TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

አቶ አገኘሁ የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወሰዱ፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ ክትባቱን የወሰዱት ዛሬ በክልሉ በተጀመረው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡

ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ክትባቱን ወስደዋል፡፡ (AMMA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#WHO #DrTedrosAdhanom

የአስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋትን ስለማስከተሉ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ በዚህ ስጋት አገሮች ክትባቱን ከመስጠት መቆጠብ የለባቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በትንሹ 5 የአውሮፓ ሀገራት አይስላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ክትባቱን መስጠት አቁመዋል ፤ ይህ የሆነ አንዲት የዳኒሽ ሴት ከደም መርጋት ጋር በተገናኘ እንደሞተች ከተነገረ በኃላ ነው።

ይህንን በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት በክትባቱ እና በደም መርጋት መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም ብሏል።

እስካሁን ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ አውሮፓውያን የአስትራዜኔካ ክትባትን ወስደዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም በበኩላቸው ፥ እስካሁን በመላው ዓለም 335 ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባት መሰራጨቱን የገለፁ ሲሆን እስካሁን ከክትባቱ ጋር በተገናኘ ምንም ሞት አለመመዝገቡን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ክትባት በአማራ ክልል፦

- ባህርዳር ከተማ ፈለገህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል፡፡

- የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ፣ የጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ እና ሌሎች አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ወስደዋል፡፡

- በሀገር አቀፍ በተሰጠው ኮታ መሰረት 108 ሺህ ዶዝ ክትባት ለአማራ ክልል ተሰጥቷል።

- በአማራ ክልል 251 ሺህ 597 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተመረምረው 7 ሺህ 392 ቫይረሱ ሲገኝባቸው 6 ሺህ 826 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡ 140 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት በአዲስ አበባ ፦

- በአ/አ የኮቪድ-19 ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።

- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ ጤና ጣቢያ ነው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር የተጀመረው።

- ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።

- የኮቪድ -19 ክትባት በቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፤ ሌላው ህብረተሰብ ክትባቱ እስኪደርሰው ድርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

- እንደ አዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ፥ የኮቪድ-19 ክትባት በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ፣ በእድሜና ለበሽታው ተጋላጭ ጤና ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሠብ ክፍሎች ይሰጣል።

- በአ/አ የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ማስጀመሪያ ላይ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከገባ ጀምሮ በሽታውን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ግንባር ቀደም ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

Via Addis Ababa Press secretary
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ።

By : EPA

የአ/አ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ዛሬ በአ/አ በተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ክትባቱን ወስደዋል።

ዶክተር ዮሀንስ ፥ በክትባቱ ዙርያ የሚናፈሱት አሉባልታዎች ሁሉ ከእውነታ የራቁ ናቸው ብለዋል። ለዚህም ምስክርና ማሳያ ይሆን ዘንድ ራሳቸው የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል።

ክትባቱ በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ክትባት የመጀሪያዉ ክትባት በተሰጠ ከ 8-12 ሳምንት ድረስ እንደሚሰጥ ነው ዶክተር ዮሀንስ ያስታወቁት።

ክትባቱ ቅድሚያ ለጤና ባለሞያዎች ይሰጣል ፤ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውንና እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ደግሞ ከጤና ባለሞያዎች ቀጥሎ ክትባቱ እነደሚሰጣቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት በትግራይ ፦

የኮቪድ-19 ክትባት በአገር አቀፍ ደረጃ በመቐለ መሰጠት ተጀምሯል።

መርሐ ግብሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በመቐለ አጠቃላይ ሆስፒታል አስጀምረውታል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ተከትበዋል።

ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች እና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል። - ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#NewsAlert

የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ለመቀየር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ።

በቀጣይ 6 ወራት በጥናት ላይ ተመስርቶ የአማራ ህዝብን ታሪክና ስነ ልቦና የሚያንፀባርቅ ሰንደቅ ዓላማ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውልም ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል ነው የተባለው።

