ምን ያህል የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምርጫ ተሳተፉ?
6ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ምርጫዎች ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በምርጫው ለመሳተፍ በኦላይን እንዲመዘገቡ መደረጉ እና ምርጫውን ከመጡበት አከባቢ ላይ ሄደው እንዲሳተፉ መወሰኑ ነው።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከሚያዚያ አጋማሽ አንስቶ ለ15 ቀናት የመራጮች ምዝገባ እንዲያካሂዱ ተገልጾ ነበር። በኃላም ቦርዱ ለተማሪዎቹ ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መስጠት እንዳለበት በማመኑ ምዝገባው እስከ ግንቦት 17 ተራዝሞ ነበር።
ለመሆኑ ምን ያህል ተማሪዎች በምርጫ 2013 ለመሳተፍ ተመዘገቡ? ብለን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ጠይቀናል። በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በምርጫው ይህ ነው የሚባል ተሳትፎ እንዳልነበራቸው የቦርዱ መረጃ ጠቁሞናል።
ከአርባ (40) በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ፤ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ለመምረጥ በቁ የሆኑ ወጣቶች በሚገኙበት ፤ የግንዛቤው አድማስም ሰፊ በሚባልበት እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ባሉባቸው ተቋማት ለምርጫው የተመዘገቡት ተማሪዎች አራት ሺ ሰባ አምስት (4,075) ብቻ ናቸው።
ከነዚህ 4,075 ውስጥ ምን ያህሉ ሰኞ ዕለት ድምፅ ሰጡ የሚለውን ገና አልታወቀም።
ከ 38 ሚሊዮን በላይ መራጭ በተመዘገበበት ምርጫ 2013 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተሳትፎ በዚህ ልክ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ችግሩን አጥንቶና መርምሮ ማወቅ ያስፈልጋል።
#TikvahFamily
@tikvahethiopia

#Live
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
ከላይ ባያለው Voice Chat 'Join' የሚለውን በመጫን በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

Audio
AudioLab
የኢትዮጵየ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን መግለጫ በቀጥታ መከታተል ላልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን የድምፅ ቅጂውን አያይዘነዋል (9 MB) ።
የተነሱ ዋና ጉዳዮች ያልናቸውን በፅሁፍ የምናጋራችሁ ይሆናል።
@tikvahethiopia
የተነሱ ዋና ጉዳዮች ያልናቸውን በፅሁፍ የምናጋራችሁ ይሆናል።
@tikvahethiopia
#ምርጫ2013
ምርጫ ከተደረገባቸው 440 ምርጫ ክልሎች ውስጥ 221 የሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ውጤቶቻቸውን መለጠፋቸውን ወይዘሪት ሶሊያና አሳውቀዋል።
ከምርጫ ክልሎቹ መካከል ከ50 % በላይ የሚሆኑት ናቸው ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶቻቸውን የለጠፉት።
በአማራ ክልል 40 የምርጫ ክልሎች ውጤት የለጠፉ ሲሆን በኦሮሚያ 125 የምርጫ ክልሎች ውጤት ለጥፈዋል ተብሏል።
አዲስ አበባ ከተማ ባሉ 10 የምርጫ ክልሎች ውጤት አሳውቀዋል፤ በከተማ ያሉ ሌሎች የምርጫ ክልሎች ቆጠራ አለመጠናቀቁ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ፦ በደቡብ ክልል በቁጫ የምርጫ ክልል ሲካሄድ የነበረው ቆጠራ እንዲቆም ተወስኗል።
ቆጠራው እንዲቆም የተወሰነው በነበረው ተገቢ ያልሆነ አሰራር እና የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነ ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስ ገልጸዋል።
ቦርሩ በቁጫ የምርጫ ክልል በሂደቱ ላይ ተገቢ ያልሆኑ አሰራሮች እንደነበሩ ቅሬታዎች ለቦርዱ ሲቀበል የነበረ ሲሆን ጉዳዩ እስኪጣራ ቆጠራ እንዲቆም ተወስኗል።
በምርጫ ክልሉ ሲቀርቡ ከነበሩት ቅሬታዎች በተጨማኢ የጸጥታ ችግር እንዳለ ቦርዱ መረጃ ስለደረሰው ቆጠራው ቆሞ የምርጫ ቁሳቁሶች ባለበት ታሽጎ እንዲቀመጥ ወስኗል።

