትላንት ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል::

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጅ መሰረትም የከተማው የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፡፡

ሆኖም የከተማችን ነዋሪዎች ሆነው በተለያዩ ምክኒያቶች መታወቂያ ያልወሰዱ ነዋሪዎች ካሉ በልዩ ሁኔታ በሚመለከተው አካል ተጣርቶ እና ተረጋግጦ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚዘጋጅላቸው ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
ኤርትራ የምርመራ ሪፖርቱን አልቀበልም አለች።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተመድ የጋራ የምርመራ ቡድን ዛሬ ይፋ ያደረጉትን ሪፖርት ኤርትራ እንደማትቀበለው አሳውቃለች።

ዛሬ ከሰዓት የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

ኤርትራ በምርመራው ላይ የተሳተፉ አካላትን ገለልተኛነት ጉዳይ ያነሳች ሲሆን ምርመራው አካሄድና ትክክለኛነት እንዲሁም ህጋዊነት ላይ ጥያቄዎችን አንስታለች፡፡

ሪፖርቱ ላይ ኤርትራን የተመለከቱ መረጃዎች ተዛብተው መቅረባቸውን ኤርትራ የገለፀች ሲሆን ምርመራው ከምስክሮች ተዓማኒነት፣ ከተደረገበት ጊዜ እና ከሸፈናቸው ቦታዎች አንጻር ውስንነቶች ያሉበት ነው ብላለች።

የኤርትራን ጦር መዳኘትም ሆነ ለተጎጂዎች ፍትህ መስጠት ከተፈለገ የሚቻለ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሌሎች በኤርትራ ህግ መሰረት ገለልተኛ እና እውነተኛ ምርመራን ለማድረግ በሚችሉ አካላት ነው ብላለች።

ኤርትራ ምንም ዐይነት ማረጋገጫና ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ያለቻቸውን የአክሱም ጭፍጨፋና ሌሎች ጾታዊና በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ ጥቃቶችንም አንስታለች።

በእዚህም ጣምራ ሪፖርቱ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፃ ፤ ኤርትራ ፈርማ ህግ ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ማክበሯን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። እነዚህን ህጎች በሚጥሱ የሰራዊት አባላት ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂ እንደምታደርግ ኤርትራ ገልፃለች።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

#አልዓይን
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የንግድ ችሮታ (AGOA) ማስወጣታቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸውን ኋይት ሃውስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከንግድ ችሮታው እንዲትወጣ ፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ የጻፉት ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል። አሜሪካ ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ጥልቅ…
#AGOA

" አሜሪካ አጎዋን በተመለከተ ያሳለፈችውን ውሳኔ ልታጤነው ይገባል " - ኢትዮጵያ

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ከቀረጥ ነጻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቃሚነቷ ለማገድ ያስተላለፈችውን ውሳኔ እንድታጤነው ኢትዮጵያ ጠይቃለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካን የአጎዋ ውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ ፥ አሜሪካ ያሳለፈችው ውሳኔ አግባብነት የሌለው እና የአሜሪካ መንግስት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑን ገልፃለች።

በውሳኔው ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት የሌላቸውን ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋልም ብላለች።

እንዲሁም በግበዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት በእጅጉ እንደሚጎዳውም የገለፀው ኢትዮጵያ አሜሪካ ውሳኔውን እንድታጤነው ጥይቃለች።

#ENA

@tikvahethiopia
" ... አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ መለስ ዜናዊ ይገዙበት ወደነበረው አገዛዝ መመለስ እንደማይፈልግ እናውቃለን ምርጫቸውንም እናከብራለን " - ጄፍሪ ፌልትማን

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልት ማን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ ደርሷል ሲሉ ተናገሩ።

ፌልትማን ይህንን ያሉት በአሜሪካ የሰላም ተቋም ተገኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ፌልትማን ፥ አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወገንተኛ አቋም እንዳላት መቆጠሩ ስህተት መሆኑ እና በጦርነቱ ላይ የሚሳተፉትን ሁሉንም ወገኖች እንደምትቃወም ተናግረዋል።

ህወሓት ጦርነቱን ወደአፋር እና አማራ ክልሎች መግፋቱና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለፅ በአስቸኳይ ከክልሎቹ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የTPLFን ከትግራይ ክልል ውጭ መስፋፋት በተደጋጋሚ አውግዘናል ያሉት ፌልት ማን አሁንም TPLF ከአማራ እና አፋር ክልሎች በአስቸኳይ እንዲወጣ እንጠይቃለን ብለዋል።

ፌልት ማን በኢትዮጵያ ጦርነቱ እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት ከዚህ ቀደም በነበረበት ሊቀጥል እንደማይችልና ለዓመታት የዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ስምምነት ውጤት ለመሰረዝ እንዲሁም በጦርነቱ ላይ በተሳተፉ ሁሉም ወገኖች ላይ ማዕቀብ ለመጣል መዘጋጀቷን ተናግረዋል።