ነባሩ ሰንደቅ ዓላማ አንድን ፓርቲ የሚወክል እንጂ የአማራ ህዝብን ስነ ልቦና የማያንፀባርቅ በመሆኑ በህዝቡ ተቀባይነት ማጣቱም በምክር ቤቱ ተገልጿል። (AMMA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ፦

ፖል ካጋሜ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ሆነዋል።

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ጃኔት ክትባቱን ሲወስዱ የሚያሳይ ፎቶግራፍም በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ይፋዊ ትዊተር ገጽ ላይ ተለቋል።

ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የኮሮና ክትባት የወሰዱ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ሆነዋል፡፡

እስካሁንም በሩዋንዳ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባን መውሰዳቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ።

የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት በሶማሌ ክልል በይፋ አስጀምረዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጅግጅጋ በሚገኘው የካራማራ ሆስፒታል በመገኘት ነው ክትባቱን ያስጀመሩት።

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ገራዶች እና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሶማሌ ክልል 108 ሺህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት መረከቡን ያስታወቁት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የሚገኙ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች በተቻለ ፍጥነት ክትባቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦ - የትግራይና አማራ ክልል አስተዳደር እና ወሰን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ የትግራይ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ። - በ3 ቀናት ብቻ ከ70 ሺ በላይ ሰዎች ከምዕራብ ትግራይ መፈናቀላቸውን የትግራይ አስተዳደር ማሳወቁ። - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕወሓት የሚያሰራጫቸው የውሸት መረጃዎች ለአስተዳደሩ ፈተና እንደሆኑበት ማሳወቁ። - አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ…
#NewsAlert

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል ተብሎ ለቀረበው ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው የቀጠናውም ሆነ ዓለም አቀፍ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ከቀናት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል «የዘር ማጥፋት/ማፅዳት» ተፈፅሟል ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም።

ብሊንከን በንግግራቸው በክልሉ የተፈጠረው ቀውስ እንዲመረመር እና የኤርትራ ወታደሮች እንዲሁም የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ግፊት እንዲደረግ መጠየቃቸው ይታወሳል።

የብሊንከንን ንግግር ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡት ውንጀላ መሬት ላይ የሌለ እና ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መሆኑንም መግለጫው አንስቷል፡፡

መንግስትም ተፈጽሟል ለተባለው ማንነትን መሰረት ያደረገ የጥቃት ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካባቢያዊም ሆኑ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትና አጣሪ ባለሙያዎች ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አስታውቋል፡፡

አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በጉዳዩ ላይ ከዘርፉ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር አስፈላጊውን ምርመራ ለማድረግ ስለመዘጋጀቱም ነው የገለጸው፡፡

https://telegra.ph/Tigray-03-13

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በሲዳማ ክልል ይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ተመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሲዳማ ክልል ባለስልጣናት ተገኘተው ነበር።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ294.5 ሄክታር ላይ የተገነባ ሲሆን እምቅ የእሴት ጭማሬ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን፣ የወተት ተዋጽኦዎችን፣ ስጋ፣ የዶሮ እርባታ፣ ቡና እና ጥራጥሬዎችን እንደሚያጠቃልል ተገልጿል።

* ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይርጋለም የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ምዕራብ አርሲ ዞን ኤበን ወረዳ አርሲ ወረዳ ተጉዘው ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ።

የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ክትባቱን የወሰዱት በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በመቐለ ጠቅላላ ሆስፒታል ተገኝተው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

ዶ/ር ሊያ ፥ በመላው ሀገሪቱ ለኮሮና ቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን በቀዳሚነት ያገኛሉ ብለዋል፡፡

የክትባቱ አቅርቦት በአለም አቀፍ ደረጃ ውስንነት ስላለው እና ሁሉንም የህብረተስብ ክፍሎች ማዳረስ የማይቻል በመሆኑ ህብረተሰቡ ክትባት መጣ ብሎ መዘናጋት እንደሌለበት እና ቫይረሱን መከላከያ መንግደ በአግባቡ እንዲተገብር አሳስበዋል።