በድሬደዋ በ6 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው ቦርዱ ገለጸ።
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች የክልል ምክር ቤት ምርጫ ሳይካሄድ እንደቀረ እንዲሁም ከስድስቱ በአንዱ ጣቢያ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ጭምር ሳይካሄድ መቅረቱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ገልጿል።
ሪፖርቱ አሁን እንደደረሳቸው የገለጹት የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ''የክልል ምክር ቤት የድምጽ መስጫ ወረቀት አልደረሰንም'' በሚል ምርጫው ሳይካሄድ እንደቀረ የምርጫ ክልሉ ኃላፊ መግለጹን የጠቆሙ ሲሆን ይህንን ግን አስቀድመው ሪፖርት አለማድረጋቸውን ነው ያነሱት።
በእነዚህ ጣቢያዎች ላይ ምን ይሆናል የሚለውን ቦርዱ መመልከቱን አንስተው ''እነዚህ ጣቢያዎች ላይ አንድ ፖርቲ ብቻ ነው የሚወዳደረው። የአንድ ፖርቲ ውድድር ስለሆኑ በክልል ምክር ቤት ደረጃ የሚኖረውን ውጤት አይቀይሩትም ስለዚህ ምንም አይነት ተጨማሪ ምርጫ ማድረግ አያስፈልግም ብሎ ቦርዱ ወስኗል'' ብለዋል።
ከስድስቱ አንዱ ጣቢያ ላይ ከክልል ተወካዮች ምክር ቤት በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም አለመካሄዱን ያነሱት ወ/ሪት ሶልያና ''...በአጠቃላይ የተወካዮች ምክር ቤት ውጤት ታይቶ ውጤቱን የሚቀይር ከሆነ ተጨማሪ ውሳኔ ቦርዱ የሚወስን ይሆናል።'' ሲሉ ገልጸዋል።
6ቱ ጣቢያዎች ከዚህ ቀደም የመራጮች ምዝገባ በትክክል ያልተካሄደባቸው ተብለው የተለዩ እንደሆኑ ያስታወሱት ወ/ሪት ሶሊያና ለዚህ ችግር መፈጠር ኃላፊነት የሚወስደው አካል የቱ ነው የሚለውን እያጣሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

#Ethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :
• የላብራቶሪ ምርመራ - 5,307
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 112
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ 288
አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 275,881 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,309 ህይወታቸው ሲያልፍ 258,491 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,988,902 ደርሰዋል።

#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ
ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ሂደት ላይ በፓርቲዎች (በተለይ ደግሞ በባልደራስ ፓርቲ) ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች በተወሰኑት ላይ ምላሽ ሰጥቷል።
ለቅሬታዎቹ እና አቤቱታዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ናቸው።
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በየምርጫ ጣቢያው በተለጠፈው የውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ተሰረዟል/ተደልዟል ስለሚባለው ጉዳይ ?
ወ/ሪት ሶሊያና : ምርመራ አድርገናል ፤ የየምርጫ ክልል ኃላፊዎች ስርዝ ድልዝ ተደረገበት የተባለውን ጣቢያ ተመልከትው ችግር ይኑርበት አይኑርበት የሚለውን ድጋሚ ቆጥረው እያረጋገጡልን ነው፤ የውጤት ማሳወቅ ሂደት ላይ ስርዝ ድልዝ መኖሩ ነው እንጂ ችግር ያለበት አልተገኘም፤ በቆጠራው ላይ ያለው እና የተፃፈው ቁጥር ትክልል ነው የሚል ሪፖርት ደርሶናል።
የምርጫ ቆጠራው ችግር አለበት ስለሚባለው ጉዳይ ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)
ወ/ሪት ሶሊያና : በአዲስ አበባ አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሁሉም ፓርቲ ወኪሎች ተገኝተው ነው ቆጠራ የተደረገው ፤ አ/አ ላይ የፓርቲ ወኪል ለምርጫ ጣቢያ ልኮ የምርጫ ጣቢያ አልቀበልም ያለበት ምንም አይነት ምርጫ ጣቢያ የለንም ፤ ሁሉም ቦታዎች የፓርቲ ወኪሎች ተገኝተዋል ፤ እራሳቸው ወኪሎቻቸውን እስከላኩና አቅማቸው ፈቅዶ ከ1 ሺህ በላይ ጣቢያዎች ላይ እስካስቀመጡ ድረስ። ወኪሎቹ የምርጫ ሂደቱ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ተከታትለው ውጤቱ ላይ ፈርመዋል ሁሉም ቦታዎች ላይ ማለት ይቻላል። ወኪሎች ያሉባቸው ፊርማዎች ኖረውን ነው የመጣነው የምርጫ ሂደቱን ስናደርግ።
ይቀጥላል👇

