ችሎት !
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዕግድ ላይ የሚገኘው የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ አስተዳዳሪ እንዲሾም ውሳኔ ሰጠ፡፡
ዓቃቢ ህግ በአ/አ ከተማ የሚገኘው የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የማይቀሳቀስ ንብረት ኪራይ ለህውሐት ቡድን ለሽብር ተግባር እየዋለነው ብሎ ንብረቱን ማሳገዱ ይታወሳል፡፡
ይህ የታገደው የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የማይቀሳቀስ ንብረትን የሚያስተዳድር አካል ሊሾም ይገባል ሲል ዓቃቤ ህግ መከራከሪያ ነጥብ አንስቶ ተከራክሮ የነበረ ሲሆን በዶ/ር አዲስ አሌም ባሌማ በኩል ደግሞ የታገደው ንብረቴ ቤተሰቦቼ የሚተዳደሩበት በመሆኑ መተዳደር ያለበት በቤተሰቦቼ ነው ሲሉ መከራከሪያ ነጥብ አንስተው ተከራክረው ነበር፡፡
ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ ንብረቴን ቤተሰቦቼ ናቸው ማስተዳደር ያለባቸው ሲሉ ያቀረቡትን መከራከሪያ ነጥብን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ንብረቱን የሚያስተዳድር ሌላ አስተዳዳሪ አካል እንዲሾም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
@tikvahethiopia

#MinistryofPeace
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ዶክተር አኔቴ ዌበር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይየታቸው ወ/ሮ ሙፈሪያት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ልማት በተለያዩ መስኮች እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዶ/ር አኔቴ ዌበር በበኩላቸው፥የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም ዘመናት የቆየውን መልካም የዲፕሎማሲያዊ እና የልማት ትብብር ለመቀጠል ያለውን ጠንካራ ፍላጎት መግለጻቸውን የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከባህር ዳር ተነስቶ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ።
ከባህር ዳር ተነስቶ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ሱሉልታ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋለው መሳሪያ 83 ትንሿ ሽጉጥ፣ 199 ኤም ፎርቲን ጥይት እና 10 ሺህ 865 የሽጉጥ ጥይት መሆኑ ታውቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና አዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ተጠርጣሪ የሆኑት ሹፌሩና ረዳቱ ተይዘዋል።
#ኢፕድ

''ቱኒዚያ በድጋሜ ለተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ተገቢ ያልሆነ ድጋፍ ለማድረግ እየተዘጋጀች ነው'' - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
ቱኒዚያ ድጋሚ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የግብፅን ሀሳብ ብቻ የሚደግፍ የውሳኔ ሀሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጀች በመሆኑ አፍራሽ አካሔዷን ለመቀልበስ የላይኛው የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት በጋር መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ይህን ያሉት ከላይኛው የናይል ተፋሰስ አባል ሐገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
የላይኛው ተፋሰስ አገራት አምባሳደሮችም በበኩላቸው በቀረቡት ሃሳብ ላይ በመንተራስ ድንበር ተሻጋሪ ሃብቶችን ለጋራ ልማት ለማዋል የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ እንዲሁም የአፍሪካን ጉዳይ በአፍሪካዊያን መፍታት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ቱኒዚያ ለተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ተገቢ ያልሆነ ድጋፍ ለማድረግ ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ቢደረግባትም በድጋሚ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጓን አንስተው፣ ይህ ውሳኔ ቢወሰን የሁሉም የላኛው ተፋሰስ አገራት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችልና ይህን ሃሳብ ለመቀልበስ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን የቱኒዚያ አካሄድ በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን የሶስትዮሽ ድርድር ጥረት የሚያደናቅፍ መሆኑን ገልጸው፣ አገራቱ ኒውዮርክ ለሚገኙት ሚሲዮኖቻቸው ይህንኑ እንዲገልጹላቸው ጠይቀዋል።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ነው።

#iCog
የኮምፒዩተር ዝንባሌ ያላቸው ልጆች የክረምቱን ጊዜ ይበልጥ እንዲጠቀሙት ይመከራል።
መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት በዛሬው የዲጂታል ዘመን መሰረት መጣል ያለበት ገና ከልጅነት እንደሆነ ይታመናል። ለዚህ ደግሞ በዘርፉ ሞያዊ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ሚናቸው ቀላል አይደለም።
ወደፊት የተሻለ የሥራ ዘርፍ የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም ነገሮችን በፍጥነት የመረዳት፤ ችግር ፈቺነት፣ በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ ፣ የፈጠራ ክህሎት ተወዳዳሪ እንደሚሆኑ የአይኮግ ላብ መስራች ቤቴልሔም ደሴ ትገልጻለች።
እነዚህን ክህሎቶች በቀላሉ ለመማር የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ (Coding) ትክክለኛው ዘርፍ እንደሆነም ታስረዳለች። ይህንን ትምህርትም ህጻናት በጊዜ መማር ቢጀምሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደሚኖረውም ታነሳለች።
ይህንን በመረዳት ልጆች የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችን፣ የተለያዩ የኮምፒውተር ችሎታዎችን እየተማሩ እግረ መንገዳቸውን እንደ ችግር ፈቺነት፣ በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ፣ የፈጠራ ክህሎት እና ሌሎችም አስፈላጊ ክህሎቶችን በሥልጠና በክረምቱ ወራት iCog Anyone Can Code ይሰጣል።
ይህ የክረምት ሥልጠና ዓለም አቀፍ ጭምር ሲሆን በክፍያ የሚሰጥ ነው። ይህንን ሥልጠና አምስት ህጻናት በአካል በመገኘት እንዲሰለጥኑ 10 ህጻናት ደግሞ በonline መማር እንዲችሉ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ነጻ የትምህርት እድል ቀርቧል።
እዚ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ወላጆች ልጆቻቸው ለምን መማር እንደሚፈልጉ ቪዲዮ ቀርጻችሁ @iCogACC_bot ላይ መላክ ትችላላችሁ። ስለ ሥልጠናው ሙሉ መረጃ https://icogacc.com/register ላይ መመልከት ይችላሉ።

#Tigray
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጸዋል።
በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው አዲስ አበባ የሚገኙ የመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ከ2 እስከ 3 ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ይገልፃሉ።
በአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምሩ የነበሩት መምህራን፤ የደሞዝ ክፍያው የተዛባው ከጥቅምት 2013 ጀምሮ ቢሆንም በመሀል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ተወካዮች በኩል ክፍያ ተፈጽሞላቸው እንደነበር ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ የ3 ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እና በባንክ ያላቸውን ገንዘብ እንዳይጠቀሙ የባንክ አካውንታቸው መታገዱን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይገልጻሉ።
በመቶዎች የሚቆጠሩት መምህራኑ፤ የሚሰሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙበት አካባቢ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዝውውር ቢጠይቁም ጥያቄያቸው ተቀባይነት አለማግኘቱን ተናግረዋል።
የተለያዩ መምህራን ተደራጅተው ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የደሞዝ ጥያቄ በደብዳቤ ያቀረቡ ሲሆን ሚኒስቴሩም ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ገልጾላቸው ነበር።
ይሁን እንጂ እስካሁን ደሞዛቸው እንዳልተከፈላቸውና የአብዛኞቹ መምህራን የባንክ አካውንት አለመለቀቁን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀዋል። #አዲስማለዳ
@tikvahuniversity

በጋይንት ነፋስ መውጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንድ ተዘረፈ፤ ወደመ።
በህ/ተ/ም/ቤት አሻባሪ ተብሎ የተፈረጀው "ህወሓት" በጋይንት ነፋስ መውጫ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገብርዬ ቅርንጫፍ ሙሉ ለሙሉ ዘርፎ ማውደሙን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለምነው ስዩም አሳወቁ።
ስራ አስኪያጁ ይህን ያሳወቁት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ነው።
ከዝርፊያ እና ውድመት ባለፈ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ እንደተገደለ ተገልጿል።
የባንኩ ስራ አስኪያጅ አቶ አለምነው ፥ ህወሓት ባንኩን በመሳሪያ በመደብድብ የኤቲ ኤም (ATM) ማሽኑን ጨምሮ የባንኩን ቋሚ ሀብቶች ሙሉ ለሙሉ አውድሞታል ብለዋል።
የህወሓት ታጣቂዎች የዘረፉትን ገንዘብ ሳይጨምር ከአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሀብት ኪሳራ ማድረሳቸውን አክለዋል።
አቶ አለምነው እንዳሉት፤ ህወሓት የተቋሙንና የግለሰቦችን መረጃ የያዙ ፋይሎችን፣ ኮምፒዩተሮችን፣ የዳታ ሰርቨሩን፣ ጠረጴዘና ወንበሮችን ጨምሮ አጠቃላይ የባንኩ ንብረት ላይ ኪሳራ አድርሷል ሲሉ አስረድተዋል።
ቋሚ ንብረቶችን ከማውደሙ በተጨማሪ ካዝና ውስጥ ከነበረው ገንዘብ ውጭ በኤቴም ማሽን ውስጥ ያለውንም ሰብሮ ዘርፏል ብለዋል።
የህወሓት ታጣቂዎች የባንኩን ጥበቃ ሠራተኛ አንደገደሉት ገልጸዋል፡፡
ወደ 4 ሺ የሚሆኑ የደንበኛ ፋይሎች ከጠቅም ውጭ እንደሆኑ ገልፀው ፤ ወጭና ገቢ የተደረጉ የመረጃ ዶክመንቶች አገልገሎት በማይሰጡበት ደረጃ ተበታትነው እንደጠፉ ተናግረዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/EPA-08-25
ፎቶ፦ ኢፕድ