#MoH
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቷል! "ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤ በተደረገው ምርመራ አንድ (1) ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች እንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" - ኢንጂነር ታከለ ኡማ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ከገባ 1 ዓመት ሞላው።

ልክ በዚህ ሰዓት ነው የዛሬ ዓመት ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ እንደገባ በይፋዊ መግለጫ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተነገረው።

መጀመሪያ ግን በወቅቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ናቸው በፌስቡክ ገፃቸው ፥ "...አንድ (1) ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች እንቆጠብ" ሲሉ መልዕክት ያሰራጩት።

በኃላም ዶ/ር ሊያ እና ዶ/ር ኤባ በቴሌቪዥን ወጥተው ኮቪድ-19 የተያዘ የመጀመሪያው ሰው እንደተገኘ ፤ ስለግለሰቡ ዝርዝር መረጃ ለህዝብ ይፋ አደረጉ።

ብዙዎችም በሰሙት ነገር እጅግ ተሸበሩ፤ ተጨነቁ።

በወቅቱ የነበረ ሁኔታ በጥቂቱ ፦

- ኢ/ር ታከለ ቀድመው ማሳወቃቸው t.iss.one/tikvahethiopia/47204
- የእነ ዶ/ር ሊያ መግለጫ t.iss.one/tikvahethiopia/47206
- ማስክ እና ሳኒታዘር ለመግዛት የነበረው ሰልፍ t.iss.one/tikvahethiopia/47215
- የሳኒታዘር እና ማስክ ዋጋ መጨመር ነዋሪዎችን አማሮ ነበር t.iss.one/tikvahethiopia/47226
- የወቅቱን ሁኔታ ተጠቅመው ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎች t.iss.one/tikvahethiopia/47231
- የዶ/ር ቴድሮስ (WHO) #TheSafeHandsChallenge t.iss.one/tikvahethiopia/47241
- በወቅቱ የነበረው የትግራይ ክልል መንግስት በአስቸኳይ ነፃ የጥሪ ማዕከል ማዘጋጀቱ t.iss.one/tikvahethiopia/47243
- በወቅቱ እጅግ መነጋገሪያ ከነበረው ጉዳይ በኮቪድ-19 ተጠርጥሮ ሲወሰድ አምቡላስ ሰብሮ ያመለጠው ሰው t.iss.one/tikvahethiopia/47307
- ከ3 ቀን በኃላ በሰበር ዜና መንግስት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የሚሉና ሌሎች ውሳኔዎች ማሳለፉ t.iss.one/tikvahethiopia/47372
- ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የዶ/ር ቴድሮስን ጥሪ ተቀብለው የንፁህ እጆች ዘመቻን መካፈላቸው t.iss.one/tikvahethiopia/47386
- አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የመንግስት ዋነኛ ተቃዋሚ መሪው አቶ ጃዋር እና ሎሎችም፣ ጋዜጠኞች የንፁህ እጆችን ዘመቻ መቀላቀላቸው t.iss.one/tikvahethiopia/47387
- በመከላከያ ሰራዊት አዲስ ምልመላ ፣ ፍቃድ፣ በሰራዊት ካምፕ እና መኖሪያ ቤት ግንኙነት መገታቱ t.iss.one/tikvahethiopia/47505
- እርዳት ማሰባሰቡ፣ መተባበሩ ፣ መተጋገዙ t.iss.one/tikvahethiopia/47686
- በየቦታው ርቀት እንዲጠበቅ ፣ ሰዎች እጅ እንዲታጠቡ ዘመቻ መደረጉ።

ብዙ ብዙ...

በወቅቱ ሁሉም ሰው ፣ ሚዲያው ወሬው ሁሉ ስለ ኮቪድ-19 ነበር። በእጅጉ ጥንቃቄ እንዲደረግም ይቀሰቀስ ነበር። የሰዎች ጭንቀት ፍርሃትም አይሎ ነበር።

ዛሬስ ?

