* Update
ለመስከረም ሃያው ምርጫ ለድምፅ መስጫ እና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች አሰራጭቶ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
መስከረም 20 ፦
- በሐረሪ ክልል፣
- በሶማሌ ክልል
- በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ለሚያካሂደው ምርጫና ሕዝበ ውሣኔ፤ ለድምፅ መስጫና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች ተሰራጭተዋል።
ሥርጭቱ ዐርብ መስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን ሐረሪ ክልል፣ ሶማሌ ክልል እና ደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ላይ የሚሠራጩትን ቁሳቁሶች የጫኑ መኪኖች አዲስ አበባ ከሚገኘው የቦርዱ ጊዜያዊ መጋዘን መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደየጫኑበት ምርጫ ክልል ተንቀሳቅሰው ጨርሰዋል።
በአዲስ አበባና ቅርብ አካባቢዎች ለሐረሪ ተወላጆች ለተከፈቱት ምርጫ ጣቢያዎች የሚሠራጩትን ቁሳቁሶች ደግሞ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መድረስ ያለበትን የጊዜ እርዝማኔ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንደሚጠናቀው ቦርዱ ዛሬ ከሰዓት አሳውቋል።
@tikvahethiopia

* መስቀል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፤ መጪውን የመስቀል በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቋል።
የቤተክህነቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበዓሉ አከባበር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መግለጫ ስጥተዋል።
ባለፈው ዓመት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በጥቂት ሰዎች በዓሉ መከበሩን ያወሱት ምክትል ስራ አስኪያጁ ዘንድሮ ተገቢውን የጥንቃቄ ተግባራት በመከወን በድምቀት ለማክበር ታስቧል ብለዋል።
በታሰበለት ጊዜና ድንቅ የግንባታ ስራ በተጠናቀቀው መስቀል አደባባይ ላይ የሚከበረው በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የመስቀል በዓል በድምቀት እንዲከበር በርካታ የቤተክርስቲያኗ ኮሚቴዎች እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የበዓሉ ስነ ስርዓቶች እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ይከወናሉ ብለዋል።
Credit : AMN

* Addis Ababa
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 5 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ክላስተር 04 በተለምዶ ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ የሚገኘውና ቤላ ፒዛ (BELLA PIZZA) እየተባለ የሚጠራው ሬስቶራንት ድንገት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል።
የእሳት አደጋው ከምግብ መስሪያው ማድቤት ውስጥ በሚገኝ የጋዝ ሲሊንደር ድንገተኛ መፈንዳት የተነሳ መሆኑ ተጠቁሟል።
በአደጋው አምስት የድርጅቱ ሰራተኞች ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸዋል።
አደጋው ከዚህ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር በሰራው ስራ የአደጋውን መጠን መቀነስ መቻሉን ተገልጿል።
ጉዳት የደረሰባቸውን 5ቱ ግለሰቦች ለህክምና ወደ ካዲስኮ ሆስፒታል መላካቸውንና በድርጅቱ የወደመው ንብረት ግምት እየተጣራ ነው።
መረጃው የቦሌ ወረዳ 7 ፕሬስ ነው።
@tikvahethmagazine

ፎቶ : የአዲስ አበባ መንገዶች አዲስ ገፅታ !
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የመንገድ ድልድዮች በሥዕል ስራ እና የመንገድ ዳርቻዎችን የማሳመር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ ተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አማካኝነት በቦሌ ዋና መንገድ ስር ባሉ ድልድዮችን የኢትዮጵያ 🇪🇹 ታሪካዊ ቅርሶች ፣ የሸገር እና የእንጦጦ ፓርክ የመሳሰሉ ለከተማዋ የውበት ገፅታ ድምቀት የሆኑት ቦታዎችን የሚያሳዩ የቀለም ቅብ እና የስዕል ስራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
በተጨማሪ በከተማዋ በሚገኙ ዋና ዋና መንገድ አካፋዮች እና መንገድ ዳርቻዎችን ውብና አረንጓዴ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጠቁሟል።