ማንነታቸው የማይታወቁ ጣቢያዎች ተከፍተው ነበር ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)
ወ/ሪት ሶሊያና : ፍፁም ሀሰት ነው። አዲስ አበባ ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ጣቢያዎች የሉንም። ሁሉም ጣቢያዎች ኮድ አላቸው፤ ኮድ የሌላቸው ያገኘናቸው 2 ጣቢያዎችን እንኳን ድጋሚ ኮድ ሰጥተን ምርጫ እንዲካሄድ አድርገናል።
አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የባልደራስ ፓርቲን ውጤት እያሳነሱ እንዲፅፉ ተደርገዋል ? (የባልደራስ ፓርቲ ቅሬታ)
ወ/ሪት ሶሊያና : ይህ ፍፁም ሀሰት ነው። ፓርቲ ወኪሎች ያሉባቸው ቦታዎች ከሆኑ የፓርቲ ወኪሎቻቸው እራሳቸው ይህን አይተው ዝም አይሉም። ወኪሎቹ እራሳቸው እንደዚህ ያለ አቤቱታ አቅርበው (በእኔ ፓርቲ ላይ ያለው ውጤት በትክክል አልተቆጠረም/በትክክል አልተፃፈም ብለው) ያቀረቡት ሪፖርት የለም። ያን አይነት አቤቱታ የቀረበበት የምርጫ ጣቢያም የለንም።
በወረቀት እጥረት የተነሳ ደጋፊዎቻችን ወደቤቶቻቸው ሄደዋል ተብሎ ስለተነሳው ቅሬታ ?
ወ/ሪት ሶሊያና : እስከ ለሊቱ 7 ሰዓት ከ10 ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት አከናውነናል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ባለመኖሩ የተቋረጠብን ምርጫ ጣቢያ የለም። ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ነበር ነገር ግን ባለው እያካሄዱ እያለ ተጨማሪ ወረቀቶችን ማድረስ ችለናል። ስለዚህ መሰረታዊ የሆነ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተቋርጦ የድምፅ መሥጫ ወረቀት ባለመኖሩ የተነሳ ሰው ተበትኖ/ተመልሶ ኑ ወረቀት መጥቷል እና ድምፃችሁን ስጡ የተባለበት አንድም ቦታ የለም፤ ስለዚህ ወረቀት አልቆ ደጋፊዎቼ ተመለሱ የሚለው በከፍተኛ ደረጃ #የተሳሳተ መረጃ ነው።

በአዲስ አበባ ድምፅ ሰጪው ረጅም ሰልፍ ነበረበት የሚልም ቅሬታ ነበር ፤ይሄ ጉዳይ እንዴት ይታያል ?
ወ/ሪት ሶሊያና : ምንም ጥያቄ የለውም ፤ በተወሰነ ደረጃ የድምፅ ሰጪዎች መንገላታት ቢያሳዝንም በሌላ በኩል ሲታይ ድምፅ ሰጪዎች በድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ ረጅም ሰዓት ወስደው በከፍተኛ Trunout ወጥተው ድምፅ መስጠታቸው በጣም የሚያስደስት ነው፤ ይህም በቦርዱ በጥሩ ጎኑ የታየ ነው።
በአጠቃላይ በአ/አ የነበረው ምርጫ በወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፦
"... አዲስ አበባ በጣም ጥቂት ችግር ካለባቸው ፤ አብዛኛው የምርጫ ሂደት (ሁሉም ማለት ይቻላል) ፓርቲዎች ሆኑ የግል ተወዳዳሪዎች ወኪሎቻቸውን ያስቀመጡበት ፤ በቆጠራ ሂደቱ ላይ አብዛኛዎቹ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሂደቱ እስኪጠናቀ ድረስ ታዝበው #ፈርመው የሄዱበት የቆጠራ ሂደት ያካሄድንበት ነው። በእርግጥ በአዲስ አበባ ጣቢያዎቹ ብዙ ቢሆኑም በከፍተኛ ደረጃ የፓርቲ ወኪሎች የተገኙበት ፣ ታዛቢዎች የተገኙበት፣ ዜጎች በጣም በረጅም ሰልፍ ሰዓት ወስደው የመረጡበት ፣ እስከ ለሊቱ 7 ሰዓት ሰፍል ላይ ያለው ሰው እንዳይቋረጥ ብለን ማንኛውም ድምፅ ሰጪ ድምፁን እንዲሠጥ ያደረግንበት ፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከልሎች ቦታዎች በተሻለ ሁኔታ ግልፅ የሆነበት እና ሚዲያን የሲቪክ ማህበራትም ፣ የፓርቲ ወኪሎች እኛም እራሳችን እየዞርን ያየንበት ነው።"
#TikvahEthiopia

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በውሃ እጥረት ምክንያት ነዋሪዎች እየተቸገሩ ነው።
ከዚህ ቀደም ፕሮግራም ውሃ የሚመጣባቸው አካባቢዎች ላለፉር ተከታታይ ቀናት ውሃ ማግኘት አልቻሉም፤ ይህም ደግሞ በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከሰሞኑ እየታየ ካለው የውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ምላሽ ሠጥቷል።
ባለስልጣኑ እንደሚለው ከሆነ ሰሞኑን በመዲናይቱ በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የውሃ ምርት እና ስርጭት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው።
የኤሌትሪክ መቆራረጥ ችግሩ በአቃቂ ጉድጓዶች እና ግፊት መስጫ ጣቢያዎች ላይ መፈጠሩንም ገልጿል፤ ይህ ሁኔታ ውሃ ለደንበኞቹ በወጣው መረሀ ግብር መሰረት እንዳይሰጥ ችግር እንደፈጠረበት አስውቋል።
በዚህም ፦
- ገላን አካባቢ፣
- ሳሪስ፣
- ሀና ማርያም፣
- ሀይሌ ጋርመንት፣
- ላፍቶ፣
- ጀሞ፣
- ቆሬ፣
- ሳር ቤት፣
- ሜክሲኮ፣
- ልደታ፣
- ጌጃ ሰፈርና ቤቴል አካባቢዎች ውሃ ለማሰራጨት #አልተቻለም ተብሏል።
በተጨማሪ ፥ በለገዳዲ ጉድጓዶች ላይ በየሰዓቱ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በባለስልጣኑ አገልግሎት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የችግሩን ስፋት በመረዳት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰራጨው ፅሁፍ ጠይቋል፡፡