ዛሬ ግን በሀገራችን ወረርሽኙ አስከፊ ደረጃ ላይ ሲደርስ መዘናጋቱ ጨምሯል ፤ በየዕለቱ የሰዎች ህይወት ያለፋል ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ ፣ የፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአቅም በላይ ሆኗል፣ ከመንግስት ኃላፊዎች ጀምሮ ጉዳዩ ተዘንግቷል ፣ መንግስት ብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ሲያደርጉ ያበረታታል ፣ በሚያዲያም ቅስቀሳ ይደረጋል ፤ አርአያ የሚሆንም ሰው ቀንሷል።

ዛሬም የጤና ባለሞያዎች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ወረርሽኙን እየተጋፈጡ ነው (እናመሰግናለን) !

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የዋጋ ንረቱን መቋቋም አልቻልንም"

በኢትዮጵያ በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ መቋቋም ከሚቻለው በላይ እየሆነ እንደሆነ የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።

በተለይ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች በኪራይ ቤት ፣ ለልጆች የትምህርት ቤት ክፍለው፣ የምግብ ፍጆታው ተጨምሮ ኑሮን ክፉኛ አክብዶባቸዋል።

ጤፉ፣ በርበሬው፣ ፉርኖ ዱቄት ፣ ዘይት ... ጨምሯል ፤ ምን ያልጨመረ አለ ? በርካቶች ከሚያገኙት ገቢ አንፃር ሲተያይ ጭማሪው ፍፁም የሚመጣጠን አልሆነም።

የምናገኘው ገንዘብ እዛው ነው፤ የእያንዳንዱ መሰረታዊ ፍጆታ ዋጋ ግን በየጊዜው እየጨመረ ነው ፤ መኖር ከበደን የመፍትሄ ያለህ ሲሉ የቲክቫህ አባላት አቤት ብለዋል።

@tikvahethiopia
2 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ !

By : አል ዓይን (am.al-ain.com)

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ለአል ዓይን ኒውስ አስታውቀዋል።

አቶ አምዶም ገብረስላሴ ፥ በገዛ ፈቃዳቸው አለመልቀቃቸውን የገለፂ ሲሆን ፓርቲያቸው ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ከሰሞኑ ከሰጠው መግለጫ እና እርሳቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ካደረጓቸው ቃለ መጠይቆች ጋር በተያያዘ ከኃላፊነት መነሳታቸው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ተደፈሩ የተባሉ የትግራይ ሴቶችን በተመለከተ አደረግሁ ባሉት ንግግር እና ከሰሞኑ ወደ ክልሉ አቅንቶ ከነበረ ዓለም አቀፍ የሚዲያዎች ቡድን ጋር በተያያዘ ከተፈጠሩ ግርግሮች ጋር በተያያዘ መነሳታቸውን ጠቁመዋል፡፡

አቶ አምዶም ፥ “የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አይደለም ከኃላፊነት ያነሳኝ” ሲሉ ተናግረዋል።

እርሳቸው “አላውቀውም” የሚሉት “የፌዴራል ሚዲያ ኮሚቴ” ለጊዜያዊ አስተዳደሩ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መነሳታቸውን ገልፀዋል።

አቶ አምዶም ፥ ከኃላፊነት መነሳታቸውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ትናንት ማታ ቢሯቸው ጠርተው እንደነገሯቸው እና ደብዳቤ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

በእርምጃው ቅር የሚላቸው ምንም ዐይነት ነገር እንደሌለ የገለጹ ሲሆን በዓረና አመራርነታቸው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የኮንስትራክሽን፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ በተመሳሳይ መልኩ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ነው አቶ አምዶም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Alert😷

በ24 ሰዓታት ውስጥ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 30 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደረገ።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,654 የላብራቶሪ ምርመራ 1,483 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 846 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 174,054 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,540 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 142,041 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 464 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ውድ የቲክቫህ አባላት በየዕለት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በየዕለቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እየተሸጋገር ፤ የሰዎችንም ህይወት እየቀጠፈ ፤ በርካቶችንም ለስቃይ እየዳረገ ነውና ጥንቃቄ አይለያችሁ ስንል አደራ እንላለን።

የሁላችሁንም አባላት ሙሉ ጤናችሁን እንመኝላችኃለን!

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT