TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁሙ መቀጠሉን ቢገልፅም ህወሓት ዳግም "ቀልድ" ሲል አጣጥሎታል።

የፌዴራል መንግስት አሁንም ቢሆን ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁሙን አክብሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስገንዝቧል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም የህወሓት ኃይል ወደ አፋር እና አማራ ክልል በመግባት ትንኮሳ እየፈፀመ መሆኑን ፣ ትግራይ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊዎችን እንደሚገድል ፣ እርዳታ እንዳይደርስ እያደረገ መሆኑን ፣ ህፃናትን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑን ገልፀዋል።

አሁንም የመንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም እንደቀጠለ መሆኑን ያነሱት ቢለኔ ፥ ይህ ማለት ግን ትንኮሳ ሲፈፀምበት ምላሽ አይሰጥም ማለት እንዳልሆነ ተናግረዋል።

የፀጥታ ኃይሎች ትንኮሳና ጥቃት በመፈፀም ሳይሆን ለሚደርስባቸው ትንኮሳ ምላሽ በመስጠትና በመከላከል፣ የሲቪሎችን ደህንነት በመጠበቅ ተሰማርተው ይገኛሉ ብለዋል።

መከላከያውና የፀጥታው አካላት የራሳቸው እይታ አላቸው ሲቪሎች ሊረዱት የማይችሉት ወታደራዊ ግምገማዎች እና እርምጃዎች አሉ ይህም በነሱ በኩል ቢገለፅ ጥሩ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የህወሓቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተኩስ አቁሙን እና የጥሞና ጊዜውን ቀልድ ነው ሲሉ ድጋሚ ያጣጣሉት ሲሆን እንደማይቀበሉትም ተናግረዋል።

"ትግራይን አንቆ ይዞ የጥሞና የሚባል ጊዜ የለም ፤ መንበርከክ የሚባል ቃል በትግራይ መዝገበ ቃላት ውስጥ የለም" ሲሉም ተናግረዋል።

በጦርነቱ ድል እንደነሱ ሲናገሩ የተደመጡት አቶ ጌታቸው "እየተከተልን እርምጃ መውሰድ ነበረብን እሱን አድርገናል፤ እያንዳንዱን ኢንች የትግራይ መሬት ነፃ እናወጣለን ኤርትራ የያዘችው መሬትም አለ ይህንንም ነፃ እናወጣዋለን በዚህ ጥርጣሬ የለንም" ብለዋል።

@tikvahethiopia
ቴዲ አፍሮ የክብር ዶክትሬት ሊሰጠው ነው።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ አፀደቀ።

ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

ቴዲ አፍሮ ነገ ወደ ጎንደር በመሄድ ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን የሚቀበል ይሆናል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 24 በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5,710 ተማሪዎችን ያስመርቃል።

@tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

Mygerd.com በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

እስካሁን 898 ሰዎች ባደረጉት ስጋፍ 114,435 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡ 47 ሰዎች ደግሞ ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020

ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦
- ሀብታም አለሙ
- ነፃነት ደስታ
- ወርቅውሃ ጌታቸው

በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦
- ጌትነት ዋለ
- ለሜቻ ግርማ
- ታደሰ ታከለ

ድል ለሀገራችን🇪🇹ኢትዮጵያ !

@tikvahethsport
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 6,803 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 476 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ አምስት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 326 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
ቲክቫህ ስፖርት 👇
https://t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ፦ • የሀገር መከላከያ መቐለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞችን ለቆ ከወጣ ሳምንት ሊሆነው ነው። እስካሁን በክልሉ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት ፍፁም አዳጋች ሆኗል። ዓለም አቀፍ ለጋሽ ተቋማት አሁንም በትግራይ ክልል ችግር ላይ ለወደቁ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ፈታኝ ሁኔታዎች ስለመኖራቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ። እንደተለያዩ ዓለም አቀፍ…
#Tigray

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ የተናጠል የተኩስ አቁም አቅድርጎ ሰራዊቱን ወደ ኃላ መሳቡን ማሳወቁ አይዘነጋም።

ለተኩስ አቁሙ የተለያዩ ሀገራት እንዲሁም ተቋማት ድጋፋቸውን ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወቃል።

ተኩስ አቁሙ ይዘልቅ ዘንድ ግጭትም እንዲገታ ተግባራዊነቱ በሁሉም የግጭቱ ተሳታፊዎች እንዲሆን ሲጠየቅም ነበር።

በወቅቱ "ህወሓት" የተናጠል ተኩስ አቁሙን "ቀልድ" ሲል አጣጥሎት ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጡ አይዘነጋም፤ ነገር ግን ህወሓት ምላሽ ያገኘ አይመስልም።

ዛሬ በድጋሚ ህወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ ከዚህ ቀደም ያወጣውን ባለ7 ነጥብ አቋም አሻሽሎ አቅርቧል።

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎቱን አለኝ ያለው ህወሓት ፤ ዳግም ባወጣው የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት እና የሽግግር ሂደት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህኛው የተኩስ አቁም ለማድረግ ያወጣው ቅድመ ሁኔታ ፦

- በትግራይ የተቋረጡ የኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮምዩኒኬሽን፣ የባንክ ፣ የትራንስፖርት ፣ የጤና እና የንግድ እንቅስቃሴዎች መጀመር አለባቸው።

- የአገር መከላከያ አባላት የሆኑትን ጨምሮ ማንነታቸውን መሠረት ተደርጎ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በመላው አገሪቷ የትግራይ ተወላጆች የጅምላ እስር ይቁም።

- የ2013 ዓ.ም. እና የ2014 ዓ.ም. በጀት ይለቀቅ፡ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ።

- የሰብዓዊ እርዳታ ለማድስ ለሁሉም አይነት የትራንስፖርት አማራጮች በርካታ መተላለፊያ ኮሪደሮች ክፍት መደረግ አለባቸው የሚሉት ይገኙበታል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ህወሃት ከጦርነት ድርጊቱ እንዲታቀብና የሰብአዊ ዕርዳታ እንዳያስተጓጉል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠየቁ።

አቶ ደመቀ ጥያቄውን ያቀረቡት ከካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኖ ጋር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በትግራይ ክልል ስላለው ፖለቲካዊና ሰብአዊ ሁኔታ በተመለከተ የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኖ ሀገራቸው የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ እንዲደረስ የሚትፈልግ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ ፤ የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ እንዲዳረስ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ያሳለፈ መሆኑን ጠቅሰው ፤ የህወሃት ቡድን ግን የሰላማዊ መንገድን ከመከተል ይልቅ የዕርደታን መተላለፊያዎች በመዝጋት በአማራና በአፋር ክልል አዲስ ጦርነት መክፈቱን አስረድተዋል፡፡

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ መንግስት በክልሉ ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር እንዲሁም ሲያደርግ የቆየውን የሰብአዊ ድጋፎች ዕውቅና ከመስጠት መቆጠቡ ፤ ኢትዮጵያን ያሳዘነ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።

ካናዳን ጨምሮ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተውን የተኩስ አቁም ውሳኔን ህወሃት እንዲያከብር ጫና እንድደረግበት እና የቡድኑ ጥፋት ድርግቶች እንዲወገዙ አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/MoFA-Ethiopia-07-29

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ህወሃት ከጦርነት ድርጊቱ እንዲታቀብና የሰብአዊ ዕርዳታ እንዳያስተጓጉል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠየቁ። አቶ ደመቀ ጥያቄውን ያቀረቡት ከካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኖ ጋር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው። በትግራይ ክልል ስላለው ፖለቲካዊና…
"ህወሓት በከፈተው አዲስ ግጭት 200 ሺህ ዜጎች ተፈናቅለዋል"

የኢትዮጵያው ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኖ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህ ውይይታቸው ላይ የ"ህወሃት ቡድን" በከፈተው አዲስ ግጭት ምክንያት ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች 200 ሺህ ዜጎች እንደተፈናቀሉ የገለፁ ሲሆን ይህ ጉዳይ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡን ሊያሳስበው ይገባል ብለዋል።

አቶ ደመቀ በመስከረም ወር ላይ የሚመሰረተው አዲስ መንግስት ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማካሄድ ዕቅድ እንዳለው የገለፁ ሲሆን ህጻናት ልጆችን ጭምር ወደ ጦርነት እያሰማራ እና በአዲስ አከባቢዎች ጦርነት እየከፈተ ያለው የህወሃት ቡድን ድርጊቱን እንዲያቆም መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Afar

በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የእርዳታ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑ ከክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የአፋር ክልል መንግስት በህ/ተ/ም/ቤት ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሀት በፈንቲ ረሱ ዞን በኩል በከፈተው ጦርነት በርካታ ህዝብ ተፈናቅሎ በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልሎ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን የህይወት አድን ስራ ለመስራት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ የተጠየቀ ሲሆን የድጋፍ አካውንቱ የሰመራ ከተማ ወጣቶች በቅርቡ ባካሄዱት ኮንፈረንስ በተመረጡ ወጣቶች እንደተከፈተ ነው የተገለፀው።

የአካውንት ቁጥሩ 👉 1000422198974 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መሆኑ የተነሳ ሲሆን ከገንዘብ ባለፈ በአይነት ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ተገልጿል። ድጋፉን አስመልክቶ በስልክ ቁጥር 0911960546 (በኡመር መሀመድ ዱባ) ፣ 0911441847 (በሰዲቅ ሁሴን መሀመድ) ስልክ በመምታት መረጃ መቀበል ይቻላልም ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020 ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦ - ሀብታም አለሙ - ነፃነት ደስታ - ወርቅውሃ ጌታቸው በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦ - ጌትነት ዋለ - ለሜቻ ግርማ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA🇪🇹

አትሌት ለሜቻ ግርማ 3,000 መሰናክል በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድሩን አድርጎ 8:09.83 #አንደኛ ሆኖ አልፏል።

በሁለተኛው ምድብ ውድድሩን ያካሄደው የሀገራችን ልጅ አትሌት ጌትነት ዋለ 8:12.28 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፤ ወደቀጣይ ዙር አልፏል።

በመጨረሻው ሶስተኛ ምድብ ውድድሩን ያካሄደው አትሌት ታደሰ ታከለ 8:24.69 በሆነ ሰዓት 8ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020 ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦ - ሀብታም አለሙ - ነፃነት ደስታ - ወርቅውሃ ጌታቸው በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦ - ጌትነት ዋለ - ለሜቻ ግርማ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA🇪🇹

800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ :

አትሌት ሀብታም አለሙ ወደ ቀጣዪ ዙር አልፋለች።

የ800 ሜትር ሴቶች የ ማጣርያ ውድድሯን ያካሄደችው አትሌት ሀብታም አለሙ 2:01.11 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።

ሀብታም የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን ከነገ በስቲያ ቅዳሜ የምታካሂድ ይሆናል።

በሌላኛው ምድብ የ800 ሜትር የማጣርያ ውድድሯን ያካሄደችው አትሌት ነፃነት ደስታ 2:01.98 በሆነ ሰዓት #አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች ።

አትሌት ነፃነት ደስታ ከሌሎች የምድብ ማጣሪያ ውድድሮች የተሻለ ሰዓት ካላት የማለፍ እድል የነበራት ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል።

አትሌት ወርቅውሃ በመጨረሻው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ላይ አልተሳተፈችም ፤ ለምን ? ስለሚለው ለጊዜው መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

@tikvahethsport
ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከዶ/ር ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ተወያዩ።

የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት (UN) የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር መወያየታቸው ታውቋል።

ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበር ወ/ሮ ሙፈሪያት በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው አሳውቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉን ወ/ሮ ሙፈሪያት ገልፀዋል።

በተጨማሪ፦
- ሀገሪቱን ስለምትገኝበት የለውጥ ሂደት፣
- በቅርቡ የተካሄዘው ሀገራዊ ሰላማዊ የምርጫ ሂደት
- በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ላለፈው አንድ አመት በመካሄድ ላይ ስላለው ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ የምክክር ሂደት ገለጻ አድርገዋል።

@tikvahethiopia
ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

ዛሬ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የዓለም ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው በ10,000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።

ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶቻችን፦
- ሰለሞን ባረጋ
- ዮሚፍ ቀጄልቻ
- በሪሁ አረጋዊ

በተጨማሪ የ5,000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል።

ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ፦
- ሰንበሬ ተፈሪ
- ጉዳፍ ፀጋዬ
- እጅጋየሁ ታዬ

ውድድሮቹ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚደረጉ የወጣው ፕሮግራም ያሳያል።

@tikvahethiopia