#UN : የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 76ኛ አጠቃላይ ስብሰባ በኒውዮርክ መካሄድ ጀምሯል።
በኒውዮርኩ ስብሰባ ከ100 በላይ የዓለም መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች ተሳታፊ ናቸው።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንም ስብሰባውን ለመካፈል ኒውዮርክ ይገኛሉ።
ይህ ስብሰባ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ቀውስ ጨምሮ በበርካታ ዓለማቀፍ ፈታኝ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

#EthiopianNationalDefenseForce
" የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ስሕተት ነው " - ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮን
የኢትዮጵያ ጦር ከፍተኛ መኮንኖች ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።
በግንባታው ስፍራ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የምድር ሃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ናቸው።
ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ አባላት በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ የመግስት የሰራ ሃላፊዎች የጉብኝቱ ተካፋይ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ፣ ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተከናወነ ያለውን እረፍት አልባ የሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም አድንቀዋል። ምስጋናም አቅርበዋል።
ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮን በጉብኝቱ ወቅት ባሰሙት ንግግር ፥ "የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ስሕተት ነው" ብለውታል።
አክለውም ፥ " ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የሚቀሳቀሱ የውክልና ጦር አስፈፃሚዎች ከወስጥም ሆነ ከውጭ የሚቀሳቀሱ ቅጥረኛ ሃይሎች ምንም አይሳካላቸውም" ሲሉ ተናግረዋል።
Credit : ENDF

ነእፓ እና ኢዜማ እራሳቸውን ከምርጫ አገለሉ።
የመስከረም 20 ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት በቀሩበት በዚህ ወቅት ተጨማሪ 2 ፓርቲዎች ምርጫውን አንሳተፍም ብለው ራሳቸውን አግልለዋል።
ከቀናት በፊት ኦብነግ በሱማሊ ክልል ምርጫ አልሳተፍም የሚል ውሳኔ ማሳለፉ አይዘነጋም።
አሁን ደግሞ በሶማሌ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ለክልል ም/ቤት እጩዎችን አቅርበው የነበሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የነፃነትና የእኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ከምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።
ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ከውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉበትን ምክንያት በዝርዝር ያሳወቁ ሲሆን ፤ ከዘረዘሯቸው ምክንያቶች መካከል፦
- በሶማሌ ክልል በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ ሂደት እና ከአጠቃላይ የምርጫ ሕግና ሥርዓት ጋር በተያያዘ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀረቡ ቅሬታዎች ሊፈቱ ባለመቻላቸው።
- ከዚህ በፊት ተሰርቆ የነበረው የምርጫ ቁሳቁስ በአዲስ እንዲተካ ጠየቅን አሁን ግን ቀድሞ ተዘርፎ በነበረው ካርድ ወደ ምርጫ በመገባቱ ምርጫው ተዓማኒነት ስለማይኖረው።
- የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መዋቅር ከመንግሥት መዋቅር ጋር የተዋሀደ በመሆኑ የምርጫውን ፍትሀዊነት እና ተዓማኒነት ያሳጣል። ... የሚሉት ይጠቀሳሉ።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫ ማግለል ጋር በተያያዘ ትላንት በሰጠው አስተያየት በምርጫው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እንደሌለና ቦርዱ ምንም የሚቀይረው ነገር እንደሌለ አሳውቋል።

የነእፓ አመራሮች አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ በቀለ ገርባን በእስር ላይ በሚገኙባቸው ማረሚያ ቤቶች ተገኝተው ጎበኙ።
በነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶክተር አብዱልቃድር አደም የተመራ የፓርቲው አመራር ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ፓርቲው አሳውቋል።
የነእፓ አመራሮች በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙትን የባልድራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን እና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙትን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮች አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ጃዋር መሀመድን ነው የጎበኙት።
በጉብኝቱ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች ያሉበትን ሁኔታ እና የፍትህ ሂደቱን በተመለከተ ውይይት መደረጉን ፓርቲው አሳውቋል።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮችን ጨምሮ ማንኛውም ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ ጉዳዩ የህግ የበላይነትን ባከበረ ሁኔታ ሊታይለት ይገባል ብሎ በጽኑ እንደሚያምን ገልፆ ይህንኑ አቋሙን የማረሚያ ቤቶችን በመጎብኘት የፍትሕ ስርአቱ በትክክል እየተተገበረ መሆኑን እንደሚከታተል ጠቁሟል።