TIKVAH-ETHIOPIA
በሳዑዲ አረቢያ በስደት ላይ የነበሩ 380 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገቡ። ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና የሠላም ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው አቀባበል አድርገውላቸዋል። አሁን የገቡትን ጨምሮ 2 ሺህ የሚሆኑ ከስደት ተመላሾች ዛሬ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሁለት ሳምንት ጊዜ…
#Update
ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ 1931 ዜጎቿን ወደ አገራቸው መልሳለች።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ 40 ሺህ ዜጎችን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።
በዚህ መሰረትም ትላንት 1,252 ከሪያድ እና 679 ከጂዳ በአጠቃላይ 1931 ዜጎች በስድስት በረራዎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ 1931 ዜጎቿን ወደ አገራቸው መልሳለች።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ 40 ሺህ ዜጎችን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።
በዚህ መሰረትም ትላንት 1,252 ከሪያድ እና 679 ከጂዳ በአጠቃላይ 1931 ዜጎች በስድስት በረራዎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ የሳዑዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፎ ነበር። የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።…
#Update #SaudiArabia
በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲቆም ተወሰነ።
ውሳኔው የተላለፈው ማህበረሰቡ ባለፉት ጥቂት ቀናት እጅግ በሚያኮራ መልኩ ፈጣን ድጋፍ በማድረግ በቂ የሆኑ ቁሳቁሶች በመለገዙ፤ ለግዜው እነዚህን ቁሳቁሶች በአግባቡ መጠቀም ስለሚያስፈልግ መሆኑን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅህፈት ቤት አሳውቋል።
ነገር ግን እንደ አስፈላጊነቱ ቆንስላው በድጋሜ የቁሶች ድጋፍ ካስፈለገው ጥያቄውን ሊያቀርብ እንደሚችል ጠቁሟል።
በቀጣይ ቀናት በማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች #የምግብ አገልግሎት ሲያስፈልግ ከቁጥጥር ከደህንነትና ከተገቢ የስራ ዕቅድና አፈፃፀም አኳያ አመቺ እንዲሆን ከቆንስላ ጽ/ቤቱ እና ከኮሚኒቲው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ብቻ ድጋፉ እንዲቀርብ ጥሪ ቀርቧል።
የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና በዚህ ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት በመከሰቱ ዕርዳታ ማድረግ የሚችሉ ካሉ እንዲያቀርቡ መጠየቁ አይዘነጋም።

የሶማሊያ ጦር 41 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደለ።
ጦሩ በዛሬው ዕለት በመዱግ ክልል ውስጥ የወሲል ከተማን ሊያጠቁ ነበር / ጥቃት ሊከፍቱ ነበር ያላቸውን 41 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድሏል።
በነበረው ግጭት 3 ከሶማሊያ ጦር እንዲሁም 5 ከጋልሙዱግ የዳርዊሽ ኃይሎች መገደላቸው ተሰምቷል።
በሌላ መረጃ የሶማሊያዋ #ፑንትላንድ ዛሬ 21 የአልሸባብ አባላትን ዛሬ ረሽናለች።
አባላቱ ጋልካዮ፣ ቃርዶ እና ጋሮዊ በተባሉ የተለያዩ ሶስት አካባቢዎች ላይ መረሸናቸውን የፑንትላንድ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኛ ጄነራል መሃሙድ አብዲ መሃመድ አረጋግጠዋል፡፡
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተገደሉት የአል ሸባብ አባላቱ ባለፉት 13 ዓመታት ውስጥ በተለያዩ የፑንትላንድ አካባቢዎች በተፈጸሙ ግድያዎች ጥፋተኛ ነበሩ ተብሏል፡፡
ከጎሳ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞች፣ ከመንግስት ባለስልጣናት ግድያ ጀርባ እንደነበሩ ፍርድ ቤት ገልጿል።
መረጃው ከጎብጆግ ፣ አልዓይን ኒውስ ፣ SNTV (የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን) የተውጣጣ ነው።

ኢትዮጵያ በየዕለቱ ሪፖርት የምታደርጋቸው የ #COVID19 ታማሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ እየመጣ ነው፤ በአንፃሩ ከበሽታው የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
ከረጅም ወራቶች በኃላ ዝቅተኛው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር ዛሬ ሪፖርት ተደርጓል።
በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የ24 ሰዓታት ሪፖርት 54 ሰዎች ብቻ ናቸው በኮቪድ-19 እንደተያዙ የተገለፀው።
ከ100 መቶ በታች የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር ሪፖርት ሲደረግ ከወራቶች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካሁን 275,935 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከነዚህ መካከል 259,044 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር 12,575 ነው።