ዛሬ 4 ሰዎችን አሳፍሮ ከድሬድዋ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ የነበረ ET-AMl መለስተኛ አውሮፕላን በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ወድቋል።
በፕሌኑ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በህይወት መትረፋቸውም ታውቋል፡፡
አውሮፕላኑ ዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 አካባቢ በኮምቦልቻ ወረዳ ቄረንሳ ጋረአሮ በተባለ ቦታ መውደቁን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ ተናግረዋል፡፡
ከተሳፋሪዎች መካከል በአንደኛው ተጓዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ወደ ድሬደዋ ለህክምና መላኩንም ገልጸዋል፡፡
ሌሎች ተጓዦች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን በስፍራው ተገኝተው እንደተመለከቷቸው የገለጹት ኃላፊው በአካባቢው ያለው የአየር ሁኔታ ጭጋጋማ እንደነበረም ተናግረዋል፡፡
መረጃው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia

አሜሪካ የ "ህወሓት ኃይሎች" በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘር እንዲያቆሙ አሳሰበች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ቃል አቀባይ የሆኑት ጄሊና ፖርተር በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ዛቻ እንዲሁም ጥቃት እየደረሰ እንደሚገኝ ሪፖርቶች እንደደረሷቸው ገልጸዋል። ይህ ጥቃት በአፋጣኝ እንዲገታ አሳስበዋል።
"ከህወሓት ጋር ግንኙነት ባላቸው ታጣቂ ኃይሎች እና በትግራይ ሚሊሻ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በክልሉ ውስጥ ጥቃት እየተሰነዘረ እንደሆነ የሚያሳዩ አስተማማኝ መረጃዎች ደርሰውናል። ይህም በጣም አስግቶናል" ብለዋል ቃል አቀባይዋ።
በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ እንደሆነ የሚጠቁሙ አስተማማኝ ሪፖርቶች እንደደረሰው የገለጸው የአሜሪካ መንግሥት ሁኔታው በእጅጉ እንዳሳሰበው አመልክቷል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጄሊና ፥ "ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ታጣቂ ኃይሎች ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘር እንዲሁም ዛቻ እንዲያቆሙ እንጠይቃለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በግጭቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዲሁም ሰብዓዊ እርዳታ ሰጪዎች ላይ ጥቃት እንዳይሰነዘርም አሳስበዋል።
በሌላ በኩል UN እንደ አዲስ ያገረሸው ሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጿል።
በትግራይ ክልል በሚገኙ ሁለት የስደተኞች መጠለያዎች የሚኖሩ ወደ 24,000 የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች ሰብዓዊ ድጋፍ እንደተቋረጠባቸው አሳውቋል።
በሪፖርቱ በማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች እና በአቅራቢያቸው ግጭት መኖሩን ገልጾ ሁለት ስደተኞች ተገድለዋል ብሏል።
24 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች የተጠለሉባቸው ጣቢያዎችን መድረስ አለመቻሉን ያሳወቀ ሲሆን "በመጠለያ ጣቢያዎቹ ምግብ እና ውሃ አልቆ ሊሆን ይችላል" ብሏል።
#BBC

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በደቡብ አፍሪካ ባሳላፍነው ሳምንት በነበረው አመፅ እና ዝርፊያ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች ተዘዋውረው ጎበኙ።
አምባሳደሩ በደቡብ አፍሪካ ግዛቶች በቴሚቢሳ እና በሰዌቶ ባሳለፍነው ሳምንት ንብረታቸው የወደመባቸው አካላትን በአካል ተገኝተው ጎብኝተው ነበር። በዚህ በያዝነው ሳምንት በኩዋዙሉ ናታል እና በፒተር ማርስበርግ ተገኝተው ከተጎጂ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አድርገዋል።
ትላንት እረብሻ እና አመፁ በእጅጉ የጎዳት ደርባን ከተማ በመገኘት ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ጎብኝተዋል። በቦታው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋርም ውይይት አድርገዋል።
ከጉብኝቱ በኃላ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም በደ/አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ነገር በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልፀው ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር በቅርበት እየተነጋገሩ መሆኑን አክለዋል።
Video and photo credit :- EK_ሚዲያ
Faya (Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