ፌልትማን ፥ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ መለስ ዜናዊ ይገዙበት ወደነበረው አገዛዝ መመለስ እንደማይፈልግ እናውቃለን ምርጫቸውንም እናከብራለን ያሉ ሲሆን TPLF ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቃወሙም ተናግረዋል።

"ይሄ TPLF መንግስቱ ኃ/ማርያምን ለመጣል እንደተንቀሳቀሰበት 1991 (እኤአ) አይደለም። እዚህ ላይ ገልፅ መሆን ፈልጋለሁ TPLF ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሚያደርገውን ማንኛውንም ጥረት ሆነ አዲስ አበባን ለመክበብ የሚያደርገውን ጥረት እንቃወመናለን፤ ከTPLF አመራሮች ጋር በነበረን ግንኙነትም ይህንን ግልፅ አድርገን ነግረናቸዋል" ሲሉም ተደምጠዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Jefery-Feltman-11-03
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA " አሜሪካ አጎዋን በተመለከተ ያሳለፈችውን ውሳኔ ልታጤነው ይገባል " - ኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ከቀረጥ ነጻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቃሚነቷ ለማገድ ያስተላለፈችውን ውሳኔ እንድታጤነው ኢትዮጵያ ጠይቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካን የአጎዋ ውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል። ኢትዮጵያ ፥ አሜሪካ ያሳለፈችው ውሳኔ አግባብነት የሌለው እና የአሜሪካ መንግስት…
" የአሜሪካ መንግስት ኢትጵያን ከአጎአ ለማገድ ባስተላለፈው ውሳኔ በጣም አዝነናል " - የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

አሜሪካ ያሳለፈችው ውሳኔው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና በማድረስ በሴቶችና ህፃናት ላይ አሉታዊ ጉዳት እንደሚያሰርስ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፥ ኢትዮጵያ የገጠሟትን ችግሮች ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ያለ ሲሆን ይህ ውሳኔ ከጥር 1/2014 ጀምሮ መሻር አለበት ሲል ገልጿል።

" በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን መንግስታችንን ለማፍረስ እየሞከረ ያለው አማፂ ሃይል በህዝባችን ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እና ሰላምንና የህግ የበላይነትን ወደነበረበት ለመመለስ የምናደርገውን ጥረት አሜሪካ እንድትደግፍ እናሳስባለን"ም ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም የሰብአዊ መብት ክስ በጥሞና ይመለከታል ያለው ሚኒስቴሩ " ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነትና በንቃት እየተከታተልን ምርመራዎችን እያደረግን ነው" ሲል አሳውቋል።

" የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር ምርመራ እንዲያካሂድ መፍቀዳችን ለዚህ ማሳያ ነው" ብሏል።

አክሎም " ለዚህ አይነት ምርመራ የሚገዛው ለከፍተኛው የግልጽነት እና የታማኝነት ደረጃ ቁርጠኛ የሆነ መንግስት ብቻ ነው" ሲል ገልጿል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከባድ ወንጀሎችን የፈጸሙትን ሁሉ ለፍርድ ለማቅረብ የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጠኛ ነውም ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba መሳሪያ ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ባለጦር መሳሪያ ግለሰቦች በ2 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ደህንነት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አሳሰቡ። የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ወቅታዊ ፀጥታን በተመለከተ መግለጫ ተሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንደር እርስ በርስ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተፈቅዷል ብለዋል። አደረጃጀቱ ከፀጥታ…
" የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ነገ ድረስ ተራዝሟል " - ዶ/ር ቀነዓ ያደታ

በአዲስ አበባ የጦር መሳሪያ እንዲመዘገብ ትናንት በተላለፈው ጥሪ መሰረት ነዋሪዎች በከተማዋ በሚገኙ ፓሊስ ጣቢያዎች በመቅረብ እያስመዘገቡ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፤ የከተማዋን ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ከዚህ ቀደም ቢመዘገብም ባይመዘገብም እንደ አዲስ እንዲያስመዘግብ ቢሮው ጥሪ ማቅረቡ አስታውሰዋል።

ይህንን ጥሪ ተከትሎ መሳሪያ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በእጃቸው የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ወደየፖሊስ ጣቢያዎች በመቅረብ እያስመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

አስቀድሞ በተላለፈው ጥሪ መሰረት ምዝገባው ትናንት እና ዛሬ ብቻ የሚከናወን ቢሆንም ምዝገባው የተጀመረው ትናንት ከሰአት በኋላ በመሆኑ የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ነገ ተራዝሟል ብለዋል ዶ/ር ቀነዓ።

Credit : ኢፕድ

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ !

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከቱ የሚያመለክቱበት ነፃ የስልክ መስመር ይፋ ሆነ።

ነዋሪዎች አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከቱ የሚያሳውቁበት ነፃ የስልክ መስመር " 9977 " ነው።

#ሼር #SHARE

@tikvahethiopia