አሜሪካ ?
የአሜሪካ የስለላ ድርጅት CIA ዋና ኃላፊ ከታሊባን መሪ ጋር በሚስጥር መገናኘታቸው እየተዘገበ ነው።
የCIA ኃላፊውና የታሊባን መሪው ሰኞ ዕለት ነው ካቡል ውስጥ መገናኘታቸውን አንዳንድ ምንጮች ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን መናገራቸው የተገለፀው።
በዊሊያም በርንስ (የCIA ኃላፊ) እና ሙላህ ባራዳር (የታሊባን መሪ) መካከል ውይይት ስለመደረጉ የሚያረጋግጥ ነገር ከሁለቱም ወገን በኩል እስካሁን አልተነገረም።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ የአሜሪካ ኃይሎችን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ቀነ ቀጠሮ አስቀምጠዋል።
በተጨማሪ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ያሉ የወዳጅ አገራት ወታደሮች በዚሁ ቀነ ቀደብ መሠረት እንደሚወጡ ይጠበቃል።
አንዳንድ ምንጮች እንደ New York Times ፣ Washington Post ፣ Associated Press እና NPR ላሉ የአሜሪካ የዜና ወኪሎች እንደተናገሩት CIA እና ታሊባን በሚስጥር ተገናኝተዋል።
ነገር ግን እስካሁን ድረስ በጣም ትንሽ መረጃ ነው በጉዳዩ ላይ የወጣው።
ይህ መረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ ታሊባን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና ያለውን የአፍጋኒስታን መንግሥት መሸሽ ተከትሎ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ወዲህ አሜሪካና እና ታሊባን ያደረጉት የመጀመሪያው ግንኙነት ይሆናል።
እስከ5800 የሚደርሱ የአሜሪካ ወታደሮች እስካሁን ድረስ በካቡል ኤርፖርት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች እና አገሪቱን ለመልቀቅ የሚፈልጉ አፍጋኒስታናውያንን ጥበቃ እያደረጉላቸው ነው።
#ቢቢሲ

* HERQA
በበይነ-መረብ(online) እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው የግል ተቋማት ቁጥር 5 መድረሱን ኤጀንሲው አሳወቀ።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ በዋለው በበይነ-መረብ ትምህርት የእውቅና አሰጣጥ መመሪያ መሰረት ፈቃድ በበይነ-መረብ(online) እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው የግል ተቋማት ቁጥር 5 መድረሱን ኤጀንሲው አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም ኤጀንሲው ለ4 ተቋማት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን አሁን ላይ ለሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ኦፍ አድሚኒስትሬሽን የትምህርት መስክ በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር በበይነ-መረብ የትምህርት አሰጣጥ ተማሪ ተቀብሎ እንዲያስተምር መፍቀዱን አሳውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ በበይነ-መረብ(በኦንላይን) ሞዳሊቲ የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር እንዲያስተምሩ በኤጀንሲው የተፈቀደላቸው 5 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1) ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ
2) ኢቲ ኦንላይን ኮሌጅ
3) ኤስቲ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ
4) ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ እና
5) ላይፍ ማፕ ኮሌጅ ናቸው፡፡
ከተጠቀሱት 5 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ሲሆኑ፤ ሌሎች በበይነ-መረብ (በኦንላይን) ትምህርት የእውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው ያላቸው በማስመሰል በተለያዩ የኢንተርኔት አውታሮች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁ ህገ-ወጥ አካላት መኖራቸው ታውቆ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሁሉም ህብረተሰብ አካላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤጀንሲው በጥብቅ ያሳስቧል፡፡
@tikvahethmagazine

በወገዳ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።
በደቡብ ጎንደር ዞን ወገዳ ከተማ አስተዳደር ሰሞናዊ የፀጥታ ችግሮች፣ ዘረፋና ስርቆቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ተገልጿል።
በተለይም ደግሞ ከወትሮዉ በተለየ ሁኔታ የህገ ወጥ ጥይት ተኩስ በመባባሱና በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ስጋትና ረብሻ አድሮባቸዋል፤ነፍሰ ጡር እናቶችና የጤና ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ለከፋ ችግር በመጋለጥ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
ይህንንም አስመልክቶ ትላንት ነሀሴ 18/2013 ዓ.ም የወገዳ ከተማ አስተዳደር የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ከወረዳዉ ፖሊሶች ጋር የጋራ ዉይይት አካሂደው ነበር።
በዉይይቱ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በዉይይቱ መጠናቀቂያ ላይ የከተማ አስተዳደሩን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ ከነሀሴ 18/2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ የጋራ ማደማደሚያ ላይ ተደርሷል።
እነኝህም፦
- ማንኛዉም አካል ከምሽቱ 2:00 በኋላ በከተማዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
- መሳሪያ የሚተኩስ የግልም ሆነ የመንግስት ታጣቂ ቢኖር ከነመሳሪዉ ተይዞ በህግ የሚጠየቅ ይሆናል።
- ሰሞኑን ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሓት ቡድን ለመከላከል ሲባል ገጀራ፣ ጩቤ እና ሌሎችም የስለት መሳሪያዎች የተቀበሉ ወጣቶች ለሰጣቸዉ ተቋም መመለስ አለባቸዉ፤ ይህ ካልሆነ ግን በህግ ተይዘዉ ንብረቱ እንዲመለስ ይደረጋል።
- ማህበረሰቡ ከሰላምና ደህንነት ተቀማቱ ጋር መረጃን በመለዋወጡና ህገ ወጦችንና ወንጀለኞችን ለህግ አሳልፎ በመስጠቱ በኩል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።
ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው የስማዳ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።