#ETHIOPIA
ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ፦
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ ከወቅቱ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ መረጃ ለኢዜአ ሰጥተዋል።
መረጃውን የሚከተለው ነው፦
- ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች ሰሞኑን እየታየ ያለው ጭጋጋማ አየር ከክረምቱ የአየር ትንበያ አንጻር ይጠበዋል።
- በክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ሊመዘገብ ይችላል።
በዚህም ፦ የምስራቅ አጋማሽ በሚል የሚጠሩ አካበቢዎች በአብዛኛው መደበኛና በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ መተንበዩን ተናግረዋል።
- ሰሞኑን የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የክረምት ተጠቃሚ በሆኑ አካባቢዎች የታየና በክረምቱ ወቅት የሚጠበቅ ክስተት ነው።
- ጭጋጋማ አየር በኢትዮጵያ ለአጭር ጊዜ በሐምሌና በነሐሴ ወራት የሚታይ ነው፤ የአየር ሁኔታው ዘላቂነት ላይኖረው ይችላል።
- ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ እይታን የሚጋርድ እንዲሁም እይታዎች በአጭር ርቅት የተገደቡ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው። የእይታ መጋረድ በአየርና በየብስ ትራንስፖርት ላይ ተጽእኖ የሚያደርስ በመሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
- የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕና ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ጭጋጋማው አየር ከአየር ትራንስፖርት ጋር የሚኖረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ዕለታዊ መረጃዎችን ለተቋማቱ እየሰጠ ነው። የሚሰጡ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ተቋማቱ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ

TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ ከወቅቱ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ መረጃ ለኢዜአ ሰጥተዋል። መረጃውን የሚከተለው ነው፦ - ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች ሰሞኑን እየታየ ያለው ጭጋጋማ አየር ከክረምቱ የአየር ትንበያ አንጻር ይጠበዋል። - በክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ሊመዘገብ…
#ጥንቃቄ
ከወቅቱ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት ፦
1. በጭጋጋማው የአየር ሁኔታ ምክንያት በየብስ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች እና መንገደኞች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል።
2. ከመደበኛ በላይ ዝናብ በሚጥልባቸው አካባቢዎች የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። የሚዘንበው ዝናብ በግብርና ምርቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በማሳ ላይ የሚንሳፈፈውን ውሃ የማጠንፈፍና የውሃ ቦይ መቅደድ ያስፈልጋል።
3. በከተሞች የጎርፍ ማስወገጃ ቱቦዎችን መጥረግና የጎርፍ ማሳለጫ መንገዶች ማበጀት ይገባል።
4. ለጎርፍ ተጋላጭ በሆነ በረባዳማ መሬት ላይ የሚኖሩ ዜጎች በዝናብ ምክንያት አደጋ እንዳይደርስባቸው ድጋፍ ማድረግ፤ ዜጎችም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።
5. የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በተለይም በተፋሰሶች የጎርፍ ቅድመ መከላከል ስራዎች ማከናወን ይገባል።
#ENA

በእነ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ 74 ሰዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።
በክስ መዝገቡ ላይ ፦
- ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
- ጄነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሳኤን፣
- ሜ/ ጄነራል ዮሀንስ ወ/ጊዮርጊስ
- ብ/ጄነራል ምግባይ ሀይለ
- ሜ/ጄነራል ሀለፎም አለሙ
- ሜ/ጄነራል ሀለፎም እጅጉ
- ሜ/ጄነራል አታኸልቲ በርሄ
- ሜ/ጄነራል ማሾ በየነ
- አቶ ሀዱሽ አበበ እና ቢኒያም ተወልደ ጨምሮ 74 ሰዎች ተካተውበታል።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች ፦
• የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ
• በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችል የትግራይ ማእከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ በማደራጀትና በመምራት
• በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣በፌዴራል ፖሊስ እና በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ እንዲሁም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ ላይ ጥቃት በማድረሳቸዉ ነዉ፡፡
ዐቃቤ ህግ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸዉን ከ500 በላይ የሰዉ ምስክሮችን፣ ከ5ሺህ ገፅ በላይ የሆነ የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የቴክኒክና የቪዲዮ ማሰረጃዎችን አያይዞ ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡
ክሱ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 272829 የሽብር መዝገቡ ተከፍቶ ጉዳዩን እየተመለከተዉ ይገኛል፡፡
#የፌዴራል_ጠቅላይ_አቃቤ

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ታዘዘ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ደጀኔና ጣፋና አቶ ሀምዛ አዳነ ( ቦረና ) ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ አዘዘ፡፡
አራቱ ተከሳሾች በሶስት ቀጠሮ በራሳቸው ፍቃድ ፍርድ ቤት አንቀርብም በማለታቸውን ተከትሎ ዓቃቢህግ በባለፈው ቀጠሮ በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱም ዛሬ ማረሚያ ቤቱ እንዲያቀርባቸው ያዘዘ ቢሆንም ዛሬም አንቀርብም በማለት መቅረታቸው ተሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም አራቱ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ በማዘዝ ለሀምሌ 30 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡
ይህ መረጃ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን የምትከታተለው ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ነው።